Telegram Web
Audio
ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)
አዲስ ሙሃዶራ

ርእስ:- የሰውና የጂን ሸይጧኖች

🎙ኡስታዝ ዐብዱልቃዲር ሐሰን (ሀፊዘሁላህ)

በአሊቾ ዊሪሮ ወረዳ በገድራት ቀበሌ ጮል  መንደር በአል-አቅሳ መስጂድና መድረሳ የቀረበ

#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
አል ፈታዋ
በሸይኽ ዐብዱልሐሚድ (ሀፊዘሁላህ)
አል ፈታዋ

🎙በሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሀፊዘሁላህ)

በአሊቾ ዊሪሮ ወረዳ በገድራት ቀበሌ ጮል  መንደር በአል-አቅሳ መስጂድና መድረሳ የቀረበ

#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
Audio
በኡስታዝ ታጁ (አቡ ሙዓዝ) ሀፊዘሁላህ
አዲስ ሙሃዶራ

ርእስ:- የሠለፎች መንገድ!

🎙ኡስታዝ ታጁ (አቡ ሙዓዝ) ሀፊዘሁላህ

በአሊቾ ዊሪሮ ወረዳ በገድራት ቀበሌ ጮል  መንደር በአል-አቅሳ መስጂድና መድረሳ የቀረበ

#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (www.tgoop.com/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
በዩኒቨርስቲ ካሉ መጥፎ ልማዶች መካከል፦

➧ እንደሚታወቀው ዩኒቨርስቲ ማለት የአስተሳሰብ ለውጥ የሚመጣበት የስልጣኔ መስመሩ የሚገኝበት ከሌላው በተሻለ መልኩ ሀገር ለመረከብ ቤተሰብ ለመምራት ወዘተ የተሻለ መንገዶች የሚቀመሩበት መድረክ ነው ተብሎ ይታሰባል።
➜ ከመሆኑም ጋር የሰለጠኑ ሀገር ለመረከብም ሆነ ለየትኛውም ሀላፊነት ዝግጁ የሆኑ ተማሪዎች እንዲመመረቁ ሁሉ በሌላ በኩልም ከመሰልጠን ይልቅ መሰይጠን፣ ከመትጋት ይልቅ መተኛት፣ ከመለወጥ ይለቅ መቀወጥ፣ ከመማር ይልቅ መሽቀርቀር... የሚያምራቸው በርካቶች ናቸው።
➧ እዚህ ስራ ፈቶች ትምህርቱን ትተዋልና የሚቀላቸው የተለያዩ ፈሳዶችን ወደተማሪዎች ማምጣት ነው። በተለይም ተመራቂ ተማሪዎችን ወደተለያዩ ጥፋቶች ለማስገባት የሚጥሩ የሸይጧን አገልጋዮች በርካታ ናቸው። Half life, GC birth day... እያሉ በርካታ ኮተቶችን ወደተማሪዎች ያስጠጋሉ።
🔎 አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! አንተ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ! እነዚህ ስራ ፈቶች ወደፈበረኳቸው ኮተቶች ዘወር እንዳትሉ እናንተን አይመለከትም። እናንተኮ የላቀ አላማ ያላችሁ የዘላለሙን ህይወት ለመውረስ ጉዞ የጀመራችሁ የሀያሉ አላህ ባሮች ናችሁ።

➜ በተለይ ደግሞ አብዛኛው ሙስሊም ተማሪ ጭምር የሚሳተፍበት ተመራቂዎች ከመመረቃቸው በፊት አብረው ለአመታት ከቆዩዋቸው ጓደኞቻቸው ጋር እንዲሁም ከመምህራን ጋር በመሆን የተለያዩ ዝግጅቶችን በማዘጋጀት ሴትም ወንድም በተቀላቀለበት መልክ በአንድ ቦታ በማሳለፍ የሚከውኑት ዝግጅት አለ። ይህ ድርጊት በሚከተሉት ሰበቦች አይፈቀድም።
1ኛ ያለምንም አስቀዳጅ ምክንያት ኢኽቲላጥ አለበት። ❴ካፊር ሴቶችም ወንዶችም ሙስሊም ሴቶችም ወንዶች ያለምንም ግርዶሽ ይደባለቃሉ❵
2ኛ አብዛኞቹ እንደሚያደርጉት ሴቶችም ወንዶችም ዝግጅት ያቀርባሉ። ❨ግጥም፣ ምስጋና፣ ጭውውት ወዘተ❩ ሴት ልጅ ወንዶች ባሉበት ማንኛውም ነገር ማቅረብ አትችልም። ❮{ስለሙስሊሟ እያወራሁ እንደሆነ ተገንዘቡ}❯
3ኛ በካሜራ የታጀበ የፎቶ ትርዒት ሊያደርጉት ይችላሉና በቀጥታ ከሸሪዓ ጋር በሚቃረን ተግባር ተሳታፊ ለማድረግ ያቀርባል።
4ኛ ከባድ ፈተና ይፈጠራል።
   🔎 ተማሪዎቹ ወደ ፕሮግራሙ ሲሄዱ ለምርቃት ያሰፉትን ሙሉ ልብስ (ሱፍ) በመልበስ ነው። ሌላም የሚዋቡበት ነገር ካለ ለመፈፀም ወደኋላ አይሉም። በዚህ መልኩ ሙሽራ ከመሰለ በኋላ ከሴቶች ፊት ይቀርባል። እሷም አላህን ካልፈራች ሽቅርቅር ብላ ትመጣለች። በየመሃሉ እየተያዩ ፕሮግራሙ ይቀጥላል። በሱፉ ገጭ ብሎ ፕሮግራም ሊያቀርብ ከፊቷ ገጭ ይላል። ልብ ይባል 98% የሚሆነው ተማሪ ያላገባ (ማግባት የሚፈልግ ነው) በዚህ ሁኔታ ይቀጥላሉ። ታዲያ ሴቶች አይፈተኑምን? በጣም ይፈተናልንጅ! ወንዱም በተመሳሳይ መፈተኑ አይቀርም። በዚህ ላይ የሸይጧን ሴራ እና የነፍስያ ድክመት ሲደመርበት የሚፈጠረውን አስቡት!

➧ በየትኛውም ዩኒቨርሲቲ የምትገኙ ሙስሊም ወንድም እህቶች ሆይ! በዚህ አይነት ዝግጅት ላይ አትሳተፉ! መምህሮቻችንን እናመስግን ካሉ በአግባቡ ይሁን እንጂ በምስጋና ስም በሱፍ ሽክ ብሎ በመገኘት ለምስጋና ነው ብሎ መፎገር ሸም ነው። በዚህ አይነት ቀውጢ ካላመሰገንከኝ የሚልህ ካለ የራሱ ጉዳይ ዋና ያንተ የእምነት ጥንካሬ ነው። አንተ ዛሬን የምትኖር ነገን የማታውቅ ጭፍን አይደለህም። በዚህ ሀገር ዘርተህ በነገው ዘውታሪ ህይወት ምርትህን ትወስዳለህና ተጠንቀቅ!

ነገሮችን ቀለል አታድርጉ! ለሸይጧን በር አትክፈት ጥንቃቄ ያስፈልጋል። ለትንሽ ደቂቃዎች ነው ምን ችግር አለው አይባልም። በሱፍ ሽክ ብለህ እህትህን አትፈትናት! አንድ ልታገባ 20 መፈተን ምን ይሉታል። በእርግጠኝነት ሴቶች ባይኖሩ እንደሙሽራ መዋቡ ትኩረት አያገኝም ነበር ግን እነሱን ለመፈተን ሽር ማለት የልብ መታመምን ያሳያል። አንቺስ ብትሆኚ እህቶ እውነት ቦታዬ ነው ብለሽ አምነሽበት ነውን? አንቺም ተውበሽ ፊትሽን ቀይረሽ በጠባብ ልብሶች ተወጣጥረሽ ከሆነ የምትሄጅው መጨረሻው ይከፋል። ኒቃቢስቷማ ለምን ትሄድ? እራሷን ለመፈተን? አዎ ጥናት ያላንገላታው በስንፍና የተከነባ ከልቡ ውበት ይልቅ የቆዳው ውበት በሚያሳስበው ሚስኪን በሱፍና በመሳሰሉት ፏ ስላለ በሱ ለመፈተን ትሄድ? በፍፁም ቦታሽ አይደለም አዎ በፍፁም።

🏝 እንደጥቅል እኛ ሙስሊሞች በዘፈቀደ የምንቀሳቀስ አይደለንም እያንዳንዱ ተግባራችን ሸሪዓችንን የማይቃረን መሆን አለበት። ከምንም በላይ ጥንቃቄ በሚያስፈልግበት ሁኔታ መዘናጋት ዋጋ ያስከፍላል።

🕌 አቅሷ የወራቤ ዩንቨርሲቲ ሰለፊይ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓህ

🕌 مسجدالأقصى جماعة السلفيين في جامعة ورابي

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
🏖
https://www.tgoop.com/wru_selefy_official_chanel

🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~ 𝕘𝕣𝕠𝕦𝕡
🏝
https://www.tgoop.com/Werabeuniversitymuslimstudents

አስተያየት ለመስጠት
➴➘➷➴➘➷
https://www.tgoop.com/WRU_Student_Bot
አሳፋሪዎች ናቸው!

የዲላ ዩኒቨርስቲ አመራሮች እንኳን ኒቃብ ጥቁር ማስክ መልበስ አይቻልም እያሉ ነው።

👉 እኔ ያልገባኝ ኒቃቡንስ የደህንነት ስጋት ነው አሉ! ማስኩስ? ወይስ የነሱ ደህንነት የሚደፈርሰው የሴት ልጅ ከንፈር እና ጥርስ ሲሸፈን ነው? ኧረ ሸም ነው! በግልፅ መሰይጠን አይሆንባቸውም?

👌 ነቃብ አውልቂ ስትባል አይሆንም ብላ በእምነቷ ለመጣባት እንቅፋት በዱዓ እንደበመርታት ኒቃቧን አውልቃ በማስክ የምትቀይር እንደት ታሳዝናለች!? በማስክም ከለከሉ ቀጥለው ፀጉሯንም አትሸፍኚው ማለታቸው አይቀርም። ምክንያት አሁን ተሸንፋለችና ቀጣይም እና መሸነፏን ያልማሉ።

👉 ዩኒቨርስቲው ❝የትምህርት ሚኒስቴር የተቋማትን አስተዳደርና መመሪያዎችን ተከትሎ የሚተዳደር ነውና ተቋሙ ያንን ነው እያደረግን ያለነው❞ በማለት የገለፀው ነጭ ውሸት ነው። ለመሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድረው የዲላ ዩኒቨርቲን ብቻ ነውን? ኒቃብ የሚፈቀድባቸው ግቢዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ውጭ ናቸውን? ሲዋሹ ትዝብትን ከግምት አያስገቡም!

🔎 ለማንኛውም ኒቃብ ማለት መልክ የሰውነት አካል ማለት ነው። የሰውነት አካል ደግሞ አይጣልም።

https://www.tgoop.com/AbuImranAselefy/9701
ከብዙ ጥረቶች በኋላ ተሳካ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
አ ል ሃ ም ዱ ሊ ላ ህ

🔎 ከዚህ በፊት በሸይኻችን አቡ ዘር ሀሰን አቡ ጦልሃ አላህ ይጠብቃቸውና በሚከተለው ርዕስ ተለቆ ነበር፦

🏝 الْكَلِمَاتُ النَّافِعَةُ الذَّهَبِيَّة في بَيَانِ أُصُوْلِ وَمَنْهَجِ الدَّعْوَةِ السَّلَفِيَّة

ሸይኻችን ተጨማሪ አስፈላጊ ነጥቦችን በመጨማመር እና ሙሉ ሀረካውን በማስቀመጥ አጠናቀውት ከዛም በሁለት ሙጀለድ ተዘጋጅቶ ቀረበ

👌 𝙥𝙙𝙛 ❴የሁለቱም መጀለድ 𝕤𝕠𝕗𝕥 𝕔𝕠𝕡𝕪❵ በቅርቡ ይለቀቃል። አላህ ከፈቀደ ደግሞ ታትሞ በኪታብ መልኩ በእጃችን የምንይዘው ያድርገን!

https://www.tgoop.com/UstazAbuzarhassenAbutolha/11913
እህቴ ሆይ! እምነትሽ ያዘዘሽን ሒጃብ በአግባቡ ለብሰሽ አክብሪው
———
ሒጃብን ሸሪዓው በሚያዘው መልኩ ዘውትር ለብሶ ማክበር ነው እንጂ የሒጃብ ቀን የሚባል የተለየ ቀን የለውም!!
"
ሒጃብ ማለት እስልምና በሴት ልጅ ግዴታ ያደረገባት ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበት ሰፊ ልብስ እንጂ በአመት አንዴ አናቷ ላይ ብጣሽ ሻሽ ጠምጥማ ቀን ለይታ የምታከብረው ነገር አይደለም!!
"
ሒጃብ ማለት ሴት ልጅ እዚህች አለም ላይ ከተለያዩ ባለጌዎች ሙሉ አካሏን የምትሸፍንበትና የተለያዩ ጨዋ ወንዶች ደግሞ እርቃኗ በመሄዷ እንዳይፈተኑ የምታደርግበት ከፈጣሪዋ አላህ ዘንድ የታዘዘችው በህይወት ዘመኗ ሁሉ የማትለየው ልብስ ነው።
"
ሒጃብ ማለት ሸይጧን እና የእስልምና ጠላቶች እንደሚፈልጉት የምትለብሰው ልብስ ሳይሆን የፈጠራት ፈጣሪዋ እንዳዘዛት ዘውትር የምትለብሰው ወደ ፈጣሪዋም የምትቃረብበት የፅድቅ ልብስ ነው።
"
ሒጃብሽን ዘውትር ሸሪዓው በሚፈልገው መልኩ በመልበስ አክብሪው!! የባለጌዎችና የጅሎች መዝናኛ የዐይን ማረፊያ አትሁኚ።
"
ሒጃብ ማለት ፈጣሪሽ እንድትለብሺው ከእናቶችሽ ከነ ዓኢሻ፣ ከነ ኸዲጃ፣ እንዲሁም ከታላቁ ነቢይ ልጅ ከነ ፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሁም) እኩል እንዲህ በማለት ያዘዘሽ የፈጣሪ ትእዛዝ ነው:-

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ

«አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አል-አህዛብ 59

የአላህን ንግግር ልብ በይ! እህቴ:- «ይህ (በጨዋነታቸው) እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው፡፡» አለ፣ አንቺ ጨዋ ሴት ከሆንሽና በባለጌዎች እንዳትደፈሪ፣ እንዳትለከፊ ከፈለግሽ በስርኣት አላህ ባዘዘሽ መልኩ መልበስ ነው፣ በተቃራኒው ደግሞ ሸሪዓው ከሚፈልገው የሒጃብ አይነት ውጪ ከሆንሽ ራስሽን ለባለጌዎችና ለብልግና እያመቻቸሽ ነው ማለት ነው።
🔸የኢስላም ጠላቶች ይህን ጠንቅቀው ያውቁታል። ለዚያም ነው ሙስሊም ሴቶችን ለባለጌ ወንዶች አጋልጠው ለመስጠት በየ ተቋሙና አቅማቸው በቻለው ሁሉ በት/ት ተቋማትና በመንግስት ተቋማት የሙስሊም ሴቶችን ስርኣት ያለው እምነታቸው የሚያዛቸውን አይነት ሒጃብ እንዳይለብሱ የሚጥሩት። ሙስሊም እህቴን ሒጃቧን ካስወለቋት ለዲኗ ግዴለሽ እንድትሆን ያደርጓታል፣ ምን ይህ ብቻ በመስተፋቅርና በተለያየ መንገድ እምነቷንም የሚያስቀይሯትን ተኩላ ከሀዲ ወንዶችን ይልኩባታል።
"
ሒጃብሽን አላህ ባዘዘሽ መልኩ ከለበሺው ነገ በአኼራ ሰውነትሽ እሳት እንዳይነካውም ይከላከልልሻል። ሒጃብሽ እምነትሽ ነው፣ ሒጃብሽ ስብእናሽ ነው፣ ሒጃብሽ ማንነትሽ ነው!! ሒጃብሽን አውልቀሽ ት/ት የለም!፣ ማንነትሽን ክብርሽን ሽጠሽ ዱኒያዊ ጥቅም ጥንቅር ብሎ ይቅር እንጂ በሒጃብሽ ተደራደርሽ ማለት በእምነትሽ መደራደር እንደሆነ ጠንቅቀሽ እወቂው!! ጥላቻቸው ከእምነትሽ እንጂ ከጨርቁ አይደለም!!።
"
የሒጃብ ቀን ምናም እያሉ ሚያጃጅሉሽን ትተሽ ፈጣሪሽ ከሰባት ሰማይ በላይ ያዘዘሽን ትእዛዝ አክብረሽ ዘውትር አላህ በሚፈልገው መልኩ ሒጃብሽን ጠብቂ!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (www.tgoop.com/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
الكلمات_النافعة_الذهبية_الجزء_الأول.pdf
9.1 MB
ኪታቡ ተ—ለ—ቀ—ቀ
                    
🔍 اسم الكتاب : ➴➴➴
🏝 «الْكَلِمَاتُ النَّافِعَةُ الذَّهَبِيَّة في بَيَانِ أُصُوْلِ وَمَنْهَجِ الدَّعْوَةِ السَّلَفِيَّة»

⬅️ المجلد الأول

🔎 የኪታቡ ስም ፦ ➴➴➴
🏝የሰለፍያ ዳዕዋ አካሄድን እና መሰረቶችን በማብራራት ዙሪያ ጠቃሚ እና ወርቃማ ንግግሮች

የሁለተኛውን ጥራዝ ለማግኘት
➴➴➴➴
https://www.tgoop.com/UstazAbuzarhassenAbutolha/11953

📝 كَتَبَهُ : أَبُو طَلْحَةَ أَبُو ذَرَ بْنُ حَسَنِ بْنِ إِمَامٍ الْإِثْيُوْبِي الْوَلْوِيَ «حَفِظَهُ الله»


📝 ዝግጅት ፦ በታላቁ በሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን ኢማም አቡ ጦልሃ አል`ኢትዮጵይ አልወሎውይ አላህ ይጠብቃቸው!

➩ ጥራዝ አንድ
➩ የገፅ ብዛት 487
➩ በወስጡ በአስራ አራት ክፍሎች የተዘጋጁ የተለያዩ ርዕሶች ተካተዋል።
https://www.tgoop.com/UstazAbuzarhassenAbutolha/11953
الكلمات_النافعة_الذهبية_الجزء_الثاني.pdf
8.7 MB
ኪታቡ ተ—ለ—ቀ—ቀ
                    
🔍 اسم الكتاب : ➴➴➴
🏝 «الْكَلِمَاتُ النَّافِعَةُ الذَّهَبِيَّة في بَيَانِ أُصُوْلِ وَمَنْهَجِ الدَّعْوَةِ السَّلَفِيَّة»

⬅️ المجلد الثاني
🔎 የኪታቡ ስም ፦ ➴➴➴
🏝 ❝የሰለፍያ ዳዕዋ አካሄድን እና መሰረቶችን በማብራራት ዙሪያ ጠቃሚ እና ወርቃማ ንግግሮች❞

የመጀመሪያውን ጥራዝ ለማግኘት
➴➴➴➴
https://www.tgoop.com/UstazAbuzarhassenAbutolha/11953

📝 كَتَبَهُ : أَبُو طَلْحَةَ أَبُو ذَرَ بْنُ حَسَنِ بْنِ إِمَامٍ الْإِثْيُوْبِي الْوَلْوِيَ «حَفِظَهُ الله»

📝 ዝግጅት ፦ በታላቁ በሸይኻችን ሸይኽ አቡ ዘር ሀሰን ኢማም አቡ ጦልሃ አል`ኢትዮጵይ አልወሎውይ አላህ ይጠብቃቸው!

➩ ጥራዝ ሁለት
➩ የገፅ ብዛት 473
➩ በወስጡ በዘጠኝ ክፍሎች የተዘጋጁ የተለያዩ ርዕሶች ተካተዋል።

https://www.tgoop.com/UstazAbuzarhassenAbutolha/11954
አዲስ የደርስ ማስታወቂያ

"ሉዙሙ አስ-ሱና ፊ ሸርሂ ኡሱል አስ-ሱና"
"የሱና መሰረቶችን በማብራራት ላይ ሱናን አጥብቆ መያዝ"


አዘጋጅ: ዶክተር ሑሰይን ሙሀመድ አስ-ስልጢ ሀፊዞሁሏህ

የሚያቀራው : ኡስታዝ ዩሱፍ አህመድ ሀፊዞሁሏህ

የሚቀራው : በባህር ዳር  ቡኻሪ መስጅድ

ዘወትር ከሰኞ እስከ እሁድ
ከዝሁር በፊት

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://www.tgoop.com/alateriqilhaq

كن على بصيرة
🎙️. قال الإمام ابن بطّة العكبريّ - رحمه الله -:

*‏"مَنْ كَرِه الصّواب مِنْ غيره، ونصر الخطأ من نفسه؛ لم يُؤمن عليه أنْ يسلبه الله ما علمه، وينسيه ما ذكره، بل يُخاف عليه أن يسلبه الله إيمانه".*

📚. ‏[(الإبانة الكبرى ١/ ٥٤٧)]
📢 ልዩ የሙሐደራ ዝግጅት ከቃጥባሬ 🔊

እነሆ በቀቤና ልዩ ወረዳ ቃጥባሬ ቀበሌ አሊፍ መስጂድ የፊታችን እሑድ ጥር 25/2017 ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል።

በዕለቱ ከተለያዩ ቦታዎች የሚመጡ መሻኢኾችና ኡስታዞች ተጋብዘዋል።

ተጋባዥ እንግዶች

1⃣ ሸይኽ ዐብዱልሐሚድ ያሲን አልለተሚይ

2⃣ ሸይኽ ሙባረክ ሑሰይን

3⃣ ኡስታዝ በሕሩ ተካ

4⃣ ኡስታዝ አቡ ሐመዊያ ሸምሱ ጉልታ

በአላህ ፈቃድ እጂግ የሚጠቀሙበት ፕሮግራም ይሆናልና ፕሮግራሞትን አመቻችተው፣ ወዳጅ ዘመድዎን ጋብዘው በሰዓቱ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።

ፕሮግራማችን ከጠዋቱ 2:30 ስለሚጀመር ቀድመው ይገኙ።

🔊 ለሴቶችም በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል።

🕌 ቃጥባሬ አሊፍ መስጂድ


https://www.tgoop.com/DarAnnedwa
የእለተ ጁምዓ ሱንናዎችና ስርኣቶች
—————
መታጠብና መቀባባት
ከሰልማነል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “አንድ ሰው በእለተ ጁምዓ ታጥቦ፣ ከመፀዳዳትም የቻለውንም ተፀዳድቶ፣ ከሚቀባባ ነገርም ተቀባብቶ፣ ቤቱ ውስጥ ከሚገኝ ሽቶ ተቀብቶ፣ ከዚያም ከቤቱ ወጥቶ በሁለት ሰዎች መካከል ካልለያየ፣ ከዚያም የተፃፈለትን ከሰገደ፣ ከዚያም ኢማሙ በተናገረ ጊዜ ዝም ካለ፣ በዚያች ጁምዓ እና በቀጣዩዋ ጁምዓ መካከል ያለውን ወንጀል ይቅር ይባላል።” [ቡኻሪ 883 ላይ ዘግበውታል]

ከሌላ ጊዜ የተሻለ ቆንጆ የሆነውን ልብስ መልበስ
ከሙሀመድ ኢብን የህያ ኢብን ሂባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “አንዳችሁ ለእለተ ጁምዓ ከሌላ ጊዜ የተሻሉ ሁለት ልብሶችን ብይዝ የተሻለ ነው” [አቡዳውድ 1078 ላይ የተዘገበ ሲሆን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል]

በጊዜ ወደ መስጂድ መግባት
ከአቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ለጀናባ የሚታጠብ አይነትን ትጥበት የታጠበ፣ ከዚያም (ወደ መስጂድ) የተጓዘ ሰው ልክ ግመል ለሶደቃ እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ልክ ለሶደቃ ከብት (ላም) እንዳቀረበ ነው፣ በሶስተኛው ጊዜ የተጓዘ ሰው ልክ ቀንዳማ የሆነ ሙክት እንዳቀረበ ነው፣ በአራተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፣ በአምስተኛው ጊዜ ወደ መስጂድ የተጓዘ ሰው ለሶደቃ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣ መላኢካዎች ኹጥባውን ለማዳመጥ ይሳተፋሉ።” [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

መስጂድ ከገቡ በኋላ በሁለት ሰዎች መካከል አለመለያየት (በሁለት ሰዎች ትከሻ ላይ አለመረማመድ)
ጃቢር ኢብን ዐብደላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ:- የአላህ መልእክተኛ ﷺ እየኾጠቡ እያለ አንድ ሰው ገባ፣ ሰዎች ላይ እየተረማመደ ነበርና የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉት:- “ቁጭ በል! በእርግጥም አስቸግረሃል አርፍደሃልም።” [ኢብን ማጀህ 923 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል]

ሱረቱል ከህፍን መቅራት (ማንበብ)
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “በእለተ ጁምዓ ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ሰው በእርሱና በበይተል ዐቲቅ መካከል ብርሃን ይበራለታል።” [አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 6471 ላይ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ዱዓ ማብዛትና በእለተ ጁምዓ ዱዓ ተቀባይ የሚሆንባትን ሰኣት መጠባበቅ
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:- “የጁምዓ ቀን አስራ ሁለት ሰኣት ነው፣ ከእርሷ ውስጥ አንዲት ሰኣት አለች ሙስሊም የሆነ ባሪያ በዚያች ሰኣት አላህን ከጠየቀ አላህ የጠየቀውን ይሰጠዋል፣ (ያቺን ሰኣት) በመጨረሻ ሰኣት ከአስር በኋላ አካባቢ ፈልጓት።” [ሶሂሁል ጃሚዕ 8190 ላይ አልባኒ ሶሂህ ነው ብለውታል።]

ከአነስ ኢብን ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የዱዓ ተቀባይነት የሚከጀልባትን ሰኣት ከአስር በኋላ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ እስከምትቃረብ ድረስ ባለው ጊዜ ፈልጓት።” [ትርሚዚይ 1237 ላይ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሀሰን ብለውታል።]

በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
ከሶፍዋን ኢብን ሱለይም (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል:- “የጁምዓ ቀን እና የጁምዓ ሌሊት ከሆነ (ከገባ) በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ።” [በሶሂሁል ጃሚዕ 776 ላይ አልባኒ ሶሂህ ብለውታል።]

ማሳሰቢያ:- ይህ ተግባር የሚመለከተው ወንዶችን ነው። በተለይ ሽቶ ተቀብቶ መውጣት ለሴት ልጅ ሙሉ በሙሉ ሀራም ነው። ሴቶች ምንም አይነት ጌጣጌጥ ያለውን እና ወንዶችን ሊፈትን የሚችል ልብስም ሆነ ሽታ ያለው ቅባትና ሽቶ ሳይጠቀሙ ሙሉ በሙሉ የሴቶችን ሸሪዓዊ ስርኣት ያሟላ አለባበስ ለብሰው በአደብ ወደ መስጂድ መሄዱ አይከለከሉም።
✍🏻ኢብን ሽፋ (www.tgoop.com/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
የሰይጣን ድንፋታ
 
ባየህ ጊዜ፡-
      የኔዎቹን ክንብንቤ
      የኔዎቹን ሽፍንፍኔ
ባየህ ጊዜ፡-
     የኔዎቹን ጅቡንቡኔ
     የኔዎቹን ዝይንይኔ፤
ለምን ይሆን- አራስ ነብር እንዳየ - አይንህ የሚፈጥ?
ለምን ይሆን - እንጥልህ እስኪወርድ - የም'ደነግጥ?
ለምን ይሆን - በቁጭትህ ማእበል - የምትናወጥ?

እንስቶችህ ሆነው - ለእርቃን ሩብ ጉዳይ
ውብ ገላቸው ሆኖ - የጎዳና ሲሳይ፤
    ሆና እያለች ሚስትህ - በግድ የለበሰች
    ሆና እያለች እህትህ - ለብሳ ያልለበሰች  
    ሆና እያለ አማትህ - ለብሳ እንዳለበሰች
   ሆና እያለች ልጅህ - ለብሳ እንዳወለቀች፤
አክስት፣ እናቶቼ - ስለተከናነቡ
ሚስት፣ እህቶቼ - ስለተሸፋፈኑ
እንስት፣ ልጆቼ - ስለተጀቧቦኑ
በኒቃብ ተውበው - ስለተዘየኑ፤
      ለምን ይሆን የምትለኝ፡-
          "ባህላችን - በዶዘር ፈንጅ ተናደ
          "እሴታችን - በ'ቶን እሳት ነደደ
          "ትውፊታችን - አገር ጥሎ ተሰደደ"?
ከዚህ ወዲያ ምን አለ?
የጋኔን ሹክሹክታ
የሰይጣን ድንፋታ፡፡

ካይን፣ ከከንፈር ላይ - የሚሰነቀሩ
ከፊት፣ ከጡት ላይ - የሚቸነከሩ
ከፀጉር፣ ዳሌ ላይ - የሚተከሉ
ከባት፣ ተረከዝ ላይ - የሚቸከሉ
       የዝሙት ቀስቶች
       ያመንዘራ ጦሮች
       የሰይጣን አረሮች
መክነው ውለው - መክነው ስላደሩ
ከስረው ሰንብተው - ከሽፈው ስለቀሩ?
      እንዴት ትለኛለህ፡-
         "ባህላችን - በዶዘር ፈንጅ ተናደ
         "እሴታችን - በ'ቶን እሳት ነደደ
        "ትውፊታችን - አገር ጥሎ ተሰደደ"?
ከዚህ ወዲያ ምን አለ?
የጋኔን ሹክሹክታ
የሰይጣን ድንፋታ፡፡

እንስቶችህ  ሆነው - እትዬ እርቃን ቀረሽ
                         -  ያልለበሰች ለባሽ
ውብ ገላቸው
  - እንደ ሳልባጅ ጨርቅ - ክፉኛ ተረካክሶ
  - እንደ መኸር ገለባ - በየቦታው ተልከስክሶ
ውብ ገላቸው - ሜዳው አንሶት
          - አደባባይ ጠቦት
         -  ጎዳናው ተፍቶት
በየቀዬ - በየስርጣስርጡ ሲመናሽ
በየጢሻ - በየጉራንጉሩ ሲፍነሸነሽ፤
 
ለምን ትለኛለህ፡-
"ባህላችን - በዶዘር ፈንጅ ተናደ
"እሴታችን - በ'ቶን እሳት ነደደ
"ትውፊታችን - አገር ጥሎ ተሰደደ"?

ከዚህ ወዲያ ምን አለ?
የጋኔን ሹክሹክታ
የሰይጣን ድንፋታ::

በዶክተር ጀማል ሙሃመድ

የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

https://www.tgoop.com/alateriqilhaq

كن على بصيرة
Audio
AudioLab
በአረቅጥ ሰለፊያ መስጂድ ላይ የተደረገ ሙሀዶራ

በሸይኽ ዐብዱል ሀሚድ አል-ለተሚይ ሃፊዘሁሏሁ

ርዕስ↪️ በዒልም ዙሪያ

ቀን፦ 23//05//2017



https://www.tgoop.com/arekitselefiya_jemea
https://www.tgoop.com/arekitselefiya_jemea
የቢድዐህ ባለ ቤቶችን መለያየት አይክበዳችሁ!!
———
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አውስተው እንዲህ አሉ:-
{احْشُرُوا الَّذِينَ ظَلَمُوا وَأَزْوَاجَهُمْ} الصافات ٢٢
«እነዚያን ነፍሶቻቸውን የበደሉትን ሰዎች ጓደኞቻቸውንም ሰብስቡ፡፡” በተባለ ቀን ጓደኛ ከመሆን በአላህ ይሁንብኝ በዚህ ሀገር የቢድዐህ እና የስሜት ባለ ቤቶችን መለያየት ቀላል ነው።» [አል-ካፊየቱ ሻፊያ…]

ኢማሙ'ል አል-ባኒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
በብቸኝነት ምንም አይነት ግኑኙነትና የሚያሰባስብ ነገር የሌለን ሆነን መሞት ለኛ የተሻለ ነው በአንዲት ነጥብ አላህንና መልክተኛውን ከምናምፅ። ለእኛ በጥመት ከመሰባሰብ ቁርኣንና ሀዲስን በመፃረር ላይ በሚያዘጋጁት መንገድ፣ ሸሪዓውን የሚፃረር መሆኑን እያወቁ ከትእዛዙ ብዙውን እያመፁ ከእነሱ ጋር ከመሰባሰብ ብቸኝነት በላጭ ነው።” [ሲል ሲለቱል ሁዳ ወንኑር]

የየመኑ ሙሀዲስ በመባል የሚታወቁት ሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሓዲ'ል ዋዲዒይ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
ሠለፊይ የሆነ ሰው: የተሰጠውንም ያህል (ጥቅምና ገንዘብ) ቢሰጠው ሱናን፣ ደዕዋን አይሸጥም! እሷ ከገንዘብም ከዝምድናም ከሁሉም ነገር በላጭ ናት!!።” [አል ኢማም አል'መዒይ 253]

ስንቱ ነው "አገሌኮ የረጅም ጊዜ ጓደኛዬ ነው፣ አገሌማ ቤተሰብ ስለሆነ ነው፣ አገሌማ ወደ ሱንና ለመምጣት ሰበብ ሆኖኛል…" እያለ በጭፍን ወደ ቢድዐህ እና ጥመት የሰመጠው?! ወደ ሱንና እንድትመጣ ሰበብ ቢሆንህም ሱንናን ከተወ እሱን ትተህ ሱናን አጥብቀህ መያዝ ነው!፣ ይህ ጓደኝነትና ቤተሰባዊነትም ከሐቅ ከተቀደመ ነገ አላህ ፊት ያዋርዳል!! ሐቅ ከሁሉም በፊት ቀዳሚ ነው!! ፈፅሞ ከሐቅ ጋር የሚወዳደር ነገር የለም!!

በዚህ ወቅት ስንቱ ነው ሱናን ለገንዘብ፣ለክብርና ለዱኒያ ጥቅማጥቅም ሽጦ ትላንት ያውቀው የነበረውን ሐቅ መልሶ ሲተች፣ ትላንት ያወግዘው የነበረውን ባጢል መልሶ ሲያደንቅና እውቅና ሲሰጠው የሚስተዋለው!! ትክክለኛ ጥመት ማለት ይህ ነው!!
አላህ በሐቅ ላይ ፀንተው ከሚገናኙት ባሪያዎቹ ያድርገን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (www.tgoop.com/ibnshifa)
#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
የሴት ልጅ መስተካከልና መበላሸት በባሏ ላይ ከባድ ተፅእኖ ያሳድራሉ!!
—————

➡️ ሀሰኑል በስሪይ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ:-

መካ ውስጥ ልብስ ሻጭ የሆነ አንድ ሰው ዘንድ ልብስ ለመግዛት ቆምኩኝ፣ እየማለ ልብሱን ማወደስ ጀመረ፣ ይህን ጊዜ ከሱ መግዛቱን ተውኩት። ከእንደዚህ አይነት ሰው መግዛቱም ተገቢ አይደለም አልኩና ከሌላ ሰው ገዛሁኝ። ከዚያም  ከሁለት አመት በኋላ (ወደዚያው) ጉብኝት  አደረግኩ፣ እርሱ ዘንደም ቆምኩኝ፣ እየማለም እያወደሰም ሆኖ አላገኘሁትም፣ ለርሱም እንዲህ አልኩት:- ያ  ከአመታት በፊት ያገኘውህ ሰው አይደለህምን? አዎ ነኝ አለ፣ ከዚህ በፊት ከነበርክበት ሁኔታ አሁን ወደ ምመለከትህ ሁኔታ ምን አወጣህ? እየማልከና እያወደሰክም ሆነህ አላይህም፣ አልኩት።

እንዲህ በማለት መለሰ:-
1⃣ ለኔ አንዲት ሚስት ነበረችኝ፣ ትንሽ ነገር ይዤ ስገባ የምታመናጭቅና አሳንሳ የምትመለከት፣ ብዙም ይዤ ስገባ አሳንሳ ተየዋለች፣ ከጊዜ በኋላ ሞተች።

2⃣ ከሷ በኋላ ሌላ ሴት አገባሁ፣ ወደ ሱቅ መውጣት ስፈልግ ልብሴን ይዛ "እገሌ ሆይ! አላህን ፍራ ጥሩ ነገር እንጂ አትመግበን፣ ትንሽ ብታመጣልን ብዙ አድርገን እንቆጥረዋለን/እናብዛዘዋለን፣ ምንም ይዘህ ባትመጣ እንኳን እናግዝሃለን።" ትለኛለች።
[ምንጭ:- አል ሙጃለሰቱ ወጀዋሂር አል-ዒልም 5/251]

↪️ ጥያቄ ለእህቶቼ፣ ለመሆኑ እናንተ ከየትኛዋ ሴት ናችሁ ከመጀመሪያዋ ወይስ ከሁለተኛዋ???
መልሱን… ለአላህ ብላችሁ ከልባችሁ ቆም ብላችሁ በማሰብ ለራሳችሁ መልሱት!።

ከመጀመሪያዋ የሆናችሁ አላህን (ተባረከወተዓላ) ፈርታችሁ ተፀፅታችሁ ወደ ሁለተኛዋ ተመለሱ!!

ከሁለተኛዋ የሆናችሁ ሸይጧን ድንበር እንዳያሳልፋችሁ ነፍሳችሁን ዝቅ እንድትልና ከጌታዋ ከጃይ እንድትሆን አድርጓት!። አላህ ፅናት እንዲሰጣችሁም የዘውትር ዱዓችሁ ይሁን!! ምክንያቱም ይህ እጅግ በጣም ከባድ ነገር ነውና

ባል ሆይ! ለቤተሰብህ ሀራም አታብላ!! የሚስትህንና ልጆችህን ሰውነተ በሀራም አትገንባ!!
የትውልዱ መበላሸት አንዱ ምክንያት ሰውነት በሀራም መገንባቱ ነው!!

ሚስት ሆይ! ባልሽ ከነ ልጆችሽ ሀራም እንዳያበላሽ አደራ በይው!! በሀላሉ አምጣ እንጂ ትንሹም ይበቃል ብለሽ በትንሹም ተብቃቂ!!

ተቅዋ (አላህን መፍራት) ማለት በትንሹ መብቃቃትና ለቀጣዩ አለም መዘጋጀት ማለት ነውና!! አንገብግበሽ አንቺንም ልጆችሽንም ሀራም እንዲያበላችሁ አታድርጊው!!
ኢብን ሽፋ: (www.tgoop.com/ibnshifa)

የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
2025/02/02 19:35:38
Back to Top
HTML Embed Code: