#ቅዳሜ_ስዑር
ከስቅለት በኋላ ያለው ይህ ቅዳሜ በተለያየ ስያሜ ይጠራል፡፡ ይኽውም ‹‹ቀዳም ስዑር›› ዐቢይ ሰንበት ቅዱስ ቅዳሜ እየተባለ ነው፡፡
1. ቀዳም ስዑር ይባላል፡፡ ይህ ስያሜ ሰንበት በአይሁድ መሻሩን ያመለክታል፡፡
2. ዐቢይ ሰንበት ይባላል፡፡ ሰንበት ዕረፍት ማለት ስለሆነ ይህም ቀን ጌታችን ሁሉንም ሥራ ፈጽሞ በመቃብር አርፎበታልና ትልቁ ሰንበት ለማለት ዐቢይ ሰንበት ተብሏል፡፡
3. ቅዱ ቅዳሜ ይሉታል፡፡ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን በመቃብር ያኖሩት በማዘጋጀቱ ቀን ዓርብ
.ማታ ሰንበት ሲጀምር ሲል ነበር፡፡ ቅዳሜም ከገባ በኋላ እንደ ትዕዛዛቱ ሰንበት ስለሆነ አረፉ፡፡ (ሉቃ.23÷56)
.ሐዋርያት ጌታችን ከተያዘ ጊዜ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ድረስ እህል አልበሉም በዚሀም መሰረት በቤተክርስቲያናችን ከዓርብ ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ድረስ እህል አይበላም፡፡ ይህም አክፍሎት ተብሎ ይጠራል፡፡ ሕዝቡ ከጾመው ምግብ በካህኑ በኩል ለድሆች ማካፈል እንደሚገባው ያመለክታል፡፡ ጌታችን ‹‹ሙሽራው የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል ያን ጊዜ ይጾማሉ›› ብሎ አስቀድሞ ተናግሯል፡፡ (ማቴ9÷15)
በዚህ ዕለት ሞተ ወልደ እግዚአብሔርን የምናስብበት ብርሃነ ትንሣኤውን የምንናፍቅበት ቀን መሆኑን አንዘንጋ፡፡
ክርስቲያኖች ቅዳሜ ጠዋት በቤተ ክርስቲያን ተሰባስበው ጸሎቱ ሲፈጸም “ገብረ ሰላመ
በመስቀሉ- ክርስቶስ በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ፤ ሰላምን ፈጠረ፤ የምሥራች” ይባባላሉ፡፡
ለተሰበሰበ ሁሉ የምሥራች ምልክት የሚሆን ቄጤማ ይታደላል፡፡ ምእመናንም ይህን
እየሰነጠቁ በራሳቸው ያስሩታል፡፡ ወደ ቤተ ክርስቲያን ላልመጡት ደግሞ ካህናት
በየበኩላቸው ልብሰ ተክኅኗቸውን ለብሰው መስቀልና ቃጭል ይዘው ቄጤማውን
“የምሥራች” እያሉ ይሰጣሉ፡፡

ከትንሣኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
✞ ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡
ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
✞ እሁድ- ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡

ከሀና ማህጸን የአዳም ተስፋ ታየች
በኀጢአት የደረቀው የሰው ህይወት በድንግል መወለድ በተስፋ ለመለመ
ጨለማው ዓለም በድንግል መወለድ ብርሃን ሆነ
የሊባኖስ ተራራ በብርሃን ተከበበ
ሊባኖስ የብርሃን መቀነት ታጠቀች
ሊባኖስ በብርሃን አጥር ታጠረች
ኢያቄም የደስታ ካባ ደረበ
ሀና የደስታ አክሊል ደፋች
የብርሃን እናት ድንግል ተወልዳለታለችናችና
የዓለም ሞት በህይወት ተቀየረ
ሰማይ ከሀና ማኅፀን ተወለደች
የሐና ማሕጸን የሰማዯ መውጫ ሆነ
የውርስ ኀጢአት ከድንግል ራቀ
ሰወች ሁሉ በውርስ ኀጢአት በሚወለዱበትን ያለውርስ ኀጢአት ንጹህ ሁና ወላዲተ አምላክ ተወለደች
ከኢያቄም አብራክ ነጭ እንቁ አበራች
ከሀና ማኅጸን ጸአዳ ርግብ ወጣች
የሀና ታሪክ ተቀየረ
ሀና የእግዚአብሔር ወልድ አያቱ ተባለች
ሰማያት ሰለሰማዯ መወለድ ዝማሬ ዘመሩ
ምድር ሰማይን በመሸከሟ እልል አለች
ሰማዯ በምድር ታየች
የአበው ተስፋ መሰረት ተጣለ
አይሁድ አፈሩ
ቤተ ክረርስቲያን የድንግልን መወለድ አበሰረች
በ5485 ዓመተ ዓለም ድንግል ተወለደች
ፀሐይ ሊወጣ ሰማይ ተገኘች
ሰማዯ ከሰው ተወልዳ ፀሐይን ወለደች
እመቤቴ በመወለድሽ የአበው ተስፋ እውን ሆነ።
የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለያችሁ🙏🙏

እመብርኅን ሆይ🙏🙏
ዘመኔ ወደማለቂያው እየተቻኮለ ነውና ባጌጥኩብሽ ስምሽ ምዕራፌ ይደምደም፤ ዓለም ሲላት በጨዋ ደንብ፣ አሊያ በሙግት አንዳንዴም በዱላ አንቺን ልነጥቀኝ ተሰልፋብኛለችና በአንድ ዓይኔ ሰላም ባንቺ ሁሉን ልጋፈጥ፤ በመሳቄ ውስጥ ያለውን ለቅሶ፣ በለቁሴዬ የተጠቀለለውን ደስታ ካንቺ ውጪ ማንም አያቅልኝም ለዚህ ነው በተራ ቃላት፣ በአንደበት መከፈት የማላወጋሽ፤ በመሶብ የቀረበው ገበታ፣ በሳጥን ውስጥ ያለው እንቁ ቢያጓጓም አንቺን መካድ ተቀምጦበታልና ሙት ነው፤ ያላንቺ ከምለብሰው ሙሉ ኩተኛ ልብስ ከአንቺ ጋር ሆኜ መታረዜ ከፍታዬ ነው፤ ተወዳጅ አምላክ ልጅሽ የሕይወቴን ሹሩባ እያለቀስኩ የሚሰራልኝ እንዲያምርብኝ ነውና በእንባዬ አልርገመው፤ እንደ እስራኤል ዘስጋ የግብፅ አመሌ አለቀኝ ብሎ ያገኘውትን እንዳላመልክ እርጂኝ፤ ምንም ባልተፈጠረ ሰዓት ከልጅሽ ማንም አይለየኝም ባልኩበት አፌ በችግሩ ሰዓት የትላንቱ ማ'በያ ጥቅስ ጠቅሼ ቤቴ እንዳልወሸቅና የድብቅ ሰባኪ እንዳልሆን በሁለቱም ተቃራኒ ቦታ ፅኑ ልጅሽ ልሁን፤ ወሬ ብቻ በናጣት፣ ማስመሰል ባደወራት፣ ቦታውን መምሰል በሸመናት፣ በስሜት በቀመለችው ምድር እድል ፈንታዬን ፅዋ ተርታዬን አትሙዪው፤ የደጃፌን መቃን የበጉን ደም ቀቢልኝ የነፍስ ሞቴ ይለፈኝ፤ ሆዶች ብቻ በተሰለፍበት አሰላለፍ ገብቼ እንብላው እንብላው ብቻ እንዳልጮህብሽ ሁሌም ከሆዴ በላይ በሕሊናዬ ሰልፍ አውጪኝ። አሜን እመፍቅር ሆይ ከልጅሽ ጋር ነይልን ተመልሰሽ!🙏🙏

አንድ አይነ ስውር ህጻን ልጅ "አይነ ስውር ነኝ እባካችሁን እርዱኝ" የሚል ጽሁፍ ይዞ መንገደኛውን ይማፀናል
ከፊት ለፊቱ ባስቀመጠው የገንዘብ መሰብሰቢያ ዘንቢል ውስጥ ትንሽ ሳንቲሞች ተቀምጠዋል
በዚያ መንገድ ሲያልፍ የነበረ አንድ ሰው ሳንቲም ከመፀወተው በኃላ እይነ ስውሩን አስፈቅዶት ጽሁፉ የተጻፈበትን ወረቀት ገልብጦት ከጀርባው ሌላ ጽሁፍ ጻፈበት
ወዲያውኑ እግረኛው ሁሉ ዘንቢሉ ውስጥ ሳንቲም እየወረወረ ሞላው
የዚያኑ ቀን ረፋድ ላይ ሰውዬው ወደ አይነስውሩ ልጅ ባቀናበት ወቅት "ምን ብለህ ነው የጻፍከው? ከዚያን ሰአት ጀምሮ እኮ ዘንቢሌ በሳንትም ተሞላ" ሲል ይጠይቀዋል
"ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው: እኔ ግን ላየው አልችልም" የሚል ነው የጻፍኩልህ ብሎ መለሰለት
👇🏾
ሁለቱም ጽሁፎች የልጁን አይነስውርነት ይገልጻሉ ነገር ግን ሰዎች ሲያነቡት የኮረኮራቸው የዛሬን ቀን ውብነት ለማየት መታደላቸው ሲረዱ ነው
ዛሬን ማየትህ እድለኛ ነህ !!🙌🏼
@ Zemelak Endrias

ምክር ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
የምንወደው ጓደኛችን ቢሞትብን ለቀናት ሐዘን እንቀመጣለን። ብር ቢጠፋብንም እንዲሁም እንቆጫለን። ዕለት ዕለት ሐጢአት ስንሠራ ግን ጥቂትስ እንኳ አናስብም ። መቼ ይሆን የምንነቃው?
ልብስ የተሰጠን ከብርሃናዊ ልብሳችን ስለተራቆትን ነው /ዘፍ. 3፥20/። ታድያ በኃጢአታችን ምክንያት በተሰጠን ልብስ ልባችንን ከፍ ከፍ የምናደርገው ስለምንድ ነው?
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ንገሩኝ ከእኛ መካከል የሚኖርበትን ቤት በቆሸሸ ቁጥር የማያጸዳው ማነው? ታድያ የእግዚአብሔር ማደርያ የኾነው ሰውነታችንን በንስሐ መወልወያ የምናጸዳው መቼ ነው?
ልጆቼ ንስሐ ግቡ እንጂ በኃጢአታችሁ ምክንያት በፍጹም ተስፋ አንዳትቆርጡ። ወዳጄ ሆይ! ማፈር የሚገባህ ኃጢአት ስትሰራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አይደለም። ኃጢአት ሕመም ነው። ንስሐ ደግሞ መድኃኒቱ ነው። ከኃጢአት ቀጥሎ ህፍረት አለ ፤ ከንስሐ ቀጥሎ ግን በጌታ የኾነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሐም እናፍራለን።

እንደለመደችው ዛሬም ጎረምሳዋን ይዛ ገብታለች የሴት ጎረምሳ አይጣል ነው!!ከሷ አጠገብ የተከራየሁበትን ቀን እስክረግም ታበሳጨኛለች።ከወንዷ ብዛት ደሞ ምን ሰአት አስገብታቸው ምን ሰአት እንደሚወጡ ይገርመኛ።ልክ ሰአቷን ጠብቃ ማቀሰቷን ስትጀምር ትንሿ እህቴ ብንን 01...
አረ ምንድነው? አደይ አመማት እንዴ?ትለኛለች ...
ህመሟ ሴሰኝነት መሆኑን አታውቅም።አደይ የዋህ ናት ሰው ቀና ብላ አታይም ግን ደሞ ለሊቱን ስትዳራ አድራ ጠዋት ነጠላ አደግድጋ ቤተክርስትያን ስትሄድ ሳይ ይባስ እናደዳለሁ... እመቤቴን እያሉ መማል፤ ገብርኤልን መዘከር ፤መዝሙር በልቅጦ መዋልኮ መንግስተ ሰማያት አያገባም....ደሞ የተከበረ ስራ ያላት ሴት በወንድ ተለክፋ ዛር እንዳለበት ስታጓራ መስማት ያሳዝናል።ቆይ ምን ጎሏት ነው??ምን ስትል እዚ ውስጥ ገባች?? ደሞስ የምታመጣው ማንን ነው??በየቀኑስ አይደክማትም?? እዚህ ቤት ከገባሁ አንስቶ የሁል ጊዜ ጥያቀረዬ ነው
የአደይን ወንዶች ለማየት ሁሌ አቅዳለሁ ተሳክቶልኝ ግን አያውቅም።ዛሬ በለሊት ተነስቼ ወደ ቤተክርስትያኗ ለመሄድ ተሸፋፍና ስትወጣ እኩል በሩን ከፍቼ ወጣሁ ቀድማ ያስወጣችው ሰው እንደሌለ እርግጠኛ ነበርኩ ግን ደሞ አሁንም አጠገቧ ወንድ አለመኖሩ አስደንግጦኝ አፈጠጥኩባት።አደይም አስተያየቴ ግራ ያጋባት
ትመስላለች ....
ሰ..ላም አደርሽ አደይ?(ጎን ጎናን በአይኔ እየሠለኩ በጥርጣሬ እያየኋት
አለሁ ብሬ ምነው በለሊት በሰላም ነው??
አረ ሰላም ነው ወደ ቤተክርስትያን እየሄድሽ ነው መሠለኝ
አይ ብሬ ቤተክርስትያንማ ከሄድኩ ስንት ጊዜዬ
ምን እና በለሊት ነጠላ ለብሰሽ የት ነው ምትሄጂው??
ሆስፒታል ነው ምሄደው አንተ ባለቤቴኮ አንተ ከመከራየትህ በፊት አብሮኝ ነበር ሚኖረው አንተ ግን አታቀውም፡፡ታሞ ሆስፒታል ከገባ ወራት ተቆጠሩ ከስራ ስንመጣ የሚነዳት መኪና ተበላሽታ ልትወድቅ ስትል እኔን ለማትረፍ እሱ በራሱ በኩል መኪናዋን አጋጫት ይኸው እኔ ምንም ሳልሆን እሱ ግን አሁን ድረስ ኮማ ውስጥ ነው.....
አደይ ፀጥ ስትል ጭራሽ ሌላ ጥያቄወችን አእምሮዬ ይፈጥር ጀመር...ይሄንን ሁሉ ዋጋ የከፈለላት ወንድ ላይ ነው ምትወሰልተው??ምን አይነት ሴሰኛ ናት??ደሞ የዛሬ ጎረምሳዋን የት ከታው ነው??ጥያቄዬ እየተደራረበ ሲመጣ ለመተንፈስ ያህል ወሬዬን ቀጠልኩላት
ታድያ ለሊት ማነው ሚያድርለት ማለት አንቺ....
አዎ ባክህ ቀን ቀን ከስራዬ ጋ እየተሯሯጥኩ አሳክመዋለሁ ለሊት ግን.....
ለሊት ግን ወንዶችሽን ለማን ትተሽ??(በውስጤ እየተንሾካሾኩ እስክታወራ ጠበኳት
በተፈጠረው አደጋ አእምሮዬ ላይ የቀረ ምስል አለ የትም ቦታ ብሆን ለሊት ለሊት እኔ ባይታወቀኝም ሳቃስት ሳምጥ ስጮኽ ነው ማድረው።ይሄ ደሞ ሌሎች በሽተኞችንም ባሌንም ይበጠብጣል።ለዚህ ዶክተሩ ለሊቱን ነርሶች ሊከታተሉት፤እኔ ደሞ ቤት እንዳድር ነገረኝ...ይኸው ለሊቴን ስባትት አድራለሁ ይቅርታ እናንተንም ረበሽኳችሁ ....
ለደቂቃወች መሀላችን ፀጥታ ነገሰ አደይ ትላንቷን እያሰበች እኔ ደሞ በአእምሮዬ ፈጥሬ የረገምኳት የሠደብኳት ያንቋሸሽኳትን እያሰብኩ እራሴን ክፉኛ ታዘብኩት።ሰው በሚያስበን በሚመዝነን በሚገምተን ልክ እግዚአብሔር ቢያይ ማናችን እንተርፍ ነበር??አንዳንዶቻችን ግዜ ኖሮን ሳይቸግረን ሳይጨንቀን ቤተክርስትያን መሄድ ስንሰንፍ ሌላው በብዙ ስቃይ እና መከራ ውስጥ ሆኖ ደጁን የመሣምያ ጊዜ እንኳን እያጣ ልቡን ቤተመቅደስ አድርጎ እየፀለየ እያመሰገነ በመከራ መንገድ እያለፈ ፈጣሪውን ያስባል።አይገርምም ሰው በማያውቀው ሲፈርጀን እግዚአብሔር ግን በሚያውቀው በደላችን እንኳ ይምረናል አደይን ቀና ብሎ የማየት አቅም አልነበረኝም የሰራሁትን ስህተት እያሰብኩ እንዳቀረቀርኩ...
ብሬ እቺን በቤተክርስትያን ስታልፍ ሙዳይ ውስጥ ክተትልኝ ነርሶቹ ሳይወጡ ልድረስ(ጥድፍ እያለች የተጠቀለለች መቶ ብር ሰጥታኝ ወደ በሩ አመራች ኡፍፍ ታድላ በአደይ ቀናሁባት!!
chach

ፍልሰታ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የእመቤታችን ወዳጆች ነሐሴ ወር የእመቤታችንን ፍቅር
የምንገልጽበትን ጾመ ፍልሰትን ይዞ መጥቶልናል ፡፡
<ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ
ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም
የእመቤታችንን ሥጋ ከ ጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን
በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን
ለማመልከት ይነገራል።
ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬
ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን
መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው።
ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው
ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።
ሃይማኖታዊ መሠረት
እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን
ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በ ሊባኖስ ተወልዳለች። <እምሊባኖስ
ትወጽዕ መርአት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች > እንደተባለ
። እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ
መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከ ኢየሱስ
ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከ ዮሐንስ
ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር
ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ
ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የ ውዳሴ
ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የ መልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬
ነው። [1]
ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው
ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል
አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ
እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣
አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን
ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ
አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ
ከሐዋርያው ከ ቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር
አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው
ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩
ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው
በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና
በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ
ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው
ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ
ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር
ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር
ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ
ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ
ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ
ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር
ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ
ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም
እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም
ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ
እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ»
አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በ ነሐሴ
መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል።
ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት።
እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች»
በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ
የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት
ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው
ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል
ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው
መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን
አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን
ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና
ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት
የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም
ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ
ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች።
ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ
ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።
የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ
ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ
ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር
፲ ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ
ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት
ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል
ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ
ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት
ታቦት ትባላለች።
ንጉስ ሰሎሞን ም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪
ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ
ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ
...ዉበቴ»" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ
ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች»
እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ
በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት
ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት
። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን
እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የእመቤታችን ወዳጆች ነሐሴ ወር የእመቤታችንን ፍቅር
የምንገልጽበትን ጾመ ፍልሰትን ይዞ መጥቶልናል ፡፡
<ፍልሰታ > የሚለው ቃል የሚገልጸው ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ
ቦታ ለቆ መሔድን መሰደድን መፍለስን ያመለክታል። ይህም
የእመቤታችንን ሥጋ ከ ጌቴሴማኒ ወደ ገነት መፍለሱን
በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ስር ከነበረበት መነሳቱን
ለማመልከት ይነገራል።
ጾመ ፍልሰታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፷፬
ዓመት በዚች ምድር ኖራ እንደ አንድ ልጇ መሞቷን
መነሳቷንና ማረጓን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት የጾሙት ጾም ነው።
ጾሙ ከነሐሴ ፩ ቀን እስከ ነሐሴ ፲፮ ቀን ሲጾም የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ከደነገገቻቸው
ሰባቱ አጽዋማትም አንዱ ነው።
ሃይማኖታዊ መሠረት
እመቤታችን ከአባቷ ከኢያቄም እና ከናቷ ከሐና ነሐሴ ፯ ቀን
ተጸንሳ ግንቦት ፩ ቀን በ ሊባኖስ ተወልዳለች። <እምሊባኖስ
ትወጽዕ መርአት ፦ ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች > እንደተባለ
። እምቤታችን በእናት አባቷ ቤት ሦስት ዓመት፤ በቤተ
መቅደስ አሥራ ሁለት ዓመት፤ ከልጇ ከወዳጇ ከ ኢየሱስ
ክርስቶስ ጋር ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ፡ ከ ዮሐንስ
ወልደዘብዴዎስ ዘንድ አሥራ አራት ዓመት ከዘጠኝ ወር
ቆይታ በ ፷፬ ዓመት ዕድሜዋ በ፵፱ ዓ/ም ከዚህ ዓለም
በሞት ተለይታለች። የእመቤታችንን ስም የሚገልጹ የውዳሴ
ጽሑፎችም በእድሜዋ ልክ ተደርሰዋል። ለምሳሌ የ ውዳሴ
ማርያም ቁጥር ፷፬ ነው፤ የ መልክአ ማርያም ቁጥርም ፷፬
ነው። [1]
ባረፈች ጊዜ ቅዱሳን ሐዋርያት ተሰባስበው አስከሬኗን ይዘው
ወደ ጌቴሴማኒ መቃብር ለማሳረፍ ሲሄዱ አይሁድ ለተንኮል
አያርፉምና ተተናኮሏቸው። ቀድሞ ልጇ ሞቶ ተነሳ፣ አረገ
እያሉ ሲያስቸግሩን ይኖራሉ: ደግሞ አሁን እሷም ተነሳች፣
አረገች ሊሉ አይደል በማለት አይሁድ ተሰባስበው አስከሬኗን
ለማቃጠል ሲተናኮሉ እግዚአብሔር በተአምር ከነዚያ
አይሁዶች አድኗቸዋል ። የእመቤታችንንም አስከሬን ነጥቆ
ከሐዋርያው ከ ቅዱስ ዮሐንስ ጋር በገነት በዕፀ ህይወት ስር
አኑሯቸዋል ። ከዚያ በኋላ ሐዋርያት ሥጋዋን አግኝተው
ይቀብሩት ዘንድ በአረፈች በስምንተኛው ወር ከነሐሴ ፩
ጀምሮ እስከ ነሐሴ ፲፬ ቀን ድረስ ሁለት ሱባዔ ይዘው
በአሥራ አራተኛው ቀን ሥጋዋን ከጌታ ተቀብለው በጸሎትና
በምህላ በፍጹም ደስታ በጌቴሰማኔ አሳረፉት ። በ
ሦስተኛውም ቀን ተነስታ ስታርግ ከሰኡቃዊያን ወገን የሆነው
ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ አያት። እርሱም በቀብር ስርዓቱ
ጊዜም አልነበረም። ሀገረ ስብከቱ ህንድ ስለነበር
ሊያስተምር ወደዛው ሂዶ ነበርና። በዚያም ሲያስተምር
ሰንብቶ በደመና ተጭኖ ሲመጣ ያገኛታል። ትንሳኤዋን ከርሱ
ሰውራ ያደረገች መስሎት አዝኖ «ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ
ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ
ነውን ?» ብሎ ቢያዝንባት እመቤታችንም ከርሱ በቀር
ማንንም ትንሳኤዋን እንዳላየ ነግራ አጽናናችው። ለሌሎቹ
ሐዋርያትም እንዲነግራቸው ለምልክትም /ለምስክርም
እንዲሆነው ሰበኗን /መግነዟን ሰጥታው አረገች። ቶማስም
ኢየሩሳሌም ደርሶ ሐዋርያትን «የእመቤታችን ነገርስ
እንደምን ሆነ?» ሲል ቢጠይቅ «አግኝተን ቀበርናት እኮ»
አሉት። እርሱ ምስጢሩን አዉቆ ደብቆ «ሞት በጥር በ ነሐሴ
መቃብር» እንዴት ይሆናል ? አይደረግም ይላቸዋል።
ሊያሳያቸውም መቃብሩ ዘንድ ሂደው ቢከፍቱት አጧት።
እርሱም «አታምኑኝም ብዬ እንጂ እርሷስ ተነስታ አርጋልች»
በማለት ሁኔታውን ተረከላቸውና ለምስክር ይሁንህ ብላ
የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው። ከዚህ በኋላ ለበረከት
ይሆናቸው ዘንድ ሰበኑን ተካፍለው ወደየአህገረ ስብከታቸው
ሄዱ። ዛሬ በቅዳሴ ጊዜ ዲያቆኑ በሚይዘው የመጾር መስቀል
ላይ በሁለት ቀዳዳዎች አልፎ ተጠምጥሞ የምናየው
መቀነት መሰል ጨርቅ የዚያ ሰበን ምሳሌ ነው።
በዓመቱ ሐዋርያት ከያሉበት ተሰባስበው ቶማስ ትንሳኤሽን
አይቶ እኛስ እንዴት ይቀርብናል ብለው ከነሐሴ ፩ ቀን
ጀምርው ሱባዔ ቢይዙ ከሁለት ሱባዔ በኋላ እንደገና
ትንሳኤዋንና እርገቷን ለማየት በቅተዋል። ሐዋርያዊት
የሆነች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናም
ምእመኖቿ ከእመቤታችን በረከትን እንዲያገኙ ይጾሙ ዘንድ
ይህን ሐዋርያት የጾሙትን ጾም እንዲጾሙ አዉጃለች።
ምእመናንም በተለየ መልኩ በጾም በጸሎት በሱባዔ ጽሙድ
ሆነው ይህን ወቅት ያሳልፋሉ።
የእመቤታችን ትንሳኤ ድንገት እንደእንግዳ ደራሽ እንደ ዉሀ
ፈሳሽ የተደረገ ሳይሆን በቅዱሳት መጻሕፍት በትንቢተ
ነቢያት የተገለጸ ነው። ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር ፻፴፩ ቁጥር
፲ ላይ «አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ አንተና የመቅደስህ
ታቦትም» ይላል። በዚህም ምዕመናንን ወደ ምታሳርፍበት
ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህ ታቦት ድንግል
ማርያምን ይዘህ ተነስ አለ። ታቦት የጽላት ማደርያ እንደሆነ
ሁሉ እምቤታችንም ለክርስቶስ ማደርያ በመሆኗ አማናዊት
ታቦት ትባላለች።
ንጉስ ሰሎሞን ም በመኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን ምዕራፍ ፪
ቁጥር ፲ ላይ «ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፤ ወዳጄ ሆይ
ተነሽ፡ ውበቴ ሆይ ነይ» ብሏል። እዚህ ላይ «ወዳጄ
...ዉበቴ»" የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ናት ። ክቡር ዳዊት መዝሙር ፵፬ ቁጥር ፱ ላይ «በወርቅ
ልብስ ተጎናጽፋና ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች»
እንደሚል ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛነቱን ከፈጸመ
በኋላ ወደ ቀደመ ክብሩ እንዳረገ እመቤታችን ቅድስት
ድንገል ማርያምም በቀኙ ትቀመጥ ዘንድ «ተነሽ ነይ» አላት
። እንግዲህ ይህንና የመሰለዉን ሁሉ ይዘን የእናታችንን
እረፍቷን ትንሳኤዋን እንዘክራለን እንመሰክራለንም።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
+ ከታቦር ተራራ አትቅር +
የወንጌላውያን ትሕትና ይደንቃል ፣ ማቴዎስ ማርቆስ ሉቃስ ስለ ደብረ ታቦር ሲጽፉ ዮሐንስ አልጻፈም። ዮሐንስ ተመርጦ የተገኘበትን ታሪክ "ተመርጬ" ብሎ አልጻፈም። የቀሩት ወንጌላውያን ደግሞ "እኛ የሌለንበትን ነገር አንጽፍም" አላሉም። አንድ ወንጌል እየሰበኩ የሚፎካከሩ ፣ የአንድ ቤት ጣሪያ እየሠሩ ቆርቆሮ የሚሻሙ የእኛ ዘመን አገልጋዮች አልነበሩምና እነርሱ ያልተመረጡበትን ታሪክ ለመናገር ተሯሯጡ። እኛን የማያካትት ክብር ፣ እኛን የማይጨምር ድግስ ጉዳይ ሲነሣ ለማይጥመን ፣ እኛ የሌለንበትን ፎቶ እንኳን ለማየት የማንፈልግ ፣ በእኛ በኩል ያለፈን ነገር ብቻ የምናራግብ ፣ የሌለንበትን ነገር ጥሩም ቢሆን እንኳን ለምናጣጥል "በእኔ በቀር ባዮች" ትምህርቱ ድንቅ ነው።
ሌላ ማሳያም አለ ማቴዎስ ወንጌላዊው ስለ ራሱ ታሪክ ሲጽፍ "ማቴዎስ የተባለ ቀራጭ በመቅረጫው ተቀምጦ" ብሎ በኃጢአት ከተዘፈቀበት ሥራ ላይ ወደ ክርስትና እንደተጠራ በግልጽ ሲጽፍ ሌሎቹ ወንጌላውያን ግን በሐዋርያት ዝርዝር ላይ ማቴዎስ ያሉትን ሰው ስለ ቀድሞ የቀራጭነት ሥራው ሲጽፉ ግን ሌዊ የሚል ተለዋጭ ስሙን ተጠቅመዋል። ትሑቱ ማቴዎስ ግን በሌሎች ወንጌላውያን የተሸሸገ የቀድሞ የኃጢአት አኗኗሩን ለእግዚአብሔር ይቅር ባይነት ማሳያ እንዲሆን ስለፈለገ ጭራሽ በሐዋርያት የስም ዝርዝር ላይ "ቀራጩ ማቴዎስ" ብሎ ራሱን ጠርቷል።
የሚገርመው ከቀራጭነት ከተጠራ በኋላ በቤቱ ታላቅ ድግስ ደግሶ ጌታችንን ከኃጢአተኞች ጓደኞቹ ጋር የተቀበለ መሆኑን በሌሎች ወንጌላውያን ሲጽፉ ማቴዎስ ግን ቀራጭነቱን አጉልቶ እንዳልጻፈ ሁሉ የግብዣው ነገር ደጋሹ እርሱ መሆኑን አድበስብሶ በመጻፍ አልፎታል።
★ ★ ★
ቅዱስ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" አለ። "ለእኛ" መልካም ነው የሚለው ቃል ድንቅ ነው። በእግዚአብሔር ቤት መኖራችን መልካምነቱና ጥቅሙ ለእኛ ነው እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። የማንጠቅም ባሪያዎቹ ስሙን በአሕዛብ ዘንድ ከማሰደብ በቀር ለእርሱ ምን እንጠቅመዋለን። ለዚህም ነው ቅዱስ ባስልዮስ "ጌታ ሆይ የአንተ አምላክነት ለእኔ ያስፈልገኛል እንጂ የእኔ ፍጡርነት ለአንተ አያስፈልግህም" ያለው።
ስለዚህ ጴጥሮስ "ለእኛ መልካም ነው" አለ።
"ብትወድስ ሦስት ዳስ እንሥራ" አለ ፣ ጌታ ካልወደደ እንኳን ሦስት አንድ ዳስ መሥራት አይቻልም ፣ እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ" ስለዚህ "ብትወድስ" አለ።
የዋሁ ጴጥሮስ ለእኔ ልሥራ አላለም ፣ የሐዲስ ኪዳን ሐዋርያ ነኝ ብሎ የብሉይ ኪዳን ነቢያትን ከማክበር ወደ ኋላ አላለም። "አንተ ዓለት ነህ በዚህች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራታለሁ" በተባለ ማግስት ለነቢያቱ ድንኳን ሊቀልስ የጠየቀ ከጴጥሮስ በቀር ማን አለ?
ከእግዚአብሔር አብ ግን "አትሙት" እስከማለት ለደረሰው ለነጴጥሮስ ንግግር "የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት" የሚል ትእዛዝ መጣ። ሃሳቡ ድንቅ ቢሆንም ቃሉን ሳይሰሙ ዳስ መሥራት መጀመር አይቻልም።
በዚያ ላይ ጌታ የመጣው በደብረ ታቦር ድንኳን አስጥሎ ሊኖር ሳይሆን በቀራንዮ በተሰቀለበት በመስቀሉ ካስማ በደሙ ድንኳን ተክሎ ሊያስጠልለን ነው። ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ "ጴጥሮስ ሆይ ለአንተ የፊቱን ብርሃን እያየህ በዚህ መኖር መልካም ነው ፣ እኛ ግን የምንድነው በተራራው ሲኖር ሳይሆን ወርዶ ፊቱን በጥፊ ሲመታ ነው" ብሎታል።
ጴጥሮስ የዋሁ "በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ" ላለው ለክርስቶስ ድንኳን ሊቀልስ ጠየቀ። በሰማይ "በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ድንኳን" ላለችው ሊቀ ካህናት ድንኳን ሊሠራ ለመነ። እዚህ አለ ሲሉት እዚያ ለሚገኘው ፣ በመንፈስ እየተነጠቀ አድራሻውን ለመወሰን ያስቸግር ለነበረው ኤልያስ እንዲቀመጥ ተስፋ አድርጎ ድንኳን ልሥራ አለ። እጅግ የተዋበችና በወርቅ በሐር ያጌጠችን የኦሪት ድንኳን ለሠራው ሙሴ ዓሣ አጥማጁ ጴጥሮስ ድንኳን ልሥራለት አለ። ሐዋርያት ነቢያቱን ሊያስተናግዱ የለመኑባት ደብረ ታቦር ፣ ሐዋርያት ነቢያቱን ለጌታ ቀኝ አዝማች ግራዝማች አድርገው በድንኳን አስቀምጠው እነርሱ እንደ ሎሌ ከደጅ ሊኖሩ የጠየቁ እነ ጴጥሮስ እንደምን ይደንቃሉ? ጴጥሮስ ሆይ አሁን በሰማይ ድንኳኖች ውስጥ እያገለገልህ ይሆንን? ደብረ ታቦርን አይተህ በደስታ "እንኑር" ያልከው ጴጥሮስ ሆይ የገነት ደስታ ስታይ ምን ተሰምቶህ ይሆን?
በእሳት ድንኳን ለመኖር ተስፋ የምናደርግ "በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" የተባልን እኛስ ምንኛ የታደልን ነን?
★ ★ ★
በታቦር ተራራ ላይ የጌታችን ልብስ እንደ ፀሐይ አበራ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ከፀሐይም በላይ ነው ፣ ፀሐይ አይቶ የወደቀ የለም የጌታችንን ልብስ ሲያዩ ግን የወደቁት ያበራው ከዚያ በላይ ስለሆነ ነው" ይላል።
ከጌታችን በዚያ ተራራ ከሙሴና ኤልያስ ጋር ነበረ። ሙሴ እንደምናውቀው ጽላቱን ተቀብሎ ሲወርድ ሕዝቡ "እባክህን ተሸፈንልን" ብለውት ፊቱን በመጎናጸፊያው ሸፍኖ ነበር። የሙሴ አምላክ ክርስቶስ ግን ደቀ መዛሙርቱ ሲወድቁ አይቶ በልብሱ እንዳይሸፈን ያበራው ፊቱ ብቻ ሳይሆን ልብሱም ነበር።
" አጣቢም በምድር ላይ እንደዚያ ሊያነጣው እስከማይችል በጣም ነጭ ሆነ" ማር 9: 3
የሚለው ቃል ምንኛ የሚደንቅ ነው። በምድር ላይ ያለ አጣቢ ቢፈትግ ቢታገል የዚያን ያህል ሊያነጻው የማይችለው ነጭ እንዴት ያለ ነው? መቼም ሁላችን የምናውቀው ነጭ ነገር ሁሉ በምድር ላይ ባለ አጣቢ የታጠበ ስለሆነ እንዲህ ነው ማለት አንችልም። ብቻ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በምድር ያሉ አጣቢዎች ከሚያነጡት በላይ ልብስን ማንጣት ይችላል።
ይህ ቃል በኃጢአት እድፍ ልብሳችን ላደፈ ሁሉ መጽናኛችን ነው።
መቼም የምድር አጣቢዎች አቅማቸው ውስን ነው።
ቆሽሸን ያዩን ሰዎች ብንታጠብም አያምኑንም ፣ ቢያጥቡልንም በኅሊናቸው የሚያስቀሩብን ቆሻሻ አለ።
በሰው ዓይን አንዴ ቆሽሸህ አትገኝ እንጂ ከተገኘህ መቼም ነጭ አትሆንም። አንተ ግን የደብረ ታቦሩ ብርሃን መድኃኔ ዓለምን ብቻ "እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ" በለው
በዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

ጷግሜ 3 ቅዱስ እሩፋኤል 🙏
እንግዲህ ከባህሪው ቅድስና ፍጥረቱን በጸጋ ቅድስና መርጦ የሚለይ እግዚአብሔር አክብሮ እንዲህ ያለ ሰማያዊ ፀጋ ከሰጣቸው ቅዱሳን መላእክት መካከል በስልጣኑ ሊቀመናብርት (የመናብርት አለቃ) የሆነ በሹመት ፈታሔ ማኅጸን (ማሕጸን የሚፈታ) ከሳቴ እውራን (የእውራንን ዓይን የሚያበራ) ሰዳዴ አጋንንት (አጋንንትን የሚያባርር) ፈዋሴ ዱያን (ድውያንን የሚፈውስ)፣ አቃቤ ኆኅት (የምህረትን ደጁ የሚጠብቅ) ተብሎ የተገለጠ ከሊቃነ መላእክቱ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ተከትሎ የሚነሳ መልአክ ራሱን እንዲህ በማለት ገለጠ « የቅዱሳንን ጸሎት ከሚያሳርጉ ወደ ከበረ ወደ ገነነ ወደ እግዚአብሔር ጌትነት ከሚያገቡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ» (ጦቢ.12÷15)
ይህ የከበረ ታላቅ መልአክ ሰሙ የእብራይስጥ ሁለት ቃላት ጥምረት ውጤት ነው፡፡ ሩፋ ማለት ጤና፣ ፈውስ፣ መድኃኒት ማለት ሲሆን ኤል ሚለው በሌሎቹም መላእክት ስም ላይ የሚቀጠል ስመ አምላክ ነው ይህም « መልአኬን በፊትህ እሰዳለሁ….. ስሜ በእርሱ ስለሆነ . አታስመርሩት» (ዘጸ.23÷20-22) እዳለው ነው፡፡
ታዲያ ሩፋኤል የሚለው በጥምረት ከአምላክ ለሰዎች የተሰጠ ፈውስ የሚለውን ይተካል «በሰው ቁስል የተሾመ ከከበሩ ከመላእክት አንዱ ሩፋኤል ነው፡» (ሄኖ.6÷3)
ይህ መልአክ እንደሌሎቹ ሊቃነ መላእክት ሁሉ የሰው ልጆችን ይጠብቃቸዋል(ዳን.4÷13 ዘጸ. 23÷20 መዝ. 90÷11-13 )
ያማልዳል፣ ከፈጣሪ ያስታርቃቸዋል፡፡(ዘካ.1÷12)
በፈሪሀ እግዚአቤሔር እና በአክብሮተ መላእክት ያሉትን ድናቸዋል (ዘፍ.49÷15 መዝ.3÷37)
« እግዚአብሔር ሃይሉን የሚገልጥበትን ቅጣቱን ሊያሳይ ቢወድ አስቀድሞ መርጦ በወደዳቸው ለይቅርታ የተዘጋጁ የይቅርታ መላእክትን ያመጣል» (ሮሜ.9÷22)
ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀመናብርትን ድንቅ ገቢር ተአምራቱን ያዩ ምዕመናን
……የወላድ ማኅፀን እንዲፈታ
ስለተሸመ ከጌታ
አዋላጅ ብትኖር ባትኖርም
ሐኪም ሩፋኤል አይታጣም
በምጥ ጊዜ ሲጨነቁ የባላገር ሴቶች ሁሉ
የመልአኩን መልክ አንግተው ማርያም ማርያም ይላሉ
ማየጸሎቱን ጠጥተው ቶሎ ፈጥነው ይወልዳሉ ……
እያሉ ደጅ ጠንተው ይማጸኑታል፡፡
ዜና ግብሩን ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ከተናገረለት በመነሳት በቅዱሳን ላይ ድንቅ የሆነ እግዚአብሔር በመልአኩ አድሮ ያደረጋቸውን ተግባራት አበው የበረከት ምንጭ በሆነ ድርሳኑ ላይ አኑረው የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ሰጥተውናል፡፡ በጉልህ ሠፍረው ከምናገኛቸው ብዙ ድንቅ ሥራዎች መሀል ጥቂቶቹን እነሆ
~~~> በሥነ-ስዕሉ የተማጸኑ፣ በምልጃው ታምነው የጸኑ ቴዎዶስዮስንና ዲዮናስዮስን በገሃድ ተገልጾ ለንግስናና ለጵጵስና ክብር አብቅቷቸዋል፡፡
~~~> የንጉስ ቴዎዶስዮስ ልጅም ጻድቁ አኖሬዋስም በፈጣሪው ህግ እየተመራ የሊቀ መናብርቱን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ አሳንጾ ሲያስመርቅ ለበለጠ ክብር ልቡን አነቃቅቶ ለታናሽ ወንድሙ ለአርቃዴዋስ የነጋሢነት ስልጣኑን ትቶ መንኖ በስውርና በጽሙና እዲኖር ረድቶታል፡፡
~~~> በሊቀጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን አባቶች ለሊቀመናብርቱ ክብር በአሣ አንበሪ ጀርባ ላይ ያሳነጹትን መታሰቢያ ቤተ መቅደስ በወደቡ አጠገብ በእስክንድሪያ ሳለች ጠላት ዲያቢሎስ አነዋውጾ ለምስጋና የታደሙትን ምዕመናን ሊያጠፉ አሣ አንበሪውን ቢያውከው ወደ ሊቀመናብርቱ ተማጽነው እርዳን ቢሉ ፈጥኖ ደርሶ በበትረ መስቀሉ (ዘንጉ) ገሥጾ ከጥፋት ታድጓቸዋል፡፡
በቅዱስ መጽሐፍም እንደተገለጠው
~~~> ሣራ ወለተ ራጉኤልን አስማንድዮስ ከተባለው የጭን ጋንኤን ሲታደጋት የጦቢያን አባት የጦቢትን ዓይን አበራለት (መጽሐፍ ጦቢት)
ከዚህም አልፎ የይስሐቅን እናት ሣራን፣ የሶምሶንን እናት (እንትኩይን) ምክነታቸውን የቆረጠ ወልዶ ለመሳም ያበቃቸው ይኸው ፈታሔማኅጸን የልዑል እግዚአብሔር መልአክተኛ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡
ከመልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ረድኤት ያሳድርብን አሜን !!!

አንቺን ብሎ ማርያም....
በየአመቱ ሁሌ እየመጣ ይጎፈላል።ካልደበደብኩሽ
ይላታል፡፡ማርያምን እኮ ነው...እዚህ ምድር ላይ ማንን ትጠላለህ ቢባል ቀድሞ የሚጠራው የማርያምን ስም ነው.....ሲሰድባት ለአፉ ለከት የለውም።ደሞ እጁ ላይ የያዘውን ድንጋይ ብታዩት ሀገር ይጨርሳል።በየአመቱ "አንቺን ብሎ ማርያም" እያለ እየዛተ ነው ያረጀው.....
አንቺን ብሎ ማርያም!!!አንቺን ብሎ አዛኝ!!አንቺን ብሎ እናት!!ደግ ብቶኚ እኔን ትበድያለሽ??ሀቄን ትወስጃለሽ?? ብቻዬን ትጥዪኛለሽ??አንቺ ብሎ ማርያም!! በዚ ዲንጋይ ነበር ማለት...
ንግሷ ተጀምሮ እስኪያልቅ በሯ ላይ ሲጎፈላ አምሽቶ በረድ ሲልለት ወደ ከተማ ይመለሳል።በአመተ ክብሯ እግዚኦ እየተባለ ቢለመን፤በሽማግሌ ቢመከር፤በጎረምሶች
ቢታሰርም እሱ ግድ አይሰጠውም።በአመቱ ያው እራሱ ጉልላት ሆኖ ነው ሚመጣው..አይለወጥም።
ዛሬ ጉልላት የት ሄደ?? ምነው ጭር አለሳ??( አለ ጓደኛዬ ገና ቤተክርስትያን እንደደረስን
አረ ሰአቱን ጠብቆ ይመጣል....ደሞ የሱ ነገር...አሁን ታቦቷ ሲወጣ ብቅ ይል የለ?(ብዬ ወሬዬን ከአፌ ሳልጨርስ አረንጓዴዋ ታክሲ ስትበር መጥታ አጠገባችን ቆመችና
ብዙ ወጣቶች ከመኪና ወርደው አንዳች ነገር ከመኪናው
ለማውጣት ሲጣደፉ የሁለታችንም ቀልብ መኪናዋ ላይ አረፈ...
በስመአብ ወወልድ ጉልላት!! አለ ጓደኛዬ ቀደም ብሎ...
ምንድነው ምን ተፈጠረ?? ብዬ እኔም ከአንገቴ ስንጠራራ ጉልላትን በደም የተለወሰ ፊት አይቼ ደንዝዤ ቀረሁ...
ወጣቶቹ ለሬሳ የቀረበ የተዝለፈለ አካሉን ተሸክመው ለንግስ በተሰለፈው ምእመን መሀል ሰንጥቀው ወደ ማርያም ግቢ ሲዘልቁ ከጓደኛዬ ጋ ሳናወራ ተጣድፈን ተከተልናቸው....
ምንድነው??ምን ጉድ ተፈጠረ??ጉልላት ምን ሆነ?? (አሉ አባ መቋሚያና ፅናፅላቸውን እንደያዙ ባዶእግራቸውን እየተጣደፉ መጥተው።ከማህሌቱ ተጠርተው እንደመጡ ያስታውቃል..
በዋዜማው ጠጅ ቤት ነበር አሉ...ጠዋት ማዞሪያ ድልድይ ውስጥ ወድቆ ነው የተገኘው። ሆስፒቲል አድርሰነው ቤት አስገቡት ደክሟል አሉ...ጉልላት ደሞ ቤት የለው....(አለ አንዱ ጎረምሳ
ውይ የአደራ ልጄን.... እኔን እኔን..በሉ ቤት አግቡት
አባ ካባቸውን እየሰበሰቡ ቤታቸውን ከፍተው ሲገቡ ገልላትን ይዘን ተከተልናቸው ቀድሞም መድሐኒት አዋቂ ናቸው።ቁስል እጃቸው ላይ አይበረክትም፤ህመም ከፊታቸው አይቆምም፤ ፀሎታቸው ጠብ አትልም፤እቤታቸው ገብተን እንደቆምን
በሉ ሂዱ ውጡ እናንተ... አይዟችሁ አሉ ሲጣደፉ።እሺ ብለን ወጣን ....
ቆይ የጉልላት ፀባይ ምንድነ?? ለምንድነው በዚህ ልክ ማርያምን ሚጠላት??አለኝ ጓደኛዬ እጁን አገጩ ላይ አድርጎ እንደተከዘ
ማርያም እናቴን ቀማቺኝ ነው ሚለው....እርግጥ ጉልላት ከልጅነቱም የተበደለ ነው።እናቱን በሰፈሩ የማያውቃት የለም።እሱን አርግዛ እስከምጧ ቀን ድረስ አሻሮ እየቆላች ቀንስራ እየሰራች እቺ ቤተክርስትያን ስትሰራ በጉልበቷ እና በደሀ ገንዘቧ ትረዳ ነበር።በኋላ ጉልላት ተወለደ።ያኔ የማርያም ቤተክርስትያንም እየተሰራ ጉልላቱ ላይ ደርሶ ስለነበር ልጇን ጉልላቴ አለችው።የሚገርመው ግን እሱ አደለም... ወልዳው በአራስነቷ ቁስሏ ሳይጠግ አቅሟ ሳይበረታ ጉልላቷ ሲሰራ አሸዋ እያቀበለች ድንገት ወድቃ እዚያው ሞተች።ጉልላትም ያለ አሳዳጊ በመንደሩ ሰው እርዳታ ሲያድግ ይህንን የእናቱን ታሪክ እየሰማ ነበር...በቃ ከዛ ወዲህ ይኸው እድሜ ልኩን ከማርያም ጋ ጥሉ
እንደከረረ ዛሬ ደረሰ...
ልጆች አላችሁ....?በሉ ኑ አንሱና አልጋላይ አድርጉልኝ አሉ አባ ከበራቸው ብቅ ብለው
ሁሉም ተበትኖ ስለነበር እኔና ጓደኛዬ ስንሮጥ ተከትለናቸው ገባን።የጉልላት ደሙ ተጠርጎ ቁስሉ ታክሞ ተሸፍኖ ሞት ከሚመስል እንቅልፉ ነቅቶ
ማሪኝ እመብርሀን ....ማሪኝ እናቴ....አትቀየሚኝ.... ትቼዋለሁ....ማርያም...ማርያም....ይቅር በዪኝ እያለ
ያቃስታል
በል ትንሽ እረፍ ጉልላቴ አሁን ደና ነክ....አየህ እናትህ ስምህን ስትሰይመው በዋዛ አደለም። የቤተክርስትያን ጉልላቷ በሰጎን እንቁላል ይመሰላል።ግዙፏ ሰጎን እንቁላል ከጣለች በኋላ እንቁሏሏን አቅፋ እስኪፈለፈል ድረስ አይኗን ከእንቁላሉ እንደማታነሳው አንተም ብትዝትባት ብትሰድባት አይኗን ካንተ አትነቅልም ዞሮ መግቢያክ ናት።እናትህ ይህችን ጉልላት ስትሰራ ወድቃ ብትሞትም ለህንፃዋ ግን ከገንዘቧ እስከ ደሟ ከፍላለች ማርያም እናትህን ቀምታህ ሳይሆን ወደ እቅፏ ወስዳት ነው።አንተ ምትጠላት ማርያም ለኛ ጉልላታችን ናት ሰገነታችን ናት መድሀኒታችን ናት።ይኸው አንተም ዘመንህን ስትዝትባት ኖረህ ሀኪም
ያቃተው በሽታህን ፈውሳ በእለተ ቀኗ በምህረት ጎበኘችህ
እንዳተ ዛቻና ስድብ ቢሆንማ.....አሁን ተው ጉልላቴ
ተመለስ ...ተው ግድየለም (አባ ቁስሉን በመስቀል
እየደባበሱ በስስት እያዩት ሲያወሩ ጉልለላት ሳል በቀላቀለ ድምፅ
አንቺን ብሎ ማርያም!!....ብሎ ፀጥ ሲል ደንግጠን
እያየነው
"ማን አፈረ' ብሎ ቀጠለ
እውነትም "አንቺን ብሎ ማርያም ማን
አፈረ ማንም!! አሉ አባ በፈገግታ ሁላችንንም
እያዩ።
Chacha

ፅጌ ፆም መስከረም 26 ይጀምራል
ስደቷ የሰው ዘርን ለማዳን ነበር!!!
ስደት፣ ልመና፣ ልቅሶ፣ ዝርፊያ፣ ስድብ፣ ርሀብ ፣ ጥም ፣ ባይተዋርነት ...
..........................
አምላክን ለማዳን እንዲሁም አዳምን ለማዳን ብላ
በማታውቀው የግብጽ በረሀ እግሯን የአሸዋው ግለት እየገረፋት ተሰደደች።
እንባ ጠራጊዋ እመ አምላክ አለቀሰች።
ከህጻነቷ ጀምሮ እስከ እረፍቷ ድረስ ልቅሶ አልተለያትም።
ስጋና ነፍስ መጋቢዋ እመ አምላክ ተራበች፣ ተጠማች።
ሰጭዋ እናት ኮፌዳ ይዛ በየመንደሩ ፍርፋሪ ለመነች።
በእሷ ልጅ ምክንያት ሄሮድስ የገሊላን ህጻናት በጠቅላላ
እንደ ገደለ ስትሰማ በበረሀው ላይ አለቀሰች ።
+ የሚበላ ቁራሽ ለመለመን መንደር ሄደች። ባዶዋን ተመለሰች።
የልጇ የወርቅ ጫማ ተሰርቆ ጠበቃት። ቁራሽ ላላገኝ የልጄን
ጫማ አሰረኩኝ ብላ አለቀሰች።
+ ከእትማን ቤት ስትለምን ኮቲባ ልጇን ቀምታ ምድር ላይ ጣለችባት።
እመ አምላክ አለቀሰች ፣ ልጇም አለቀሰ።
+ በበረሀ ሲከራተቱ ሽፍቶች የልጇን ልብስ ገፈው ዘረፏት።
ይገሉብኛል ብላ # አለቀሰች።
...............................
እመ አምላክ ስታለቅ ልጇ ፈጣሪ አልቅሷል፣ ዮሴፍ አልቅሷል። ሰሎሜ አልቅሳለች።
መላእክት ሚካኤል፣ ገብርኤል፣ ዑራኤል..........አዝነዋል።
ያላዘነው ዲያቢሎስ ብቻ ነው። ጥንት በሄሮድስ ልብ አድሮ እመብርሃንን አሰደደ።
አዳምን ለማውጣት ተንከራተተች።
አዳምን ለማዳን በ33 ዓም ልጇ ተሰቀለ። ከመስቀሉ ስር ሆና
አለቀሰች።
በአምላክ እናት ስደት ያልደረሰባት መከራ የለም። ተርባለች፣ ተጠምታለች፣ ተሰድባለች፣
ተንገላታለች፣ በፀሐይ ተቀቅላለች፣ እሾህ ተወግታለች፣ እንቅፉት ተመታለች፣ ተዘርፋለች፣ የሰው ፊት አይታለች፣
ፍርፋሪ ለምናለች፣ ባይተዋር ሆናለች፣ ብርድ ተበርዳለች፣ ቤተሰቧን ናፍቃለች፣
ልጇን እንዳይገሉባት ተሰቃለች፣ አልቅሳለች ፣ በአቀበቱ በቁልቁለቱ ደክማለች፣ ... 3 ዓመት ከመንፈቅ በስደት ፣ 64 ዓመት የመከራ ፀጋ ለብሳለች።
ምንጭ 81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ.....
የድንግል ማርያም ምልጃ በረከት አይለየን

በአንድ ወቅት አንድ መነኩሴ የወይራ ዘይት ዛፍ ተከለና ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መጸለይ ጀመረ ፤ "ጌታ ሆይ ለዛፌ ይጠቅም ዘንድ ዝናብን አዝንብልኝ" አለ። እግዚአብሔርም ጸሎቱን ተቀብሎ ዝናቡን አዘነበለት ፤ ዛፉም ውኃን በጣም ጠግቦ አፈሩ ረሰረሰ። ለዛፉ ይጠቅም ዘንድ ግን ከመጠን በላይ የረሰረሰው አፈር መድረቅ ያስፈልገው ነበር። ስለሆነም መነኩሴው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ "ጌታ ሆይ ብዙ ፀሐይ በዛፉ ላይ እንድታወጣ እለምንሃለሁ" አለ። እግዚአብሔርም በለመነው መሠረት ፀሐይ አወጣለት ፤ ዛፉም አደገለት። መነኩሴው ልመናውን ቀጠለ "ጌታ ሆይ የዛፉ ሥር እና ቅርንጫፍ ይጠነክር ዘንድ ጥቂት ውርጭ ላክልኝ" አለ። እግዚአብሔርም በጠየቀው መሠረት ውርጩን ላከለት ፤ ከዚያም ዛፉ ከውርጩ የተነሣ ጠወለገ ሞተም።
መነኩሴው በኹኔታው በጣም ተናድዶ ወደ አንድ መነኩሴ ሔዶ የገጠመውን ታሪክ እና ቅሬታውን ያለማጉደል አጫወተው ኀዘኑን አካፈለው። ሁለተኛው መነኩሴ ታሪኩን ከሰማ በኋላ "እኔም እንደ አንተ የወይራ ዘይት ዛፍ አለኝ ተመልከት" አለው ፤ የእርሱ ዛፍ በመልካም ኹኔታ አድጋለች። ሁለተኛው መነኩሴም ቀጥሎ "እኔ ግን ከአንተ በተለየ መልኩ እጸልያለሁ ፤ ይህን ዛፍ የፈጠረው እርሱ ነውና ፤ ከእኔ የተሻለ የሚያስፈልገውን እንደሚያውቅ ለእግዚአብሔር ነገርኹት ፤ እግዚአብሔርም እንዲንከባከበው በጸሎት ጠየቅኹት ፤ እርሱም ጸሎቴ ሰምቶ ተንከባከበው" በማለት አስረዳው።
በእኛም ሕይወት እንዲህ ነው ፤ የሚያስፈልገንን በትክክል የምናውቅ መስሎን እንለምናለን ፤ ነገር ግን ለእኛ የሚያስፈልገንን ያለማጓደል የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ "፥በሙሉ ልብ እንመነው! "የምፈልገውን ሳይሆን የሚያስፈልገኝን ስጠኝ" እንበለው።
አነ ዘክርስቶስ