መንግስት እዳ ሳይከፍል ቀነገደብ አሳለፈ
መንግስት ከ10 አመት በፊት ከግል አበዳሪዎች ተበድሮት የነበረውን እንድ ቢሊየን ዶላር ከነወለዱ 100 ሚሊየን ዶላር በጥቅሉ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ዶላር ባለፈው ታህሳስ 2 ቀን መክፈል ቢኖርበትም ሳይከፈወል መቅረቱ ታወቀ።
እኤአ በ2014 ዓም በአስር አመት ከነወለዱ እከፍላለው በማለት መንግስት ለመጀመሪያ ጊዜ ዩሮ ቦንድ ሸጦ እንድ ቢሊየን ዶላር መወስዱ ይታወሳል።
እስከ ባለፈው አመት (2016ዓም) ታህሳስ ወር ድረስም በየጊዜው ወለድ ሲከፍል ቆይቶ ነበር።
ሆኖም ካለፈው አመት ታህሳስ አንስቶ ወለድ መክፈል ሟቋረጡ አይዘነጋም። በወቅቱም ኢትዮጵያ ዲፎልት ካደረጉ የአፍሪካ አገራት ተርታ መካተቷ ሲዘገብ ነበር።
በአንፃሩ መንግስት ወለድ መክፈል ያቆመው ከአገራት በተወሰደ ብድር መክፈያ ሽግሽግ ላይ ደርድር ላይ በመሆኔ እና የዩሮ ቦንዱ መክፈያ ጊዜም እንዲሸጋሸግልኝ እየተነጋገርኩ በመሆኑ ነው ሲል ማሳወቁ ይታወሳል።
ሆኖም እስካሁን ድረስ ከአገራትም ሆነ ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር እየተደረገ ያለው ድርድር ፍፃሜ አላገኘም።
ቅዳሜገበያ

በዩኤስኤይድ (USAID) ውስጥ ትርምስ መፈጠሩ ተሰማ፡
የአሜሪካ መንግስት ሁሉም በሚባሉ የአገሪቱ እርዳታዎች ላይ ለዘጠና ቀናት እገዳ መጣሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት ለእስራኤልና ግብፅ ከሚቀርቡት የሰብአዊነት የምግብና ወታደራዊ ድጋፎች በስተቀር ሁሉም የእርዳታ ፕሮግራሞች እንደተቋረጡ ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎ የአሜሪካ አለም አቀፍ ልማት ኤጀንሲ የሆነው ዩኤስ ኤይድ ከሞላ ጎደል ከስራ ውጭ ሆኗል፡፡ በተጨማሪም በትሪሊዮን ዶላር የሚቆጠር ለዚህ ድርጅት የተመደበ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ የታገደ ከመሆኑም በላይ ፕሮግራሞቹ በመቋረጣቸው በርካቶች ከስራ እየተቀነሱ ይገኛሉ፡፡
አሲሶየትድ ፕሬስ እንደዘገበው እስካሁን ባለው መረጃ ሁለት መቶ አርባ የዩኤስ ኤይድ ሰራተኞች ከስራ ተባረዋል ወይንም ከነበሩበት ቦታ ወደሌላ ተዘዋውረዋል፡፡ በሚቀጥሉት ቀናት ደግሞ በሺህ የሚቆጠሩ የድርጅቱ ሰራተኞች ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥማቸውም ፅፏል፡፡ ይህን በተመለከተ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ እንደዘገበው ደግሞ የዩኤስኤይድ የሰራተኞች ቅጥርና ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ኒኮላስ ጎትሊብ ለሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ሚስጢራዊ ኢሜይል ልከዋል፡፡
ይህ ኢሜይል የአሜሪካ የመንግስት ብቃት አስተዳደር በርካታ የዩኤስኤይድ ሰራተኞችን እንዲያባርሩ ትእዛዝ እንደሰጣቸው የሚገልፅ ነው፡፡ እሳቸው ግን ይህንን ከሰራተኞች ደንብ ውጭ የሆነ ውሳኔ ለመፈፀም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በግዳጅ እረፍት እንዲወስዱ መደረጉን አስረድተዋል፡፡ ጨምረውም በርካታ የዩኤስኤይድ ሰራተኞች በድርጅቱ ውስጥ የሚኖራቸው ቆይታ አጭር መሆኑን የሚገልፅ መልእክት አስፍረዋል፡፡
የመንግስት ብቃት አስተዳደር የሚባለው መስሪያ ቤት በትራምፕ መንግስት የተፈጠረ አዲስ ተቋም ሲሆን የሚመራውም ባለሀብቱ ኤለን መስክ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ተቋም እንዳለው ባለፈው አመት ስድስት ነጥብ ሰባት ትሪሊዮን የነበረውን የአሜሪካ መንግስት ወጪ ወደአንድ ትሪሊዮን የመቀነስ እቅድ አለው፡፡ ተቋሙ ይህንን ወጪ የመቀነስ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ያነጣጠረው ደግሞ ዩኤስኤይድ ላይ ነው፡፡
በመሆኑም በዚህ ሳምንት ወደሀምሳ ያህል ከፍተኛ የዩኤስኤይድ ባለስልጣናት እንዲባረሩ ማድረጉን ዋሽንግተን ፖስት ገልጿል፡፡ በአለማችን ላይ ትልቁ የምግብ ድጋፍ አቅራቢ የሆነው ዩኤስ ኤይድ በዚህ የተነሳ ትርምስ ውስጥ መግባቱን ዘገባው ጨምሮ አስረድቷል፡፡ ዘሃበሻ

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚደንት ሆነው ተመረጡ።
ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤ ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧቸዋል።
ተመራጩ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
በተያያዘ ዜና ጉባኤው አቶ ተመስገን ጥሩነህን እና አቶ አደም ፋራህን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚደንቶች አድርጎ ከፍተኛ በሆነ ድምጽ መርጧል።
ሁለቱ ምክትል ፕሬዚደንቶች በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በጉባኤተኛው ፊት ቃለ መሀላ መፈፀማቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Forwarded from Capitalethiopia
#CapitalNews ከሁለት ዓመታት በፊት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረዉ የብድር ጣሪያ በመጪው በመስከረም ሊነሳ እንደሆነ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመጠን በላይ በሆነ የብድር ስርጭት ምክንያት የተከሰተዉን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ለመቋቋም በሚል ከነሐሴ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባንኮች በሚሰጡት የብድር ጣሪያ ላይ ገደብ ጥሏል።
ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ስራ የገባው የብድር ጣሪያ ባንኮች አመታዊ የብድር እድገታቸው ከቀደመው የብድር ክምችት መጠን በ14 በመቶ ብቻ እንዲያድግ የሚያደርግ የነበረ ሲሆን ባለፈው ወር መጨረሻ እድገቱ ወደ 18 በመቶ እንዲሆን በማዕከላዊ ባንኩ ተወስኖ ነበር።
ሆኖም ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባንኮች የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ ተጥሎ የቆየው ጣሪያ በቀጣይ መስከረም ይነሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዚህም በቀጣይ በዘርፉ ሊኖር የሚችል እድገት የተሻለ እንደሚሆን ከአሁኑ ተስፋ ተጥሎበታል።
አይኤምኤፍ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ስር ባደረገው የቅርብ ጊዜ ግምገማ፣ የገንዘብ እና የፋይናንስ ሁኔታዎች ጥብቅ ሆነው የቆዩ ቢሆንም የአዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውጤታማነት አሁንም ደካማ ነዉ ሲል ገልጿል።

መከላከያ ሚንስቴር፣ "አሸባሪ" ባለው ቡድን ላይ ባለፈው ሳምንት የድሮን ጥቃት የፈጸመው በጅቡቲ ውስጥ እንጂ በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ እንዳልኾነ ማስተባበሉን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል ዘግቧል።
መከላከያ ሚንስቴሩ፣ በድሮን ጥቃቱ ስምንት የቡድኑ አባላት እንደተገደሉ ማስታወቁን ዘገባው ጠቅሷል። በጥቃቱ ቁጥራቸው ለጊዜው ያልታወቁ ሰላማዊ ሰዎች ጭምር እንደተገደሉ የገለጠው ሚንስቴሩ፣ በክስተቱ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩን ማስታወቁም ተገልጧል።
የድሮን ጥቃቱ የተፈጸመው፣ ከኢትዮጵያ ድንበር ስድስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አዶርታ በተባለ አካባቢ ነበር ተብሏል። የፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌህ አማካሪ፣ የጥቃቱ ዒላማ የጅቡቲ አፋሮች አማጺ ቡድን መኾኑን ማረጋገጣቸውንም የዜና ምንጩ ዘገባ ያመለክታል።

እናት ፓርቲ የጣሪያ ግድግዳ/ ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ
እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ ከሚያዝያ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ያደረገው የጣሪያ ግድግዳ/ ንብረት ግብር መመርያ እንዲቆም የመሠረተው ክስ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ። ፓርቲው ዛሬ እንዳለው ክሱ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት መመሪያው "ተፈጻሚ ሊሆን አይገባም" ሲል ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ወስኗል። መመሪያው"ሕግን ባልተከተለ መንገድ እና የከተማ አስተዳደሩ ባልተሰጠው ሥልጣን የወጣ በመሆኑ" እንዲሻሻል ሲል መበየኑን ፓርቲው ገልጿል። እናት ፓርቲ የግብር መመሪያውን በዘፈቀደ የተጫነ ነው የሚለው።
የፓርቲው የሕግ እና ሥነ ሥርዓት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ዋለልኝ አስፋው ፣ ቢሮው መመርያውን "በሕግ ሥልጣን ሳይሰጠው ያወጣው" ነው በሚልም ለአስተዳደር ችሎት ክስ መስርቶ መቆየቱን ዛሬ አስታውቀዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ክስ ላይ "ፓርቲው የክስ ምክንያት የለውም፣ ክሱ በይርጋ የታገደ ነው" በማለት ወደ ፍሬ ነገር ክርክር ሳይገባ ውድቅ ተደርጎ መዝገቡ ሊዘጋ ይገባል ብሎ ተከራክሮ እንደነበር እናት ፓርቲ ገልጿል።
ሆኖም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ያቀረባቸውን መቃወምያዎች ውድቅ በማድረግ ወደ ፍሬ ነገር ክርክር መገባቱን ፓርቲው አስታውቋል። ፍርድ ቤቱ መመርያው "የመመርያ አወጣጥ መርኾዎችን በመከተል የወጣ አለመሆኑን፣ መመርያው የወጣውም የንብረት ግብር አዋጅ ባልወጣቡት በመሆኑ" ተፈጻሚ አይሆንም ሲልም መወሰኑን ፓርቲው ገልጿል።
የእናት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይፈ ሥላሴ አያሌው ፓርቲው የውሳኔውን አፈጻጸም እንደሚከታተልና ለዚህም ሲባል "የፍርድ አፈጻጸም ሥልጣን ላለው የአፈጻጸም ፍርድ ቤት ፋይል ለመክፈት" በዝግጅት ላይ ነው ማለታቸውን ከጀርመን ድምፅ ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

Capital News: የባንኮች የማበደር ገደብ ሊነሳ ነዉ | ተግባራዊ ያልተደረገዉ ህግ | የኢባትሎ አስደናቂ ዉ...
https://youtube.com/watch?v=fzD9AZKu0ZA&si=YdrJJsoq7i4SEUt_

YouTube
Capital News: የባንኮች የማበደር ገደብ ሊነሳ ነዉ | ተግባራዊ ያልተደረገዉ ህግ | የኢባትሎ አስደናቂ ዉጤትጉድለት ምን ታሰበ?
ከሁለት ዓመታት በፊት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረዉ የብድር ጣሪያ በመጪው በመስከረም ሊነሳ እንደሆነ ተገለፀ l የህግ ለዉጥ የተደረገ ቢሆንም አሁንም ህጋዊ የፍጥነት ገደቦች በአዲስ አበባ ተግባራዊ እየተደረጉ አለመሆኑን አንድ ጥናት አመላከተ l ግዙፉ የመንግስት የሎጂስቲክስ ድርጅት የሆነው የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ በተያዘው የበጀት ዓመት አስደናቂ አፈፃፀም አስመዘገበ
…
…
ዩኤስኤይድ (USAID) መፍረስ ያለበት ተቋም ነው” ሲል ኤለን መስክ ተናገረ፡፡ ቢሊየነሩ ኤለን መስክ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ድርጅት የሆነውን ዩኤስኤይድን በተመለከተ ከፕሬዝደንት ትራምፕ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቋል፡፡ ከውይይታቸውም በኋላ ይህ ተቋም መፍረስና መዘጋት እንዳለበት ስምምነት መድረሳቸውን አስረድቷል፡፡
የአሜሪካ የመንግስት ብቃት አስተዳደር መስሪያ ቤት ሀላፊ የሆነው መስክ ዩኤስኤይድን ‹‹የወንጀል ድርጅት›› ሲልም ወቀሳ አቅርቦበታል፡፡ የቴስላ ባለቤት የሆነው መስክ ጨምሮም ‹‹የዩኤስ ኤይድ ሰራተኞችን በተመለከተ ከፕሬዝደንቱ ጋር በዝርዝር ተነጋግረንበታል፡፡ ይህ ትልቅ ኳስ በትሎች ተወሯል፡፡ በመሆኑም ሁሉንም ነገር ከስር መሰረቱ ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ የዩኤስኤይድ ችግር ከጥገናም በላይ ነው፡፡ ድርጅቱ በመፍረሱ ላይ እሳቸው ማለትም ፕሬዝደንቱም ተስማምተዋል›› ብሏል፡፡
ኤለን መስክ በኤክስ ስፔስ ላይ ይህንን አስተያየት የሰጠው የሚመራው የመንግስት ብቃት አስተዳደር መስሪያ ቤት ተወካዮች በዋሽንግተን የሚገኘውን የዩኤስኤይድ ዋና ፅህፈት ቤት መረጃዎች መመልከታቸውን ተከትሎ ነው፡፡ ከቀናት በፊት በዋና ፅህፈት ቤቱ የሚገኙ ሚስጢራዊ መረጃዎችን የዩኤስ ኤይድ ከፍተኛ አመራሮች ለማሳየት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀው ነበር፡፡ ይሁንና በዚህ የተነሳ ሁለት ከፍተኛ የዩኤስ ኤይድ አመራሮች ከስራ እንዲባረሩ ከተደረጉ በኋላ መረጃዎቹን ለማግኘትና ለመመልከት እንደተቻለ ዘገባዎች አስረድተዋል፡፡
ዩኤስ ኤይድ በመላው አለም ከሴቶች ጤና ጀምሮ እስከ መጠጥ ውሀ፣ ኤችኤቪ ኤድስ፣ የሀይል አቅርቦትና ፀረ ሙስና ትግሎች ድረስ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ሲያቀርብ የቆየ ተቋም መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ትራምፕ አገራቸው የምትሰጠውን ማናቸውንም እርዳታዎች ለዘጠና ቀናት እንድታቆም ያስተላለፉትን ትእዛዝ ተከትሎ ይህ ተቋምም እንቅስቃሴዎቹን ማቋረጡን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በዚህ የተነሳም በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት በዩኤስ ኤይድ ድጋፍ የሚከናወኑ በርካታ ፕሮጀክቶች እንዲቆሙ ተደርገዋል፡፡ በሌላ በኩል የዩኤስ ኤይድ ድረ ገፅና የኤክስ አካውንት ከቅዳሜ ጀምሮ መዘጋቱን ማስታወቃችን አይዘነጋም፡፡

ስዊዘርላንድ ለኤርትራ ስትሠጠው የቆየችውን የቴክኒክ ድጋፍ ከቀጣዩ ግንቦት ወር ጀምሮ ለማቋረጥ መወሰኗን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ስዊዘርላንድ ላለፉት ስምንት ዓመታት ለኤርትራ የቴክኒክ ድጋፍ ስታደርግ የቆየችው፣ የአገሪቱ መንግሥት የዜጎቹን ስደት በመግታትና ስደተኞችን መልሶ በመቀበል ረገድ ተባባሪ እንዲኾን ለማበረታታት እንደነበር ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
ኾኖም የስዊዘርላንድ መንግሥት በቅርቡ ባደረገው ግምገማ፣ ይህ ግብ እንዳልተሳካና የኤርትራ መንግሥት ስደተኞችን ለመቀበልም ኾነ በጉዳዩ ላይ ለመነጋገር ተባባሪ እንዳልኾነ ማረጋገጡን ዘገባዎቹ ጨምረው አመልክተዋል። ባሁኑ ወቅት 7 ሺሕ ያህል ኤርትራዊያን ስደተኞች ስዊዘርላንድ ውስጥ የተጠለሉ ሲኾን፣ 200ዎቹ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖባቸዋል ተብሏል። ስዊዘርላንድ ለኤርትራ በዋናነት የምትሠጠው ድጋፍ፣ ለወጣቶች የሙያ ሥልጠናዎችን መስጠት ነው።

ከአዲስ ፍቅረኛዋ ጋር ለመኖር የባሏን ኩላሊት ያሸጠችው ህንዳዊት
ኩላሊቱ በጥቁር ገበያ ቢሸጥ ለሴት ልጃቸው የትምህርት ወጪና ጥሎሽ እንደሚሆን አሳምና ነው የተሸጠው
ከኩላሊት ሽያጭ የተገኘውን ከ11 ሺህ በላይ ዶላር በፌስቡክ ከተዋወቀችው አዲሱ ፍቅረኛዋ ጋር እየተዝናናችበት ነው ተብሏል
በምዕራብ ቤንጋላ ሳንካሬል በተባለች ከተማ ነዋሪ የሆነችው እንስት ባሏ የአካል ክፍሉን እንዲሸጥ ያሳመነችው የሴት ልጃችን የትምህርት ወጪ ለመሸፈንና ለትዳር እድሜዋ ሲደርስ ለጥሎሽ የሚሆን ገንዘብ እንዳንቸገር በሚል ነው።
ባል መጀመሪያ ላይ የሚስቱን አንድ ኩላሊትህን ሸጠን ችግራችን እንለፍ በሚለው ሀሳብ በፍፁም እንደማይቀበለው ቢገልፅም የወራት ውትወታዋ አቋሙን እንዲለውጥ አድርጎታል።
ባል የቤተሰቡን ወቅታዊ የገንዘብ ችግር እና የልጁን የወደፊት ህይወት ለማቃናት መስዋዕትነት መክፈሉ ጥቅሙ እንደሚያመዝን አምኖበት የሚስቱን ጥያቄ መቀበሉን ያወሳል።
በህንድ የሰው የአካል ክፍልን መሸጥ ወንጀል በመሆኑ የኩላሊት ሽያጩ ሚስት በፈለገችበት ጊዜ አልተካሄደም፤ በጥቁር ገበያ ኩላሊት ገዥ ፍለጋው አንድ አመት ወስዷል ይላል የሂንዱስታን ታይምስ ዘገባ።
ከሶስት ወራት በፊት ስሙ ያልተጠቀሰውን ህንዳዊ ኩላሊት የሚገዛ አንድ ሰው ተገኝቶ 1 ሚሊየን የህንድ ሩፒ (11 ሺህ 500 ዶላር) ለሚስቱ መሰጠቱንም ዘገባው ጠቅሷል።
ድብቅ አቅዷን ለማሳካት ረጅም ጊዜን የጠበቀችው ሚስት ከባሏ አንድ ኩላሊት ሽያጭ የተገኘው ገንዘብ በእጇ እንደገባ በቤቷ ማደርን በመተው አድርሻዋን ታጠፋለች።
ጉዳዩ ግራ ያጋባው ባል የሚስቱን መጥፋት ለፓሊስ ሲያሳውቅ ልቡን በሀዘን የሚሰብር መረጃ ደርሶታል።
የባሏን ኩላሊት በልጃቸው አመካኝታ ያሸጠችው እንስት ባራክፖር በተባለ ከተማ በፌስቡክ ከተዋወቀችው አዲስ "ፍቅረኛዋ" ጋር እንደምትኖር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ክህደት የተፈጸመበት ባል ከፖሊስ በተሰጠው ጥቆማ ሚሰቱና አዲሱ ፍቅረኛዋ ወደሚኖሩበት ቤት ከ10 አመት ልጃቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ቢያቀናም የልጁ እናት ሚስቱ ከቤት አልወጣም ብላለች።
በር ለመክፈት ፈቃደኛ ካለመሆኗ ባሻገር ለልጇ አባት "የፈለከውን ነገር ማድረግ ትችላለህ፤ የፍቺ ማመልከቻ እልክልሀለው" ማለቷም ልቡን እንደሰበረው ተናግሯል።
ግለሰቡ በተደራረበ ሀዘን ውስጥ ልጁን በብቸኝነት ማሳደግ ጀምሯል።
ዘገባው የአል ዐይን አማረኛ ነው::

በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳዬ እንደገለፁት በመዲናዋ 429 ሺህ 829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል፡፡
ይሁንና እስካሁን ባለው ሂደት 228 ሺህ 222 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር መፈፀማቸውን በመግለፅ ይህም የዕቅዱ 51 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
የቤትና ቦታ ግብር በተለምዶ የአፈር፣ የቤትና ጣሪያ በሚሉና መሰል ስያሜዎች እስከ የካቲት 30 ድረስ የሚሰበሰብ የግብር አይነት መሆኑ ተገልጿል።

ኬንያ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች!
ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር በምትዋሰንበት የድንበር ግዛቶቿ ላይ ባሉ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ ያነጣጠረ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯን አስታወቀች።የኬንያ መንግሥት የጦሩ አባላት ተደብቀውባቸዋል ባላቸው የማርሳቤት እና ኢሲዮሎ ግዛቶች ላይ "ወንጀለኞችን የማስወገድ" የተሰኘ ከፍተኛ የጸጥታ ዘመቻ ባለፈው ወር ጥር፣ 25/ 2017 ዓ.ም መጀመሩን ገልጿል።
እነዚህ ግዛቶችን "ድንበር ዘለል የወንጀል ድርጊቶችን ለማሳለጥ የሚጠቀምባቸው ናቸው" ሲል የኬንያ መንግሥት ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት ሰኞ ጥር፣ 26/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ቡድኑን ወንጅሎታል።የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ ጥሰቶች የሚወነጅለው "ሸኔ" እያለ የሚጠራው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኬንያ ግዛቶች ውስጥም ህገወጥ የማዕድን ማውጣትን ጨምሮ ሌሎች ጥሰቶች እየፈጸመ ነው ኬንያ ወንጅላለች።
የኬንያ ብሔራዊ ፖሊስ ቡድኑ "በተለያዩ ህገወጥ የጦር መሳሪያ፣ አደንዛዥ ዕጾች ዝውውር፣ ህገወጥ የማዕድን ማውጣት ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ንግድ ተሰማርቶ ይገኛል" ብሎታል በመግለጫው።የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት "ለገንዘብ ሲል እገታዎችን በመፈጸም እንዲሁም ድንበር ዘለል ወረራዎችን በማካሄድ እና በጎሳዎች መካከል ግጭቶች እንዲቀሰቀሱ በማድረግ ለኬንያ የብሔራዊ ደህንነት ከፍተኛ ስጋት" ሆኗል ሲል መግለጫው አስፍሯል።
የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በበኩሉ ቡድኑን መወንጀል አዲስ ነገር እንዳልሆነ ጠቅሶ በዘረፋዎችም ሆነ በህገወጥ ተግባራት እንዳልተሳተፈ እና "ለፍትህ" የሚታገል ድርጅት መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።"እንዲህ አይነት ጥሰቶችን የሚፈጽሙ አካላትን ከኬንያ መንግሥት ጋር በመተባባር እንደሚዋጉ" የጦሩ ዋና አዛዥ አማካሪ ጂሬኛ ጉዴታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኬንያ በታጣቂዎቹ ላይ የጀመረችው ዘመቻ ባለፈው ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ወደ ኬንያ ተጉዘው ከአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው።በውይይቱ ላይ የኬንያው የብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ኑረዲን ሐጂ ተገኝተው ነበር።
ታጣቂው ቡድን "በኬንያ ቦረና እና በኢትዮጵያ ኦሮሞ መካከል ያለውን የባህል ትስስር እንዲሁም ቅርብ ዝምድና በመጠቀም በማርሳቤት እና ኢሶዮሎ ግዛቶች ውስጥ ባሉ ህዝቦች መካከል ሰርጎ በመግባት በድንበር አካባቢ በሚኖሩ ማህበረሰቦች ላይ ጥሰቶችን" እየፈጸመ ይገኛል ብሎታል የኬንያ ፖሊስ መግለጫ።
መግለጫው አክሎም "ቡድኑ በሴቶች እና በታዳጊዎች ላይ ወሲባዊ ጥቃቶችን ጨምሮ ማስፈራራት፣ በኃይል ንብረትን መውሰድ በአካባቢው በመፈጸሙ ማህበረሰቡን ለሰቆቃ ዳርጎታል" ብሏል።
ህይወትን፣ ንብረትን እንዲሁም ሰላምን ለማስጠበቅ በግዛቲቱ ተደብቀው የሚገኙ "የኦሮሞ ነጻነት ወንጀለኞችን ለማስወገድ" የኬንያ ብሔራዊ የፖሊስ አገልግሎት የወታደራዊ የመጀመሪያ ምዕራፍ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን የአገሪቱ ፖሊስ ምክትል ዋና አዛዥ ጊልበርት ማንጊሲ እንዲሁም የወንጀል ምርመራ አገልግሎት ዳይሬክተር መሀመድ አሚን በትናንትናው ዕለት ገልጸዋል።
Via BBC

#CapitalNews ከዩ.ኤስ.ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን እንዳያስተላልፉ ማስጠንቀቂያ ተሰጠ
በአሁኑ ወቅት ከዩ.ኤስ.ኤይድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙ ድርጅቶች በማናቸውም መልኩ ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑንና ይህነ በሚተላለፉ ተቋማት ላይ እርምጃ እወዳለሁ ብሏል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለሁሉም የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በጻፈው እና ለካፒታል በደሰረዉ ደብዳቤ ላይ እንደተገለፀዉ ያለ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግልፅ ፍቃድ ንብረት የማስተላለፍ፣ የማስወገድ ወይም የመሸጥ ወይም ከመደበኛ/ፕሮጀክት ስራዎች ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲንቀሳቀሱ ጠይቋል።
ይሁን እንጂ በማናቸውም መልኩ ሃብትና ገንዘብን ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ የተከለከለ መሆኑን የገለፀው ባለስልጣኑ ይህንን ማሳሰቢያ በመተላለፍ በሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ ጠቁሟል።
ከሰሞኑ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩ.ኤስ.ኤይድ) በኩል የእርዳታ ማቆም ውሳኔ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንና ዝርዝር ሁኔታዎችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል የሚያከናዎን መሆኑን ተቆጣጣሪ አካሉ አስታውቋል ።

በሰው ልጆች አፈጣጠር ሣይንሳዊ ምልከታ 3.18 ሚሊዮን ዓመት እድሜ እንዳለው የሚገመተው የሉሲ ወይንም ድንቅነሽ ቅሪተ-አጽም አውሮጳ ውስጥ ለዕይታ ሊቀርብ ነዉ ተብሏል።
በሰሜን ምሥራቅ የኢትዮጵያ ክፍል አፋር ውስጥ ከግማሽ ምእተ ዓመት በፊት የተገኘው ይህ ቅሪተ-አካል ከዚህ ቀደም ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለዕይታ ተወስዶ ነበር ።
አሁን በአውሮጳ፤ ቼክ ዋና ከተማ ፕራኅ ብሔራዊ ቤተ-መዘክር ለመጀመሪያ ጊዜ ለዕይታ ይቀርባል ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ።

ከ5 ሺህ በላይ ሰራተኞች ውላቸው እንዲቋረጥ መመሪያ ተሰጠ።
ጤና ሚኒስቴር በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ (USAID) ድጋፍ የተቀጠሩ ከ5 ሺህ በላይ ስራተኞችን ውል እንዲቋረጥ መመሪያ ሰጠ።
ጤና ሚኒስቴር ከአሜሪካ መንግሥት በሲዲሲ (CDC) ወይም ዩኤስኤይድ (USAID) አማካኝነት በተገኘ የበጀት ድጋፍ የሚከናወን ማንኛውም ስራም ሆነ ክፍያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጃንዋሪ 24 ,2025 ጀምሮ እንዲቋረጥ ማሳሰቢያ እንደደረሰው ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው እና በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ተፈርሞ ለሁሉም የክልል ጤና ቢሮዎች የተሰራጨው ደብዳቤ " በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ የተቀጠሩ እና ተቋማችሁ ከCDC ወይም USAID ጋር በሚያደርገው ውል መሰረት የተቀጠሩ ሰራተኞችን በተመለከተ ስራ ላይ እንዲውል አሳስባለሁ " ይላል።
ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የደብዳቤውን #ትክክለኛነት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በሰጡን ተጨማሪ ማብራሪያ በመላው ሃገሪቱ በሲዲሲ እና ዩኤስኤይድ አማካኝነት በኮንትራት እያገለገሉ ያሉ ሰራተኞች ቁጥር 5 ሺህ እንደሚሻገር ገልጸዋል።
ሚንስትሩ " ሰው እንዲዘጋጅ ነው እንጂ የአሜሪካ መንግሥትም ሃሳቡን ሊቀይር ይችላል የተቀየረ ነገር ካለ የሚቀጥል ይሆናል አሁን ባለው ሁኔታ ግን ድጋፉን ካቋረጠ ሌላ መፍትሄ ማፈላለግ ያስፈልጋል " ብለዋል።
" ለዚህ ደግሞ ሰራተኞቻችን እንዲዘጋጁ ከመንግስት ጋርም ንግግር እየተደረገ ነው ያለው የመንግስት ሰራተኞች ስራውን እንዲያስቀጥሉ የCDC እና USAID ሰራተኞች ስራውን እንዲያቆሙ ተወስኗል " ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው በዝርዝር ምን አሉ ?
" እኛን በዋናነት የሚመለከተን በጀቱ በቀጥታ በእኛ በኩል ስለሚመጣ የሲዲሲ ሰራተኞችን ነው ዩኤስኤይድ ግን ቅጥር የሚያከናውነው በራሱ በኩል ነው ውሉንም የሚያቋርጡት ራሳቸው ናቸው።
የአሜሪካ መንግሥት ሃሳቡን ቀይሮ ሌላ መረጃ የሚያስተላልፍ ከሆነ እኛም ሌላ መረጃ የምናስተላልፍ ይሆናል አሁን ባለው የአሜሪካ መንግስት ውሳኔ ግን ኮንትራታቸውን ማቋረጥ አስፈላጊ በመሆኑ ይህንን ደብዳቤ አስተላልፈናል።
ከ5 ሺ በላይ ይሆናል ትክክለኛ ቁጥራቸውን ለማወቅ መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየሰራን ነው ሁሉም በኮንትራት ናቸው ኮንትራታቸው በየአመቱ ይታደሳል ስራቸውም ከኤች አይ ቪ ጋር የተገናኙ ስለሆነ አብዛኞቹ የቆዩ ሰራተኞች ናቸው።
በጣም አስፈላጊ በመሆናቸው ነበር በዚህ ያህል በጀት ተቀጥረው ሲሰሩ የነበረው 15 እና 20 ዓመት የሞላቸውም አሉ ስራው ላይ ችግር ሊያመጣ ይችላል።
በአንድ ጊዜ ይሄን ያህል ሰው ከሴክተሩ ከተቀነሰ ችግር ሊፈጠር ይችላል ዋናው ነገር ግን ስራው እንዳይስተጓጎል ሃላፊነቱን ላለው የመንግስት ሰራተኛ እያስተላለፉ መሄድ ያስፈልጋል።
ቀላል ስራ አይደለም የሚጠብቀን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን።
የመጨረሻ ውሳኔዎችን አልሰማንም ከአሜሪካ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውሳኔዎች እየተላለፈ ስለሆነ ዛሬ ሌላ ነገ ሌላ ነው የሚባለው ሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ተመሳሳይ ነገር ነው እያደረጉ ያሉት ከሁሉም ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።
የዓለም ጤና ድርጅትም በቦርድ ደረጃ ከሁሉም የአፍሪካ ሃገራት ጋር ውይይቶችን እያደረገ ይገኛል።
ሰራተኞችም እንዲያውቁ እኛም ጫናውን ለማሳወቅ እና መፍትሄው አብሮ ለመፈለግ እንዲቻል ለመንግሥትም አሳውቀናል ስራ እንዳይጎዳ ከፍተኛ ጥንቃቄ ይደረጋል።
በዚሁ ከቀጠለ ሌላም ከባባድ ውሳኔዎች ሊወሰን ይችላል የመድኃኒት ግዢ እና ሌሎችም ድጋፎች ሊቋረጡ ይችላሉ አይታወቅም እንዳይቋረጥ እና እንዲቀጥል እኛም እንደሃገር የምንችለውን ጫና እናደርጋለን።
በውስጥ አቅም በውስን የሰው ሃብት ባለን በጀት ስራዎች እንዳይስተጓጎሉ በሽታዎች ተመልሰው ከፍ እንዳይሉ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶችን እያደረግን እንገኛለን በሚቀጥሉት ጊዜያት የሚመጡ ውጤቶችን እና ቀጣይ ውሳኔዎችን እናሳውቃለን " ብለዋል።
#TikvahEthiopia

በማረሚያ ቤት ውስጥ ፎቶ ተነስተዋል በተባሉት ታራሚዎች ዘንድ ተንቀሳቃሽ ስልክ በፍተሻ መገኘቱን የፌደራል ማረሚያ ቤት አስታወቀ
ከሰሞኑ በማረሚያ ቤት የአየር መንገድ ደህንነትን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል ተብለው በወንጀል ተከሰው ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው የሚከታተሉ እነ ጆን ዳንኤል ከማረሚያ ቤት ሆነው ለቀውታል በተባለ ፎቶ ዙሪያ ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን የማረሚያ ቤቱን አስተዳደር ጠይቆ ምላሽ አግኝቷል።
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዋና ዳሬክተር አቶ ገረመው አያሌው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ስልኩ በፍተሻ ተገኝቷል።
ይህን ባደረጉ አካላት ላይ የማጥራት ስራ ተሰርቶ ጥፋተኛው ላይ በአሰራሩ መሠረት በህግ አግባብ ተመጣጣኝ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑንም አቶ ገረመው ለብስራት ተናግረዋል።