Telegram Web
ሸይኹ ግን ምን ነካቸው?
================
ሸይኽ ሙሐመድ ሀሚዲን በባንክ ላይ በጣም ሲሳሳቱ ግራ ይገባኝ ነበር:: << ፊቅሕ ደካማ ቢሆኑም የዐረብኛ ቋንቋ ጎበዝ ናቸው >> ብለውኝ ይሆናል ብዬ ነበር:: እሳቸውን ልትተች ነው ወይ የሚልም አይጠፋም:: ልተቻቸው አይደለም:: ምን ነክቷቸው ነው ልል እንጂ::

ቪዲዮው እዚሁ አለላችሁ:: አይቶ መፍረድ ነው:: የአማርኛውን የቁርአን ትርጉም ሁላ ስህተት ነው ይላሉ:: ንግግራቸው ይዘገንናል::

<<ኢስቲዋእ ማለት በየትኛውም ዲክሺነሪ ወደ ላይ ከፍ አለ >> ብለው ይናገራሉ:: ግዴሎትም እነሸይኽ ዘመኑ ማንም ማንንም የማያሞኝበት የመረጃ ዘመን ነው:: የትኛውም ዑለማ በብልጭታ የሚገኝበት ወቅት ላይ ነን::

ኢስቲዋእ ትርጉሙ ወደ ላይ ከፍ ማለት ነው?

- ዲክሽነሪ ሳንገልጥ እንየው:: መስጂድ ሶላት ልንሰግድ ስንሰለፍ ኢማሙ << ኢስተው>> ይላል:: ይህንን ቃል ያልሰማ ሰጋጅ የለም:: ሰጋጁ ምንድነው የሚያደርገው? ሰልፉን ያስተካክላል:: <<ተስተካከሉ>> ማለት ስለሆነ:: እንደ ሸይኽ ሙሐመድ ሀሚዲን አተረጓጎም ከሆነ ሚንበሩ ላይ ውጡ:: ወይም ተንጠራሩ ወይም እላይ በላይ ተደራረቡ ነው የሚሆነው:: በዚህ ትርጉም ነው የቀደምት ትርጉም ተሳስቷል ያሉን::

- ቁርአን ውስጥ ከ34 ቦታ በላይ ታገኙታላችሁ:: አንዱም ቦታ ወደ ላይ ከፍ አለ የሚል ትርጉም አይሰጥም:: ፈረስ መጋለብ ላይ እንኳ <<ሊተስተው>> የሚለው ኮርቻው ላይ ስትወጡ የሚል ትርጉም ሳይሆን ወጥታችሁ .. እ? ... ስትስተካከሉ, ስትመቻቹ, ስትደላደሉ ማለት ነው:: ወደ ላይ ከፍ አለ ለማለት ሌላ ደጋፊ ቃል ይፈልጋል::

- የዲክሺነሪ ትርጉሙንማ ጎልግላችሁ ገርቡት::
Via Hassen injamo
ነገ የዓረፋ ፆም ነው
ነገን ማለትም እለት ቅዳሜን/ የዓረፋ ቀንን መፆም የ 2 አመት ወንጀል እንደሚያስምር በሀዲስ መጥቶልና።
ሳንዘናጋ ይህን የተከበረ ቀን ፁመን ለማሳለፍ ከአሁኑ ሰአት ጀምረን ኒያ እንድናደረግ
ኒያው👌
ነወይቱ ሶውመ ገغዲን ዐን ሶውሚ የውሚ ዐረፋህ ተጦውዐን ሊላሂ ተዓላ
نويت صوم غد عن صوم يوم عرفة تطوعا لله تعالى
FUAD MUNA ¬ YEBEG YALEH
<unknown>
የበግ ያለህ

ፉአድ ሙና
ከዶክቶር ሸይኽ ጀሚል ሀሊም አል ሁሰይኒይ የተላለፈ መልዕክት (አሏህ ይጠብቃቸው)

ምስጋና ለአለማቱ ጌታ አሏህ ይሁን አሏህ በሰይዳችን ሙሀመድ እና ንፁህ ፣ ደጋግ በሆኑ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ሶላትን ያውርድ ፦ በመቀጠል ወንድሞቼ እና እህቶቼ በዚህ በተከበረው ፣ በተላቀው እና በተባረከው የሂጅራ አመት መጀመሪያ ላይ እኔንም እናንተንም ወደ አሏህ ተውበት እንድናደርግ አስታውሳለው ፤ ሰዎችን ተውበት እንዲያደርጉ እና ወደ አሏህ ፣አሏህን ወደ መታዘዝ ፣ አሏህን ወደ መገዛት እና አሏህን ወደ ማውሳት ፣ ወደ ዲናዊ ዕውቀት እና ዲናዊ ዕውቀትን ተግባር ላይ ወደ ማዋል እንዲመጡ እንድትጠሯቸው አስታውሳቹሀለው።

ይህንን ጠቃሚ ጉዳይም አስታውሳቹሀለው ዲየሪቢይ "ሙጀረባቱ ሷሊሂን" ላይ የጠቀሱት ሲሆን ፦ ከሙሀረም የመጀመሪያው ቀን ላይ አየቱል ኩርሲይ ሶስት መቶ ስልሳ ጊዜ (360) ይቀራል ፡ መጀመሪያቸው ላይ በስመላን ይቀራል (ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ይላል) ማለትም ሁሉንም እያንዳንዱን ሲቀራ መጀመሪያ ላይ በስመላን ይቀራል (ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ይላል)።  እናም (ዲየሪቢይ) እንዲህ ይላሉ ፡ (ይህንን የቀራ) በዛ አመት ከተረገመው ሸይጣን መጠበቂያ ምሽግ ይሆንለታል። እንደዚሁም በውስጡ አሏህ እንጂ ሌላ የማያውቀው ብዙ ጠቃሚ ነገሮች አሉት። ከዛም (አየቱል ኩርስይን ቀርቶ) ሲያበቃ እንዲህ ይላል፡

"اللهمَ يا مُحَوِّلَ الْأَحْوَالْ حَوِّل حَالِي إِلَى أَحْسَنِ الأحوال بِحَوْلِكَ وَقُوَتِكَ يَا عَزيزُ يَا مُتَعَالْ، وَصَلَى الله على سيّدّنا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم".

❮❮❮www.tgoop.com/shamilunkamil❯❯❯
አንድ ኢኮኖሚስት ሆስፒታል ገብቶ በዶክተር ቦታ ተቀጥሬ ልስራ ቢል ማንም ያንን ስራ እንደማይሰጠው እርግጥ ነው ።
ልክ እንደዛ ሁሉ ወሀቢያ በሱፊዮች መስጂድ ተቀጥሬ ላስተምር ቢል የሚሰማው አይኖርም።
#አንድነት_በሰለፎች_መንገድ_ብቻ_እና_ብቻ
በጨለማው ዘመን ሴት ልጅ ከነ ነብሷ ስትቀበር ፍትህ የሰጧት ውዱ ነቢያችን ﷺ ነበሩ💔
በየመን የ5 አመት ልጅ ደፍሮ የ ገ ደ ለ ው ሰው የአካባቢው ሰው በተሰበሰበበት በጥይት ተመቶ እንዲሸኝ ተደርጎ እንደገና በክሬን አንጠልጥለውታል #ይህ_ነው_አንጀት_አርስ_ፍርድ
የኛ ሀገሩም ፍርድ ይህ ነው መሆን ያለበት
#ፍትህ_ለሄቨን
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😔😭😭😭😭😭😭😭
ሙስጠፍ አለች ምላሴ
አፍቅራዉ ከሩህ ከነፍሴ
አላዉቅም ሰዉ ከአንቱ በቀር
በዘመን በታሪክ መዝገብ
በዚህ ልክ ፍጡር ሲፈቀር 💕💕🖤
ከነቢ ስም ርቄ ወጥቼ ካያችሁ
ቅሩልኝ ፋቲሀን እንደሞትኩ አውቃችሁ
ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ❤️
Live stream finished (5 minutes)
2025/03/04 11:40:17
Back to Top
HTML Embed Code: