tgoop.com/Humanity02H/11
Last Update:
1,እንኳን ተኝተህ ነቅተህም ትሄዳለህ
.
.
.
.
ከባለፈው የቀጠለ
===========
ጊዜን የሚያባክኑ አሥራ አምስት(15) ነገሮችንም በጥናታቸው ዘርዝረዋል፤
አንደኛ፦ ስለ ሕይወት ያለን የተዛነፈ አረዳድ፣
ሁለተኛ፦ ጥርት ያለ የሕይወት ግብ አለመኖር
ሶስተኛ፦ በነገሮች ላይ መወሰን አለመቻል፣
አራተኛ፦ የስሜት መዘበራረቅ መፈጠር፣ አምስተኛ፦ ስንፍና፣
ስድስተኛ፦ ትኩረት ማጣት፣
ሰባተኛ፦ የሚመች ጊዜ መጠበቅ፣
ስምንተኛ፦ ሱስኝነት፣
ዘጠነኛ፦ እንቅልፍ ማብዛት፣
አስረኛ፦ የዝቅተኝነት ስሜት፣
አስራ አንደኛ፦ ብዙ በማይጠቅሙ ነገራቶች ላይ ማተኮር፣
አስራ ሁለተኛ፦ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም፣
አስራ ሶስተኛ፦ ትኩረት ፈላጊ ባሕልና ቤተሰብ ውስጥ መሆን፣
አስራ አራተኛ፦ ፍጹማዊነትን መጠበቅ፣
አስራ አምስተኛ፦ የመዝናናት ትርጉም መሆናቸውን ገልጸዋል። እዚህ ያልተጠቀሱ ነገር ግን እንደግል የሚመለከቱንን ነገሮች ደግሞ ነቅሶ የማስወገድ ጉዳይ የሚመለከተው እኛኑ መሆኑ መረሳት የለበትም።
ምሁራኑ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም የሚከተሉትን አሥር ነገሮች ማድረግ ወሳኝ መሆኑንም አስፍረዋል፤
አንደኛ፦ ሕይወትን ከዓላማ ጋር ማሰር።
ሁለተኛ፦ ጊዜ ገዳይ ነገሮችን የተቻለውን ያህል ማስወድ።
ሦስተኛ፦ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች ለይቶ ቅድሚያ መስጠት።
አራተኛ፦ አሉታዊ ልማዶችን መንቀልና አዎንታዊ ልማዶችን መከተል።
አምስተኛ፦ ተግባርን በትናንሹ መከፋፈል።
ስድስተኛ፦በአስፈላጊው ቦታ እምቢ ማለትን መልመድ።
ሰባተኛ፦ ጥርት ያለ ግልፅ የህይወት ግብ መከተል።
ስምንተኛ፦ አእምሮን የሚያነቃቁና የሚያድሱ ነገሮችን ማድረግ።
ዘጠነኛ፦ በተመረጠ ሰአት የተመረጠ ነገር ማድረግ።
አስረኛ፦ ስሜትን ማደስ ናቸው። (በዋናነት ከዶ/ር ኢሃብ ፊክር እና ከዶ/ር ዐሊይ ዐባስ የድምፅ ትምህርቶች ላይ የተቀነጨቡ ናቸው)
ታላቁ ቁርአንም ስለ ጊዜ በተለያዩ አንቀጾቹ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ይሰጣል። ለምሥሌ የሚከተሉትን አንቀጾች እንመልከት፤
.
.
.
.
.
ይቀጥላል.....
============
ምንጭ፦ የማር ጠብታ ከሚለው መጽሓፍ
============
Join our telegram channel for,more topic፦
https://www.tgoop.com/Humanity02H
BY Human and Humanity
Share with your friend now:
tgoop.com/Humanity02H/11