Telegram Web
We extend our deepest gratitude to the remarkable Hana Hailu—writer, TV host, and motivational speaker—for her outstanding role as a panel coordinator at the Netsebrak Leadership Conference (NLC) 2024. Her eloquence, expertise, and inspiring presence elevated the discussions and left an indelible mark on all who attended.

Thank you, Hana, for exemplifying excellence and embodying the spirit of purpose-driven leadership.

#NLC2024 | Lead with Purpose, Serve with Integrity.

Telegram | Facebook | TikTok | LinkedIn | Youtube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Cv እያስገባችሁ ለስራ የማይጠሯችሁ ከሆነ ይሄንንን ቪዲዮ ይሄ መረጃ ለእናንተ ነው...
የሚፈልጉትን ስራ በቀላሉ ለማግኝት ከእርሶ የሚጠበቀው እንዴት እንደሚያገኙት ማወቅ ብቻ ነው

"Unlocking potential with #AbriPro 💼

በዚህ ሊንክ ይመዝገቡ link - https://forms.gle/6QjbaxCxAq5aMR5y8

በ200 ብር ብቻ
ብርታት ጄኔሬሽን በተሰኘው ፕሮጀክታችን በ2024 በሰራው ጠቅላላ ስራ ላይ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ በመሆን ስራውን የገመገምን እንዲሁም ቀጣይ እቅዶችን የተወያየን ሲሆን በዝግጅታችን ላይ አንጋፋ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እና ጋዜጠኞች እንዲሁም የአጋር ድርጅት ሀላፊዎች ተሳትፈዋል!

ስለነበረን ቆይታ እንዲሁም ስለነበረን የአንድ ዓመት ጉዞ ከ እ
በድርጅታችን አብሪማይንድስ ስም ከልብ አመሰግናለሁ!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ተጀመረ
ለጥቂት ጊዜ ብቻ ያገለገሉ ልብሶችን እንዲሁም ከተዘጉ ሱቆች ፣ ከተቆለፉ ሻንጣዎች ፣ በክብር ከተሰቀሉበት ቁም ሳጥን  የተረከብናቸውን ልብሶች አድሰን አርመን አስተካክለን ወደ ሱቅ እየመለስናቸው ነው!

እስከ አሁን በእንደ አዲስ ለ5 ሰዎች ቋሚ የስራ እድል ለ15 ሰዎች ደግሞ ጊዜያዊ የስራ እድል ፈጥሯል።

- በቀጣይ ጊዜ ከሚገቡ ልብሶች 10% በዩኒቨርስቲ ትምህርት ላይ ላሉ ሴቶች የመመረቂያ ልብስ እንዲሁም ስጦታ የምናዘጋጅ ይሆናል!
- በተጨማሪም አብራችሁን በተለያየ ዘርፍ እንዲሁም በዚህ ቢዝነስ ላይ መስራት የምትፈልጉ ሰዎች በራችን ክፍት ነው!

እጅግ ተመጣጣኝ እንዲያውም ዝቅተኛ በሚባል ዋጋ. ......ዘመናዊ እና ብራንድ ልብሶችን እንገዛለን እንሸጣለን እናከራያለን!

አድራሻ:22 ጎላጎል አደባባይ ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ የሚወስደውን መንገድ እንደጀመሩ ያለው የመጀመሪያው ህንጻ
ከጤናአዳም ካፌ ያለበት 3ተኛ ፎቅ

Telegram
https://www.tgoop.com/endeaddislibs

Tiktok
https://www.tiktok.com/@endeaulgj1m?_t=8sQahCgJyib&_r=1
እንደ አዲስ PLC
* ከተከፈተ አንድ ሳምንት ሆኖታል
* ሁሉም እቃዎች ከገበያው እና ከዋናው ዋጋ ከ50% በላይ ይቀንሳሉ....
*አብዛኛው እቃ አዲስ ነው ለምሳሌ ስራ ካቆሙ ሰዎች ፣ከተዘጉ ሱቆች ፣ እንዲሁም ከውጪ ሀገር ከመጡ ሰዎች የወሰድናቸው ናቸው...ቢሆንም ሁሉም በሁለተኛ ዋጋ ይሸጣሉ! Second Hand Price

*እስከ አሁን በእንደ አዲስ ለ5 ሰዎች ቋሚ የስራ እድል ለ15 ሰዎች ደግሞ ጊዜያዊ የስራ እድል ፈጥሯል።

*በቀጣይ ጊዜ ከሚገቡ ልብሶች 10% በዩኒቨርስቲ ትምህርት ላይ ላሉ ሴቶች የመመረቂያ ልብስ እንዲሁም ስጦታ የምናዘጋጅ ይሆናል!
* በተጨማሪም አብራችሁን በተለያየ ዘርፍ እንዲሁም በልብስ ሽያጭ ስራ በጋራ መስራት የምትፈልጉ ሰዎች በራችን ክፍት ነው!
በቅርብ ቀን በተለያዩ አዳዲስ ነገሮች እንመለሳለን!

አድራሻ:22 ጎላጎል አደባባይ ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ የሚወስደውን መንገድ እንደጀመሩ ያለው የመጀመሪያው ህንጻ
ከጤናአዳም ካፌ ያለበት 3ተኛ ፎቅ

Telegram
https://www.tgoop.com/endeaddislibs

Tiktok
https://www.tiktok.com/@endeaulgj1m?_t=8sQahCgJyib&_r=1
#ባለጊዜ
"አንድ ሰው ሁሌ ባለጊዜ አይሆንም ለሌላ ባለጊዜ ቦታ ይለቃል ለማለት ነው!" አሉ

ጊዜህን ተጠቀምበት!
መሰማት ጊዜያዊ ነው! ስልጣን ጊዜያዊ ነው! ደስታም ሀዘንም ለጊዜው ነው......ጊዜህን ካላወክ እና ካልኖርክበት አንተ ብትኖርም Expired ልታደርግ ስለምትችል......ጊዜህን እወቅ
እኔም #ባለጊዜ ነኝ!

በከባዱ የተፈተነች በከባዱ የተሸለመች
ድካሟን እየተሸፈነላት ስኬቷ ያደመቀላት
ልወድቅ ነው እያለች እጇን ይዞ ያሻገራት
ውለታዋን ያልከፈለች የምንጊዜም ባለዕዳ ፣በምህረት ኑሪ የተባለች ፣ እስትንፋስ የተቀጠለላት ፣ ሳይገባት በአምላኳ የተወደደች እሷ ባለጊዜ ሴት እኔ ነኝ!

በህይወት እስካለን፣እግዚአብሄር እድሜ እስከጨመረልን ድረስ እስትንፋሳችን ካልቆመ እኛም ባለጊዜ ነን!
ዛሬ እንዲ ሆን.....

የተሰበረ የመሰላችሁ ነገር መልሶ እንደገና ይሰራላችሁ!
በሸክላ ሰሪው እጅ ተይዛችሁ ቅሩ! እንደገና ለመሰራት ከእርሱ መራቅ አይሁንባችሁ....

እጄ ላይ የነበረን ነገር ተበላሸ በቃ ብዬ በተለይ ዛሬ በጣም ከፍቶኝ ነበር!

ደሞ በሌሊት እንዲህ አለኝ መፍትሄውንም ነገረኝ

ከጭቃ ይሠራው የነበረውም ሸክላ በእጁ ላይ ተበላሸ፤ ሸክላ ሠሪውም በሚፈልገው ሌላ ቅርጽ መልሶ አበጀው።
ሸክላ ሠሪው እንደሚሠራው፣ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አይቻለኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ጭቃው በሸክላ ሠሪው እጅ እንዳለ፣ እናንተም እንዲሁ በእጄ ውስጥ ናችሁ።
ኤርምያስ 18:4-6

የሚናገረው፣ የሚሰማው ፣ የሚያየው አንድ አምላክ ይቅረባችሁ!
#የእኔ_ልደት_እና_ገዢው_መንግስት
ነገሩ ፖለቲካ የሆነበትን ምክንያት ከታች አንብቡት !
(ጉዳዩ ላይ ይበልጥ ለማተኮር እና ለመረዳት እንዲጠቅማችሁ ከኢትዮጲያ መንግስት ውጪ አስቡ) አንድ ሰው የአንድ ሀገር ጠቅላይ ሚኒስቴር ከመሆኑ በፊት እያንዳንዱ የግል እና የቤተሰብ ጉዳይ ፣ ጥቃቅን እና ትልልቅ የቤት ውስጥ ሀላፊነት ያስጨንቀዋል።
ወደ መንግስት ስልጣን ከመጣ በኋላ ግን ስለሚበላው ምግብ ፣ ስለመኪናው ነዳጅ፣ ስለተገዛው አስቤዛ ወይም ሌላ ጥቃቅን ወጪዎች አይመለከተውም።
መሪው ጥሩ ይሁን መጥፎ ፤ትክክል ቢሰራም ባይሰራም - የቀን እና የሌሊት ሀሳቡ መንግስት እና የመንግስት ጉዳይ ይሆናል።

ታዲያ በዚህ ጊዜ አስቀድሞ ያስጨንቀው የነበረውን የግል ጉዳዮቹን የሚያስፈጽም እና የእርሱ ጉዳይ የሚያስጨንቃቸውን ሰዎች መንግስት ይመድባል። እርሱ ትኩረቱን መንግስት ላይ ሲያደርግ መንግስት ደግሞ ትኩረቱን እርሱ ላይ ያደርጋል።
በተለየ መልኩ ለሚበላው ፣ ለሚለብሰው ፣ ለሚቀመጥበት፣ለሚጠጣው ሻይ ሳይቀር ሳይቀር ሀላፊነት በሚወስዱ ሰዎች ይከበባል ለዛም የሚሆነውን በጀት የሚመድበው መንግስት ነው!

እናንተ የእግዚአብሄር ጉዳይ ላይ ስታተኩሩ እግዚአብሄር የእናንተ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። እናንተ የእግዚአብሄር መንግስት ዋናችሁ ሲሆን የእግዚአብሄር መንግስት የእናንተን ጉዳይ ዋናው ያደርጋል። ይበልጥ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ስትጠጉ ይበልጥ የእግዚአብሄር መንግስት በእናንተ ጉዳይ ሀላፊነት ይወስዳል።ቤተመንግስት አካባቢ ስትጠጉ የመንግስት ያህል ትጠበቃላችሁ…አንድ ባለስልጣን ሌላ ሀገር ሲሄድ እንዴት ደንነቱ እንደሚጠበቅ ሰምቼ ነበር ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን የመንግስታት ጉዳይ ይሆናል።

በቃ ይሄው ነው
ገዢው እና ትልቁ መንግስት የሰማዩ ነው!

ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት ይጨነቃሉና፤ የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል።
ማቴዎስ 6:31-33

ያለፈው አመቴ በብዙ መናወጥ እና በጣም ትልልቅ ድሎች ነበሩት ግን ጉዳዬ ሁሉ በቁጥጥሩ ውስጥ እንደሆነ ደጋግሜ ተረድቻለሁ። ፈተናዎቼ ቀጠዩን መጽሐፎቼን ወልደዋል ፤በመልካምም ሆነ በክፉ በህይወቴ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ደግሞ የመጽሐፉ ገፀ ባህሪ ሆነው የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል።

🎂🎂🎂የ28ተኛ አመት የልደት ቀኔ ላይ ሆኜ ለራሴ እንዲ እለዋለሁ አይንሽን ከራስሽ ጉዳይ ላይ አንሺ ....የእግዚአብሄር ጉዳይ ዋናሽ ይሁን!

የበለጠ ትኩረት የሚስበውን የፖለቲካ ወሬ ስለሆነ ይህንን መልዕክት እንድታነቡት እድሉን ልጠቀም ብዬ ነው ጉዳዩን መንግስታዊ ያደረኩት። ይቅርታ 😃😁

@hanahailu
Channel photo updated
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
One of my favorite speech.
Full speech...m
አሁን ደግሞ የ #ሽልማት ጊዜ ነው....
እንኳን ደስ ያለሽ የሚያስብል #ደግ_ዜና
በ2025 IEA /International Exellenece Award / ተሸላሚ ለመሆን ታጭቻለሁ!
=የፊታችን እሮብ በዱባይ ደሴት ቅንጡ ሆቴል አትላንቲስ ዘ ፓልም በሚዘጋጀው የሽልማት ዝግጅት ላይ ከሚሸለሙ ጥቂት ሰዎች አንዷ እኔ ሆኛለሁ።
=ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጲያ በዚህ ሽልማት ላይ ትሳተፋለች!
ይህ ሽልማት በተለያየ ዘርፍ በማህበረሰባቸው ውስጥ በጎ ተፅኖ ያላቸውን ሰዎች ከአለም ላይ ጠርቶ የሚሸልም ሲሆን በLondon Press ድጋፍ ይዘጋጃል!

ልጨርስ ነበር ግን እንዲህ ብዬ እንዴት እጨርሳለሁ?
-
¶ ነገሩ በመጀመሪያ ውሸት መስሎኝ ነበር ቀጥሎም የሚሸልሙት አካላት የአረብ ኢምሬትስ ባለስልጣናት እና የWBR አዘጋጆች መሆናቸውን ሳይ እና ደብዳቤው ሲደርሰኝ ተደንቄያለሁ!

¶ በስተመጨረሻ እንዲህ ልበል....
ይሄም በእግዚአብሄር አይን ቀላል ነው!
ተንጠራርቼ የማልደርስባቸውን ነገሮች ገፍቶ ወደ እኔ የሚያስጠጋ አምላክ አለኝ!

¶ እንኳን በአለም አቀፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ መሸለም ተገብቶኝ መሆኑን እንጃ ግን በአደባባይ ቆሜ ስታዩ በድብቅ የሰራልኝን እና የሰራኝን ጌታ #እዩልኝ!

እሮብ በዱባይ ላይ ኢትዮጲያ ከፍ ትላለች
#ዱባይ #IEA #Award
ሙሴ የቱን ወደ ላይኛው ከፍታ ቢወጣ እግዚአብሄር ወደ እሱ ዝቅ ካላለ በስተቀር አምላኩን ሊያወራውም ሊያገኘውም ሊደርስበትም አይችልም!
እግዚአብሔር (ያህዌ) በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወረደ፤ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ.... ወጣ።
ዘፀአት 19:20

እናንተ የራቃችሁን ነገር እንድትደርሱበት ወደ እናንተ ጠጋ ያደርገዋል።
ፀጋ እንደዛ ነው ....የራቀን ያቀርባል.....
እግዚአብሄር ለእናንተ መውጣት በሆነው ነገር ላይ ይውረድላችሁ።
የማትደርሱበት የሚመስላችሁ የትኛውም ከፍታ ይቅረባችሁ.....
በእኔ ሁኔታ፣አዕምሮ ፣ችሎታ እና የገንዘብ አቅም መሆን የማይችሉ ነገሮች እየሆኑ ነው። እግዚአብሄር ለእኔ እንዲሁ ነው ያደረገው


ምስሌን ፍለጋ ሀሙስ በሻርጂያ የሴቶች ፎረም በሚኖረን ስልጠና ላይ ያገኙታል!

ነገ ደግሞ በአትላንቲስ ዘ ፓልም ሽልማታችንን እንወስዳለን!

እግዚአብሄር ይክበርበት!
2025/02/23 00:09:54
Back to Top
HTML Embed Code: