tgoop.com/HawiiEr/14148
Last Update:
አምስቱ የገዳ አስተዳደር ክልሎች (የአሁኑን የገዳ የአስተዳደር ክልሎች አይመለከትም)
****
1. ራያና አሴቦ/ወሎ
2. መጫና ቱለማ
3. ሰቦና ጎና
4. ሲኮና መንዶ
5. ኢቱና ሁምበና ናቸው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኦሮሚያ ተብሎ የሚጠራው ክልልና ሌሎችም ቦታዎችን ያጠቃልላል።
ፊንፊኔ ሲባል የነበረው ክልል ከአባሙዳ መቀመጫ አካባቢ ተነስቶ ዙሪያውን ከ50-60 ኪ.ሜ እንደሚሰፋ ብዙ ሽማግሌዎች ያስረዳሉ፡፡
ፊንፊኔ ዙሪያዋን የሚጠብቁ ሰዎች ነበሩ፡፡ በአካባቢዋ ይኖራሉ፤ የአባሙዳ ከብቶችንም ይጠብቃሉ: ኑሯቸውንም ይኖራሉ፡፡ በአፋን ኦሮሞ ሰርከምቱ ተብለው ይታወቁ ነበረ።
በፊንፊኔ ዙሪያ አሁንም ያሉና በጥንትም ጊዜም የነበሩ ወደ ቅዱስ የአባሙዳ ክልል መግቢያ አምስት በሮች አሉ። እነዚህ በሮች ቀደም ሲል ሌላ ስሞች እንደነበሯቸው ቢታወቅም ወደ ወረራው ዘመን አካባቢ ግን በሚከተሉት ስሞች ይታወቁ ነበር።
1. የሰንዳፋ በር- በነጂማ ዋሪ፣ ግቤ አቤቤ ቱፋ
2. የአዳማ በር - በሞጆ ቦጠራ
3. የአምቦ በር- በቱፋ ሙና
4. የወሊሶ በር - ትክሴ ጅማ
5. ሜጢ በር- ቱፋ ሙና፤ በነጎተ-ወሰርቢ ሎከዎች ይጠበቅ ነበር።
በአምስቱም የፊንፊኔ በሮች ሁሉም አባገዳዎች የራሳቸውን ስጦታዎችና የዓመቱን ግብር ይዘው በራሳቸው በር የሚከተለውን መዝሙር እየዘመሩ ይገባሉ፡፡
1. Ayyaani Ke Walla,
The day on which you are celebrated is Walla.
2. Naqaan Ke Salbaanii
Your offerings are brought to you on the three days of Salbaanii.
3. Horri Ke Finfinnee
Finfinnee is where we water our Cattle.
የዚህን ስንኝ ሌላ ትርጉም ከአቶ ቦርቦር ቡሌና ከአቶ ዲዶ ጉዮ (በባህሉ ምሁራን) የተሰጡትን አቶ አለማየሁ ኃይሌና ቡድኑ እንደሚከተለው መዝግበዋል (2006፡93).
Nuti warra soddom booroo
እኛ በ30 ቡድኖች የተሰደድን፣
Kan soddomaan godaanu
እኛ 30 የመጀመሪያ ሠፈራዎችን የመሠረትን፣
Kan soddomaan uchuuma buusu
እኛ 30 የመጀመሪያውን እሳት ያነደድን፣
Kan soddomaan diina balleessuu
እኛ 30 ነን ጠላትን ያስወገድን፣
Muudaan Keenya Finfinnee
ቅዱስ ቦታዎች ጉዞ የሚደረገው ወደ ፊንፊኔ ነው፣
Finfinnee Waaqa Jaallee
ፊንፊኔ በእግዚአብሔር የተወደደች ቦታ፣
Malkaa Jabduu bulle
መልካ ጀብዱ አደርኩ፣
Akkasiin Okkfalle
በዚህ ዓይነት ባሕሉ ሁልጊዜ በሕይወት እንዲቆይ ለማድረግ ችለናል፡፡
ፊንፊኔና ታሪኳ
BY Save Oromia 💪
Share with your friend now:
tgoop.com/HawiiEr/14148