tgoop.com/Ketbeb_mender/3476
Last Update:
♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️
ክፍል ፲፫
✍ደራሲ - አብላካት
ለግማሽ ሰዓት ያህል ጋደም አልኩኝና ስልኬ ሲጠራ ተነሳሁ። ማይለፍ ነበር......
"ተዘጋጀሽ ?"
"ውይ ተኝቼ ነበር በጣም ይቅርታ አሁን እዘጋጃለው"
"እሺ እኔም እየደረስኩኝ ነው ቶሎ ውጪ።" ስልኩ ተዘጋ .....በህይወቴ ለብሼ ለምወጣው ነገር ቦታ ሰጥቼ አላውቅም ይህን ስል ግን ተዝረክርኬ እወጣለው ሳይሆን መልበስ ያለብኝን ነገር በአግባቡ እለብሳለው እንጂ ለእንደዚህ አይነት ነገር ተጨንቄ አላውቅም። ማይለፍን ካወኩት በኋላ ግን ያስጨንከኝ ጀመር እሱ ፊት አምሮ ለመታየት ሳይሆን ይዞኝ እሚገባባቸው ቦታዎች በሙሉ ደረጃቸውን የጠበቁ በመሆናቸው እንደቦታው ሆኜ መገኘት ስላለብኝ ነው። ረዘም ያለ ቀሚስ ምርጫዬ በጣም እምወደው ሳቢ ለልደቴ የሰጠችኝ እሚያምር ነጭ ቀሚስ አለኝ በሱ ቀሚስ ስንት ጉድ አሳልፈናል.....እሱን ለበስኩና ብዙም ሂሉ ከፍ ያላለ ታኮ ጫማዬን ተጫምቼ ወጣሁኝ። እንደተለመደው መታጠፊያው ጋር እየጠበቀኝ ነበር ዛሬ ደሞ ከመኪና ወርዶ ስልኩን እየነካካ ነበር ሳየው ደነገጥኩኝ አለባበሱ እና ቁመናው እንኳን ሴት ወንድም ያስደነግጣል..... ጥቁር መነፅር ፣ ነጭ ፒትልስ ሹራብ በበርገንዲ ከለር የሱፍ ኮት ፣ ነጭ ሱሪ በጥቁር ጫማ ሁፍፍፍፍ በቃ ልክ እኔ እምወደው አይነት አለባበስ። ሰው እንዴት ሁሉን ይታደላል ከመልክ መልክ ከፀባይ ፀባይ ሁሉ ነገሩ ፅድት ያለ ልጅ ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም አይደል እሚባለው.... ቀና ሲል አየኝና ስልኩን ወደ ኪሱ ከተተው
"አምሮብሻል" አለኝ ከላይ እስከታች እየተመለከተ
"ያንተን ያህል ባይሆንም። ግን አመሰግናለሁ"....ፈገግ እንደማለት አለና በሩን ከፍቶልኝ ገባሁኝ። ከኋላ የነበረውን ጊታር አምጥቼ
" አታለማምደኝም ?" አልኩት
"አንቺ ፍቃደኛ ከሆንሽ ደስ እያለኝ አለማምድሻለው"
"አመሰግናለሁ። ግን ወዴት እየሄድን ነው ?"
"አንድ በጣም እምወዳቸው አባት አሉ እሳቸውን አስተዋውቅሻለው"
"ምንህ ናቸው ?"
"ስንደርስ ታያቸዋለሽ" አለኝና ጉዟችንን ቀጠልን... መኪናውን ያቆመበትን ቦታ አይቼውም አላውቅም ከመኪናው ከወረድን በኋላ አስፓልቱን እንደተሻገርን መቆርቆሮ የተሰራ እና ከላዩ ደግሞ ሸራ የታጠረበት ትንሽዬ ቤት ጋር አንኳኳ...ከቤቱ ውስጥ አንድ እድሜያቸው በግምት ከሰባ እስከ ሰባ አምስት በሚሆን የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ፀጉራቸው እና ፂማቸው ወተት የተደፋበት ይመስል ነጭ ነው ለካ ሁሉም በዕድሜ ሲሆን ያምራል ሽበት ባልወድም እንደሳቸው እሚሆን ከሆነ ግን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ቢኖርብኝም አይቆጨኝም። ሲታዩ ግን እርጅናን እምቢ አሻፈረኝ አልቀበልም ያሉ ነው እሚመስሉት። አንገታቸውን ብቅ በበሩ ብቅ አደረጉና......
"አንተ ነህ እንዴ ጌታ መሳይ" አሉ ጎርነን ባለ ድምፅ ወደ ማይለፍ እየተመለከቱ። "ጌታ መሳይ ?" አልኩኝ በውስጤ
"አዎ ጋሼ እኔ ነኝ" አላቸው ከዛም በሩን ከፈቱት እና ወደ ውስጥ ገብተው ሶስት ወንበር ተራ በተራ ውጪው ላይ አስቀመጡ ከዚያም በራቸውን ዘግተው .....
"በሉ ቁጭ በሉ". አሉን ወደ ወንበሩ እየጠቆሙ
"መጀመሪያ እሷን ተዋወቃት ጋሼ። ቃልኪዳን ትባላለች ጓደኛዬ ናት"
"ቃልኪዳን ?" አሉና አንገታቸውን አቀረቀሩ። ከዚያም መልሰው "ይሁና" አሉና እጃቸውን ዘርግተው ጨበጡኝ። ነገሩ ግራ ቢገባኝ ለመጠየቅ ግን ድፍረቱ አልነበረኝም እየተብሰለሰልኩ ወንበሩ ላይ ተቀመጥኩኝ።
"ቃልዬ ወዴት ሄድሽ ?" አለኝ ማይለፍ
"አይ አለሁ ዝም ብዬ ነው"
"እሺ ። ጋሼ ማለት ልክ እንደ አባቴ ነው በጣም ነው እምወደው ለዛም ነው ላስተዋውቅሽ የፈለኩት"
"አዎ ለኔም ልክ እንደ ልጄ ነው ከነሱም በላይ ሳይሆን አይቀርም እምወደው።" ብለው ፈገግ አሉ
"ፍቅራችሁ ደስ ይላል" አልኳቸው ቀጠል አድርጌ
"እናመሰግናለን። አሁን ምሳ ይዤ እስክመጣ ጋሼን አጫውችው" ብሎኝ ሄደ። "ግራ የገባኝ ግን እንደ አባት እሚወዳችፕው ከሆነ ምናለ ደህና ቤት ቢያኖራቸው መቼስ ለሱ አቅቶት አይደለም ለአፍ ብቻ አባቴ ማለት ምን ዋጋ አለው። ደህና ሆቴል እንኳን አይታየኝም ለምግቡስ ቢሆን ከዛ ከሰፈሩ ይዞላቸው አይመጣም። ከራሴ ጋር እያወራሁኝ ሳይታወቀኝ እየተናደድኩኝ ነበር ግን ምን አናደደኝ ምናልባት እንደጠበኩት ሆኖ ስላላገኘሁት ይሆን ?" ብቻዬን ስብከነከን አስተውለውኛል መሰል
"ምነው ልጄ ደህና አደለሽም እንዴ?" አሉኝ እንደመደንገጥ አልኩና
"አይ ደህና ነኝ ይቅርታ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ ነው። ግን ድፍረት ካልሆነብኝ አምድ ነገር ልጠይቅ ጋሼ ?"
"የምን ድፍረት ነው ጠያቂ አይደል እንዴ የጠፋው በይ ጠይቂ"
"እሺ ጋሼ ለምንድነው ማይለፍን ጌታ መሳይ የሚሉት ?"
"ሁሉም ሰው እኮ የጌታ አምሳያ ነው ስራው እኮ ነው እንደ ጌታም እንደ ሎሌም እሚያደርገው"
"ይቅርታ ግን አልገባኝ"
"እዮልሽ ልጄ አምላክ በራሱ አምሳል ፈጠረን እኛ ደግሞ ወደ ምድር ስንመጣ ገሚሱ እውነትም ጌታውን መስሎ ይኖራል ገሚሱ ደግሞ ሰይጣንን መስሎ ይኖራል በመልክ ሳይሆን በስራው። ማይለፍ ደግሞ ከባህሪም ከስነምግባርም ጌታን መሳይ ነው ለዛም ነው ጌታ መሳይ ያልኩት አሁንስ ተረዳሽኝ ልጄ ?"
"እእ አዎ ጋሼ አሁን ገብቶኛል አመሰግናለሁ" አልኳቸው። ድንገት አጠገባችን አንድ ወጣት መቶ ቆመ...
"ዛሬ ጥያቄ የለህም ?" አሉት
"ሲገባኝ እጠይቃለው" አላቸውና አሁንም እዛው ባለበት ቆመ
"እስከዛው ወደ ኋላ ተመለስ አትቁም "
"ላስብ ብዬ እኮ ነው ጋሼ"
"ያልገባህን ምን አሳሰበህ ሲገባህ ታስባለው ለአሁኑ ተመለስ"
"አመሰግናለሁ ጋሼ" ብሏቸው ወደ መጣበት ተመለሰ። ንግግራቸው እና ሁኔታቸው ግራ አጋባኝ ሂድ ተመለስ ጠይቅ ምንድነው እሚያወሩት እያልኩኝ ሳለው
" ሳምሶን ይባላል ሁሌም ከቤተሰቡ ጋር ሲጋጭ እዚህ ጋር መቶ ይቆማል ያኔ እኔም ችግሩን ስለማውቀው እንዲህ እያልኩኝ እመልሰዋለው እሱም ቶሎ ይሰማኛል ምክንያቱ ደግሞ ንዴት ውስጥ ሲሆን ነው ከእነሱ ጋር እሚጣላው እናም ንዴቱ ሲበርድለት እንደተጣላ እንጂ ለምን እንደተጣላ አያስታውስም። ለዛም ነው ዛሬ ጥያቄ የለህም ስለው ሲገባኝ እጠይቃለው ያለኝ የፀቡ መንስኤ ምን እንደሆነ ካላወቀ ምን ይጠይቃል እንዴትስ ሊገባው ይችላል የቆመው ደግሞ ምክንያቱን እያብሰለሰለ ነው ላልገባው ነገር መብሰልሰል ምን ሊፈይድ ንቆ መተው ነው እንጂ ስለዚህ እሚሻለው ያልገባውን እንዳልገባው ትቶ ሰላም መፍጠሩ ነው እሚበጀው ብዬ ነው ወደ ኋላ ወደ መጣበት የመለስኩት። አንዳንዴ ባልገባን ባላወቅነው ነገር ከራሳችን ጋር የሙጥኝ ተያይዘን እንታገላለን ጥያቄም እሚጠየቀው ውሉ ሲታወቅ ነው አልያ በዘፈቀደ እምንጓዘ ከሆነ መድረሻ እንደሌለው ደራሽ ወንዝ ነው እምንሆነው " አሉኝ እና ቢያንስ ውሀ እንኳን ላምጣልሽ ብለው ወደ ውስጥ ገቡ።
ንግግራቸው ትንሽ ግራ ቢያጋባም የተናገሩት ግን ላስተዋለው ትልቅ ትምህርት ነው ወደ ራሴ መለስ ብዬ በንዴቴ ምክንያት ከስንቱ ተጣልቼ በኋላ ግን ስረጋጋ የፀቡ መንስኤ እንኳን ትዝ እማይለኝ ጊዜ እንደነበር መለስ ብዬ ሳስታውስ ይገርመኝ ጀመር።
ይቀጥላል........
ቀጣዩ ክፍል እንዲለቀቅ እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ
ለአስተያየት- @Yetomah_Bot
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
BY የብዕር ጠብታ✍📒📖
Share with your friend now:
tgoop.com/Ketbeb_mender/3476