Telegram Web
⭐️Neonatal Sepsis and Surgical Complications: Medical History and Management at ICMC General Hospital

🔹Medical History (Neonatal Course)

The patient is a neonate born to a 28-year-old primigravida mother who received antenatal care and delivered via cesarean section at 38 weeks of gestation due to oligohydramnios and intrauterine growth restriction (IUGR). Birth weight was 2.2 kg.

Immediately post-delivery, the neonate was admitted to the NICU and remained for the first 3 days. Empirical antibiotic therapy with ampicillin and cefotaxime was initiated and continued for 5 days. The neonate was then discharged to room-in with the mother.

🔹 Readmission
On day 6 of life, the infant developed abdominal distention and respiratory distress and was readmitted to the NICU. He was made NPO and started empirically on vancomycin and cefepime, later revised to vancomycin and meropenem for 1 day. Due to clinical deterioration, the neonate was referred to our facility for further management.

🔹On Admission to Our Facility
V/S: - PR: 165 RR:82  T: 36.0 SPO2: 91 on iNO2 RBS: 30mg/dl  Wt: 3kg
ABD: - Tense abdomen and hypoactive abdomen
CNS:- Poor suckling, unsustained

Investigations
CBC: Left shift with severe thrombocytopenia
CRP: Elevated
Organ Function: Hypoalbuminemia
Abdominal X-ray: Dilated bowel loops

Abdominal Ultrasound: Ascites (?spontaneous bacterial peritonitis)
- Pelvicalyceal dilatation
- Bilateral echogenic kidneys suggesting possible diffuse renal parenchymal disease
- Mild left-sided urinary tract dilation

Echocardiogram: Small atrial septal defect (ASD), left-to-right shunt

Lumbar Puncture: Frank pus obtained and sent for culture
Blood Culture: Grew Enterococcus faecalis

🔹Management and Clinical Course
- Started on piperacillin-tazobactam and meropenem
- Kept NPO, supported with minimal feeds (MF) of amino acids, calcium, and potassium chloride
- Required inhaled nitric oxide (iNO₂)

On the second day of admission, the neonate developed seizures and apnea, unresponsive to calcium and IV phenytoin. Cardiopulmonary resuscitation (CPR) was performed for a few minutes, after which the neonate was stabilized. Multiple inotropes were initiated, and the neonate was intubated, sedated, and placed on mechanical ventilation.

Due to worsening abdominal signs (bilious vomiting, shiny and silent abdomen), laparotomy was deemed high risk, and peritoneal drainage was performed. Bilious drainage was noted for the first 2 days, then gradually decreased, with concurrent improvement in abdominal status.

The patient came out of shock by day 5 and was extubated on day 6. Clinical improvement continued, and trophic feeds were initiated and gradually advanced to full feeds.

🔹Complication and Final Outcome
Despite initial improvement, the neonate developed worsening respiratory distress and depressed reflexes on day 13 of antibiotic therapy. Laboratory tests revealed:
- Rising WBC count
- Worsening thrombocytopenia
- Further elevation in CRP
Fungal sepsis was suspected, and fluconazole was initiated. The infant showed marked clinical improvement within 3 days of antifungal therapy.

The neonate completed 21 days of antibiotics and was discharged in stable condition after a repeat blood culture showed no growth.

⭐️ ICMC General Hospital  ⭐️
     "we care for your health"


For more information and appointment
☎️
0116678646 / 0949020202
or free call 📞 9207

Telegram  https://www.tgoop.com/icmcgeneralhospital
facebook  https://web.facebook.com/icmcgeneralhospital

tiktok         https://www.tiktok.com/@icmc_general_hospital?_t=ZM-8ti59Ze8ylJ&_r=1

📍Around CMC square behind Tsehay Real Estate


@HakimEthio
51👏10👍1
ምዝገባ ጀምረናል |ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ
=======================

Programs we offers:

Undergraduate programs
👉Doctor of Medicine
👉Doctor of Dental Medicine
👉Medical Laboratory Science

Post graduate programs
👉MPH in General Public Health 
👉MPH in reproductive health
👉MPH in Public Health Nutrition

Contact Address:
👉Bisrate Gebreal, Doba Building, Addis Abeba , Ethiopia
.👉Telegram: https://www.tgoop.com/Sante_Medical_College
👉Phone: +251-944-36-80-87
👉Email: [email protected]
👉https://www.santemedicalcollege.edu.et
5
በምስሉ እንደሚታየው 35 ዓመቱ የሆነ ታካሚ 6 ወር የቆዬ የግራ ታፋው ላይ እባጭ በቀዶ ህክምና በስኬት ተወግዶለት (biopsy result Low grade sarcoma) ያሳየ ሲሆን IHC ውጤት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል

የእጅና እግር የስጋ ካንሰር (Extremity Soft Tissue Sarcoma)፡ ቁልፍ እውነታዎች እና እይታ

‎ሶፍት ቲሹ ሳርኮማ (STS) በጡንቻዎች፣ የሰውነት ስብ፣ ነርቮች፣ ጅማቶች፣መገጣጠሚያዎች እና የደም ሥሮች ውስጥ የሚነሳ ብዙ ያልተለመደ ካንሰር ነው። እንደ አሜሪካ ሳርኮማ ድርጅት 40-60% የሚሆኑት ሶፍት ቲሹ ሳርኮማዎች በእጆች/እግሮች ላይ ይገኛሉ።

📊 ዓለማቀፍ እና ያልተመጣጠኑ ሁኔታዎች

‎· የማጋጠም መጠን (Incidence)፡ ዓለም አቀፍ ደረጃ የህመምተኞች ብዛት ከ 54,630 (1990) ወደ 96,200 (2021) ጨምሯል፣ ነገር ግን በዕድሜ ልክ የተመደበ የማጋጠም መጠን (ASIR) ወደ 0.05 ከ100,000 ቀንሷል።

‎· የሞት መጠን (Mortality)፡ ዓለም አቀፍ ደረጃ የሞት መጠን ቀንሷል፣ ነገር ግን ከመቶ ዝቅተኛ የሆኑ የማህበራዊ-ኢኮኖሚ መረጃ (SDI) ክልሎች ውስጥ የመብዛት እና የህክምና ተደራሽነት ችግሮች የሞት ምጣኔውን ከፍ ያደርጉታል።

በታዳጊ አገሮች (ለምሳሌ በአፍሪካ/እስያ ክፍሎች) ውስጥ የASIR መጠን ዝቅተኛ (1.25 በ100,000) ቢሆንም፣ ይህ በከፊል በትክክል ባልታወቁ ሳርኮማዎች ምክንያት ነው፤ የሞት መጠን ግን ከፍተኛ ሆኖ ይገኛል።

‎· የ2033 ትንበያ፡ የህመምተኞች ብዛት በ2033 (~95,600 በዓለም አቀፍ ደረጃ) ሊጨምር ይችላል፣ እና ከፍተኛው ጫና በእድሜ እየገፉ ያሉ ህዝቦች እና ከፍተኛ SDI ክልሎች ውስጥ ይታያል።

📌 የሳርኮማ ዓይነቶች በጥቂቱ

‎1. ሊፖሳርኮማ (Liposarcoma)፡ በስብ ህዋሳት ውስጥ ይገኛል፣ ብዙውን ጊዜ በዳሌና በክንድ ላይ ይወጣሉ።

‎2. ሊዮሚዮሳርኮማ (Leiomyosarcoma)፡ በስስ ጡንቻ ህዋሳት ውስጥ ይገኛል።

‎3. ሲኖቪያል ሳርኮማ (Synovial Sarcoma)፡ በመገጣጠሚያዎች አቅራቢያ ይገኛል።

‎4. ያልተለየ ፕሊሞርፊክ ሳርኮማ (Undifferentiated Pleomorphic Sarcoma - UPS)፡ የመሰራጨት አቅሙ የከፋፀባይ አለው፤ በእግር ላይ ይታያል።

‎5. የክፉ አይነት ፔሪፌራል ነርቭ ሽፍን እጢዎች (Malignant Peripheral Nerve Sheath Tumor)፡ በክንድ/እግር ነርቮች ላይ ይገኛል።

⚠️ ምልክቶች፡ ምን ማየት አለብን?

‎· እብጠት (Lump or swelling)፡ ከ5 ሴንቲ ሜትር በላይ፣ እየጨመረ የሚሄድ፣ ወይም ጥልቅ ቦታ ያለው።

‎· ህመም (Pain)፡ በነርቮች ወይም ጡንቻዎች ላይ ጫና በሚፈጥር ጊዜ።

‎· የተገደበ እንቅስቃሴ (Limited mobility)፡ በመገጣጠሚያዎች አቅራቢያ ሲከሰት።

ማስታወሻ፡ 23% የሚሆኑት ታካሚዎች መጀመሪያ ላይ በትክክል ሳይታዎቁ ይቀራሉ፣ ይህም ህክምና እንዲዘገይ ያደርጋል።

🔬 ለህመሙ የሚያጋልጡ ነገሮች (Risk Factors)

‎· የዘር አይነት በሽታዎች (Genetic syndromes)፡ ለምሳሌ ሊ-ፍራውመኒ፣ ኒውሮፋይብሮማቶሲስ።

‎· የጨረር ህክምና (Radiation therapy)፡ 5-10% የሚሆኑት የSTS ህመሞች ይህን ያጋጥማቸዋል።

‎· ስር የሰደደ እብጠት (Chronic lymphedema)፡ ለምሳሌ ሊምፋንጂዮሳርኮማ።

‎· ኬሚካሎች (Chemicals)፡ ለምሳሌ ቪኒል ክሎራይድ፣ አርሴኒክ (ደካማ ግንኙነት አለ)።

🌍 በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያሉ ተግዳሮቶች

‎· የዘገየ ልዬታ (Diagnostic Delays)፡ የተጨባጭ ምርመራ መሳሪያዎች (እንደ MRI/biopsy) እና ልዩ ስፔሻሊስቶች አለመኖራቸው ምክንያት ያልተጠበቁ የእባጭ ማውጣት (unplanned excisions) እና እግር/እጅ ክፍሎችን መቁረጥ (amputations) ከፍተኛ ሆኖ ይገኛል።

‎· የህይወት ቆይታ ልዩነቶች (Survival Gaps)፡ በታዳጊ አገሮች ውስጥ ያለው አማካይ የህይወት ቆይታ 30 ወር ሲሆን በከፍተኛ ገቢ አገሮች ደግሞ ከ60 ወር በላይ ነው።

‎· የግብዓት ልዩነቶች (Resource Gaps)፡ ዝቅተኛ SDI ክልሎች ውስጥ የሳርኮማ ማከሚያ ማዕከላት እጥረት ይታያል፣ ይህም የሕክምና ውጤትን ይቀንሳል።

🛡️ምን ማድረግ እንችላለን?

‎· ዕውቀት (Awareness)፡ ስለ አደገኛ ምልክቶች (እየጨመረ የሚሄድ እብጠት >5 ሴ.ሜ.፣ ህመም) ያስተዋውቁ።

‎· ልዩ የሳርኮማ ማከሚያ ማዕከላትን ማቋቋም ፡ በተጨባጭ ምርመራ (MRI/ባዮፕሲ) እንዲጠኑ ያበረታቱ።

‎· ዓለም አቀፍ ድጋፍ (Global Advocacy)፡ በተለይ በተደበቁ ክልሎች ውስጥ የስነ-ደዌ መሰረተ-ልማት እንዲሻሻል ድጋፍ ማድረግ።

📢 ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ ነው!

‎· ጁላይ የሳርኮማ ግንዛቤ ወር (Sarcoma Awareness Month) ነው።

‎· የታካሚዎችን ታሪኮች ያካፍሉ የመዘግዬት ዕድልን ለመቀነስ ይረዳል (ለምሳሌ 13% የሚሆኑት ታካሚዎች ልዩ የህክምና እስፔሻሊስት አያገኙም)።

‎· ድጋፍ ያድርጉ፡ ለSarcoma Foundation ወይም Sarcoma Alliance መመስረት ድጋፍ ያድርጉ።

💡 የጥሪ መልዕክት!

‎· ሰውነትዎን ይወቁ፡ ከ5 ሴ.ሜ. በላይ የሆነ እየጨመረ የሚሄድ እብጠት ካለ ለዶክተር ይንገሩ።

‎· የህክምና እኩልነትን ይጠይቁ፡ በዝቅተኛ ገቢ አገሮች ውስጥ የሳርኮማ ህክምና እንዲሻሻል ይደግፉ።

‎· ይህን ልጥፍ ያካፍሉ

#የሳርኮማ_ዕውቀት #ExtremitySarcoma #ዓለም_አቀፍ_�ለጋ #ካንሰር_እንክብካቤ_እኩልነት #ሶፍት_ቲሹ_ሳርኮማ

ዶ‎/ር ካሳሁን ምትኩ ጠቅላላ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት @ ዓለም ሆስፒታል ቡታጅራ)

‎telegram - https://www.tgoop.com/Behaset
‎tik tok- https://www.tiktok.com/@dr.kassahun?_t=ZM-8xXq1Uxnq2H&_r=1
‎face book
https://www.facebook.com/share/1Mpmhj7Uem/
‎linkedin -https://www.linkedin.com/in/kassahun-mitiku-b92373270

@HakimEthio
28👍3👏2
Diathesis/Vulnerability- Stress Model
***
የአዕምሮ ህመም መንስኤው ይህ ነው ብሎ አንድ መንስኤን መበየን ያስቸግራል:: ይልቁኑ የ ስነ-ህይወታዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማህበራዊ ምክንያቶች ድምር ውጤት ነው::

🔴 የአዕምሮ ህመም ከ Stress-Diathesis Model አንጻር ምን ይመስላል?

አንዳንድ ሰዎች በተለያየ ምክንያት (ለምሳሌ በ Genetics) ለአዕምሮ ህመም ተጋላጭነታቸው ከፍ ያለ ነው:: ይህ ተጋላጭነት Vulnerability/Diathesis ይባላል::

ታዲያ ይህ ተጋላጭነት መኖሩ ብቻውን ለአዕምሮ ህመም መከሰት በቂ ምክንያት አይሆንም ፤  Stress ሲፈጠር እንጂ:: እነዚህ Stress: ማህበራዊ/ስነልቦናዊ ጫናዎች፣ እጽ መጠቀም እና የመሳሱ ጉዳዮችን ያጠቃለለ ነው:: እነዚህ ጫናዎች: ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች የአዕምሮ ህመሞች እንዲከሰቱባቸው ቆስቋሽ ምክንያቶች ይሆናሉ ይለናል Diathesis/Vulnerability-Stress model ::

▫️ለምሳሌ ለ Schizophrenia የ Genetics Risk ያለበት ሰው: እንደ ካናቢስ እና ጫት አይነት እጾችን መጠቀማቸው የአዕምሮ ህመም የመከሰት እድሉን ይጨምረዋል::

▫️ለድብርት ህመም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በህይወታቸው የሚያጋጥሟቸው የተለያዩ ጫናዎች የድብርት ህመሙ እንዲከሰት ያደርጋሉ::

🔹 ከዚህ model እንደምንረዳው: ብዙዎቹ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ህመሙ የሚከሰትባቸው ለጫና(Stress) ሲጋለጡ ነው::

🔹እነዚህን ጫናዎች(Stress) ማስወገድ ወይንም በአግባቡ ማስተናገድ ከቻሉ ለአዕምሮ ህመም የመዳረግ እድላቸውን መቀነስ ይችላሉ::

ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው - የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት

https://www.tgoop.com/DrEstif

https://www.tgoop.com/HakimEthio
17👍3
ምዝገባ ጀምረናል |ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ
=======================

Programs we offers:

Undergraduate programs
👉Doctor of Medicine
👉Doctor of Dental Medicine
👉Medical Laboratory Science

Post graduate programs
👉MPH in General Public Health 
👉MPH in reproductive health
👉MPH in Public Health Nutrition

Contact Address:
👉Bisrate Gebreal, Doba Building, Addis Abeba , Ethiopia
.👉Telegram: https://www.tgoop.com/Sante_Medical_College
👉Phone: +251-944-36-80-87
👉Email: [email protected]
👉https://www.santemedicalcollege.edu.et
1
አንጎለ-ዓይን : <አይኔ ደህና ነው ብባልም ማየት አልቻልኩም>

እስትሮክ አይነ ስውርነትን ሊያስከትል ያችላል። የአንጎል አይኗን በእስትሮክ ተነጥቃ አይነ-ስውር የነበረቺው ታካሚዬ ማየት መቻሏ ከሷ በላይ ለኔ የሒወት ዘመን ደስታን ሰጥቶኛል። ታሪኳንም በሚከተለው መልኩ አቀረብኩት።

አልማዝ (ስሟ የተቀየረ) ትባላለች።የ23 አመት ወጣት ከባህር ማዶ ለመውለድ ወደ እናት ሀገሯና ወደ እናቷ እቅፍ ነው የመጣችው።ልትወልድ የደረሰች ነብሰ-ጡር ናት።ከመጣች ሳምንታት ያለፋት አይደለችም ፤አዲስ ዲያስፖራ ሆና የመውለጃ ግዜዋን በጉጉት እየተጠባበቀች ነው። አይኗን በአይኗ ልታይ መሆኗን ስታስብ ሐሴቷ ወደር የለውም።

ብዙም ሳትቆይ እራሴን አመመኝ ብላ ተናገረች። < አይዞሽ ! ቡናውን ምኑን በዪበት > ተብላ ሀገራዊ እርዳታ አግኝታ አደረች። ሔድ መለስ እያለ ቢያማትም ሐኪም ቤት የሚያደርስ አይደለም ብለው በቤታቸው ቆዩ።

ከቀናት በሗላ አስደንጋጭ ክስተት ተፈጠረ ። ሙሉ ሰውነቷን እንደ ርዕደ-መሬት ያቀጠቅጣት ጀመረ። በመሐል ፋታ እየሰጣት ሁለት ቀን ሙሉ በቤት ውስጥ አሳለፈች። የአንጎል ንዝረት ለሁለት ቀን አብሯት ቆይቶ ምን የሚከሰት ይመስላችሗል ?

ባህር አቋርጣ መምጣቷን እንደ መነሻ አድርገው <ለሀገርኛ ህመም ተጋልጣ ነው > የሚለው ሰፊው ና የተሰራፋው የማህበረሰብ አሳቤ ነው ለሁለት ቀን በእንቅጥቅጥ ውስጥ እያለች በቤት እንድትቆይ ያስፈረደባት ፤ ተፈረደባት። ነብሰ-ጡር እናት ለብዙ ደቂቃዎች በሚቆዩ የሰውነት መቀጥቀጥ/seizures / ስትጋለጥ በፅንሱ እና በራሷ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል። ሒወትንም ሊነጥቅ ይችላል።

አልማዝ ማየት አቅቷታል። ሰውንም በቅጡ እየለየች አልነበረም። አይን እያየ አንጎል ካላየ ማየት አይቻልም። ለማየት ከአይን ተነስተው የተዘረጉ የእይታ ገመዶች እስከ አንጎል-አይን ጤናማ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ማየት የምንችለው ለእይታ በሚያገለግለው የአንጎላችን ክፍል አማካኝነት ነው። አይን ደህና ቢሆን የአንጎል-አይን ከታመመ ማየት ይቸግራል፤ አንጎል ደህና ሆኖም አይን ከታመመ እንደዚያው የማየት ችግር እንዲገጥም ያደርጋል። የቅንጅት እና ርብርርብ ጥምር ውጤት ነው ማየት።

የአንጎል-አይን በልዩ ልዩ አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች ሲታመም ማየት አለመቻል ይፈጥራል። እስትሮክ አይነ-ስውርነትን ይፈጥራል። የሗለኛው የአንጎል ክፍል ለእይታ የሚውል ነው። ለዚህም ነው አንጎለ -ዓይን ወይም የአንጎል አይን ሊንለው የቻልነው ።

አልማዝ መጨረሻ ላይ ሆስፒታል ደረሰች። ማቀጥቀጥ በእናት እና በፅንስ መካከል የሚደረገውን የደም ዝውውር ያስተጓጉላል። አልማዝም ላይ የሆነው ከዚህ የተለየ ሊሆን አይችልም ፤ ይኸው ነው። ፅንሱ በሒወት ሊተርፍ አልቻለም። ሁለት ቀን ሙሉ ጠቅላላ ሰውነትን በሚያቀጠቅጥ ህመም እና እራሷን በማታቅ እናት ውስጥ ሌላ ሒወት መቀጠል አዳጋች ነው።

አልማዝን ሳገኛት ለጥሪ መልስ መስጠት የማትችል ሆና ነበር። አይኖቿ ከቁጥጥር ውጪ ሆነው ሲያሻቸው ይከፈታሉ አለያም ይዘጋሉ። ጉዳዩ አስቸኳይ መሆኑን ስለረተዳሁ የሒወት አድን የህክምና እንድታገኝ ተደረገ። በመቀጠልም አስቸኳይ የአንጎል ምስለ ምርመራ አደረግን።

የአንጎል ምስለ ምርመራው ደስ የማይል ውጤትን ገለጠ። በሗላኛው የአንጎል ክፍል ላይ በግራና በቀኝ በኩል ከፍተኛ የሆነ ጉዳት መድረሱን አሳወቀን። ከፍተኛ የጭንቅላት ቋት መጨናነቅ ይታይ ስለነበረ ይኸንን ሊቀንስ የሚችል መድሐኒት በማዘዝ የችግሩን መንስኤ ለማወቅ ሙያዊ ምርመራና እንዲደረግ ሆነ።

በአንጎልና ጭንቅላት ውስጥ በሚከሰት የደም መርጋት ችግር ተጠቅታለች። እርግዝናን ተከትሎ የሚከሰት የእስትሮክ አይነት እየተስፋፋ መጥቷል። የዚህ አይነት እስትሮክ ያልተለመደ የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን ግን እየጨመረ ይገኛል። መከላከል ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥና በአፋጣኝ ማወቅ የሚቻልበት መንገድን ማስፋፋት ግድ እየሆነ መጥቷል።

ከቀናት የህክምና ቆይታ በሗላ በሰመመን ውስጥ የነበረቺው መንቃት ጀመረች። ቤተሰቧቿን በድምፅ መለየትና ማውራት ብትችልም በአይኗ ግን ልታያቸው አለመቻሏ ሙሉ ደስተኛ እንዳትሆን አድርጓታል።<ዶክተር አይኔ ምን ሆነ > ስትል ጠየቀቺኝ።የአይን ምርመራ ይደረግልኝ ስትል በጥያቄ ላይ ጥያቄ ደራረበቺብኝ። አዎ የአይን ብረሐንን ማጣት ለሰው ልጅ ከሚገጥሙትን እጅግ አስደንጋጭ ክስተቶች አንዱ ነው።

አይዞች እይታሽ ይመለሳል ፤ችግሩ የመጣው ከአይንሽ ሳይሆን ከሗላኛው የአንግል ክፍል ችግር የመጣ ነው። አንጎልና አይኔ ምን አገናኛቸው ሳይሉ አልቀሩን ከአጠገቧ የነበሩት አስታማሚዎች። ክስተቱ አዲስ እንደሆነባቸው በቀላሉ ተረድቻለሁኝ። ቀስ ብዬ ስለ አንጎል-ዓይን እና ስለ እይታ ጠቅለል ያለ ጭብጥ ሰጥቼ እስትሮክ የአንጎል አይን የሚባለውን ሲያጠቃ አይነ ብረሐንን ሊነጥቅ ይችላል የሚለውን አብሬ ነገርኳቸው።

አልማዝ አሁን ጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።ከሆስፒታል ወጥታ ለክትትል በቅታለች።የአይን ብረሐኗ እየተመለሰ ነው ፤ሰውነቷም መታዘዝ ጀምሮል። እስትሮክ ህክምና ሰፋ ያለ ግዜን እና ትዕግስት ይጠይቃል። በእርግዝና ወቅት የሚከሰት እራስ ምታት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ታሪኳን በልብ ወልድ መልክ ባቀርበውም በእውነት ያለች ታካሚዬ ናት። በመጨረሻዎቹ የእርግዝና ወራት አለያም ድህረ ወሊድ ግዜ የሚከሰትን የእስትሮክ አይነት መከላከል የምንችልባቸውን መንገዶች ከሐኪሞ ያግኙ።

ዶ/ር መስፍን በኃይሉ : የአንጎል ፣ ህብረ-ሰረሰርና ነርቭ-ዘንግ እና ጡንቻ ህክምና እስፔሻሊስት ፤ ረ/ፕሮፌሰር
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስና ሐኪም ግዛው ሆስፒታል

@HakimEthio
34
ጥሩ የሙያ ስነምግባር ያላቸውን ትሁት የጤና ባለሙያዎችን እናመስግን

ሐሙስ ማታ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም ከትዳር አጋሬ ጋር ለወሊድ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ተገኘሁ::

ጳውሎስ ቴርሽየሪ ሪፈራል ሆስፒታል በመሆኑ ታካሚ ይበዛል:: በዕለቱ አዳር ሽፍት የነበሩ ዶክተሮች እና ሚድዋይቭስ በግልፅ የሚታየውን የሥራ ጫና ተቋቁመዉ ደስ በሚል ሁኔታ አስተናግደዉ ማዋለጃ ክፍል ላኩን:: ማዋለጃ የነበሩ ዶክተሮች እና ሚድዋይቭስ እንዲሁ ርህራሄ በተሞላበት መንገድ ተቀበሉን::

በምጥ ሰዓት ባለቤቴ ጋር እንድሆን እኝህ የርህራሄ ባለቤቶች ፈቀዱልኝ:: ሌሊቱንም ያለ እረፍት አነጉት:: በመጨረሻም በባለሙያዎች ከፍተኛ ጥረት እና ፈጣሪም ረድቶን በሰላም ተገላግላ ቤታችን ገባን::

እንዳከበራችሁን ፈጣሪ ክብሩን ያድላችሁ:: ዘመናችሁ ሁሉ ይባረክ::

ዶ/ር ስዩም, ዶ/ር ታምራት, ዶ/ር ሳሙኤል (Gynecology and Obstetrics final year resident) and others whom I miss to mention.

Midwives- እሸቱ መኮንን (ከቅድመ ወሊድ ጀምሮ ያገዘን), ትዕግስት ትልቅሰው, ምስር, አስፋ አባተ (labour ward coordinator) and others whom I miss to mention.

Neonatal Advanced life support specialist/NALS- ዓለም

Anesthesia team- ዶ/ር ዮሐንስ (Anesthesiologist), ዶ/ር ሀያት (final year anesthesiology resident), አምደ (Anesthetist).

Nurse- ብርሃኑ and others whom I miss to mention.

Pharmacist- ሙሉጌታ, ሸዋ

- Gessesse Demissie (Anesthesia Lecturer)

@HakimEthio
48
2025/09/17 19:20:47
Back to Top
HTML Embed Code: