Telegram Web
set bay haniya❤️❤️
ከ#25 እስከ 30 ዕድሜ ላይ ያለች ሴት ልክ እንደ ለንደን ከተማ ውብና ሁሉም ሊኖርባት የሚያልማት ትሆናለች 🍂
ከ#30 እስከ #35 ባለው ውስጥ ደግሞ ልክ እንደ ፓሪስ ከተማ የሚያውድ መዐዛ ያላት አበባ ትሆናለች 🌹
ከ#35 እስከ #40 ባለው እድሜዋ ደግሞ ልክ እንደ ሮም ከተማ የፍቅር መንገድ ሁሉ ወደርሷ ይወስዳል
ከ#40 እስከ #45 ባለው እድሜዋ ውስጥ እንዲሁ እንደ ባግዳድ ከተማ ውበትን ከአስተሳስብ ምጥቀት ጋር ያቆራኘች ትሆናለች 😘
#50 አመት ላይ ስትደርስ ደግሞ ልክ እንደ ኢስታንቡል ከተማ የሰለጠነች ማራኪና አስደናቂ ትሆናለች 😍
ከ#50 እስከ #60 ባለው እድሜዋ ውስጥ ደግሞ ልክ እንደ ቁድስ ከተማ ሁሉም የሚያፈቅራትና የሚያልቃት ትሆናለች 🥰
ሴትነት ❤️🤗

🍂 @Habibacalligraphy
ክፍል አንድ
🐾ያልወለደች🕊እናት🐾
:
:
:.. ...ከብርድ ልብሴ ውስጥ አንገቴን አውጥቼ ለመከፈት የሚታገለውን አይኔን ከፈት ሳደርግ መኝታ ክፍሌ በብርሀን ተከቧል እንደነጋ ገባኝና ከአልጋዬ ለመውረድ መታከክ ጀመርኩ ገና ከጠዋቱ ከአልጋዬ ሳልነሳ ድብርቱ ተጫጭኖኛል እንደ ምንም እራሴን ለማነቃቃት አልጋዬ ላይ ተቀመጥኩኝ ትንሽ የእንቅልፉ ስሜቱ ሲለቀኝ የመኝታ ልብሴን እንደለበስኩ ከኔ ክፍል ቀጥሎ ወዳለው መታጠቢያ ክፍል አመራሁ መክፈቻውን ጫን ሳረገው አልከፈት አለኝ ውስጥ ሰው እንዳለ ስለገባኝ ማንነቱን ለማወቅ ኳኳኳ አረኩት ያው ከአንድ ሰው ሌላ ማንም ስለማይገባ እሱ እንዳለ ገመትኩ "ምንድነው ሻወር ላይ ነኝ እታች ውረጂ"አለ የ ፋይሰል ድምፅ ነበር ፋይሰል ማለት ታላቅ ወንድሜ ነው እየተነጫነጭኩ "አንተ ደሞ ሁሌ እኔ ልገባ ስል ነው መታጠብ ሚታይህ ብሽቅ"ብዬው መኝታ ቤት ገብቼ ጋወን እና ሂጃብ ደርቤ ወደ ምድር ቤት ወዳለው መፀዳጆ ቤት አመራው ሰው መኖርና አለመኖሩን ለማረጋገጥ ኳኳ ሳረግ ከውስጥ ድምፅ ሰማው ብዙም ሳይቆይ ከመፀዳጃ ቤቱ ሀሩን ወጣ ሀሩን ማለት የአባቴ የጓደኛው ልጅ ነው ያው ለቤታቸው ወንድ እሱ ብቻ ስለሆነ ቅዳሜና እሁድ እኛ ቤት ነው የሚሆነው በነዚ ቀናቶችም ፋይሰልም ስራ ስለሌለው ስናዝግ እንውላለን ሁለቱ እኩያሞች ኛቸው በዛላይ በጣም ሚዋደዱ ጓደኛሞች! ሁለቱ እኔን በ 5አመት ይበልጡኛል እንደው አንዳንዴማስ ቅዳሜ እስኪደርስ ሲጨንቀኝ! ያው ከሰኞ እስከ አርብ ብቻዬን ስለምውል ይጨኝቃል ከትምህርት ቤት ወደ ቤት ከቤት ወደ ትምህርት ቤት እቤት መቶ ደሞ ለብቻ መዋል ይደብራላ?ዛሬ ግን ገና ከጠዋቱ ቢደብረኝም ፋይሰል አንድ ቦታ አሳያቹኃለው ብሎ ስላጓጓን እሱን እያሰብኩ ፈታ ማለት ጀመርኩ ከመፀዳጃ ቤት ወጥቼ ወደ ክፍሌ ለመሄድ ደረጃውን ልወጣ ስል አንድ ነገር ትዝ አለኝና እየበረርኩ ወደ ኪችን ገባው መኪያ ስታየኝ እየደነገጠች "ምነው ዳኒ ምን ያሮጥሻል አሁን ብትሰበራስ"ብላኝ የያዘችውን ሰሀን ይዛ ወደ ሳሎን ወጣች ማታ ፋይሰል ጠዋት እበላዋለው ብሎ ፍሪጅ ውስጥ ያስቀመጠው እሩዝ በስጋ(ሀኒድ)ትዝ ብሎኝ ነው ፍሪጁን ከፍቼ አወጣሁና አሙቄ ወደ ክፍሌ ይዤው ወጣው ክፍሌ እንደገባው አባባ መጣራት ጀመረ ዳኒያ ዳኒያ ሲለኝ የክፍሌን በር እየከፈትኩኝ ወይ አባባ መጣው እያልኩት ወደ ሳሎኑ ሮጥኩ ሳሎን ስገባ ሁሉም ተሰብስበዋል እንደገባው ፋይሰልን ሳየው በምልክት ቆይ አለኝ ከንፈሩን ነክሶ አይኑን እያፈጨጨብኝ እንደማይለቀኝ ስለገባኝ "አባባ አየኀው አይደል ሲያስፈራራኝ"አልኩት እናቴና አባቴ መሀል ያለው ክፍተት ቦታ ላይ እየተቀመጥኩ አባቴም ነገሩ ስለገባው "የሆነ ተንኮል ኮልሰራሽው በቀር ከመሬት ተነስቶ አይነካሽም"ብሎኝ የቀረበውን ምግብ ለመመገብ ከመብላት በፊት የሚደረጉትን ፀልቶች ብለው ሁሉም መመገብ ጀመሩ እናቴ ሰሀኔ ባዶ መሆኑን ስታይ "አንቺ ልጅ አበይም እንዴ ምን ስርአት ታጣለቸሸ"ብላ ተቆጣች የሆነ ነገር እንደሚል ስለገመትኩ ፋይሰልን ተመለከትኩት "እሷ ነገር ትብላ እንጂ ምግብማ ከየት መቶ ነጎሮሮዋም ዝቅ አይል"አለና ከት ብሎ ሳቀ እናቴ በፋይሰል ንግግር እየፈገገች መኩ በልታለች እንዴ ወይስ እላይ የተለየ ምግብ አለ እስኪ መኝታ ቤቷ ጊቢና ካለ አምጭው ብላ ፍለፊቷ ብና ወደ ምቀዳው መኪያ ተመለከተች መኪያ ማለት ሀዲማችን(እኛ ቤት ስራ የምትሰራ)ልጅ ናት እኛ ቤት ለ 7 አመት ቆይታለች ለዛ ነው መሰል ማንም እንደ ሰራተኛ አይቆጥራትም ሁሉም ይወዶታል በተለይ እንግዳ ሲመጣ የምታደርገው እንክብካብ አያምጣው ነው ሳያመሰግናት ሚወጣ የለም መኩ ከተቀመጠችበት ልትነሳ ስትል "ቁጭ በይ እራሷ ትሂድና ታምጣ አለ አባባ እኔ እያለው እሶ ስትላክ አይወድም ደስ እያለኝ እየሮጥኩ ወደ ክፍሌ ሄድኩና ቁጭ ብዬ ምግቡን ካጋመስኩት ብኃላ 3 ጉርሻ የምትሆን ሲቀር ይዤው ወረድኩ ፋይሰል ስቆይበት ጨርሼው እንደምመጣ ስላወቀ "እእእ የተላክሽው ቅድም እስካሁን ምን አቆየሽ"አለ ሁሉም መላኬን ረስተዉት ነበር "ወይኔ ለዚች ምግብ ጎሮሮዬ ላይ ልትቆም ነው እንዴ ያው ብላው ብዬ እንደተከደነ አጠገቡ አስቀመጥኩለት የኔ ምስኪን ወንድም ያለው መስሎት ሰፍ እያለ እማማ ትበያለሽ አላት እናቴ ከ አባቴ ጋር ተመስጣ እያወራች ስለነበር አልሰማችውም ቀጠል አሮጎ "ሀሩኔ ትላንት እስኪያቅርሽ በልተሻል ዛሬ የኔና የ መኩ ተራ ነው ብሎ የተከደነውን ሰሀን ከፈት ሲያረገው በሱ አበላል 1 ጉርሻ ቢህን ነው ሁላችንም ተያይተን ሳቅን እነ እማማ ሳቃችንን ሲሰሙ ወሬያቸውን አቋርጠው ምን እዳሳቀን ለማየት ፋይሰል ላይ አፈጠጡ እማማ ስለገባት "አንቺ ልጅ ግን እረፊ አንድ ቀን በጥፊ ብሎሽ"ነገር እንዳታመጪ ብላ ከተቀመጠችበት ተነሳች አባባም ተከትሏት እየተነሳ ፋይሲ በል እኛ ባለፈው ያልኩህን ሰውዬ እንያቸው ብለን ነበር እና እዛ ነው ምንውለው አይሻልም?ብሎ ጠየቀው አባባ ሁሌ አንድ ነገር ሲኖር ለ ፋይሰል ሳያማክር አያረግም"አይ አራፍ ነው ስላስለመዳቿቸው ደሞ ስትቀሩ ይከፋቸዋል"ብሎ ፈገግ አለ ፈይሰል ነበር አባባ ቀጠል አርጎ "እናንተም ከወጣቹ በጊዜ ተመለሱ ብሎ ከሳሎን ወጥቶ ደረጃውን እንደወጣ "ዳኒ ነይ"ብሎኝ እንደጠራኝ ብድግ ብዬ አባባ ወዳለበት ሄድኩ "ስወጣ አስታውሺኝ የምትውሉበትን እሰጣቿለው" ብሎኝ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ እኔም ወደ ሳሎን ገብቼ ከመኩ ጋር የተበላበትን ማነሳሳት ጀመርን የሚገርመው የፈለገ ስራ ቢበዛባት መኪያ ማንም እንዲያግዛት አትፈልግም እኔም አውቃለው ግን ሼም ነው በሚል ዝም ብዬ እነካካለው እነ ፈይሰል ቴሌቭዥን ከፍተው አስቂኝና ድንቃ ድንቅ እያዩ ይስቃሉ እነ አባባ ለባብሰው ጨርሰው እየወጡ ነበር በር ላይ ቆሜ "አባባ"ስለው የቅድሙ ትዝ ብሎት ወደኔ መጣና የጋወኔ ኪስ ውስጥ ስጉጥ አርጎልኝ መኪናውን አስነስቶ ወጡ እኛም ትንሽ እንደቆየን ለባብሰን ልንወጣ ስንል የመኩ ብቻዋን መሆን ትዝ አለኝና ለማፅናናት ያህል "ቶሎ እንመለሳለን በጣም ከደበረሽ ደሞ ደውይልኝ" ብያት ተያይዘን ወጣን መንገድ ላይ እያለን....


ክፍል ➋ #ይቀጥላል.....

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል ሁለት
🐾ያልወለደች🕊እናት🐾
:
:
:....ፋይሰል ድንገት "ግን እናንተ በቃ ዝም ብላቹ መነዳት ነው በቃ የት ነው ምትወስደን እንኳን አትሉም"አለና ፈገግ አለ እኔም ቀበል አርጌ "እእ ፋይሲ ወደየት ግድም ነን ወንድም አለም"ብዬው ከ ሀሩን ጋር ተያይተን ሳቅን በርግጥ ሀሩን ንግግሬ ነው ያሳቀው እኔ ግን ፋይሰልን ለማናደድ ብዬ ነው "አረ አሁን እኔ ስልሽ ነው ነይ ባክሽ አርፈሽ እንደ በግ ተነጂ"ብሎኝ አቀፈኝ እና የቦሌን ታክሲ ወደ ምናገኝበት አስፓልት ተሻግረን መጓዝ ጀመርን ሀሩን ብዙውን ጊዜ እኔ ስኖር ዝምታን ይመርጣል ከፋይሰልጋ ሲሆን ግን አያምጣው ነው እንደው ብዙ ጊዜ ፋይሰል ነገር ሲበላ "ምንድነው አንተ እሷ ስትመጣ ምትዘጋው ፓስወርድህ ናት እንዴ አረ በናትሽ ክፈችልኝ"እያለ ሙድ መያዝ ይቀናዋል እንዲ እንዲ እያለ አራፍ ውሎ ውለን 1፡00 ሰአት ሲል እኔና ፋይሰል ወደቤታችን ሀሩንም ወደቤቱ ተለያየን ነገ ሰኞ መሆኑን ሳስበው በጣም ጨነቀኝ እቤት ስንገባ እነ አባባ አልመጡም ነበር ቀድመናቸው ስለደረስን ደስ ብሎን የኡሻን(ማታ ላይ የሚሰገድ ስግደት) ሰግደን እነ እማማን መጠባበቅ ጀመርን በነገራችን ላይ እናትና አባታችንን እንዲ የምንላቸዎ ድሮ ልጅ እያለን በስማቸዎ ስንጠራቸው አያታችን ሰምታ ተቆጣችን "እማዬ/አባዬ በሉ ወይ ምንድነው ምትሉት ስትቀናጡ እማማ/አባባ"ብላ አስጀመረችን በሷ ቤት እኮ ማማ እና ባባ ማለቷ ነው አዪ አያቴ የኔ ተናፋቂ ክረምት መቶ እስክትመጣ ጨንቆኛል ከጓደኛም በላይ ነው ምቀርበኝ እንደው ብዙ ጊዜ አባባ እዚ ኑሪ ሲላት እንቢ ብላዋለች" የትውልድ ሀገራን የ ቤተሰቤን መሬት አልተውም ባይሆን ክረምት ክረምት እመጣለው"ይቺ የሁሌ የአያቴ መፈክር ነች እንደ ድንገት ክላክስ ተሰማን መኪያ ፈጠን ብላ ወጣችና እነ አባባ መሆናቸውን ስታይ በሩን ከፍታ መኪናው ሲገባ ዘጋችው እና እነ አባባ እስኪገቡ ከጠበቀች ብሀላ እማማን ተከትላ ገባች እነ እማማ ትንሽ ካረፉ ቡኃላ እራት በላልተን የዛሬው ምሽት በዚህ አለፈ፡፡ ጠዋት ላይ እንዴት እንደነጋ አላውቅም ብቻ የሞላሁት አላርም ድምፅ ማሰማቱን ጀመረ ስልኬን በዳበሳ ፈልጌ የሚጮኀውን አላርም አጥፍቼ እንደተኛው የክፍሌ በር በሀይለኛው ተንኳኳ የፋይሰል ስራ መሆኑ ስለገባኝ ዝም አልኩት ደግሞ እያንኳኳ "አንቺ አረ ተነሺ ዛሬ እኝኮን ቢያንስ ይለፍልሽ"ብሎ ቅድም ከሚያንኳኳበት ፍጥነትና ሀይል እየጨመረ "ዳኒ ተነሽሽ ወይኔ አረ ሴት ልጅ እስከዚ ሰአት አተኛም ቆይ ስታገቢ ምን ሊውጥሽ ነው"ብሎ የበሩን እጀታ ሲጫነው ተከፈተለት አንገቱን እያስገባ "አረ ዳኒ በአላህ ተነሽ ሰው ምን ይልሻል"አለ ይሄን ሁሉ ሲል ግን መልስ አልሰጠሁትም ነበር "ስታገቢ"ምትለዋ ቃል ግን ዶሮዬ ላይ አቃጨለች በቅፅበት ብርድልብሴን ከፊቴ እያነሳው "ስታገቢ"አልኩት ከት ብሎ እየሳቀ "እስቲ ምናለ ሌላውን ብትሰሚ በይ ተነሽ" ብሎን ትቶኝ ሄደ አይ ፋይሲ አልኩ በውስጤ የፈለገ ብንጨቃጨቅ አንድ ቀን ተሰዳድበን ወይ መቶኝ አያቅም እኔ ደሞ ነብሴ እስክትወጣ ነው ምወደው በቃ ገና ሳየው አንጀቴን ይበላኛል ለቤተሰቡ ያለው ፍቅር በተለይ ለ እማማ እሷም የልቡን ስለምታቅ ለሱ ነው ምታደላው አንድ ነገር ተፈጠረ "ፋይሲ" አንድ ነገር ከፈለገች "ፋይሲ"አይ እማማ አንዳንዴ እኔ ልጇ አልመስላትም መሰለኝ፡፡
እንደምንም ከአልጋዬ ተነስቼ ከክፍሌ አጠገብ ካለው መፀዳጃ ቤት ገብቼ ተጣጥቤ ከነ እማማ ጋር ቁርስ ለመብላት ስወርድ ማንም የለም የተበላበት ብርጭቆ እና የተበላበት የመመገቢያ ሰሀን ሱፍራው ላይ ተመለከትኩ 'እእ እነሱ ስለሌሉለት ነው እንዲ ሚቀውጠይ'አልኩ በውስጤ እነ እማማ ቁርስ እንደበሉ ገብቶኛል ግን የት ሄደው ነው? ብዬ እራሴን ጠየኩ ቁርሴን ለመብላት ወደቀረበው ሱፍራ(መመገቢያ ላስቴክ) ቀረብኩ ወዲያው ፋይሰል ከክፍሉ እየመጣ ሳሎን በር ላይ ቆሞ "ቶሎ ብይና እንሂድ"አለኝ የሸሚዙን ቁልፍ እየቆለፈ"በዚ ጠዋት የት ነው ምኔደው አንተ ልጅ ነቀልክ እንዴ"ብዬ የቀዳሁትን ሻይ ተጎነጨው "አረ ተነሺ ይበቃሻል እነ አባባ ሀናንን ሊጠይቁ ሊሄዱ ነዎ እማማ ሄዳለች አባባ ደሞ ሱቅ ሊከፍት ወቷል ቶሎ ኑልኝና እኔም በጊዜ እሄዳለው ብሏል በይ ተነሺ"ብሎኝ ጫማውን ወፈለግ ጀመረ ነገሩ ግራ ስለገባኝ "ፋይሲ ቆይ ሀናንን ወለደች?"አልኩት ድምፅን ከፍ አርጌ " አይ አንቺን እየጠበቀች ነው"አለኝ ሀናን ማለት የአባባ የእህቱ ልጅ ናት ካገባች 4 አመቷ ነው ግን ሳትወልድ ቆይታ አሁን እንደ አላህ ፍቃድ ተሳካላት ለዛ ነው ያካበዱላት ቁርሴን በላ በላ አረኩና ልብሴን ቀይሬ ከ ፋይሰልጋ አባባ ሱቅ ሄድን እንደደረስንም አባባ ወደ ሆስፒታል ሄደ እኔና ፋይሰል አምሽተን ሱቅ ዘግተን ወደቤት እየሄድን ሳለ ድምገት መኪናውን ሲጢጥጥ አርጎ አቆመው "ምነው ፋይሲ" አልኩት ደንግጬ
.....
.
.
.
ክፍል➌ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ነገ ረቡዕ ሙሃረም 9 ነው ሀሙስ ደግሞ ሙሃረም 10
10ኛውን ብቻ ከመፆም ይበልጥ የተወደደደው 9ኛውንም መፆም ነው ለማስታወስ ያህል
@Habibacalligraphy
ክፍል ሦስት
👣 ያልወለደች 🕊 እናት
:
:
:...ያልወለትእናልጥሩ ስሜት አይነበብም ደግሜ ጠየኩት"ፋይሲ እእ"አልኩት አይን አይኑን በስስት እያየው "ምንም ዳኒ ትንሽ ብዥ አለብኝ ልረጋጋ ብዬ ነው ያቆምኩት"ብሎኝ ወደ እኔ ዞረ ያየሁትን ግን ማመን ተሳነኝ እሱ ሳይታወቀው እየነሰረው ነበር "ፋይሲ አ.....ፍንጣህ እ....የደሞ ነው"አልኩት እየተንተባተብኩ አንድ ቀን መኪያ የፋይሰልን ክፍል ስታፀዳ ከ አልጋ ስር ሸሚዝ አግኝታ አሳይታኝ ነበር ሸሚዙ ደረቱ አካባቢ ቀይ ቀለም ይዟል ሁለታችንም ደነገጥን ፋይሰል ሲመጣም አግባብቼ ብጠይቀውም ጥርሴ ደምቶ ነው ብሎኝ ሊያሳምነኝ ሞከረ "ፋይሲ ወይ ሀኪም ቤት እንሂድ እየደሞ እኮ ነው ደሞ ሶፍትም ጨርሰሀል እቃው ባዶ ነው" የማረገው ግራ ገብቶኝ ከአይኔ የእንባ ጅረት ቁልቁል እየተምዘገዘገ "ዳኒ ደሞ አረ አታካብጂ አሁን ይቆማል እዙ አካባቢ ሱቅ ካለ ውሀ ብቻ እንግዛ ኪኒን አለኝ" ብሎ መኪናዋን ሊያስነሳ ከተደገፈበት ቀና ሲል ይብስ ከአፍጥጫው የሚወጣው ደም በሀይል ይወርድ ጀመረ ምን እንደማረግ ግራ ገባኝ ፋይሲ በእጁ የያዘው ደም ወደ ሹራቡ መንጠባጠብ ጀመረ አንደቴን በላኝ ያለኝ አማራጭ ሂጃቤን መቅደድ ነበር ያሰርኩትን ሂዳብ እየፈታው "ፋይሲ እኔን እሺ ወንድሜ ቆይ በዚ ትይዝበታለህ" ብዬ ከመኪናው ወርጄ ሂጃቡን የምቀድበት ድንጋይ መፈለግ ጀመርኩ ደግነቱ ብዙም ሳለፋ የእግረኛ ወንገድ ላይ አንድ ድንጋይ ተመለከትኩ በድንጋዩ የሂጃብን ጫፍ ከመታሁት ብሀላ በእጄ ቀደድኩት ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ሊያስቆመኝ አልቻለም ስሜን ለመጥራት ራሲ አቅም አጣ ወደ መኪናው ተመልሼ የቀደድኩትን ሂጃብ ሰጠሁት እና እጁ ላይ ያለውን ደም በመስኮት በኩል ወደውጪ አፈሰሰው በሂወቴ ደም እፈራለው በዛላይ የነስር ደም በዛላይ እፍኝ እፍኝ በደቂቃ የሚነስረው ሰው ማየት ይባሱን ያስፈራኝ ደሞ ወንድሜ መሆኑ ነው ከመኪናው የጎን ኪስ አንዲት ትንሽ ብልቃጥ እያወጣ "ዳኒ ውሃ አለኝኝ"እንጀቴን በላው እኛ ከቆምንበት በትንሽ እርቀት ሱቅ ይታያል ከኪሱ ብር አውጥቼ በምን ቅፅፈት ደርሼ እንደመጣው እንጃ ውሀ እና ሶፍት ይዤለት ወጣው ለካ አንዳንዴ ድንጋጤ ፈጣን ያረጋል ምነው ሁሌ እንዲ ብንሆን ብዬ ተመኘው
መዳኒቱን ሲወስድ የሚወርደው ደም እየቀነሰ ወጣ ትንሽ እንደተረጋጋ ሳይ "ወንድሜ እእ አሁንስ እየተሻለህ ነው"አይኑ ውስጥ ምላሽ አገኝ ይመስል አይን አይኑን አየዋለው "ደና ነኝ ትንሿ ግን መ

ንዳት ምችል አይመስለኝም ያለማመድኩሽ ለመቼ ነው ስለደረስን ቀይሪኝ"ብሎ በሩን ከፍቶ ወጣና ተቀያየርን የፈለገ ያለማምደኝ እንጂ ነድቼ አላቅም ግን ከፋይሲ ይበልጥ እያጣደፍኩት ከነፍን እቤት በር ላይ ቆመን ፋይሰል እጄን ይዞኝ "ዳኔ ፍቅር በአላህ እነ እማማ እንዳይሰሙ ይጨነቃሉ ደና ነኝ እኮ እሺ"ብሎ በአይኑ ተማፀነኝ ላስጨንቀው አልፈለኩም እና ተስማምተን ቤት ገባን እኔ ቀጥታ ወደሳሎን አመራው ፋይሰል ደሞ ልብስ ሊቀይር ወደ ክፍሉ ወጣ መኪያ ጊቢ ገብተን ፋይሰል ከመኪና ሲወርድ ስላየችው ደንግጣለች አይኗን እያፈጠጠች በድምፅ አልባ ቃላች በአይኗ ጠየቀችን እኔም ዝም እንድትልና የተፈጠረውን ብኃላ እኔ እንደምነግራት አስረድቻት ነው የገባነው ብዙም ሳይቆይ ፋይሰል ልብስ ቀይሮ መጣ እማማና አባባን ስሟቸው ከ እማማ አጠገብ ተቀመጠ "ስራ እንዴት ነበር"አለች እንደ ህፃን ፊቱን እያሻሸች "አልሀምዱ ሊላህ አሪፍ ነበር ያው አባባ እንዳለው ጊዜ ባይሆንም እናንተጋስ ውሎ?"አለ በስስት እያያት ሲያስቀኑ ቆይ አሁን እንዲ ሚሆኑት ማንን ለማስቀናት ነው "አራፍ ነበር የአክስታቹ ልጅ ልክ እንዳንተ ሸበላ ወንድ ዱብ አረገች ነገ ሄዳቹ ዘይሯት እሺ አበባዬ"ብላው ትክ ብላ ተመለከተችው የሌላ ጊዜ እኔ ብሆን አኩርፌ ክፍሌ ሄጄ ተኝቼ ነበር፡፡እህህ እቀናለዋ! ዛሬ ግን በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ሄጃለው አካሌ ከአ እማማና ፋይሲ አጠገብም ቢሆን አይኔ ቢያያቸውም ልቤ ግን የቅድሙ ክስተት ላይ ነው 'ልብ ካላየ አይን ቢያይ ዋጋ የለውም' ትል ነበር አያቴ ለካ እውነቷን ነው እንደድንገት የአባባ ጥሪ ከገባሁበት የሀሳብ ሸለቆ ጎትቶ አወጣኝ ለካ አባባ ደጋግሞ ሲጠራኝ ነበር "አረ አንቺ ልጅ የት ሄድሽ"አለኝ ስስ ትራስ እየወረወረብኝ "አረ አባባ የትም እዚው ነኝ"ብዬው እማማና ፋይሰል ምን እንደሚያወሩ ማዳመጥይ ጀመርኪ እማማ ለረዥም ደቂቃ ስትመለከረው ግራ እየተጋባ "አረ እማማ ምንድነው እንዲ ምታይኝ" ብሎ ወደኔ ተመለከተ
እማማ ቀጠል አርጋ "ፀሀይ ላይ ነበር እንዴ የዋልከው"አለችው አረ አይደለም ምነው ውዷ"አላት ፋይሲና እማማ ሲያወሩ ፍቅረኛሞች እንጂ እናትና ልጅ አይመስሉም እንዳንዴማስ አባባ ሁሉ ሳይቀና አይቀርም ብዬ እጠራጠራለው ከአፉ ቀበል አርጋ "እሺ አሞሀል እንዴ? በአንድ ቀን ጠቆርክ እኮ"ብላ ትክ ብላ አየችውና "ደሞ ፂምህን ተቆረጥ"ብላ ወደኔ እያየች "ዳኒ እእ ውሎ?"አለች "አይደል አሁን ነው የታየሁሻ እማማ እንዴ ቆይ ልጅሽ እሱ ብቻ ነዋ"ብዬ አባባ አጠገብ ተቀመጥኩ ብዙም ሳንቆይ መኪያ እራት አቀራርባ ተመገብንና ወደ ክፍላችን ገባን ክፍሌ ገብቼ ስለቅድሙ ክስተት ወደኀላ ተመልሼ እያሰብኩ እንቅልፍ ቢጤ ሸለብ አረገኝ እንደ ድንገት ፋይሲ ፋይሲ ተነስ ዳኒ አባባ የሚል ድምፅ ሰማው መኩ ነበረች ሁላችንም እሮጠን ስንመጣ ፋይሰል መሬት ላይ ተዘርሯል ከአፍንጫው ደም እንደ ቧንቧ ይንቆረቆራል...

ክፍል➍ ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል አራት
👣ያልወለደች 🕊 እናት👣
:
:
:...ያየሁትን ማመን ተሳነኝ ፋይሰል እንዲ ሲሆን አይቼው አላቅም እማማ ከአንገቱ ቀና አድርጋ የሲቃ ለቅሶ ታሰማለች ፋይሰል አይኑን ወደ ጣሪያው እያገላበጠ የጭንቀት እስትንፋስ ያሰማል ከአፍንጫው የሚወርደው ቀይ ቀለም አዘል ፈሳሽ ቀድሞ ይፈስ ከነበረበት ሀይል ጨምሮ ይጎርፋል ሁላችንም መላው ጠፋን ትንሽ እንደቆየን ፋይሰል ሰቅጣጭ ድምፅ አሰምቶ አይኑን ወደላይ እንደሰቀለ ፈዞ ቀረ "ፋይሲ ብዬ ከአልጋዬ ብድግ አልኩ ሰውነቴ ዛለ ፊቴ ውሀ እንደተቸለሰበት ሳፋ ውሀ በውሀ ውኖል እንደምንም ተፍጨርጭሬ ከአልጋዬ ወርጄ ወደ ፋይሰል ክፍል አመራው በሩን በዝግታ እያንኳኳው "ፋይሲ ፋይሲ" እያኩ ተጣሪው መልስ ሳጣ በሩን ከፍቼ ገባው ፋይል እልም ያለ እንቅልፍ ላይ ነው ትንሽ እንደመረጋጋት ብዬ ወደ ክፍሌ ተመለስኩ "ድንበርህን ጠብቅ "እንደተባለ ወታደር ለሊቱን ሙሉ እንቅልፍ በአይኔ አልዞር አለኝ ፈራሁ አንዱን ወንድሜን ማጣው መሰለኝ እንዳልናገር ቃል ባልገባ እናገር ነበር ግን ነገ ሀኪምጋ አብረን አንሄድም ካለኝ የግድ ለነ እማማ መናገር ግድ ሊሆንብኝ ነው እያልኩ ከራሴጋ አወጋሁ አይነጋ የለምና ነጋ ከሁሉም ቀድሜ ተነሳው መኪያ በጊዜ መነሳቴን ስታይ ተገርማ "ዳኒ ምነው ዛሬ በጠዋት? በሰላም ነው?"ብላ በጥያቄ አጣደፈችኝ እኔም ምንም ስለማልደብቃት ሁሉንም ነገርኳት ማታ ከፋይሰልም ጋር የተፈጠረውንም ጭምር ደነገጠች ለነ እማማ ካልነገርን አንገቴ ላይ ካራ ብላ ድርቅ አለች እንደምንም አስማምቼ የሀኪም ውጤቱን እንይና ከዛ እንደምንወስን ነገርኳት በዚ ተስማማን ያው መኩ ደስ ባይላትም ቁጭ ብዬ እንዳላያት ብዬ መሰራራት ጀመርኩ ከ አንድ ሰአት ቆይታ ብኃላ እነ እማማ ተነሱ እና ለባብሰው ወደ ሳሎን ገብ እማማ በጊዜ መነሳቴን ስታይ እየተገረመች "ምን ተገኘ ደሞ ዛሬ ያለመደብሽን"አለች እንደ ጨቅላ ህፃን ፊቴን እየዳበሰችኝ "ምንም እማማ ልለማመድ ብዬ ነው"ብዬ ፈገግ ለማለት ሞከርኩ እማማ ቁርስ ቀራርቦ እንዳለቀ ስታይ "መኩ ፋይሲ አልተነሳም?"አለቻት "እንጃ እማማ ልየው እንዴ"ብላ ስትነሳ "አይ ተይው ተነሺ እስኪ እይው ምን ሆኖ ነው ለወትሮ እንዲ አርፍዶ አያቅም"ብላ እንድነሳ በእጇ ገፋ አረገችኝ ደረጃውን እየወጣው እግሬ ቸብረከረከ ክፍሉ ገብቼ ምን እንደሆነ ለማየት አቅም ከዳኝ 'በባዶ ሜዳ ጭንቀት ሆሆ ምን ሆኜ ነው'ብዬ እራሴን አረጋጋሁና የፋይሰልን ክፍል አንኳኳው ደገምኩ ደጋገምኩ መልስ የለም በሩን ከፍቼ ስገባ ፋይሲ እልም ያለ እንቅልፍ ላይ ነው ለሊቱን እንዳልተኛ ገብቶኛል "ፋይሲ ተነስ ሰአት ረፍዷል እህህ" እያልኩት ብድርብሱን ከፊቱ እያነሳው "ውይ ትንሿ ነጋ እንዴ ቅይ እሺ አምስት ደቂቃ አይኔ እስኪከፈት"ብሎ ብርድልብሱን ለበሰው ትንሽ ላስቀው ብዬ "አረ ፋይሲ ተነስ ሰው ምን ይልሀል ወንድ ልጅ እስካሁን አይተኛም" ብዬ ብርድልብሱን ገፈፍኩት "አንቺ ሲንቢር እገልሻለው ውጪ"ብሎ እየፈገገ ትራስ ወረወረብኝ "እሺ ግን 5 ደቂቃ" ብዬ ወጣው ፋይሱ እንዲ ሲስቅ ልቤ ጮቤ ትረግጣለች እንጃ ደስስስ ይለኛል! እአእማማ ጋር ወርጄ እየለበሰ እንደሆነ ነግራያቸው ተቀመጥኩ እኛ ቤት አንድ ህግ አለ ሁሉም ሳይሰበሰብ እራትም ሆነ ምሳ ወይ ቁርስ አይበላም ትንሿ እኔ ሳልቀር ካልመጣው እጠበቃለው አሁንም የሆነው እሱ ነው ፋይሰል እስኪመጣ መጠበቅ ብዙም ሳይቆይ መጣ "አሰላሙ አለይኩም ደና አደራቹ"ብሎ አዘውትሮ ወደሚቀመጥበት ቦታ ሄዶ ቁጭ አለ እማማና አባባ ለሰላምታው መልስ ከሰጡት ብኃላ እማማ "ጓረምሳዬ ምነው ዛሬ በለሊት ተነሳህ"ብላ ፈገገች ፋይሲ ያ ሚያምረውን ሳቁን እየገለፈጠው "አይ እማማ ትንሽ እራሴን አሞኝ ነው"ብሎ መልሶ ያን ፈገግታውን ደገመው ቁርስ በልተን እንደጨረስን አባባ በር ላይ ሆኖ "ፋይሲ ናማስ" ብሎት የሆነ ነገር አወሩና አባባና እማማ ወደ ሱቅ ተያይዘው ሄዱ
ገና እነሱ እንደወጡ ፋይሰልን ላዋራው ወደ ቤት ገባው ክፍሉ ስለነበር ቀጥታ ወደዛው አመራው የክፍሉ በር ገርበብ ተደርጎ ተከፍቶል ቀስ ብዬ ክፋት አርጊ በሩ ላይ ቆምኩ ፋይሲ መስገጃ አንጥፎ በግንባሩ ተደፍቶ ይንሰቀሰቃል አሳዘነኝ የእህትነት አንደቴ አንሰፈሰፈኝ ከይኔ የእንባ ዘለላ የአይኔን መስመር ይዞ በጉንጮቹ ላይ ተረማምደው ወፊቴን አረጠቡት ስላላስቻለኝ ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ ፋይሰል ከተደፋበት መስገጃ ሲነሳ እሮጬ ወደክፍሌ ገብቼ በሬን ዘጋሁት በሩን እንደተደገፍኩ ቁልቁል ወርጄ መሬት ላይ ዘፍ አልኩ አቃተኝ ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ ፋይሰል ደንግጦ በሩን ያንኳኳል "ዳኒ ምን ሆነሽ ነው ማሬ በአላህ በሩን ክፈችው" እያለ ተማፀነኝ ስላላስቻለኝ ከፈትኩለት ከፋይሲ ጀርባ መኩ ነበረች ተያይዘው ገቡ"በወንድም እንዲ ድጨከናል ቆይ በጭንቀት ብሞትብሽስ"ብሎ ሲለኝ ተጠምጥሜበት ማልቀስ ጀመርኩ
ፋይሲ ግራ ተጋብቶ "ምን ሁነሽ ነው በአላህ አታስጨንቂኝ"ብሎ አይን አይኔን ያየኛል እንድነግረው ተማፀነኝ "አይሲ........
.
.
.
ክፍል➎ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል አምስት
👣ያልወለደች🕊እናት👣
:
:
: "ፋይሲ ምን ሆነህ ነበር ምታለቅሰው በቃ ክፍልህ ስመጣ እንደዛ ሆነህ ሳይህ አላስቻለኝም"ብዬ ከአይኔ የ እንባ ዘለላ አራገፍኩ ፋይሰል እንደመደንገጥ እያለ "አረ ዳኒ ምንም ሆኜ አይደለም ምን ታካብጃለሽ በይ ተነሺና ተጣጠቢ፣ለባብሺ ከዛ እንወጣለን"ብሎ ሊወጣ ሲል "ፋይሲ"አልኩት ፈራ ተባ እያልኩ "ወዬ ዳኒ ምነው?"ብሎ ቆመ "መጀመሪያ ግን ሀኪም ቤት ደርሰን እንምጣ"ብዬው በአይኔ እማፀነዋለው "እንዴ ለምን ዳኒ ምን እንሰራለን ሀናን እኮ ከሀኪም ቤት ወታለች" ባላወቀ ዳር ዳር እንደሚሄድ ስለገባኝ "ፈይሰል አትቀልድ እንሄድና በሽታህ ምን እንደሆነ እናጣራለን ቆይ መሞት ነው ምፈልገው"እያልኩ ጮህኩኝ "ፋይሰል ነው ያልሽው ዳኒ? እንዴት አስችሎሽ በሄወቴ እኮ እኔ እንደዚ ብለሽ የጠሪሽኝን ቀን አላስታውስም ዛሬ ምን ተገኘ.."እያለ ሲጮህ መኪያ እየሮጠች መጣች ከተጠርን እኔና ፋይሰል የመጀመራያ ጭቅጭቃችን ነበር መኩ ያጨቃጨቀን ነገር ሴለገባት"ፋይሲ እሺ በልና ሂድ እኛንም አታስጨንቀን"ብላ አስማምታ እንድንሄድ አሳመነችው ወዴያው ለባብሼ አንድ የግል ሆስፒታል እየሄድን ሳለ እንደ ድንገት እማማ ደወለች እና የት እንደሆንን ጠየቀችን ሀናን ጋር እየሄድን እንደሆነ ነግራያት ስልኩ ተዘጋ ከሰአታት ብሀላ ሆስፒታሉ ደርሰን ወደ ውስጥ ዘለቅን ልብ ፈራ እጆቼ መንቀጥቀጥ ጀመሩ ገና ሀኪም ቤቱ ለራሱ ሲገባ ሚከብድ ነገር አለው ደግነቱ ወረፋ አልነበረም ካርድ አውጥተን ስማችን እስኪጠራ መጠባበቅ ጀመርን ከኛ በፋች 3 ሰዎች እየገብ ወጡ በ አራተኛው "ፋይሰል ነቢል"ሲባን ብድግ አልኩ "የተጠሪሁት እኔ አንቺ ምን ቤት ነሽ" ብሎ ተነሳ አብሬው ልገባ አልፈለገም ገብቶኛል "አብረን ነው ምንገባው" ብዬው ወደ ዶክተሩ ጋር ገባን የ ዶክተሩ ክፍል እንደገባን ሁሉ ነገር ጨለመብኝ ፈሪው ፋይሲን እዚው የማጣው መሰለኝ 'ወይኔ ግን ሁሉም እህቶች እንደኔ ወንድምቸውን ይወዳሉ፤በዛላይ እንደፋይሲ አይነት ወንድም ያላቸውስ ምንኛ ታድዋል'እያልኩ ለራሴ አወራሁ ዶክተሩ አብረን ስንገባ ሲያይ እየተገረመ በተራ በተራ ያየናል
ዶክተሩ፡"እሺ ፋይሰል ምን ነበር ኬዝህ?"አለ ጠንከር ባለ ድምፅ
"ያው ይነስረኛል" አለ የኔው ጉድ እየተቅለሰለሰ
ዶክተሩ፡"በቀን በቀን ነው ወይስ..?
"አይ አልፎ አልፎ በ አስራ አምስት ቀን እንደዛ ነገር"አለ ፋይሰል የዶ ክተሩን ጥያቄ እየተሰላቸ
ዶክተሩ፡እሺ ሊነስርህ ሲል ሚሰማህ ስሜት አለ?"አሁንም ጠየቀ
"አረ የለም..."ብሎ ሳይጨርስ ከአፉ ቅብል አርጌ አረ "አረ ዶክተር ያዞረኛል ይላል"ብዬ ዶክተሩን አየሁት ከዛ አንድ 3 ጥያቄ ካከታተለ ብሀላ ደም እንዲመረመር ወደ ላቦራቶራ ላከን ደሙን ሰተን ውጤት መጠባበቅ ጀመርን እኔ ፈርቻለው አስሬ ቁና ቁና እተነፍሳለው 30 ደቂቃው እንደ 30አመት ረዘመብኝኝኝኝ እንደምንም የሞት ሞቴን 30 ደቂቃ ተቀመጥኩ ላብራቶራስቱ ውጤቱን ይዞ ወደ ዶክተሩጋ ገባ ከ ሁለት ሰዎች ብሀላ ተጠርቶ ገባን
ዶክተሩ፡ውጤቱን አብሩቹ ልሰሙ ፍቃደኛ ናቹ"አለ በአወንታ ጥንቅላቴን ከላይ ወደታች ነቀነኩለት
ዶክተሩ፡"አንተስ?" ብሎ ፋይሰልን አየው
"በቃ ይነገረን" አለ ውስጡ መፍራቱን ንግግሩ ያሳብቃል.....

ክፍል➏ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል ስድስት
👣ያልወለደች🕊እናት👣
:
:
:...ጎሮሮውን እንደመጠራረግ አለና"well እንግዲ ፋይሰል በሽታህ ትንሽ ቆይተህበት ቢሆን ኖሮ ለህይወትህ አስጊ ነበር አሁንም ቢሆን ግን ደና ነህ ማለት አይደለም በሽታው አደገኛ ስለሆነ በጥንቃቄ መዳኒትህን መውሰድ ግድ ይልሀል"አለና ወረቀት ቢጤ ላይ ጫር ጫር አረገ "እንካ ይሄን መዳኒት ግዛ መቼም አንተን ለሚያክል ጎረምሳ በአግባቡ ውሰድ አይባልም አይደል"ብሎ ፈገገ
ዶክተሩ ቀለል አርጎ ለመናገር ቢማክርም እኔ ግን የተራራ ያህል አግዝፎት ጭንቅላቴ ላይ እንደከመረብኝ ነገር ንግግሩ የጭንቅላቴን ሚዛን እያሳተ እንደሰካራምም ያንገዳግደኝ ጀመር እኔ ተረብሼ ፋይሰልን ልረብሸው ስላልፈለኩ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ወደነ ሀናን ቤት እንድንሄድ ጠየኩት እሱ ዶክተሩ ያለውን ከቁብም ሳይቆጥረው ጭራሽ የሌለ ደስ ብሎታል ሀናን ቤት እንደደረስ መኪናውን አጥሩ ጥግ አቁመን ወረድን ሀናን ስታየን ደስ አላት ያቺ ቀጫጫዋ ሀናን አሁን አምሮባት ሰውነቷ ሞላ ብሏል ቀልታለች በቃ እንቡጥ ፅጌሬዳ ነው ምመስለው ገና ሳያት ቀናው እናት መሆን አማረኝ ምነው አግብቼ ወልጄ በነበር አስባለኝ የታቀፈችውን ልጅ እመተኛው ላይ አስቀምጣ ሳመችኝ ከ ፋይሰል ጋር በቃል ሰላምታ ከተለዋወጡ ብሀላ እኔ አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጥኩ ፋይሲ ደሞ መሬት ላይ የተፈረሸው ፍራሽ ላይ ተቀመጠ ብዙም ሳይቆይ የሀናን ባል መጣ ከፋይሰልም ከኔጋም ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው የዛሬ አመት ልጅ እንቢ ብሏቸው ሀይለኛ ሰደቃ አውጥተው ነበር የዛኔ ነው እኛም የተገናኘነው ከፋይሰል ጋር ተቃቅፈው ሰላምታ ተለዋወጡ እኔን መጣና በቃላት ሰላምታ አጣደፈኝ በነገራችን ላይ የ ሀኒ ባል ፈታ ያለ ሰው ነው እና እስፔሻል ዶክተር ነው እኔም ከሀናን ጋር የቆጥ የባጡን ሳወራ ፋይሲም ከ ነቢል ጋር እየተጨዋወትን በመሀል የግዴታ ሰላቶችን ለመስገድ እየተነሳኝ 1 ሰአት ሲል ተሰናብተናቸው ወጣኝ እንዲ እንዲ እያለ ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራቶችን አርግዘው እየወለዱ ሀናን ከወለደች 4 ወር ሆናት ፋይሰልም መዳኒቱን በአግባብ እየወሰደ ከበሽታው ድኗል እንደ ድንገት አንድ ቀን ከረፋዱ 5 ሰአት ላይ አንድ ስልክ ወደ እማማ ስልክ ተደወለ የማይታወቅ ቁጥር እማማ ስልኩን አነሳችው "ሄሎ"አለች ከውስጥ ያለው ሰው ድምፅ ባይሰማኝም የሆነ መርዶ እንዳረዳት ያሳብቃል "ምን ብላ ስልኩን ለቀቀችው እኔም አብሪያት ክው አልኩኝ ለካ በሂወታችን የኛ የምንላቸው ሰዎች ሲጎዱ ወይ አደጋ ውስጥ ሲገብ ብቻ አይደለም ለካ የሚያስደነግጠን ለካ ድንጋጤያቸውም ያስደነግጠናል እማማ ክው ብላ ሳያት የኔም አሞቴ ፈሰሰ እማማ በሂወቷ እንዲ ክው ስትል አይቻት አላቅም ለዛ ደነገጥኩ "እማማ ምን ተፈጥሮ ነው"አልኳት ለመስማት አቅሙ ባይኛረኝም እሷን ለማረጋጋት እማማ ዝም አለችኝ "እማማ እእ?"አልኳች የሞት ሞቷን "ያይኔ አበባ" ብላ እንባዋን አጉረፈረፈችም በጣም ስላስጨነቀችኝ "እማማ ማልቀስ መፍትሄ አይሆንም ምን ተፈጥሮ ነው" አልኮት እማማ ያይኔ አበባ ምትለው ፋይሰልን ነው "እማማ ፋይሲ ምን ሆነ ተናገሪሪ"አልኳት እየጮህኩ "ከሰው ተጣልቶ እስር ቤት ነው"አለችኝ እርፍ! "ምን"
ብዬ የቆምኩበት ቦታ ላይ ደርቄ ቀረው "ቶሎ በይ ለ አባባሽ ደውይ ብላ ስልኳን ሰጠችኝ እጄ ተንቀጠቀጠ ስልክ ለመክፈት እስክቸገር! እማማ ሞተ እንደተባለ ሰው ቤት ውስጥ እያለቀሰች ትዟዟራለች እማማ የ ፋይሰል ነገር አያምጣው ነው ልክ በስለት እንዳገኘችው ነገር ነብሷን ትሰጠዋለች አይ እማማ ሁሌ እንዲ የምለው ለፋይሰል ያላትን ስሜት ስለማቅ ነው አንዳንዴማ እኔ ከነመፈጠራ ምትረሳኝ ይመስለኝና እፈራለው አባባ ጋር ደመልኩለት ወዲያው ወደ ፋይል ጋር ሃድ....

ክፍል ➐ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል ሰባት
👣ያልወለደች🕊እናት👣
:
:
:....ከትንሽ ደቂቃ ብሀላ አባባ ደውሎ ከ ፋይሰልጋ እየመጡ እንደሆነ ነግሮኝ ስልኩን ዘጋው እኔም እማማን ለማረጋጋት መጣጣር ጀመሬኩ እማማ ግን አይኑን ሳላየው ወሬት አይነካኝም ብላ በር ላይ ቆማ ትጠባበቅ ጀመር
ከግማሽ ሰአት ቅይታ ብሀላ እነ አባባ ቤት ደረሱ ፋይሰል ከንፈሩ ቆስሏል እንጂ ምንም አልተጎዳም እማማ ስታየው ከደስታዋ ብዛት እንደ ህፃን ልጅ ቦረቀች አመሻሽ ላይ ሁሉም ከተረጋጋ ብሀላ እማማ በምን ምክንያት ይህ እንደተፈጠረ ጠየቀችው መልስ ሳይሰጣት ተነስቶ ሊወጣ ሲል እማማ "ፋይሰል"ብላ ጮኀች ሁላችንም ደነገጥን ምክንያቱም አንድ ሰው ወትሮ ያለመደበትን ሲያረግ ያስደነግጥም አይደል አሁንም የሆነው እሱ ነው እማማ "የአይኔ አበባ" የምትለው ወንድሜ አሁን በመታወቂያ ስሙ "ፋይሰል"ቢላው እርፍ ደንግጦ ቆመ በር ላይ እንደቆመ ወደ እማማ ዞሮ "ምን ፋይሰል ነው ያልሽኝ እማማ"አለ ሁሉምም ግራ ተጋብቷል "አዎ ፈይሰል የኔ የአይኔ አበባ እንደዚ ጋጠወጥ ሆነ ብዬ ማለት ይከብደኛል ጭራሽ እያዋራሁክ ጤለኀኝ ትነሳለህ "አለች በቁጣ እማማ መናደዷ ስለገባኝ ለማረጋጋት "በቃ እማማ ደሞ እስር ቤት ቀይረውት ይሆናል"አልኳት ለማሳቅ እየጣርኩ በዚ ሆኔታ ጠዋት ደረሰ እማማና ፋድሲ በማታው ነገር ተቀያይመዋል ቁርስ ራሱ ሳይበላ ነው የወጣው የት ሄዶ ነው ጨነቀኝ እማማ እንደተነሳች ወዲያው ጠየቀችኝ እንደወጣ ነገርኳት ስልኩ ላይ ስትደውል ስልኩ ዝግ ነው ይብስ የማታው ንዴቷ ጨመረ ቁርስ በላልተው ከ አባባ ጋር ሱቅ ወጡ የነሱን እግር ጠብቄ ስልኬም አነሳውና ፋይሰል ጋር ደወልኩ ስልኩ ይጠራል ግን አይመልስልኝም ደግሜ ስደውል "ሄሎ ዳኒ ሲቅ ህኜ ነው ሰው እያስተናገድኩ ነው ብሀላ እደውላለው"ብሎ ዘጋው አሁን ትንሽ እንደመረጋጋት አልኩ ምክንያቱም ሱቅ ከፍቶ ስታየው ትንሽ ትረጋጋለች ብዬ አሰብኩ ከአንድ ሰአት ብሀላ እማማ ደወለችና ፋይሰል ሱቅ መሆኑን ነግራኝ ዘጋችው አዪ የኔ ምስኪን እናት ቀድሜ ማወቄን አላወቀችም!አራት ሰአት ሲሞላ እኔም ለባብሼ ወደ ትምህርት ቤት ሄድኩ ትምህርት ቤት ስደርስ ጨነቀኝ የልቤ ምት ከወትሮ ተለየብኝ 'ምን ሊፈጠር ነው'አልኩ ለራሴ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ትምህቱንም ሳልማር ወደ ቤት ተመለስኩ መኪያ ወዲያው ስመለስ ግራ ገቦትና "ምን ረሳሽ ?ዲኒ መቼም አንቺ ቀልብ የለሽ"ብላ ጠየቀችኝ "ባክሽ መኩ ልቤን ጭንቅ ሲለኝ ነው የተመለስኩት ጥሩ ሙድ ላይ አይደለሁም በቃ ልብሴን ልቀይርና አግዝሻለው" ብያት ወደ ክፍሌ ወጣው ልብስ ቀይሬ ከክፍል ልወጣ ስል ስልኬ ትዝ አለኝና ከቦርሳዬ አወጣሁት 5 ሚስኮል አለው አባባ ነው ክው ብዬ ቀረው ልቤም ያለወትሮ እንደዚ አልተረበሸም ስልኬ ብር ስለሌለው መኪያ እንድታስደውለኝ ወደ መአድ ቤት ስገባ መኪይ "ዳና አባባ.."ብላ ሳጨርስ "ምን ሆነ" አልኳች መኪያ ግራ ገብቷት "አረ ዳና ተረጋጊ ስልክ አታነሺም ዛሬ ትንሽ እቃ ቤት ስለሚወጣ መጋዜኑን አስለካክሉት ብሏል"አለችኝ ኡፍፍፍፍ ተረጋጋው አባባ መጋዘን የሚለው ከቤታችን ጀርባ እቃ ማስቀመጫ ይሆናል ተብሎ የተሰራው 5በ 5 ክፍሏን ነው የዋዛ እንዳትመስላቸለ ብዙ ኮተት ትይዛለች አልፍ አልፎ ስለምትከፈት አቧራዋ የጉድ ነው መኩ ስራ እየሰራች ስለነበር ከአባባ ክፍል ውስጥ ቁልፉን አውጥቼ መጋዜኑን ከፈትኩት ከቧራ ብቻ ሆኗል ይንፈስጠትና ይጠረጋል ብያ ከፈት አርጊ ተውኩት ትንሽ እንደቆየ መኩ መታ ማፀዳዳት ጀመርን እንደድንገት መኩ የሆነ የተጠቀለለ ልብስ ስታይ ከተወሸቀበት ጎትታ እያወጣችው "ዳኒ ይሄ የፋይሲ አይደል"ብላ አሳየችኝ "አው በቅርብ የገዛው ቲሸርት እኮ ነው አይ እሱ አሁን ምን ሆነ እዛጋር ወርውሪው ይታጠባል"ብያት ለመኩ ጀርባዬን ሰጠው ወዱያው መኪ በጩኀት ቀወጠችው በቅፅበት ዞር ብያ አይኗ ያለበት ቦታ ሳይ ክው ብዬ ቀረ
.
.
.
ክፍል➑ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
Forwarded from Sarah Calligraphy (ĤĄŊÏŸª) via @like
🎁 Hayat 🎁

[ From Dessie ]

[ code: #A5 ]


@saracalligraphy
● እንዲህ አይነት አለባበስ የሚከተሉ ሙስሊም እህቶችን ለማስታወስ ያህል
ይህ ሂጃብ አይደለም 🚫🚫
ሂጃብን እንዴት አርገሽ እንደምትለብሺ መመሪያ የሚሰጥሽ ፋሽን መሆን የለበትም። ኢስላም በዚህ መልኩ አይደለም ሂጃብን እንድትለብሺ ያዘዘሽ፤ ሂጃብ ማለት ፀጉርን መሸፈን ብቻ ሳይሆን አካልሽን መሸፈንና አለመገላለጥ ነው !!
😥 በአሁኑ ሰዐት ግን በሚያሳዝንና በሚያሳፍር መልኩ አብዝሃኛው ሙስሊም ልጃገረዶች ከየት እንደመጣ በማይታወቅ ፣ሀያዕን በማይገልፅና ጋጠወጥነትን አጉልቶ በሚያሳይ የአለባበስ ስርዐት ውስጥ ተዘፍቀዋል ንቁ! ንቁ! ንቁ! አላህን ፍሩ
ይህ ሂጃብ አይደለም ከመስፈርቱም አንዱንም አያሟላም። ይህ አራዳነትና ውበት የሚመስላችሁ ሴቶች ይህ አለባበስ ክብርን የሚገልፅ ሳይሆን ጋጠወጥነትንና ርካሽነትን የሚገልፅ ነው !!

◇ እናም ጊዜው ሳይረፍድ በፊት ወደ አላህ እንመለስ ትክክለኛውንም የሂጃብ አለባበስ እንከተል ።
አላህ ሁላችንንም ይምራን 🤲
www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ይህን ካሊግራፊዬን ሳየው ሁልጊዜም አዲስ ይሆንብኛል ወላህ 🥺
|አላህ| |Allah| |الله|
አንተ ጌታዬ መሆንህ ለእኔ በቂ ክብር ነው ፣ ባሪያህም መሆኔ ለእኔ በቂ ኩራት ነው ፣ አንተ ለእኔ ልክ እንደምወደው ነህ ፣ ስለዚህ ወደምትወደው ምራኝ 🤲
احبك ربي 🥺

JOIN us 👉👉 @Habibacalligraphy
ክፍል ስምንት
👣ያልወለደች🕊እናት👣
.
.
.
...የፋይሰል ቲሸርት በደም ተጨማልቋል ማመን አቃተኝ ትላንትና ጨይቄው መድሀኒቱ ካለቀ ብሀላ እንዳልነሰረው ነግሮኛል እየዋሸኝ መሆኑ ገብቶኛል መኩ ወደኔ እያየች "ዳኒ ፋይሲ አሁንም ያመዋል ማለት ነው"አለች እንባ ያቀረረውን አይኗ አይኔ ላይ ጥላ መልስ ሳልሰጣት የፋይሰል ክፍል ሄድኩ በሩን ለመክፈት እጀታውን ስስበው እንቢ አለኝ ተቆልፎል! ወትሮ ያለወደበት ለምን? የሆነ ነገርማ አለ ብዬ አሰብኩ ቀኑን ሙሉ በጭንቀት ስብሰለሰል አመሻሽ ላይ ሦስቱም አንድላይ መጡ ጊቢ መኪና አቆሙና ወዱ እማማና ፋይሲ ለመታረቃቸው እቺን ታክል አልተጠራጠርኩም ጭራሽ ተቃቅፈው ነው ወደ ቤት የዘለቁት አባባ ደሞ ዛሬ ፊቱ ደና አይደለም ጥቁርቁር ብሏል ገና ከመግባቱ ክፍሉ ገባና ተኛ እራት ቀርቧ ከአሁን አሁን ይመጣል ቢባል ዘር አልል አለ እማማ"ዳኒ አባባ እራት እየተጠበቅክ ነው ምን መሆንህ ነው በይው"አለች የእማማን ትዛዝ ተቀብዬ ወደ ክፍሉ አቀናው አባባ ያቃስታል "ምን ሆነህ ነው አባባ አመመህ እንዴ"አልኩት አተነፋፈሱ ያስፈራል "ደና ነኝ ዳኒ ድካሙም የጨማምሮ ነው ያደከመኝ እናንተ ብሉ እኔ ዛሬ ይቅርብኝ ይልቁንስ ወተት ካለ አምጪልኝ " ብሎ ላከኝ መኩን ስጠይቃት እንደሌለ ነገረችኝ ፋይሰል ከሱቅ እንዲያወጣ ስነግረው "መሽቷል" ብሎ ግግም ሲል እኔና መኩ ልንገዛ በር ላይ ስንደርስ መጣና "አቦ ነይ ተመለሺ በዚ ማታ የት ልትሄዱ ነው" ብሎ ወጣ ብዙም ሳይቅቆይ ይዞለት መጣ እንደ ዴንገት እማማ እራት እየበላን የትላንቱን ጥያቄ አነሳችቀት ፋይሰል እንደትናንትናው ጥሏት አልወጣም "ባንቺ ለመጣብኝ አይደለም መታሰር እገደላለው አንቺን እኮ ነው የሰደበብ"እያለ ለምን እንደታሰረ ተናገረ እማማ ነገሩን ለማጣራት "እኔን እንዴት?" አለች "በቃ እማማ አለፈ እኮ ሆሆሆሆ"አለና ለማስቀየስ ሌላ ነገር መቀባጠር ጀመረ አይነገ የለምና ነጋ ጨዋት ላይ አባባን ሳየው ፊቱ ልክ አይደለም "አባባ ደና ነህ አልኩት" ፊቱ ላይ የሚያስጨንቅ ገፅ ይታያል "ምንም አልሆንኩም ውዴ አትጨነቂ"ብሎኝ ሊወጣ ሲል "አባባ"አልኩት አንዳች ነገር እንደምለው ገብቶታል "ወዬ ዳኔ" አለኝና የሳሎን በር ላይ ቆመ "አባባ ካመመህ ሀኪም ቤት እንሂድ እእ"አልኩት አይንን እያቅለሰለስኩ "ቆይ ትንሽ ልየውና ከባሰብን እሄዳለው "ብሎ ከቤት ወጣ 'ምንድነው ጉድ በዚ ፋይሰል በዚህ አባባ ምን ጉድ ነው እየተፈተንን ነው እንዴ" አልኩ ለራሴ ዛሬ እማማ እቤት ናት ፋይሰል በጠዋት ሱቅ ሊከፍት ወቷል ከእማማ ጋር ገበያ ሄደን አንዳንድ የቤት እቃ ገዛዝተን ተመለስን እቤት ስንገባ መኪያ ቡና አፈላልታ ምሳ አቅርባ ጠበቀችን እማማ ደስ አላት ለነገሩ መኩ እማማን ሁሌ እንዳስደሰተች ነው እንደው እማማ ለ አጎቷ ልጅ ልትዳራት እንዳሰበች ቅድም ነግራኝ ነበር
ድክም ስላለን ተጣጠብንና የዙሁርን(ከ 6 ሰአት ብሀላ የሚደረገውን ስግደት) ሰግደን አንድላይ መመገብ ጀመርን እንደ ድንገት እማማ "መኩ"አለቻት "ወዬ እማማዬ"አለች መኩ እማማ ሁሌ ስትጠራት መልሶ ይሆ ነው ደሞኮ ሲያምርባት እማማ ምን ብላ እንደ ምትጀምር ግራ ገብቷቶል "እንደው የቅርብ ዘመድ ምትይው ሰው አዲስ አበባ የለም ማለቴም አጎት አክስ ምናምን" አለቻት እማማ ዳር ዳር እየሄደች ነው "መኪያ እንደማቀርቀር ብላ "እማማ ታሪኬን ሁሉ ታቄ የለ እኔ ማንም እንደሌለኝ ብላ ከአይኗ የእንዳዋን ዣረት ማፏፏት ጀመረች እማማ ደንግጣ "መኩ እዚ ቤት ስትኖራ አንድም ቀን እንደባዳ ቆጥረንሽም አይተንሽም አናቅም እና ምንም እንዳይከፋሽ ደሞ ምትፈልጊውን ነገር በግልፅ ተናገራ እሺ እኔም ውለታሽን እንዴት እንደምከፍል እንጃ አላህ ውለታሽን ይመልስልሽ አላህ ምርጡን ትዳር ይስጥሽ"ብላ ጀርባዋን ደባበሰቻት መኪያ ግራ ተጋብታ "ትዳር እማማ?"አለች በመገረም ድምፅ "ምነው መኩ ገና እኮ ልጅ ነሽ ታገቢያለሽ ትወልጃለሽ "አለች ዳር ዳር እያለች መሆኑ ገብቶኛል መኩ በግርምት "አረ እማማ ዛሬ ደሞ ጨዋታሽ ሁላ ተቀይሯል ሆሆሆ" ብላ ልትነሳ ስትል እማማ "መኩ"አለቻት መኪያ ልትነሳ የነበረችው እየተቀመጠች "ወዬ እማማዬ"አለቻት እማማ ሳንባዋ ውስጥ የተቃጠለውን አየር ኡፍፍ ብላ ካወጣች ብኃላ "ምን መሰለሽ የነጎቴ ልጅ መሀመድ ሊያገባሽ ይፈልጋል"አፈነዳችም! መኪያ ከተቀመጠችበት በቅፅበት ብድግ አለች ቆሌ የሚገፍ አነሳስ!..
.
.
.
ክፍል➒ #ይቀጥላል......


JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል ➒(ዘጠኝ)
👣ያልወለደች🕊እናት👣
:
:
:....እማማና እኔ አብረናት ቆምን መኩ "አልሀምዱሊላህ"አለች እኔና እማማ ተያየን የግርምት መተያየት! መኩ ምንም ሳትለን ወደ ክፍሏ አመራችና መስገጃዋን አነጥፋ በግንባሯ ተደፍታ እያለቀሰች ጌታዋን ማመስገን ተያያዘች እኔ ነገረ ስራዋ ስለገረመኝ ተከትያት ሄጄ እስክትጨርስ ጠበኳት እንደጨረሰች "መኩ"ብዬ አይኔን ፍጥጥ ቅንድቤን ሰቀል አደረኩት መኪያ እንደተገረምኩ ስላወቀች ከተቀመጠችበት ማንጣፏ እየተነሳች "ነይ ዳኒ እዚች ጋር ቁጭ በይ ሁሉንም ልንገርሽ"ብላ እየጎተተች የአልጋዋ ጠርዝ ላይ አስቀመጠችኝና መናገር ጀመረች "ዳኒ እኔ ካየሁት ጀምሮ በጣም ወድጄው ነበር ምነው ባሌ በሆነ ብዬ እስክል ድረስ ያ ልጃገረድን የሚያስንቅ አይናፋርነቱ የንግግሩ ማማር አርቆ አሳቢነቱ...አረ ዳኒ ምን ልበልሽ በቃ ያ አላት ብቻ አልሀምዱሊላህ"አለች እውነትም በጣም ተደስታለች መኪያ እኔ እስከማውቃት ድረስ አንድም ቀን እንዲ ፊቷ እያበራ ስትስቅ አይቻት አላቅም እና ተገረምኩ ቀናቶች ሳምንታትን አርግዘው እየወለዱ ወራቶች ተቆጠሩ መኪያና መሀመድ ሊጋቡ የ አንድ ወር ቆይታ ቀርቷቸዋል ዛሬ እኛ ቤት ሁሉም ተሰብስቧል አክስቴ(የሀናን እናት) ሀሩን ከነ ቤተሰቡ መኪያ ሁለት የፋይሰል ጓደኞች ሁሉም ተሰብስቧል ነገር ግን ሴትና ወንድ አብሮ አይደለም እነ አባባ ትልቁ ሳሎን እኛ ደሞ ከነ አባባ ክፍል የሚያንስ ክፍል ውስጥ ነን ስላልተቀላቀልን ሁሉም በነፃነት እያወራ ነው እኔና ሀናን አጠገብ ለአጠገብ ተቀምጠን አፍ ለአፍ ገጥመን እያወራን ነው መኩ "ዳኒ" አለች አልሰማኀትም ነበር ደጋግማ ጠራችኝ እማማ ስለሰማቻት "አንቺ እየጠራችሻ አይደል"አለችኝ ከሀናን ጋር የያዝኩትን ወሬ ትቼ ወደ መኪያ ዞሮኩ እራት እንድናቀርብ ነው መሰል ጠቀስ አረገችኝ ሀኒን መጣው ብያት ወጣው በር ላይ እንደ ደረስኩ እንደ ድንገት ሀሩን ወደ መፀዳጃ ቤት ሊሄድ ሲወጣ ተገጣጠምን "ቀጮዬ አሰላሙ አለይኩም አለኝ"እቤት መምጣቱን እንጂ አልተገናኘንም ነበር "ሀሩኔ ጀግናዬ ወአለይኩምሰላም ወራህመቱላ "ብዬው ጥቂት ደቂቃ ካወራን ብኀላ ተለያየን መዐድ ቤት ስገባ መኩ ሁሉንም ነገር አቀራርባ ጨርሳለች እጅ ሚያስቆረጥም ምግቧን ለመቅመስ ሁሉም ጓግቷል እንደጓጓ አልቀረምና ሁሉም የቀረበለትን ጥርግ አርጓ በላ ትንሽ እንደቆዩ ሁሉም በተራ በተራ እየወጡ እየተነሱ ወደ ቤታቸው ገሰገሱ እማማና አባባ ቀኑን ድክም ስላላቸው ወዲያው ወደ ክፍላቸው ገቡ ሀሩን እና ፋይሰል እንደለመዱት ቴሌቭዥን ላይ ተተክለው ይንከተከታሉ እኔና መኩ እኔ ክፍል ወጥተን ስለሰርጓ ማውራት ጀመርን መኩ በጣም ጎግታለች ነገ ከ መሀመድ ጋር ተገናኝተው ሚጨርሱትን እንዲጨራርሱ እናቴ ነግራታለች እንደ ድንገት "ፋይሲ ፋይሲ ፋይሲ በአላህ ተነስ" የሚል ድምፃ ይሰማን ጀመር ሀሩን ነበር ተሯሩጠን ወጣን እነ እማማም መጡ ፋይሰል ምንጣፉ ላይ ተዘርሯል ከአፍንጣው የጉድ ደም ይንፏፏል ሀሩን ከአንገቱ ቀና አርጓት እንደሴት ያለቅሳል እማማ ስታየው እራሷን መቆጣጠር አቅቷት መሬት ላይ ተዘረረች "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፋ"ይሉሀል ይሄ ነው ማናችን ከማን እንሁን እኔማስ ደርቄ ቀረው እዛው አንድ ቦታ ላይ እንደቆምኩ አይኔ ብቻ እያየ ፋይሰልን ይዘውት ወጡ ሁሉም ተደናግጦል ፋይሲን ይዘውት ሲመጡ የመጨረሻዬ መሰለኝ ዳግም ሲስቅ ላላየው እንደሆነ ተሰማኝ ዳግም በነገር እየተጎሻሸምን የማንጨቃጨቅ መሰለኝ ተስፋዬ ጨለመ እማማን እኔደምንም መኪያ እንድትነቃ ካረገቻት ብኃላ ተያይዘን ወደ ሆስፒታል አመራን ፋይሲ ድንገተኛ ክፍል ነው ነገረሶች ዶክተሮች ታካሚን ለመታደግ ይሯሯጣሉ 'የት ነኝ' አልኩ ለራሴ አይኔ ይይ እንጂ በደመነፍስ ነበር ምጎዘው ነገሮችን መደኀላ መለስ ብዬ አሰቡኩ ከግራ በኩል መኪያና እማማ የ ድንገተኛ በር መግቢያ ላይ ደሞ ሀሩንና አባባ ብቻ ሁሉም ውጥረት ላይ ነው እማማ ጭራሽ አቅሏን(አይምሮዋን) ስታለች ምታረገው ነገር ሁሉ በእምነት የመከልከለለ ሳያንስ በሳይንሱም አይመከርም ሆስፒታሉ ውስጥ ያለው ሰው በሙሉ እማማን እያየ ያለቅሳል ግማሹ ከንፈሩን ይመጣል አሁን እስኪ በንደዚ አይነት ጊዜ ከንፈር ይመጠጣል ሆሆ ሆስፒታል ከመጣን ሁለት ሰአት ሞላን ግን ምንም ነገር የለም እንደ ድንገት አንድ ነርስ ከድንገተኛ ክፍል ስትወጣ አንድ ዶክተር አየች "ዶክተር ስንፈልግህ አንድ ታካሚ ደክሞል እርዳን... "ብላ ሳይጨርስ ወደ ድንገተኛ ክፍሉ በፍጥነት ገባ ነርሶች ወደክፍሉ ወሯሯጥ ጀመር እንደ ድንገት አንድ ነርስ እያለቀሰች ወጣች ጥበቃው ሲጠይቃት "አሁን የገባው ልጅ ምተ"
ብላ እየተንሰቀሰቀች ወጣች እማማ ኡኡታዋን አቀለጠችው ሀሩን መሬት ላይ ተዘረረ እኔ እራሴን አላቅም ደርቄ ቀረው መኩ ፈዛ ቀርታለች አባባ እያየሁቶ መንቀጥቀጥ ጀመረ በቃ ሙሉ ቤተሰቡ ጤነኛ አይደለም ማለት ይቀላል ሀሩን እንደ ሴት ያለቅሳል እማማ ግን ከሁላችንም ባሰች መቆም መቀመጫ ከለከለችን ከትንሽ ደቂቃ ብሀላ አንድ ዶክተር መጣና "የታካሚ ፋይሰል ቤተሰቦች?"አለ ወደ'ኛ እየቀረበ "እማማ ስትቀር ሁላችንም አዎ" አልን ዶክተሩ ንግግሩን ጀመር "አዝናለው በጣም ልንረዳው ሞክረን ነበር...
:
:
ክፍል➓ #ይቀጥላል.....

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
Forwarded from Anu calligraphy🎨
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Part 3 colouring

#tutorial

Anwar calligraphy and String art

Call now and order on 0920833672
@Anu_ziaz
👇👇Join our channel for more👇👇
.................@anucalligraphy..............
👆👆👆👆ቻናላችን ይቀላቀሉ👆👆👆👆
ክፍል ➓(አስር)
👣ያልወለደች🕊እናት👣
:
:
:
.. "ግን በጣም ደም ስለፈሰሰው ወደ ራሱ እስኪመለስ ጊዜ ይወስድበታል እእእ እና ደግሞ ደም ያስፈልገዋል ፍቃደኛ የሆነ ሰው ካለ ይከተለኝና አስፈላጊውን ምርመራ ይደረግለት እና ቶሎ ለማዳን የበኩላችንን እንወጣ"ብሎ ሁላችንንም ሲያይ በድንጋጤ ተውጠናል እማማ እስካሁን ምንም እያለች አይደለም አይኗን አንድ ቦታ ተክላ ፍዝዝ ብላለች አባባ ደም ግፊቱ ተነሳበት መሰል መቆም አቅቶታል ሀሩን ከወደቀበት መሬት ይነፋረቃል ሁሉም በየፊናው የፋይሰልን መጨረሻ ይጠባበቃል ዶክተሩ ይናገር እንጂ ማንም ከቁብ አልቆጠረውም ተመልሶ መጣና ሁላችንንም ሰብስቦ ካረጋጋን ብሀላ ከአባባ ውጪ ሁላችንም ደም ለመስጠት ፍቃደኛ መሆናችንን ነገርነው አባባም ቢሆን ግን ካልሰጠው ሞቼ እገኛለው ብሎ ዶክተሩ ነው አንተ ባለብህ ህመሞች ምክንያት አትችልም! ብሎ ቁርጡን የነገረው እማማ አሁንም ምንም አታወራም ወደ ምርመራ ክፍል ሄዳ አስፈላጊውን ምርመራ ሰጠች ከትንሽ ደቂቃዋች ብኀላ ዶክተሩ መጣና እማማ መስጠት እንደማችል ነገራት ተራውን ሀሩን ገባ እሱም ከፍይሰል ደም ጋር ሚመሳሰል ደም የለውም ተረኛ እኔ ስገባ ዶክቸሩ እንደመገረም አለኛ "ኪሉሽ ሽንት ነው" አለኝ
"45" ዶክተሩ ንግግሩን ቀጠለ "እና ከሀምሳ ኪሎ ውጪ መስጠት እንደማይቻል አላወቅሽም" ብሎኝ ተያይዘን እነአባባ ወዳሉበት አብረን አመራን መኪያ እቤት እንድትሄድ አባባ ስላስገደዳት ይህን ጉድ አልሰማችም ዶክተሩ አንገቱን እያቀረቀረ"አዝናለው ከናንተ መሀል የማንም ደም ከሱጋር አይመሳሰልም እና ሌላ አማራጭ መጠቀም ግድ ይለናል እናም ከተስማማ መቀጠል እንችላለን"አለ ሁላችንም አይናችንን አጉረጠረጥንበት እንደ ድንገት ሀሩን "አማራጩን እንጠቀም ዶክተር ፋይሲን ማጣት የለብንም"ብሎ ጮኀ "እእእእ እንግዲ የአሁኑ አማራጭ ከደም ባንክ ደም መግዛት ነው"ሲል ሁላችንም "ምን" ብለን ሁላችንም ዶክተሩ ላይ አፈጠጥንበት "ያለው አማራጭ እሱ ነው ያለበዛ ልጁን ማትረፍ ለኛ የማይታሰብ ነገር ነው ስለዚ ተረጋጉና አስቡበት ደሞ ጊዜ የለንም"ብሎ ሊሄድ ሲል አባባ "ዶክተር" አለ "አቤት ተስማማቹ"አለ "አዎ ምንም ይሁን ምንም ነገር ተደርጎ ብቻ እሱ ይዳንልኝ ተስማምተናል"አለ አባባ በሀዘን ስሜት ዶክተሩ ሁላችንንም በተራ በተራ ሲመለከት በአወንታ ጭንቅላታችንን ነቀነቅን ዶክተሩ እየፈገገ "መሆን ያለበትን ነው የወሰናቹት ለዛ እንዳትቆጩ አንዳንዴ ስንደነግጥ ምናረገውን አናቅም እና መዳን ያለበትን ሰው በራሳችን እጅ ልናጣ እንችላለን እና ለህክምናው ሚሆን በቀላሉ 20,000 ያስፈልጋል" አለ አባባ "አረ ምንም ችግር የለውም ዶክተር ልጅ ብቻ ይዳን እንኳን ለልጄ ለሌላም ይወጣ የለ"ቤሎ አጠገቡ ያለው ወንበር ላይ ዘፍ አለና በረዥሙ ተነፈሰ እማማ አሁንም አትናገር አትጋገር ድንዝዝ ብላለች እኔን ልደንዝዝልሽ የኔ እናት እንዴት እንደገረጣች እንዲ እንዲ እያለ 3 ቀን ሞላው ፋይሰል ግን አልነቃም ሀኪሞቹ ተደናግጠዋል የልብ ምቱ ግን እንዳልጠፋ ያወሪሉ እማማ 3 ቀን ሙሉ ምንም አልበላችም ፋይሰል አጠገብ ቁጭ ብላ ታለቅሳለች እንደ ድንገት ማታ ላይ አባባ እንዲያርፍ ሀሩን ነግሮት እኔና አባባ ወደ ቤት አመራን አይነጋ የለምና ነግቶ ለእማማና ለሀሩን ቁርስ ይዤ ሃድኩኝ እማማ አልበላም ብላ ድርቅ ስትልብን አንዲት ነርስ ሰምታ ስትቆጣት በግድ አንድ አፏን ጎረሰች ቁርስ በልተን እንደጨረስን ልቀየርልሽ ስላት አሻፈረኝ አለች ምንም ማድረግ ስላልቻልኩ ተመልሼ ወደ ቤት ሄድኩኝ ማታ ላይ እራት ይዘን ከአባባ ጋር መጣን ወደ ሆስፒታሉ ገብተን የፋይሰል በር ላይ ልንደርስ የቅርብ እርቀት ላይ ሳለን አድርቆ የሚያስቀር ነገር አየን! የፋይሰል በር ላይ ሰው ተሰብስቧል ሰዉ ያለቅሳል ከዚ በላይ መራመድ አቃተኝ ሀሩን መምጣታችንን ሲመለከት ወደኛ እየመጣ "አባባ ፋይሰል አሁን ነቃ"ብሎ አቀፈው አባባና ሀሩን በደስታ ተቃቀፉ እኔ የደስታ እንባ ማፋለቅ ጀመርኩኝ ወደ ፋይሰል ክፍል ስንቀርብ እማማ"ልጄ ነቃልኝ ልጄ ዳነልኝ ያይኔ አበባ ዳነልኝ"እያለች ትጮሀለች ህዝብ እሷን እያየ ይንሰቀሰቃል ግማሹ ከንፈር ይመጣል እባባ ወደ እማማ ቀረብ አለና ለማረጋጋት ምከረ እማማ ግን እራሱን መቆጣጣር እንዳቃተው የ አይምሮ ህመምተኛ ዝም ብላ እየጮኀች ነው
ትንሽ እንደቆየች አባባና ሀሩን አረጋግተው ዶክተሩ መጣና አንዳንድ ምርመራ አደረገለት ወደ ከሰአት ላይ አባባና ሀሩንን ቢሮ ጠራቸው

ክፍል➊➊ #ይቀጥላል......

JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
ክፍል ➊➊ (አስራ አንድ)
ያልወለደች እናት
.
.
....ከግማሽ ሰአት ቆይታ ብኃላ አባባና ሀሩን ከዶክተሩ ክፍል ወጡ ሁለቱም ፊታቸው ገርጥቷል አንዳች መርዶ እንደተነገረው ሀዘንተኛ ፋታቸው አመድ ለብሷል ሳያቸው ደነገጥኩ "ሀሩን?" አልኩት አይኔን ለጥያቄ እያፈጠጥኩበት "ዳኒ አዝናለው ግን በዚ ሁኔታ ላይ ሆኜ ልነግርሽ አልችልም"ብሎኝ ከ ሆስፒታሉ ወጣ አባባ እየፈጠነ ወደ ፋይሰል ክፍል አመራ እማማ የፋይሰልን እጅ ይዛ ታሻሻለች አባባ እያየው እንደ ሴት ያለቅሳል "አባባ"አልኩት ምላሽ እንዲሰጠኝ እያሰብኩ ወደ ውጪ ይዞኝ ወጣና በመጀመሪያ እንድረጋጋ ካረገ ብኃላ "ዳኒዬ ልጄ"ብሎ ንግግሩን ቀጠለ "አሁን ላይ በጣም ጠንካራ መሆን አለብን እኛ ተስፋ ምንቆርጥ ከሆነ ፋይሰልን ማዳን አይቻልም እኛ ግን ጠንከር ብለን ለሱም ተስፋ ምንሰጠው ከሆነ የድሮውን ፋይሰል መልሰን እናገኘዋለን" አለና በረዥሙ ተነፈሰ ግራ ገባኝ "አባባ የምን ዳር ዳር ነው ፋይሲ ምን ሆነ ነቅቶ የለ"ብዬ አይናይኑን በተሰበረ መንፈስ እመለከተዋለው "ዳኒ ልጄ ፋይሲ ከወገቡ በታች ሰውነቱ አይሰራም እና ለትንሽ ጊዜ እንዲ ይቆያል አልያም እስከነአካቴው ላይሰራ ይችላል ግን 'ተስፋ ስጡት ብሏል ድክተሩ' "ብሎ ካለኝ ብኃላ በረዥሙ ተነፈሰ እኔ አባባ የሚለውን ማመን አቅቶን እስቃለው የ ድንጋጤ ሳቅ! ማመን አቃተኝ ግን መቀበል ስላለብኝ ብቻ አመንኩኝ እንዲ እንዲ እያለ ፋይሰል ሳምንታት አለፉት በሳምንት 3 ቀን ፊዝዮትራፒ ያረጋል ግን ምንም ለውጥ የለም ፋይሲም ተስፋ እየቆረጠ ነው እስካሁንም ህክምናውን ሚከታተለው በኛ ድጋፋ ነው ዛሬ አብሬው ውዬ ልክ 11 ሰአት ላይ ከ ጓደኛዬ ሀንዳውት ኮፒ ላረግ እዛው ሰፈር አካባቢ ወጣ አልኩኝ ከመውጣቴ በፊት የቲቪውን እሪሞት ስልኩን አጠገቡ አስቀምጬለት ነው የወጣሁት የድሮ ቢሆን መኪያ እንደ እንቁላል ትንከባከበው ነበር አሁን ግን መኪያን አደራ እንዳልላት አሁን ከባሏ ጋር መኖር ጀምራለች ያው ሰርጓ ሳምንት እንደቀረው ፋይሰል ቢታመምም ቀጠሮውን ለማክበር በሳምንቱ ሸራአ ፍርድ ቤት ሄደው ተጋብተዋል ሁሉንም ነገር አመቻችቼለት ምንም ነገር ቢሆን ወዲያው እንዲደውልልኝ ብዬ የጊቢውን ቁልፍ ይዤ ወጣው ደሞ የፋይሲ ጎደኛዋችም ቢሆኑ ቀን ቀን ስራ ስለሚውሉ እሁድ ብቻ ነው ሚመጡት ሁሩን ግን ከስራ ሲወጣ ሁሌ እና ጋር ነው መቶ ከፋይሲ ጋር ሚያድሩት አሁን አሁን ግን ፋይሲ ትንሿ ነገር ቱግ ታረገዋለች ከሰው በታች የሆነ ያህል እየተሰማው ነው መሰል ብቻውን እንዳይሆን ብዬ ክፍሉ ስገባ ከእኛቱ እቅፍ በግድ እንደተነጠቀ ህፅን ይንሰቀሰቃል ላባብለው ስሞክር ስለሚብስበት መግባቴን ትቻ ወደ ኀላ አፈገፍጋለው ሀንዳውቱን የምሰጠኝን ጓደኛዬን እየጠበኩ ሳለ አባባ ደውሎ ቶሎ ወደቤት እንድመጣ ነገረኝ ፋይሰል የሆነ ነገር የሆነ ስለመሰለኝ በ5 ደቂቃ ውስጥ እቤት ደረስኩ ሳሎን ስገባ ሁሉም አለ እማማ እንደለመደችው ፋይ

ሲን እግሯ ላይ አስተኝታ ፀጉሩን ታሻሻለች አባባ ፋት ለፊታቸው ቁጭ ብሏል"አባባ ምን ተፈጠረ?" አልኩት እያለከለኩ "አረ መጀመሪያ ተቀመጪ እስኪ ደሞ ትንፋሽሽን ሰብሰብ አርጊ አታለክልኪብን"ፋይሰል ነበር ከታመመ ለመጀመሪያ ቀን እንዲ እንደ ድሮ ሲያወራ ሁሉም ፈገግ! አለ አባባ ሁላችንም እሱን ለመስማት ዝግጁ እንደሆንን ሲያውቅ "ያው ባለፈው የመኪያ ሰርግ ሳምንት ሲቀረው ነው ይህ ነገር የተፈጠረው እና ብዙ ነገሮች ተበላሽተዋል ግን ለበጎ ነው እና አሁን ግን እንደ መልስ ጠርተናቸው ያኔ እንዳሰብነው ብንደግስስ ደሞ አሁን ፋይሲም ደና እየሆነ ነው እስቲ ምን ትላላቹ"አለ አባባ የመኪያ ነገር አይሆንለትም ቀን ከሌት ቢናገር አይጠግብም በቃ በጣም ነው ሚወዳት ልክ እንደ መጀመራያ ልጁ ለካ መወለድም መውለድም ቋንቋ ነው አንዳንድ ሰው ገና ካወቅናቸው ቀን አንስቶ ቀልባችን ወዷቸው ለዘላለም በልባችን ውስጥ ይቀራሉ አንዳንድ ሰውን ደሞ ለኛ የሚሰጠን ክብርና ቦታ ደሞችንን ስጋችንን ቆርጠን ልንሰጣቸው ባንችልም የኔ ዘር ናት/ነው ብለን እስክንል ማንነታቸው ይገዛናል እኛ ቤትም የህነው ይሆ ነው አሁን ቤቱ ላይ ፀጥታ ሰፈኟል ሁሉም አባባ የተናገረውን ነገር ከ ከአዕምሮው ጋር እየመከረ ነው መሰል እኔ ግን ምንም አላሰብኩም ምንም መናገርም አላሰኘኝም እንደ ድንገት የፋይሰል ስልክ ጠራ ስልኩን አየና እኔ ላይ አፈጠጠ ግራ ገባኝ 'ምንድነው?' እያልኩ ለራሴ ጠየኩ ፋይሰል ግን
አላነሳውም ጎን ላይ ባለው ላይት ማጥፋያ ድምፁንና ላይቱን አጠፋው አባባ "ምን አሰባቹ?" አለ እማማ ልትናገር "እእእእ ማለት..."ብላ ንግግሯን ስትጀምር የፋይሰል ስልክ ድጋሚ ጠራ አሁንም ከቅድሙ ተመሳሳይ ነገር ሲያረግ አባባ "እንዴ አንሳው እንጂ የሚፈልግህ ሰው ቢህንስ"አለው "አይ አባባ ብኃላ እኔ እደውልለታለው ሀሩን ነው" ብሎት እኔን አየኝ ግራ ገባኝ እማማ ንግግሯን ቀጠለች "እኔ ችግር የለብኝም ግን ፋይሲ የማይደብረው ከሆነ ነው"ብላ ፀጉሩን እየዳበሰች እእ "አበባዬ"አለችው እሱም እየፈገገ "አረ ለኔ ችግር የለውም አሁን እኮ ደና ነኝ አንቺስ ዳኒ" አለ "አረ ፋይሲ ደማ እኔ ከናንተ ሀሳብ እንደማልወጣ እያወክ"ብዬ ገና ሳልጨርስ "ዳኒ ሁሌ በናንተ ሀሳብ በናንተ ሀሳብ እስቲ አንድ ቀን እራስሽን ወክለሽ አውራ አንድ ቀን ይሆ 'በናን ሀሳብ እስማማለው' የምትይው ነገር ዋጋ እንዳያስከፍልሽ" ብሎ ተቆጣ በርግጥ የኛ ቤት ህግ ደስ ይላል የፈለገ ህፃን ልጅ ቢሆን አሳማኝ ምክንያት ካቀረበ ተቀባይነት አለው አንዳንድ እዚ ቤተሰብ ውስጥ መፈጠሬን እንደትልቅ እድል ነው ምቆጥረው ደሞ አባባ ዛሬ ሲመጣ ካዳሚ(የቤት ስራ የምታግዝ ሴት)ይዞ እንደሚመጣ ነግሮኝ ነበር ነገ ጠዋት እንድ ላይ እንደምናመጣ ነግሮኝ እራት በላልተን ተኛን በነገራችን ላይ አንድ ቀን የቤት ሰራቸኛ ስል አያቴ ሰምታኝ ተቆጥታኝኛለች እንደማይባልም ነግራኛለች ለዛ ነው ሰራተኛ የማልለው ጠዋት ላይ ስነሳ ድብር ነው ሚለኝ የቤቱ ስራ ሁሉ እኔን ስለሚጠብቀኝ እናደዳለው አዬ መኪያ በደና ጊዜ እንዳልሰራ ከልክላኝ አሁን ወኔው ከየት ይምጣ....
.
.
ክፍል➊➋ #ይቀጥላል......


JOIN us 👉👉👉

www.tgoop.com/Habibacalligraphy
2024/08/15 23:04:53
Back to Top
HTML Embed Code: