Telegram Web
ሰበር - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ቢሮ በገቡ የመጀመሪያው ቀን ዩናይትድ ስቴትስን ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የመውጣት ሂደት የሚያስጀምረውን የሥራ አስፈፃሚ ትዕዛዝ (Executive Order) ፈረሙ።

አሜሪካ ለዓለም ጤና ድርጅት ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ከሚያደርጉ አገሮች ግንባር ቀደሟ እንደሆነች ይታወቃል።

ከዚህ ቀደም ፕሬዝዳንቱ "ድርጅቱ ቻይናን ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተጠያቂ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል" ካሉ በሗላ አክለውም ቻይን ለመቅጣት የሚወስዷቸውን እርምጃዎች ይፋ ሲያደርጉ “ቻይና የዓለም ጤና ድርጅትን ሙሉ በመሉ ትቆጣጠረዋለች” ማለታቸው ይታወሳል።
“ አቡበከር ናስር የት እንዳለ አላውቅም “ አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት

“ ለተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ይቅርታ ጠይቄያለሁ “ አቡበከር ናስር

የሱፐር ስፖርት ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት ኢትዮጵያዊው አቡበከር ናስር ባለፉት ሁለት ሳምንታት " ወደ ልምምድ አልመጣም " ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረው ነበር።

አሰልጣኝ ጋቪን ሀንት በአስተያየታቸው “ አቡበከር የት እንዳለ አላውቅም “ ያሉ ሲሆን ቀጥለውም “ ለሁለት ሳምንታት ልምምድም አልሰራም “ ነበር ያሉት።

አሰልጣኙ አክለውም “ አቡበከርን ለማግኘት ጥረት አድርገናል ነገርግን ምላሽ አልሰጠንም ይሄ ከተጨዋቾቼ የምጠብቀው ባህሪ አይደለም ”ሲሉ ተደምጠው ነበር።

የክለቡ ቃል አቀባይ በበኩላቸው “ አቡበከር ናስርን ለማግኘት ሞክረናል ነገርግን ምላሽ አላገኘንም ስለ ደህንነቱ አስበናል ደህና መሆኑን ማረጋገጥ እንፈልጋለን “ ሲሉ ተናግረዋል።

አቡበከር ናስር በበኩሉ በይፋዊ የፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው ፅሁፍ “ ከክለቡ ጋር የመረጃ ክፍተት ተፈጥሮ ነው “ ብሏል።

“ ባለብኝ ጉዳት ምክንያት ከክለቡ ህክምና ቡድን እረፍት ተሰጥቶኝ ነበር “ ያለው አቡበከር “ በኋላም የተፈጠረውን ክፍተት ለክለቡ አስረድቼ ይቅርታ ጠይቄያለሁ “ በማለት አሳውቋል።
ትራምፕ የቲክቶክን እገዳ በአሜሪካ ለ75 ቀናት አራዝመዋል
ትላንት በታቦት ላይ ሲቀልዱ የነበሩት የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በኦሮሚያ ፓሊስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ሁሌ አዲስ ሚዲያ ሰምቷል
ከጅብ መንጋጋ ልጇን ያስጣለችው እናት

በሀዲያ  ዞን በሆሳዕና ከተማ በጀሎ ናራሞ ቀበሌ መንደር 16 ነዋሪ  ወይዘሮ  ደንባሌ አሥራት ጥር 11/2017  ዓ/ም  ከጠት 3 ስዓት  አከባቢ ላይ  ሽላንሻ  ወንዝ ልብስ ለማጠብ  የ12ዓመት ሕፃን አሥከትላ በመሄድ ሥራዋን  መከወን ላይ እያለች  ጅብ ወደ እነርሱ  ይመጣል። በአጠገብ ከነበረች  ከሌላ ሴት  ጋር  በመሆን  ይህንኑ  ህፃን በመሀል አሥገብተዉ ቆመው  ያያሉ ።

ይህ ጅብ  ማለፍ  ይቅርና በ2ቱም  ሴቶች  መከከል  ያለውን  ህፃን ዘሎ ቀኝ እግሩን ነክሶ  በመያዝ ለመውሰድ ሲሞክር   ወላጅ እናት ቀኝ እጇን  በጅብ  አፍ  ውሥጥ  በመክተት  የጅቡን ጉሮሮ በግራ እጅ  አንቃ በመያዝ በላዩላይ ትወድቃለች  አብረው   የነበረችው  ሴት ከጅብ አፍ ህፃኑን   ነጥቃ  በማውጣት   ትታደጋለች ።  በጩኸት   የወጡ ሰዎች ህፃኑን ሊባላ  የቋመጠውን ጅብ  ብዙም  ሳይሄድም  ሰዎች  ተባብሮ   ተገሏል ተብሏል።

የሀዲያ  ዞን  ፖሊስ   ህዝብ ግንኘነት ነው የዘገበው::
የአዲስ አበባ የግማሽ ዓመት የፍቺ መጠን፤ ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ በ34 በመቶ መጨመሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ ከተማ ባለፈው መንፈቅ ዓመት በይፋ የተመዘገበው የፍቺ መጠን፤ አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር በ34 በመቶ መጨመሩን የከተማይቱ የሲቪል እና የነዋሪነት ምዝገባ አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።

በዚሁ ጊዜ የተመዘገበው የጋብቻ መጠን፤ ባለፈው በጀት ዓመት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ከተመዘገበው በሰባት በመቶ መቀነሱንም ኤጀንሲው ገልጿል።

ተቋሙ ይህን የገለጸው የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸሙን አስመልክቶ፤ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 13 በዋና መስሪያ ቤቱ በሰጠው መግለጫ ነው።

የመታወቂያ ስርጭት፣ የልደት እና የሞት ምዝገባ፣ ያላገባ የምስክር ወረቀት፣ የማስረጃ የማረጋገጥ ስራን ለመዲናይቱ ነዋሪዎች የሚሰጠው ኤጀንሲው፤ በከተማይቱ የተከናወኑ ጋብቻ እና ፍቺዎችንም ያከናውናል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ፤ መስሪያ ቤታቸው ባለፉት ስድስት ወራት የመዘገበው ፍቺ 3,769 መሆኑን በዛሬው መግለጫ ላይ አመልክተዋል።

ኤጀንሲው ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት የመዘገበው ፍቺ 2,832 እንደነበር የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የዘንድሮው የፍቺ መጠን በ34 በመቶ ጭማሪ ያሳየ እንደሆነ አስገንዘበዋል።
ሁሉንም በአንድ የያዘ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ የፋይዳ መታወቂያ ቁጥር የያዘ፣ የመንጃ ፍቃድ ቁጥር ያለው እንዲሁም እንደ ኤቲ ኤም ካርድ የሚያገለግል ሁሉንም በአንድ የያዘ የነዋሪነት መታወቂያ ስማርት ካርድ ወደ ሥራ ለማስገባት በፕሮጀክት ደረጃ እየሰራ መሆኑን ጠቅሷል።

የአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪነት መታወቂያን ስማርት አርጎ አሁን ከምንጠቀምበት የተሻለ ተደርጎ ሰዎች የተለያዩ ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ ሁሉንም አገልግሎቶችን በአንድ የያዘ ካርድ በቀጣዮቹ 6 ወራት ውስጥ ወደ አገልግሎት ለማስገባት በእቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከኤጀንሲው ሰምቷል።

ካርዱ የሚሰራበት ዋነኛ አላማም አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ፣ ነዋሪዎች 3 ወይም 4 ካርድ ይዘው ከሚንቀሳቀሱ በ1 ካርድ ሁሉንም አገልግሎቶች አግኝተው አገልግሎት አሰጣጥና ተጠቃሚነትን ቀላል ለማረግ መሆኑን አሳውቋል።

ኤጀንሲው ለቲክቫህ እንደገለፀው ይህ ጉዳይ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ትስስር ሊኖር እንደሚገባና በአሁኑ ሰዓትም ፋይዳ ጋር በጋራ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ለወደፊት ደሞ ስራው ተጠናቆ ካርዱ ወደስራ ሲገባ ባንኮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ተቋማት የጋራ ትብብር እንደሚፈጠርም ተገልጿል።

ይህ አገልገሎት በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ ወደ ስራ ለማስገባት እቅድ የተያዘለት ፕሮጀክቱ አሁን ላይ ማሳያዎች (Samples) እየተሰራ ይገኛል።

አዲስ የሚሻሻለው የመታወቂያ አገልግሎት ፕሮጀክት ተግባር ላይ መዋል ሲጀምር ወይም የሚሻሻሉ፣ የሚጨመሩ ጉዳዮች ሲኖሩ ኤጀንሲው ለህዝብ በይፍ እንደሚያሳውቅም ነው ያስታወቀው።
"የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት አልፏል" - IOM

መነሻውን ከጅቡቲ በማድረግ 35 ኢትዮጵያውያንን አሳፍሮ ወደ የመን ሲያቀና የነበረ የስደተኞች መርከብ በኃልኛ ንፋስ ተመቶ በደረሰው አደጋ የ20 ኢትዮጵያውያን ህይወት ማለፉን ዓለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) አስታውቋል

አደጋው ቅዳሜ ዕለት (ጥር 10) መድረሱን፤ የ9 ሴቶች እና የ11 ወንዶች ህይወት ማለፉን የጠቀሰው ድርጅቱ በመርከቡ የነበሩ 15 ኢትዮጵያውያን እና ሁለት የየመን ዜግነት ያላቸው መርከበኞች ደግሞ በህይወት መትረፋቸውን ገልጿል።
“በኢትዮጵያ አሁን ላይ ሁሉንም ጉዳዮች  በውይይት እንፍታ የሚል መሪ እና መንግሰት ነው ያለው”  የመንግሰት ዋና ተጠሪ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር )

በብሔራዊ መግባባት ላይ ያተኮረው ሁለተኛው የፓርላማ የዜጎች መድረክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በዚህ ውይይትም በተለየ በሃገራዊ መግባባት እና በሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ዙሪያ ብዙ ሃሳቦች እና ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች እየተነሱ ይገኛል፡፡

የመንግስትን መሪ አቋምን  በተመለከተ በውይይቱ  ተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቷል፡፡

አሁን ላይ የመንግስት አቋምን በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የመንግሰት ተጠሪ  ተስፋዬ በልጅጌ( ዶ/ር) ፤ አሁን ኢትዮጵያ ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ''ሁሉንም አጀንዳዎች በውይይት እንፍታ የሚል  መንግስት ነው'' ያለው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ዶ/ር  ተስፋዬ በተለይም ሁሉንም የፖለቲካ አጀንዳዎች በውይይት እና በጠረጴዛ  ዙሪያ እንፍታ የሚል የመነግስት ተቋም ተፈጥሯል ብለዋል፡፡

ለአብነት ያነሱት  ሃገራዊ ምክክር  ምክር ቤት መቋቋሙ የመንግስት ቁርጠኝነትን በደንብ ያሳየ መሆኑን አመላካች ነው ሲሉ ገለጸዋል፡፡

የመንግሰት ተጠሪው ለዚህ ማሳይ ብለው የቤንሻነጉል ጉምዝ  ታጣቂዎች ሰላም አማራጭን መከተልን እንዲሁም የቅርቡን የእነ ጃል ሰኚ እና የመንግሰት የሰላም ስምምነትን ጠቅሰዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የመግቢያ ፍቃድ ያገኙ ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ጥለዋል

አሜሪካ ፍልሰተኞችንና ስደተኞችን ለማስተናገድ አቅም እንደሚያንሳት በመግለጽ ፕሬዝዳንት ባስተላለፉት ትዕዛዝ መሠረት፣ አዳዲስ ስደተኞችን ለመቀበል የተጀመሩ ሂደቶችን ማቆሙን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አስታውቋል። ስደተኞችን መቀበል ከአሜሪካ ጥቅሞች ጋር መጣጣም አለመጣጣሙ እስኪረጋገጥ ድረስ፣ የስደተኞች መቀበያ ፕሮግራም ታግዶ እንደሚቆይም ተገልጧል
በትግራይ ክልል ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ እንደሰጉ ነዋሪዎች ገለጹ!

በትግራይ ክልል የሚገኙ ወታደራዊ አመራሮች ትላንት በሰጡት መግለጫ በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ለሚመራው ህወሓት ቡድን ድጋፍ እንደሚሰጡ መግለጻቸውን ተከትሎ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች፣ ትግራይ ክልል ዳግም ወደ ጦርነት እንዳትገባ የሚል ስጋት እንዳላቸው ተናገሩ። ሁለቱም ወገኖች ጉዳዩን ወደ ሕዝብ አቅርበው “ይዳኙ” ብለዋል።

በሌላ በኩል ሦስት የክልሉ ፓርቲዎች በሰጡት መግለጫ፣ የወታደራዊ አመራርን በፖለቲካዊ ጉዳዮች ጣልቃ መግባት እንደሚቃወሙ በመግለጽ፣ “ወታደራዊ አዛዦቹ ከኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ያላቸው ናቸው" በማለት ወንጅለዋል።

ከከፍተኛ ወታደራዊ ጄነራሎች አንዱ፣ ኮልኔል ገብረ ገብረ ጻድቃን፣ “የትግራይ የፀጥታ ሁኔታ ከትግራይ ሕዝብ እና የፀጥታ አካል ውጭ ባለመኾኑ የውጭ ኃይል አንሻም" ሲሉ ውንጀላውን አጣጥለዋል። አክለውም "ጉዳዩ ስም ማጥፋት ነው” ብለዋል።

Via VoA
አሜሪካ የውጭ ዕርዳታ እንዲቆም መወሰኗን የሚያሳይ ማስታወሻ ሾልኮ መውጣቱ ተነገረ!

የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ዕርዳታ እንዲቆም መወሰኑን የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ለባለስልጣናት እና ለውጭ አገራት ለሚገኙ የአሜሪካ ኤምባሲዎች የላከው የውስጥ ማስታወሻ ማሳየቱ ተገልጿል።ማስታወሻው ፕሬዚዳንት ትራምፕ የውጭ ፖሊሲያቸው ውጤታማነት እና ወጥነት እስኪገመገም ድረስ ለ90 ቀናት የውጭ የልማት ድጋፍ እንዲቆም ሰኞ ዕለት ያሳለፉትን የሥራ አስፈጻሚ ትዕዛዝን የተከተለ መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

አሜሪካ ከዓለማችን ትልቁ ዓለም አቀፍ እርዳታ ለጋሽ ስትሆን፤ በአውሮፓውያኑ 2023፣ 68 ቢሊዮን ዶላር ማውጣቷን ከመንግሥት የተገኘ መረጃ ያስረዳል።የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ያስተላለፈው ትዕዛዝ ከልማት ዕርዳታ እስከ ወታደራዊ ድጋፍ ድረስ የሚሸፍን ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል።

ይህ ሾልኮ የወጣው የውስጥ ማስታወሻ ለድንገተኛ የምግብ ዕርዳታ እንዲሁም፤ ለእስራኤል እና ለግብጽ ወታደራዊ ድጋፍ በስተቀር ሁሉም የውጭ ልገሳዎች እንዲቆሙ የሚያዝ መሆኑ ነው የተነገረው።በተጨማሪም በውጭ አገራት ላሉ የአሜሪካ ኤምባሲዎች የተላከው ይህ የውስጥ ማስታወሻ፤ "እያንዳንዱ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ ወይም ማራዘሚያ እስካልተገመገመ እና እስኪጸድቅ ድረስ አይለቀቅም" ሲል ያትታል።

አክሎም የአሜሪካ ባለስልጣናት "ከእርዳታዎች ጋር በተያያዘ በአስቸኳይ የሥራ ማቆም ትዕዛዞችን እንዲያስተላልፉ እና ይህም ግምገማውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ እስኪወስንበት ጊዜ ድረስ የሚቆይ ይሆናል" እንደሚልም ዘገባው አመላክቷል።በተጨማሪም ዕርዳታዎች የፕሬዚዳንት ትራምፕን የውጭ ፖሊሲ ግቦች የተከተሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በሁሉም የውጭ ዕርዳታዎች ላይ ሰፋ ያለ ግምገማ በ85 ቀናት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ያዛል።

አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አሜሪካ በውጭ አገራት ገንዘብ ማውጣት ያለባት አገሪቷን "ጠንካራ፣ ደኅንነቷ የተጠበቀ ወይም የምትበለጽግ" ካደረገ ብቻ ነው ሲሉ ከዚህ ቀደም ተናግረው ነበር።ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ልገሳ በሚደረግላቸው የውጭ ዕርዳታ ፕሮግራሞች ላይ "ከበድ ያለ ተጽዕኖ" እንዳለው፤ አንድ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን መናገራቸውን ቢቢሲ በዘገባው አመላክቷል።
በጅማ ከተማ “በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከባለቤታቸው፣ ከሚኒስትሮች እና ከሌሎችም እንግዶች ጋር በመሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ እየተገነቡ ያሉ ፕሮጀክቶችን በትላንትናው ዕለት ተዘዋውረው ጉብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ጉብኝት በኋላ በሰጡት ገለጻ፤ በጅማ ከተማ ለተከናወኑ “የገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች “በትንሹ 15 ሺህ ቤቶች መፍረሳቸውን” ተናግረዋል።

በከተማይቱ የነበረ መስጂድ እና ከአንድ ሺህ በላይ የመቃብር ቦታ ቀድሞ ከነበሩባቸው ቦታዎች መነሳታቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። የጅማ ከተማ ነዋሪዎች “ቤቶቻቸውን ሲያፈርሱም” ሆነ ቦታዎችን ለፕሮጀክቶቹ ሲያስረክብ “ካሳ አለመጠየቃቸውን” አብይ በአድናቆት አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተወለዱበት በሻሻ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የጅማ ከተማ ህዝብ፤ ካሳ ከመጠየቅ ይልቅ “ ‘እስቲ ሃሳባችሁን አፍሱት፤ ልየው ነው’ ያለው” ሲሉም በገለጻቸው ላይ ጠቅሰዋል።

“የጅማ አካባቢ ማህበረሰብ ለእነዚህ ህልሞች፣ ለእነዚህ ሃሳቦች መወለድ የነበረው ሚና፤ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትምህርት መሆን ያለበት ነው” ሲሉም አብይ በገለጻቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከአዲስ አበባ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ 350 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው ጅማ፤ ከሌሎች ቦታዎች በተለየ መንግስት ለሚያፈልቀው ሃሳብ “የተከታይነት” (followership) አመለካከት እንዳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ 1ኛ ልዩ ስብሰባውን ያካሂዳል

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በስብሰባው የግብርና ሚኒስቴርን የ2017 በጀት አመት የ6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሚያዳምጥ ሲሆን፤ ሁለት የብድር ስምምነቶችን መርምሮ እንደሚያጸድቅም ይጠበቃል።

የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ እንዲሁም የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅም ይጠበቃል።

በተጨማሪም የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በእስክንድር ነጋ የሚመራዉ የፋኖ ሀይል ከመንግስት ጋር የሚያደርገዉ ድርድር በአሜሪካ ወይም በአውሮፓ እንዲሆን ጠየቀ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል።

የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ አልያም በአሜሪካ እንዲደረግ ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

መንግስት በዋናነት በእስክንድር ከሚመራው የፋኖ ክንፍ  ጋር በቅርቡ በቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃ እንደተወያየ እስክንድር ከኢትዮ 360 ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ገልፆ ነበር። አክሎም በድርድሩ ላይ የኢጋድ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የአሜሪካ ተወካዮች መገኘታቸውን ገልፆ ነበር።

በውይይቱ ላይ በፋኖ ክንፉ በኩል የተነሱ ነጥቦች መከላከያ አካባቢውን በግዜያዊነትም ቢሆን ለቆ መውጣት፣ ክልሉን ማስተዳደር፣ በፌደራል መንግስቱ በስልጣን መወከል፣ የድሮን ጥቃት ማቆም፣ ለተጎዳው ህዝብ ለህይወት ሳይቀር ካሳ መክፈል እና የመሳሰሉት ናቸው ተብሏል።

በመንግስት በኩል ደግሞ ትጥቅ በመፍታት ወደ ማሰልጠኛ መግባት፣ ጎጃም አካባቢ ላይ ያለውን ነገር ማስተካከል፣ በየከተማው ያለውን አደረጃጀት መረጃ መቀበል፣ ተጠያቂ የሚሆኑ አባላቱን አሳልፎ መስጠት እንዲሁም በምክክር ኮሚሽኑ ውስጥ መካተት ናቸው ተብሏል።

"በመንግስት ዝግ ስብሰባ ላይ ሲያጨቃጭቅ የነበረው የነእስክንድር ክንፍ አቅም ጉዳይ ሲሆን ግምገማውም በሀገር ውስጥና በውጭ ተቀባይነትን ለማግኘት መነጋገሩ እንደ  አማራጭ ተወስዷል" ያሉን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጫችን ሸዋ ላይ ድርጅቱ የተሻለ አቅም እንዳለው፣ ነገር ግን ጎጃም ላይ የለም የሚባል ደረጃ ላይ እንደደረሰ መረጃ ቀርቦ ንግግር ተደርጎበታል ብለዋል።

"ቢያንስ ሸዋን ማቃለሉ እንደ ጥሩ እድል በመታየቱ እና የድርድር ዝርዝር መረጃም የሚቀበሉ አለም አቀፍ ተቋማትም በመንግስት የንግግሩ ቦታ ስለተጓጓዙ ውይይቱ ተደርጓል" በማለት ሂደቱን አስረድተዋል።

"ነገር ግን አሳሳቢው ጉዳይ አሁንም ልክ እንደነ ጃል ሰኒ እንዳይሆን ነው፣ ሙሉ ሰላም ለማምጣት የተወሰነ ቡድን ሳይሆን ሁሉንም አካታች መሆን አለበት" ያሉን ደግሞ በጉዳዩ ዙርያ አስተያየት የሰጡን ተንታኝ ናቸው።

"መንግስት ነገሮችን ያቀሉልኛል ብሎ እየሄደበት ያለው ይህ ነው። ሁሉም ወደ ንግግሩ መግባት አለበት፣ አልያ እንደ  ኦሮምያ አይነት ሁኔታ ይፈጠራል፣ ይባስ ብሎም በቀረው ፋኖ ታጣቂ እና በመንግስት መካከል የሚኖረው ሁኔታ ይባስ ሊካረር ይችላል" በማለት ለሚድያችን ተናግረዋል።

Via መሠረት ሚዲያ
2025/01/27 01:24:06
Back to Top
HTML Embed Code: