KETBEB_MENDER Telegram 3555
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 25

    ደራሲ - አብላካት

"ሰላም ነው ማይለፍ ?"
"ፈጣሪ ይመስገን። በሰላም ነው ስልክሽ ዝግ የነበረው ?"
"አዎ ትንሽ ደክሞኝ ስለነበር ነው በጣም ይቅርታ"
"ይቅርታ እንኳን አያስፈልገውም እንዲሁ ስለጨነቀኝ ነው። ክላስ ወይ ስራ የለም እንዴ ?"
"ዛሬ ሁሉትም ጋር መሄድ ስላል ፈለኩኝ ነው"
"ምነው በሰላም ?"
"አንዳንዴ እረፍት ያስፈልግ የለ"
"እሱስ ልክ ነሽ። እና የት ሆነሽ ነው ?"
" ከቤተክርስቲያን እየወጣሁ"
"ቁርስ አልበላሽማ እሚመችሽ ከሆነ እኔም ስላልበላሁ አብረን እንብላ ?"
" እሺ ደስ ይለኛል"
"ሰፈራችሁ ያለው ቤተክርስቲያን ነው አደል ?"
"አዎ"
"እሺ መጣሁኝ" ብሎ ስልኩ ተዘጋ።ሁሉ ነገር ተስተካክሎልኝ ሁሌም አብሬው ደስተኛ ብሆን ምነኛ በታደልኩ...ምን ያደርጋል ህይወት ሁሌ አይሞላም አንዱን ስንል አንዱ እየተደራረበ መፈናፈኛ ያሳጣል....ላጣው አልፈልግም በጣም አፈቅረዋለው... ግን ሁኔታዎች ያስፈሩኛል በዚህ ሰዓት እናቴን በቻልኩት መጠን ልረዳት ይገባኛል ማንም እሚያግዛት የለም ሁሉም መቀበልን እንጂ መስጠትን አይፈልጉም.... የእንጀራ አባቴ እንደ ቤት አባወራነቱ ሰርቶ ቤተሰቡን ማስተዳደር ሲገባው እሱ ግን ከእናቴ ይጠብቃል ጭራሽ አረቄ ቤት ሄጄ እምጠጣበት ብር ስጭኝ ብሎ አፉን ሞልቶ ሲጠይቃት አንቀሽ ግደይው ግደይው እሚል ስሜት ይሰማኛል። ወይ የባልነት ወይ የአባትነት ሀላፊነቱን እማይወጣ ሰው ከሰው ሊቆጠር አይገባውም። ልጆቹም ከየአማን በስተቀር እንደሱ ቀንቱዎች ናቸው እንኳን ለሰው ለራሳቸው እንኳን እማይሆኑ እርባናቢሶች። ስልችት ብሎኛል የሊድያንና የየአማንን ትምህርት ቤት ፣ የመብራት ፣ የውሀ ፣ አስቤዛ ስንቱን ልቻለው የራሴም ወጪዎች አሉብኝ አሁን ትምህርት ተጀምሯል ስንት ነገር ያስፈልገኛል የቀን በቀን የታክሲ ወጪ በምኔ ይሄን ሁሉልሸፍነው ? ከየት ላምጣ ደመወዜ የየአማንን ትምህርት ቤትና የመብራት ብቻ ነው እሚችልልኝ የበፊቱ ስራዬ ይሻል ነበር እሱን ደሞ እድሜ ለእነ ሳቢ መተዌ ግድ ሆነ። አሁን የትምህርታቸውም የመብራት ክፍያም ደርሷል ኧረ ሳያልፍ አይቀርም ማታ ትቻቸው ብገባም ሊድያ ብር ስትላት ሰምቻለው። ስለ ሁሉም እግዚአብሄር ያውቃል በፊት በፊት ሳቢዬ ታግዘኝ ነበር ዛሬ ግን እሷም የለችም። ድንገት ከኋላዬ ማይለፍ መቶ ከገባሁበት ሀሳብ አባነነኝ....

"ምንድነው እንደዚህ በሀሳብ ጭልጥ ማለት ?"
"ይቅርታ አላየሁክም ነበር ብዙ ቆየህ ?"
"ለነገሩ ተሳልሜ ነው የመጣሁት። ከጨረስሽ እንሂድ" አለኝ
"ጨርሻለው" ብዬው ወጣን።
"ወደየት እንሂድ ?"
"እኔ እንጃ አንተን ደስ ወዳለህ ቦታ" አልኩትና ወደሚያቀው ቁርስ ቤት ሄድን። ያዘዝነው ቁርስ እስከሚመጣ ማይለፍ...
"አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ?" አለኝ...
"ትችላለህ"
"ማለት በሌላ መንገድ አትይው እና እውነት ታፈቅሪኛለሽ ስልሽ እኔ እንዳፈቀርኩሽ ስለነገርኩሽ ነው እሺ ያልሽኝ ወይስ ፈልገሽው ነው ?"
"ለምን ጠየከኝ ?"
"አለ አደል ደስተኛ የሆንሽ አይመስለኝም ከእኔ ጋር ሆነሽ እንኳን ሀሳብ ሌላ ቦታ ነው ምናልባት ለእኔ አዝነሽ ከሆነ እሺ ያልሽኝ ብዬ አስቤ ነው" አለኝ። በእርግጥ መጠየቁ ልክ ነው እንደ ሁኔታዬ እንለያይ አለማለቱም እሱ ሆኖ ነው...
"እዮልህ ማይለፍ ይገባኛል ግን አንተን አለመፈለግ ሳይሆን ያለሁበት ሁኔታ ትክክል ስላል ሆነ ነው ብትረዳኝ ደስ ይለኛል የእውነት አፈቅርሀለው" ብዬ መለስኩለት.....
"እንደዛ ከሆን እሺ" አለኝና ያዘዝነውን ቁርስ አብረን በላን። እሱ ስብሰባ ስለነበረው እምትሄጂበት ከሌለሽ ስራ ቦታ አብረን እንሂድ ብሎኝ አብረን ሄድን። እሱ ከስብሰባ እስኪወጣ እዛው መስሪያ ቤት ካሉት ሌሎች ሰራተኞች ጋር ደስ እሚል ጊዜ አሳለፍኩኝ። ስለምን እንደሆነ ባላውቅም ከሁለት ሰዓት በኋላ ከስብሰባ ወጡ። ከተሰብሳቢዎቹ መሀል ከእነ ሳቢ ጋር ለመዝናናት ስንወጣ እምናገኛቸው ቱጃሮችም አሉ...ምነው ባላስተዋልኩኝ እያልኩ አንጋጥቼ ፈጣሪዬን ተማፀንኩት። በእርግጥ ያደረኩት ምንም አይነት አሳፋሪ ተግባር ባይኖርም ግን ደግሞ ስለ አቶ መላኩ እንዲሰማ አልፈልግም..... በእዛ ላይ ለብዙ ሰዎች ዳይመንድ እሚሄዱ ሴቶች ከባለሀብቶቹ ጋር አብረው ተኝተው ገንዘብ ለማግኘት እንድሆነ አድርገው ነው እሚያስቡት። ምናልባት እሱም እንደዛ ካሰበ ለማሳመን ይከብደኛል....ደሞም ከአንዳንዶቹ ጋር ከዳይመንድ ውጪ አብሮ ምሳ እና እራት እስከመብላት ከውጪ እቃ እስከማስመጣት እሚያደርስ ግንኙነት ነበረኝ። እዚህ ካሉት ከአቶ ሰሎሞን እና ከአቶ እስክንድር ጋርም በተለይ ከአቶ እስክንድር ጋር ጥሩ ቀረቤታ ነበረኝ ፤  ለዚህ እንጂ ሌላ አይደለም። ከስብሰባው በኋላ የምሳ ግብዣ ስለነበር ወደዛ እንድንሄድ ጠየቀኝ.....እኔ ይቅርብኝ ብለውም ካልሄድሽ እኔም እቀራለው ብሎ ድርቅ ሲል እያቅማማሁም ቢሆን እሺ ብለው ሄድን። ትልቅ ሆቴል ነበር ግብዣው የለበስኩት ቀሚስም ያን ያህል ደባሪ አልነበረም....ምሳ ተበልቶ ከተጨረሰ በኋላ ነይ ሰዎችን ላስተዋውቅሽ ብሎኝ በእየ ጠረጴዛው እየዞርን ሰላም እያልን አቶ ሰሎሞን እና አቶ እስክንድር ጋር ደረስን......

​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ይቀጥላል....

  ✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
         @Ketbeb_Mender 
         @Ketbeb_Mender 
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯

tgoop.com/Ketbeb_mender/3555
Create:
Last Update:

BY የብዕር ጠብታ✍📒📖

Share with your friend now:
tgoop.com/Ketbeb_mender/3555

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Ng was convicted in April for conspiracy to incite a riot, public nuisance, arson, criminal damage, manufacturing of explosives, administering poison and wounding with intent to do grievous bodily harm between October 2019 and June 2020. In the next window, choose the type of your channel. If you want your channel to be public, you need to develop a link for it. In the screenshot below, it’s ”/catmarketing.” If your selected link is unavailable, you’ll need to suggest another option. Although some crypto traders have moved toward screaming as a coping mechanism, several mental health experts call this therapy a pseudoscience. The crypto community finds its way to engage in one or the other way and share its feelings with other fellow members. Telegram offers a powerful toolset that allows businesses to create and manage channels, groups, and bots to broadcast messages, engage in conversations, and offer reliable customer support via bots. Administrators
from us

Telegram የብዕር ጠብታ✍📒📖
FROM American