tgoop.com/HawiiEr/14134
Last Update:
በ1983/84 አከባቢ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለኦሮሞ አርቲስቶች ጥሪ ባቀረበ ጊዜ ጥሪውን ተቀብሎ "Hawwisoo ABO ን ከተቀላቀሉት አባላት ውስጥ አንዱ ነው።ይህ ባንድ በወቅቱ በነበረው የፖለቲካ ሁኔታ ከፈረሰ በዃላም baandii Gadaa ውስጥ ከእነ እልፍነሽ ቀኖ እና ዘሪሁን ወዳጆ ጋር ሰርቷል።ድምፃዊ ፣የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋች ፣የሙዚቃ አቀናባሪና የግጥምና ዜማ ደራሲ ነው።
ይህ ባንድሳይበተን ጉለሌ እያለ ከእነ አሊ ሸቦ፣ ዳግም መኮንን፣ ሂርጳ ጋንፉሬ ፣ኢብራሂም ሃጂ አሊ፣ እልፍነሽ ቀኖ ፣ቢቂላ ጉዮታ ጋር የተለያዩ ሙዚቃዎችን በሙዚቃ መሳሪያ አጅቦ ተጫውቷል፤ ግጥምና ዜማ አዘጋጅቷል።
በተጨማሪም የሙዚቃ መሳሪ አጅቦ ሻቢ ሼኮና ኡመር ሱላይመን ጋር "qubee qubaan siif bita" ፣ሻቢ ሼኮና ከመሀመድ ሼካ ጋር yaa Boonaa ani simalee"፣ ከሀይሉ ኪታባ ጋር "lattuu lattuu daariyaani" እና በሂወት ይኑር ይለፍ ከማይታወቀው ጅሬኛ አያና " iyoole" ከዘሪሁን ወዳጆ ጋር "sijibbe" በተጨማሪ ከማርያሜ ሀርቀካሳ ፣ከኡስማዮ ሙሳ፣ ሂርጳ ጋንፋሬ ጋርም ሰርቷል/ተጫውቷል።
fincila diddaa gabrummaa FDG ጊዜ ተደብድቧል ታስሯል።ይሄን ገዳ ባንድ የምታደራጀውም አንተ ነህ ተብሎ በተለያዩ ጊዜያት ታስራል።በርካቶች ሂወታቸውን አጥተዋል ኑሮአቸውን በትነዋል ተሰደዋል።ይሁንና ይህ አርቲስት በዋቃ ፈቃድ እዚሁ ሀገር ውስጥ ከስደትና ሞት ከተረፉ ጥቂቶች ውስጥ አንዱ ነው።
ይህ ሰው በተለያዩ አቋራጭ መንገዶች ጥቅም ሳይፈልግ ከእውነት ጋር የቆመ እዩኝ እዩኝ የማያበዛ በድሮ ትግል ስሙ ዱላ ገረመው መጠሪያ ስሙ ሙሉጌታ ገረመው ይባላል።
ሙሉጌታ ገረመው እንደ ሀበሻ አቆጣጠር መጋቢት 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰአት ቢርቢርሰ ጎሮ /ፒያሳ በሚገኘው በመልካ ሆቴል CD ስለሚያስመርቅ እንድትገኙ ተጋብዛችዃል።ጠሪ አክባሪ ነውና አይቀርም።
የመግቢያ ትኬት ለማግኘት 0911419122 በኩል መደወል ትችላላቹ።
BY Save Oromia 💪

Share with your friend now:
tgoop.com/HawiiEr/14134