Telegram Web
አራት አለም አቀፋዊ ሰርተፍኬቶች፣ ሁለት ምርጥ ሽልማቶች እና አራት አህጉራትን የመጎብኘት ዕድል በአንድ የኢትዮጵያ ካላንደር ዓመት!!! I am only here to inspire the younger generation!🙂

ሰላም ሰላም የHakim ገፅ ወዳጆች እንዴት ከረማቹ? Happy New Year to all of us here!🙏

እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ሐኪም ያሳካኃቸውን ዕድሎች ለእናንተም ጀባ ልል ወደድኩ። እንደ ግለሰብ ከሚቆጩኝ ነገሮች መኃከል እንደ ሀገር የመረዳዳት በሀላችን በጣም ውስን መሆኑ ነው። የትም አለም አቀፋዊ መድረክ ላይ ስሄድ የሚታየኝ ነገር ቢኖር የእኛ የኢትዮጵያውያን ቁጥር አናሳ መሆኑ ነው። እንደ ሀገር እነኚን ዕድሎች በአግባቡ ብንጠቀምባቸው ብዙዎቻችን ለሀገር ዕድገት የሚሆኑ ብዙ ግብዐቶችን ይዘን መመለስ እንችላለን። Anyways enough with the regrets and ጣት መቀሰሩ። Let me share the opportunities here!

I) Apollo Hospital Cancer Conclave - ይህ ዕድል በዚህ አመት ያገኘኁት ምርጡ የትምህርት ዕድል ሲሆን፤ በህንድ ሀገር የተደረገ ትምህርታዊ ዝግ ኮንፍረንስ እና የሁለት የካንሰር ማዕከላትን ጉብኝት ያደረግኩበት ነበር። በተለይም በአፖሎ ሆስፒታል ስር ባለው የቼናይ ከተማ የፕሩቶን ህክምና ማዕከል ጉብኝት ምርጡ ነበር!!! ዕድሉን ያገኘኁት በዚሁ ሐኪም ገፅ ላይ በተጀመረው የዩቱይብ ፖድካስት ምክንያት ነበር። 🙂 Effective use of Social Media ትላለህ! በነገራችን ላይ ያኔ Tiktok ስጀምር የዛሬ 3 አመት በፊት ተወርፌ ነበር "ስፔሻሊስት ቲክቶክ እንዴት ይሰራል በሚል?" 😂..... አሁን እኛ ጀምረነው የሚል የቴዲ ዮ አቋም ነው ያለኝ lol

2) European Society of Medical Oncology  Precsptorship on Cervical Cancer at Cape Town, South Africa.

ይሄ በካንሰር ህክምና ላይ ለምትሰሩ ማንኛውም ሐኪሞች(Oncologist, Gynecologist, Pathologist, Radiologist, Palliative Care specialists) መሆን የሚችል ምርጥዬ Merit Based እና በዝግጅቱ ላይ በምታቀርቡት የMedical Case የሚመረኮዝ ነው። ኬፕ ታውን እውነት ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ነችን? ያስባለኝ ዕድል ነበር። ምርጥ ሆቴል እና ምግብ ተችሎ ለሶስት ቀን የሚቆይ ዕድል ሲሆን 1000 Euros የትራንስፖርት ወጪ
ይችሏቹኃል። 

Membership is free for Sub-Saharan Africa.

https://www.esmo.org/meeting-calendar/esmo-preceptorship-on-cervical-cancer-2026-cape-town


3) American Society of Clinical Oncology - International Development and Education Award in Palliative Care ነበር።

በየአመቱ በካንሰር ህክምና ላይ የሚሰሩ አለም አቀፍ ሐኪሞችን አወዳድሮ የሚሸልም ታላቅ ውድድር ነው። በእዚህ ፕሮግራም ላይ Oncologists, Gyni-Oncologists, Surgical Oncologists, Pathologists, Anesthesiologists working on pain,  Palliative Care seniors, Hematologists and Pediatric Hemato-Oncologists ነበሩበት። ይሄ ምርጥ ዕድል ሙሉ የምግብ ፣የሆቴል ቆይታ እና ትራንስፖርትን ያካትታል። እንዲሁም አንድ በመረጣችኁት የUS ወይም የካናዳ ሆስፒታል የObservership ዕድል ከ1300 US ዶላር ጋር ይመቻቻል። IDEA-Palliative Care Award በማሸነፌ የተሰማኝን ደስታ እንዲህ በቀላሉ ልነግራችኁ አልችልም! በታላቋ ቺካጎ ከተማ የሁለት ቀን የLeadership Training እና የASCO አመታዊ የአምስት ቀናቶች ኮንፍረንስ ተሳትፎ ይኖራችኋል። እኔ በመረጥኩት የCity of Hope Hospital, Los Angeles, California ምርጡን የሶስት ቀናት የPalliative Care observership ከፕሮፌሰር William Dale ጋር ነበረኝ።

ASCO IDEA and IDEA-PC 2026 applications are open until September 30, 2025. Membership is free!!!


4) European Society of Medical Oncology's preceptorship ptogram on Gastric and Esophageal Cancers in Nairobi, Kenya

ይሄ ምርጥ ዕድል ለካንሰር ሐኪሞች እና ካንሰር ላይ ለሚሰሩ ጤና ባለሞያዎች የተሰጠ ነበር። እኔ በምሰራበት የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ስራ ባልደረባዬ የሆነው ጠቅላላ ሐኪምም መሳተፍ የቻለበት ቆንጆ ዕድል ነበር። Oncologist, Surgrons, Psthologists, Radiologists, Palliative Care Seniors, Internists, Gastroenterologists and GPs ተሳታፊ ነበሩ። ለሶስት ቀን በቆየንባቸው ጊዜያት፦ ሙሉ የምግብ እና የሆቴል ወጪ + የትራንስፖርት እስከ 1000 Euros መሸፈን ችለዋል። መሳተፋቹ በራሱ ብዙ ሰው ያስተዋውቃችኋል!!!


5) Open Medical Institute's 1 week training on Psychosocial Oncology in Salzburg, Austria.

ከአሜሪካ በሚመጡ የስፔሻሊቲው ምኁራን ለአንድ ሳምንት ቀኑን ሙሉ የሚሰጥ የሌክቸር ስልጠና ሲሆን ሙሉ በሙሉ የሚደረገው እዛው OMI ግቢ ውስጥ ነው። ግቢው ዶርሚተሪ፣ ላይብረሪ እና ሙሉ ቀን የምግብ አቅርቦት ያለው ፀዴ ስፍራ ነው። ለትራንስፖርት እስከ 1000Euros መሸፈን ይችላሉ! በተረፈ Pre-test, Post-test እና የCase presentation competition አቅፎ የያዘ purely merit based ፉክክር ነው። እኔ በተሳተፍኩበት የአንድ ሳምንት ስልጠና በጣም ብዙ የPalliative Care ነርሶች እና ሐኪሞች ፣ ኦንኮሎጂስቶች፣ ሶሻል ወርከሮች፣ ጠቅላላ ሐኪሞች፣ የpublic health ኤክስፐርቶች፣ ሳየሰኮሎጂስቶች እና የቀዶ ጥገና ሐኪሞች የነበሩበት ነበር። በየአመቱ በጣም ብዙ ዕድሎች ለሳምንት በሚቆይ ስልጠና ያሸበርቃሉ፤ አንዴ ዕድሉን አግኝታቹ ሴሚናር ካሸነፋቹ ደግሞ የObservership ዕድሎች እዛው Salzburg ይመቻቻሉ። 

ምርጧን የሞዛርትን ከተማ ሳልዘበርግን ለማየት ያብቃቹ!🙌 በተረፈ በሁሉም የጤና ፊልድ እና ዲፓርተመንት በሽ ዕድሎች አሉላቹ!!!

https://www.openmedicalinstitute.org/seminars/

እስኪ እንደ ሀገር ሰብሰብ ብለን ሰልጥነን ሰብሰብ ብለን ልምድ ቀስመን ሰብሰብ ብለን ለመሸለም ያብቃን። Then boom, Our health sector will have international insights and solutions later on!!!

My telegram for Links and files: 
https://www.tgoop.com/drmichaelshawel1221
My tiktok username: 
drmichaelshawel, theoncologist12

መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችንም!🙏🏵️💐

@HakimEthio
👍2926👏8
🌻እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና፣ የደስታ እና የመረዳዳት ዘመን እንዲሆንልዎ እንመኛለን።


🌻መልካም አዲስ ዓመት 🌼 መልካም በዓል🌻

ኦንኮ አድቫንስድ ዲያግኖስቲክ ሴንተር

📍ቁጥር 1. እንቁላል ፋብሪካ ከ ኖክ ማደያ አጠገብ

📍ቁጥር 2. አለርት ሆስፒታል አቅራቢያ ፥አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት

📍ቁጥር 3. አዳማ 04 ቀበሌ, ወደ ገንደ ጋራ በሚወስደው መንገድ ላይ እንገኛለን

📢 Join our Telegram Channel:
👉🏻https://www.tgoop.com/oncopathologydiagnosticcenter

#OncoAdvancedDiagnostics #Open24Hours
#Oncopathology
25👍3
መልካም አዲስ ዓመት

@HakimEthio
27
እንኳን ለ2018 ዓ/ም አዲስ ዓመት (እንቁጣጣሽ) በሠላም አደረሳችሁ !

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

መልካም ዓዲስ አመት።

ሳንቴ ሜዲካል ኮሌጅ | You are invited to Visit our College.

Now; we are OPEN FOR REGISTRATION for Programs:

Undergraduate
👉Doctor of Medicine
👉Doctor of Dental Medicine
👉Medical Laboratory Science

Post graduate
👉MPH in General Public Health
👉MPH in reproductive health
👉MPH in Public Health Nutrition

Contact Address:
👉Telegram:
https://www.tgoop.com/Sante_Medical_College
👉Phone:
+251-944-36-80-87
👉Email:
[email protected]
👉
https://www.santemedicalcollege.edu.et



ዕውቀትን ለህይወት እንሰጣለን!
Bringing KNOWLEDGE to LIFE!
15👏1
ፓራሲታሞል እና ኦቲዝም ፤ ትኩሳት እና ኦቲዝም:
<<ፓራሲታሞል ልጆችን ለኦቲዝም እየዳረገ ነው>> የሚለው ሰሞንኛ የጥናት ውጤት ሐተታና

ፓራሲታሞልን አንዲት ነፍሰጡር እናት በምን ምክነያት ልትወስድ ትችላለች? የሚለውን መረጃ ልስጥ። በእርግዝና ወቅት እናቶች በጀርም መወረር (Infection) ሲጠቁ የሰውነት ሙቀት መጨመር ያጋጥማቸዋል። የሙቀት መጨመር በፓራሲታሞል ይታከማል። ሌላው የራስ ምታት ህመም ሲገጥማቸው ፓራሲታሞልን ይወስዳሉ።

ከፓራሲታሞል ውጪ ለእርጉዝ ሴት ጥሩ የሆነ የህመም እና የሚቀት መጨመር ማከሚያ መ'ዳኒት የለም። አማራጭ የሌለውን መ'ዳኒት እንዳይወስዱ ያደርግ ይሆን?

አሁን ፓራሲታሞልም መዘዝ ይዞ መጥቷል የሚል ጥናት ይፋ ተደረገ በሚል በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። የጥናቱን ዝርዝር ግኝትና ምክረ ሐሳብ ለአንባቢያን ላካፍል። በዚህ ጉዳይ ላይ ሁለት ርዕሶችን አንባቢያን በጥልቀት እንዲያዩና እንዲያነቡ እጋብዛለሁ። ፓራሲታሞል እና ኦቲዝም ፤ ትኩሳትና ኦቲዝም የሚሉትን ተረድተው ሲጨርሱ በፓራሲታሞል ዙሪያ ያለውን ውዝግብ መልስ ይሰጥዎታል።

ጥናቱ በዚሁ ወርሐ ነሐሴ ይፋ የሆነ ነው። ያለፉ ጥናቶችን ሰብሰብ አድርጎ የሚደረግ የጥናት አይነትን መሰረት አድርጎ የተጠና ነው ። ጥናቱ 46 የቀደሙ ጥናቶችን አቅፏል። ከነዚህ መካከል በ6 ጥናቶች ውስጥ ፓራሲታሞል ለኦቲዝም አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳለው ሲያሳዩ ፤ በ20 ጥናቶች ውስጥ ደግሞ የትኩረት ማጣትና መቅቀዝበዝ ችግር (ADHD)፤ በተቀሩት 18 ጥናቶች ላይ ሌሎች የአዳጊ አንጎል እድገት ችግሮች እንዳሉ ተስተውሎባቸዋል።

ጠቅለል ሲደረግ Neurodevelopmental Disorders /የአዳጊ አንጎል ችግሮች / ፓራሲታሞልን በእርግዝና ወቀት በወሰዱ እናቶች ላይ ካልወሰዱት ከፍ ባለ መጠን ተከስቷል የሚል ነው። በዚህ ጥናት ላይ ፓራሲታሞልን ባልወሰዱ እናቶች ላይም ኦቲዝም እና ሌሎች የአዳጊ አንጎል ችግሮች መከሰታቸውን ያሳያል። ከዚህ የምንረዳው ፓራሲታሞል ብቸኛው የኦቲዝም መነሻ አለመሆኑን እና ፓራሲታሞልን አለመውሰድም ከዚህ ችግር ነፃ እንዳማያደርግ ነው። ልዩነቱ የቁጥር ነው።

በተጨማሪም ፓራሲታሞል መንስኤ ነው ሳይሆን የተባለው ፓራሲታሞል በወሰዱት ላይ መጠኑ ጨምሯል ነው ያለው። ይኸ ማለት የcause and effect ግንኙነት ይኑረው አይኑረው በሚለው ዙሪያ በዚህ ጥናት አልተዳሰሰም። በጥናቱ ማጠቃለያ ላይ ፓራሲታሞል አትውሰዱ የሚል መልእክት ሳይሆን አግባብነት ያለው አወሳሰድ ይኑር ነው የሚለው። መጠኑ የተመጠነ፣ ለአጭር ግዜና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ብቻ መወሰድ እንዳለበት ምክረ ሐሳብ አጥኚዎቹ አስቀምጠዋል። ለዚህ ደግሞ የሚከተለው ሌላኛው ጥናት(2) የፓራሲታሞልን አስፈላጊነት ይተነትናል።

በእርግዝና ወቅት የሚከሰት የሰውነት ትኩሳት (ሙቀት መጨመር) ካልታከመ የኦቲዝም የመከሰት እድልን በከፍተኛ መጠን እንዲጨምር ያደርጋል። የሙቀት መጨመር በተለይ ከሶስት እስከ ስድስተኛው የእርግዝና ወራት ሲኖር ኦቲዝም የመከሰት እድሉን በብዙ እጥፍ ያሳድገዋል። ይኸን አሉታዊ ተፅዕኖ ለማስቀረት ትኩሳት በአፋጣኝ መታከም አለበት። ለዚህ ደግሞ ያለን አማራጭ ፓራሲታሞል ነው። ከፓራሲታሞል ውጪ ያሉ የሙቀት ማከሚያ መድሐኒቶች ለእርጉዝ እናት አደገኛ ናቸው።

ፓራሲታሞል እና ኦቲዝም በሁለት መንገድ ይያያዛሉ። የመጀመሪናው ፓራሲታሞልን በወሰዱ እናቶች ላይ ኦቲዝም ከፍ ባለ መጠን እንዲታይ ሲያደርግ በሌላ መንገድ ደግሞ በፓራሲታሞል የታከመ ትኩሳት የኦቲዝምን መከሰትን ሲቀንስ ያሳያል። እንግዴህ ማመዛዘንና የትኛው የተሻለ ውጤት አለው? የሚለውን ገምግሞና ተወያይቶ ማስኬድ እንደሚገባ ጥናቶቹ ያሳዩናል።

<<ፓራሲታሞል ብወስድ ወይስ ባልወስድ ነው >>? የሚሻለኝ የሚለውን ጥያቄ በአፅኖት መመልከት ተገቢ ነው። አሁን ባለው የጥናት መረጃ መሰረት መውሰድ ካለመውሰድ የተሻለ ነው። ነገር ግን አወሳሰዳችን ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። የሚወሰደውን መጠን መመጠን (ሁለት ክኒን ከመውሰድ አንድ ኪኒን ማድረግ)፤ ለብዙ ቀናት ከማዘዝ ለአጭር ቀናት ማዘዝ፤ ለሙቀት መጨመር መንስኤ የሆነውን በፍጥነት ለይቶ አስፈላጊውን ህክምና መስጠት ... በትኩሳት የሚጨምረውን የኦቲዝም መጠን ቀንሶ በፓራሲታሞል መውሰድ የሚፈጠረውን ጭማሬ መቀነስ የሚያስችለን ተመራጭ እርምጃ ነው። በቀጣይ በሚደረግ ጥናት አዲስ ምክረ-ሐሳብ እስኪመጣ ማድረግ ያለብን ከላይ የጠቀስኩትን ብቻ ነው።

ልብ ይበሉ ! ፓራሲታሞል የሚሹ ሁነቶችን አለማከም የበለጠ አደገኛ እንደሆነ ጥናቶች አሳይተዋል። አግባብነት ያለው የፓራሲታሞል አወሳሰድን ተግባራዊ እናድርግ የሚለው የህክምና መርህ አሁንም መተግበር እንዳለበት ጥናቱ አስቀምጧል። ከዚህ ውጪ ፓራሲታሞልን በጭራሽ አትውሰዱ ለሚሉት ትኩሳትና ኦቲዝም የሚለውን ሁለተኛውን ጥናት ገብተው ያንብቡ። ትኩሳት ከፓራሲታሞል ከፍ ባለ መጠን ከኦቲዝም ጋር የተያያዘ አሉታዊ ተፅዕኖ አለው።

References

1) Prada, D., Ritz, B., Bauer, A.Z. et al. Evaluation of the evidence on acetaminophen use and neurodevelopmental disorders using the Navigation Guide methodology. Environ Health 24, 56 (2025). https://doi.org/10.1186/s12940-025-01208-0

2 ) Croen LA, Qian Y, Ashwood P, Zerbo O, Schendel D, Pinto-Martin J, Daniele Fallin M, Levy S, Schieve LA, Yeargin-Allsopp M, Sabourin KR, Ames JL. Infection and Fever in Pregnancy and Autism Spectrum Disorders: Findings from the Study to Explore Early Development. Autism Res. 2019 Oct;12(10):1551-1561. doi: 10.1002/aur.2175. Epub 2019 Jul 17. PMID: 31317667; PMCID: PMC7784630.

ዶ/ር መስፍን በኃይሉ : የአንጎል ፣ ህብረ-ሰረሰርና ነርቭ-ዘንግ እና ጡንቻ ህክምና እስፔሻሊስት ፤ ረ/ፕሮፌሰር
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤናሳይንስ ካምፓስና ሐኪም ግዛው ሆስፒታል

@HakimEthio
75👍10👏3
🌼 ኦንኮ አድቫንስድ ዲያግኖስቲክ ሴንተር የ2018 ዓ.ም አዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ በአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ህፃናት ህክመና ክፍል በመገኘት ለታካሚዎች የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረጉ እና በዓሉን ከሀኪሞች፣ ነርሶች፣ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች፣ ታካሚዎች እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በማሳለፉ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።
አዲሱ አመት የሰላም የደስታ እና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን!
🌼 መልካም በዓል! 🌼

📍አዳማ 04 ቀበሌ ወደ ገንደ ጋራ በሚወስደዉ መንገድ ላይ

📞 0949000086 | 0949000066
9👍1
2025/09/18 20:09:00
Back to Top
HTML Embed Code: