Telegram Web
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 23

ደራሲ - አብላካት



እኔም ከእነሱ መሀል እየነጠልኩኝ ማውራት ስለ ማልፈልግ አቤልንም ከዚህ በኋላ እኔን ብሎ እንዳይመጣ ነገርኩት.... ምክንያቱም ሳባን አውቃታለው ማናቸውም እንዲያዋሩኝ አትፈልግም እሱንም ከምታኮርፈው እኔው ብሸሽ ይሻለኛል። ሰዓቴን አመቻችቼ ስራዬንና ትምህርቴን እኩል ማስኬድ ችያለው። ገንዘቡ ያስፈልገኛል ሁሉም የእናቴን እጅ ነው እሚጠብቁት ሰርቶ እንኳን ይሄንን ልቻል እሚል የለም ሁሌም ብር ባስፈለጋት ቁጥር ከእንጀራ አባቴ ጋር መጨቃጨቋ ሰላሜን ይነሳኛል... አባቢ በህይወት እያለ ደልቶን ባንኖር እኔ እና እናቴ ግን የጎደለብን ምንም ነገር አልነበረም ምንም ሰርቶ ቢሆን እኔን ከጓደኞቼ እኩል እናቴንም ከጎረቤቶቿ አያሳንሳትም ነበር። ዛሬ ላይ ግን የየአማን እና የሊድያ የትምህርት ክፍያ ሲደርስ የወር አስቤዛ ሲያልቅባት ማጠፊያው ሁሉ ያጥራታል.....ለአንድ ለራሴ አላንስም ግን ደግሞ እናቴን በዚህ ሁኔታ እራስሽ ተወጪው ልላት አልችልም ፤ ገና ድሮ ለማግባት ስትወስን ትክክለኛው ሰው እንዳልሆነ ደጋግሜ ስነግራት የሷን ኑሮ ይኖሩላት ይመስል ሁሉም ጎረቤት የምን እራስ ወዳድነት ነው... ያንቺ አባት ከሞተ እናትሽ ህይወቷን አትኑር እንዴ እያሉ አፍ አፌን ይሉኝ ነበር....የኔ ፍራቻ ይሄ ነበር ዛሬ እናቴ ያለችበት ሁኔታ ለእሷ አይገባትም። ድሮ አግቢ አግቢ ብለው ገፋፍተው እዚህ መናጢ ላይ የጣሏት ሰዎች ዛሬ አንድ ኪሎ ሽንኩርት አይገዙላትም። ለምንድነው በሰው ህይወት ፈላጭ ቆራጭ እምንሆነው..... እናቴን የተመቀኘኋት ይመስል ሀሳቤን ሲያጣጥሉ ነበር አሁን ግን ብቻዋን ናት ያኔ ምን ነበር ያላችሁት ብዬ ዛሬ ላይ ብጠይቃቸው እርግጠኛ ነኝ መልሳቸው እሚሆነው ለሷ ብለን እንጂ አላስገደድናት ነው እሚሉኝ።

የኔን ህይወት እምኖረው እኔ ነኝ እናት እና አባቴ እንኳን የተሻለ እንዲገጥመኝ መመኘት እና መጥፎ እና ጥሩውን ሊነግሩኝ እንጂ ሊወስኑልኝ አይገባም.....የሰዎችን ሀሳብ አላጣጥልም እቀበላለው ግን ደግሞ ማንም የወሰነልኝን አልኖርም.... ነገ እኔ ብቸገር አብሮኝ እሚቸገር የለም እንዲህ አድርጊ እንዲህ ሁኚ ያለኝ ሁሉ ከንፈር ከመምጠጥ የዘለለ ምንም አያደርግልኝም። ውሳኔያችን ነጋችን ላይ ችግር እንደማይፈጥር ቆም ብለን ማሰብ አለብን ሰው ስላለን ስላበረታታን ብቻ የነሱን ሀሳብ ተቀብለን መተግበር የለብንም ባይ ነኝ። ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም ሰውም በል በል ብሎ ከመሀል ያደርስል እንጂ አብሮ አይዘልቅም።

ከክላስ በኋላ ወደ ስራ ሄጄ ስራዬን ስጨርስ ማይለፍ እራት ጋብዞኝ ደስ የሚል ጊዜ አሳለፍን....ወደ ቤት ሸኝቶኝ ሲመለስ ሊድያን ከሆነ መኪና ስትወርድ አየኋት። ሰውየውን እንደምንም ለማየት ስሞክር በእድሜ ገፋ ያለ ሰው ነው....ሹገር ዳዲ እሚባለው አይነት.... ለተራ ገንዘብ ብሎ እራስን ክብርን እንደ መሸጥ ምን ውርደት አለ ..... አንዳንዴ እንደ እህት ብትቀርበኝ እና ይህ ነገር እንደማይጠቅማት ብነግራት ብዬ እመኛለው.....እራሷን ስታጣ ዝም ብዬ መመልከቴን ሳስብ ክፉ የሆንኩ ይመስለኛል....ምንም ቢሆን የእናቴ ልጅ ናት ክፉዋን ማየት መስማት አልፈልግም። መኪናው ከሄደ በኋላ ወደ ግቢ ልትገባ ስትል እጇን ያስኳት....

"ያምሻል እንዴ አስደነገጥሽኝ እኮ! ምንድነው ?" አለችኝ...
"ማነው ሰውየው ?" አልኳት....
"ማንም አደለም ደሞ ማንስ ቢሆን ምን ያገባሻል!?"
"እሱ እኮ አባትሽ ይሆን ገና ልጅ እኮ ነሽ ለምን እንደ እድሜ አትሆኚም !"
"እራስሽን እንደ ታላቅ እህት ቆጥረሽ እየተቆጣሽኝ ባልሆነ ። ትሰሚኛልሽ የፈለኩትን ከፈለኩት ሰው ጋር መሆን እችላለው ይሄ አንቺን አይመለከትም " አለችኝ.....
"እዮልሽ ሊድያ ከዚህ እምታተርፊው እራስን ማጣት ነው እባክሽን እንደዚህ መሆንሽን አቅም"
"ነገርኩሽ እማይመለከትሽ ነገር ውስጥ ጥልቅ አትበይ። ምነው አንቺ ከዚህ የተሻለ ውሎ እምትውዪ አስመሰልሽው ከማንም ጋር ስትልከሰከሺ አደል እንዴ እምትውይው!" ብላ ንግግሯን ልትቀጥል ስትል ገፍትሬያት ወደ ውስጥ ገባሁኝ።



ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል 100❤️ ሲደርስ ይለቀቃል እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ...


ለአስተያየት - @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
The last day of 2013😥

2014 የብርሀን ዘመን እንዲሆንልን
ችቦ በማብራት ምሽቱን አድምቀነዋል

ቢለማም ቢከፋም በፈጣሪ እርዳታ ለ አዲስ ቀን እና ለአዲስ አመት ልንበቃ ሰአታት ቀርተውናል

2013 ግን ስለይክ በእንባ ነው 😘

#ግጥም_ቃና
@ilovvll
@ilovvll 👈ቤተሰብ ይሁኑ
✍️😷ወግ ይድረሰኝ😷✍️


ሚስት ፈልጉልኝ ቀበጥ - ቅብጥ ያለች፣
ለኑሮ ለፍቅር - ፍፁም የምትመች።

ሁሌ የማስብላት - እኔ ከ "እኔ" በላይ፣
ሳቅ ደስታዋን እንጂ - ክፋቷን የማላይ።

እኔም ልክ እንደ ሠው
መቼም ወጉ ደርሶኝ፣
እንደ ገጣሚዎች...
ፍቅርሽን አፍቅሬ - ሚዛን አሳንሶኝ፣

✍️
ላንቺ ያለኝን ፍቅር
ባለችኝ ወረቀት እንድሞነጫጭር
ቶሎ ነይ ሔዋኔ....
እስቲ ወግ ይድረሰኝ - ልግጠም ስለ ፍቅር


አልአዛር
@DONAY
ኦርያሬስ
፭ - ፲፪
፮:፳፪ ቀን...

@ilovvll
@ilovvll
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 24

ደራሲ - አብላካት



እኔ ከማናቸውም ጋር ንግግር ባልፈልግም ግን ደግሞ የአንዳቸውንም ክፉ ማየት አልፈልግም.....ሰዎች ህይወታችን ውስጥ ብዙ መጥፎ ነገሮችን ያደርጋሉ ያሳዝኑናል ያስከፉናል ልባችንን ይሰብሩናል ግን ለእነዛ ሰዎች በተናገሩን መጠን እየ መለስን ከሄድን ከእነሱ ያልተሻልን ሆነን እንገኛለን። እዚህ ምድር ላይ ማንም ትክክል የለም ሁላችንም ስህተት ሰርተናል ሌሎችን በሰሩት ነገር መሸሽን ምርጫ አድርጌ አላውቅም ምክንያቱም ሰውን በስራው መመዘን ተገቢ ነው ብዬ ስለማላስብ። አንዳንድ ሰዎች ማሳየት እሚፈልጉትን ብቻ ነው እሚያሳዩት እንጂ እውነተኛ ማንነታቸውን አደለም.... ውጫቸው ጭቅይት ብሎ ውስጣቸው ግን ልክ እንደ ነጭ ወረቀት የሆነ ብዙዎች አሉ.....እኔም እነ ሊድያ ምንም ያህል ቢያስከፉኝም ቢሰብሩኝም ውስጣቸው ግን ለማንም ማሳየት እማይፈልጉት መልካምነት ያለ ይመስለኛል....ምናልባት እንዲህ መጥፎ እንዲሆኑ ያደረጋቸው ምክንያት ይኖር ይሆናል። በጣም ደክሞኝ ስለነበር ወደ ውስጥ ገብቼ እናቴን
ሰላም ካልኩኝ በኋላ ስልኬን አጠፋፍቼ ተኛሁኝ። ለሊት ላይ እንደመባነን አድርጎኝ ነቃሁኝ....ለምን እንደሆነ ባላውቅም ውስጤን ሰላም እየተሰማኝ አደለም..... ስልኬን ከፍቼ ሰዓቱን ስመለከት ከሌሊቱ 9:20 ይላል ምክንያቱን ሳላውቀው እንዲሁ እንዳፈጠጥኩኝ ነጋ። በዚህ ስሜት ወደ ስራም ሆነ ወደ ግቢ መሄድ ስላል ፈለኩ ወደ ቤተክርስቲያን ሄጄ እዛ አረፍ አልኩኝ.....ከጎኔ ሶስት በእድሜ ገፋ ያሉ ሴቶች ተቀምጠዋል አባ እያስተማሩ ንግግራቸው ሀሳቤን ሰርቆት አስተምሮቱን ትቼ እነሱን ማዳመጥ ጀመርኩኝ....ከንግግራቸው እንደተረዳሁት በቅርቡ ስላበደው የሰፈራችን ወጣት ነው እሚያወሩት ልጁን ስለማውቀው ነው የአባን አስተምሮት ትቼ እነሱን እምሰማው...... ስንታየሁ ይባላል እናት እና አባቱ እሱን ከመውለዳቸው በፊት ልጅ እምቢ ብሏቸው ያልገቡበት ጉድጓድ አልነበረም.....መፍትሔ ይገኛል ወደ ተባሉበት ሁሉ ነበር እሚሄዱት.....የሰፈሩ ሰው እርግማን ቢኖርባቸው ነው.. የቤተሰብ ጣጣ ነው.. ከሷ ነው.. ከእሱ ነው ችግሩ.. እያሉ የየራሳቸውን መላምት ያስቀምጡ ነበር....መቼስ ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም አይደል ከእነ አባባሉስ የለመኑት ፈጣሪያቸው አላሳፈራቸውም ስንቴን ሰጣቸው...ብዙ ያዩበት የተገፉበት የተንከራተቱበት ልጃቸው ስለሆነ ስንታየሁ አሉት። ግን እግዜር አልፈቀደምና እንዳለመታደል ሆነ ስንቴ በተወለደ በ አንድ አመቱ እናቱ ሞተች.....የሰፈሩ ሰውም ገፊ የሚል ለማሰብ እንኳን እሚሰቀጥጥ ስም ሰጡት እናቱን ገፍቶ የገደለ እያሉ በልጅ ዓዕምሮህ መጥፎ ጠባሳን ጣሉበት ....አባቱም ልጁ ይህ ንግግራቸው እንዳይጎዳው እና ቦታ እንዳይሰጥ የተቻለውን ያህል ቢጥርም አልተሳካለትም።


ስንቴ ከሰፈር ልጆች ጋር ለመጫወት ሲወጣ የልጆቹ ወላጆች እሱ ገፊ ነው ይገላችኋል... ጠንቋይ ነው እያሉ ከሱ ያርቋቸው ነበር። አስራ ሰባት አመት ሲሞላው
አባቱ በልብ ድካም ህይወታቸው አለፈ....በዛ ሰዓት ለስንቴ ህይወት ቀላል አልሆንለት አለው የሰፈሩ ሰው ጥላች እናት አባቱን ሳይጠግባቸው መሞታቸው ችግሩን እሚያካፍለው ጓደኛ ማጣቱ ውስጡን ሰበረው.... ጠንካራ ሆኖ ለመኖር ቢጥርም ዳገት ሆነበት። እራሱን በሱስ ውስጥ ደበቀ ማጨስ ፣ መጠጣት የዘወትር ስራው ሆነ.... ከዛም አንዲት ሴት ህይወቱ ውስጥ ገባች ከሱስ እንዲላቀቅ እና የተሻለ ህይወት እንዲኖር እረዳቸው እየተለወጠ መጣ.... ዛሬም ግን የሰፈሩ ሰው እሷንም ደሞ እንደ እናት አባትህ ልትገድላት ነው እያሉ ያሽሟጥጡት ጀመር.... ፍቅረኛው ለእንደዚህ አይነቱ ንግግር ቦታ ሳትሰጥ ከስንቴ ጎን ቆመች ሊጋቡ ሽር ጉዱ እያሉ ባሉበት ሰዓት እሷም በመኪና አደጋ ህይወቷን አጣች። ይሄኔ ከእናንተም መሃል እውነትም ገፊ ነው እሚል አይጠፋም ግን የሱ ጥፋት ምኑ ላይ ነው በእግዜር ስራ እኛ ምን ቤት ነን ማነው ፈራጅ ያደረገን.... ያለ ጥፋቱ እንዴት ይወቀሳል እንዴት ይገፋል ? ከእሷ ሞት በኋላ ይሰፈሩ ሰው ዳይኖሰር እንዳየ እሱን ሲያዩ ይሮጡ ጀመር ከእሱ በእድሜ እሚያንሱ ህፃናት ሰፈር ውስጥ ሲያዩ ስንታየሁ ገፊ ስንታየሁ ሰይጣን እያሉ ያሾፉበት ነበር። ሱሰኝነቱ ከበፊቱ ተባባሰ እራሱን መጣል ከቤቱ ውጮ መንገድ ዳር ማደር ጀመረ። ከእዚህ ሁኔታ እንዲወጣ ከጓደኞቼ ጋር የተቻለንን አድርገናል ሳይሆን ቀረና የሰዉ ንግግር የእናት አባቱ ሞት ህይወቱን የቀየረችለት ያፈቀራት ሴትን ማጣቱ ዓዕምሮውን ያስጨንቀው ጀመር እየቆየ ጨረቁን አስጥሎ አሳበደው። ታዲያ የዚህ ልጅ ጥፋት ምንድነው መርጦ አልተወለደ ይሄ የእግዜር ውሳኔ እንጂ የሱ አልነበረም እኮ ለምን ይሄን ያህል ይጠላል ለምን ይሄን ያህል ይገፋል ደስተኛ ሆኖ መኖር እሚችልን ሰው በዚህ መንገድ እቅልን ማሳት ነው ትክክለኛው ፍርድ ንገሩኝ እስቲ የሰውን ተስፋ ነገውን እያጨለሙ ነው አብሮነትን ማሳየት ? በእሱ እንደዚህ መሆን ማን ተጠቀመ ? የማን ህይወት ተቀየረ ? አንዳንዴ ሰዎችን መጥቀም መርዳት ባንችል ምናለ የራሳቸውን ህይወት እንደራሳቸው ፍቃድ እንዲኖሩ ብንተዋቸው ? ጥቅም ለሌለው ነገር ለምን ሌላን ሰው እንጎዳለን ? ጥሩ ባንሆንላቸው መጥፎ መሆን ለምን ያስፈልጋል ? በተደጋጋሚ ከእነ ሳቢ ጋር ሆስፒታል ልንወስደው ብንሞክርም አልተሳካልንም ልብስ እና ምግብ እየያዝን አብረነው ውለን እመጣለን። ዛሬም ገፊ እንደሆነ እና የቤተሰብ ጣጣ ቤተሰቡን እንደነጠቀው ፣ እንዳሳበደው ሲያወሩ ስሰማ ነው ፀሎቴን ትቼ እነሱን ማዳመጥ የጀመርኩት። በሰው ለመፍረድ ያለንን ችክሉነት ለማወቅ ብንጠቀመው የት በደረስን....እራሴን ለማረጋጋት ብዬ ብመጣ ጭራሽ ከበፊቱ የባሰ ተበሳጨሁኝ...እዚህ ቆይቼ በአላስፈላጊ ንግግር ሀጥያት ከምገባ ምንም ሳልናገር ተሳልሜ ወጣሁኝ። እምሄድበት ሲጠፋኝ ማይለፍ ጋር ደወልኩለት......



ይቀጥላል.........



ለአስተያየት - @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​♥️♡:。.。 እዮሪካ 。.。:♡♥️

ክፍል 25

ደራሲ - አብላካት



"ሰላም ነው ማይለፍ ?"
"ፈጣሪ ይመስገን። በሰላም ነው ስልክሽ ዝግ የነበረው ?"
"አዎ ትንሽ ደክሞኝ ስለነበር ነው በጣም ይቅርታ"
"ይቅርታ እንኳን አያስፈልገውም እንዲሁ ስለጨነቀኝ ነው። ክላስ ወይ ስራ የለም እንዴ ?"
"ዛሬ ሁሉትም ጋር መሄድ ስላል ፈለኩኝ ነው"
"ምነው በሰላም ?"
"አንዳንዴ እረፍት ያስፈልግ የለ"
"እሱስ ልክ ነሽ። እና የት ሆነሽ ነው ?"
" ከቤተክርስቲያን እየወጣሁ"
"ቁርስ አልበላሽማ እሚመችሽ ከሆነ እኔም ስላልበላሁ አብረን እንብላ ?"
" እሺ ደስ ይለኛል"
"ሰፈራችሁ ያለው ቤተክርስቲያን ነው አደል ?"
"አዎ"
"እሺ መጣሁኝ" ብሎ ስልኩ ተዘጋ።ሁሉ ነገር ተስተካክሎልኝ ሁሌም አብሬው ደስተኛ ብሆን ምነኛ በታደልኩ...ምን ያደርጋል ህይወት ሁሌ አይሞላም አንዱን ስንል አንዱ እየተደራረበ መፈናፈኛ ያሳጣል....ላጣው አልፈልግም በጣም አፈቅረዋለው... ግን ሁኔታዎች ያስፈሩኛል በዚህ ሰዓት እናቴን በቻልኩት መጠን ልረዳት ይገባኛል ማንም እሚያግዛት የለም ሁሉም መቀበልን እንጂ መስጠትን አይፈልጉም.... የእንጀራ አባቴ እንደ ቤት አባወራነቱ ሰርቶ ቤተሰቡን ማስተዳደር ሲገባው እሱ ግን ከእናቴ ይጠብቃል ጭራሽ አረቄ ቤት ሄጄ እምጠጣበት ብር ስጭኝ ብሎ አፉን ሞልቶ ሲጠይቃት አንቀሽ ግደይው ግደይው እሚል ስሜት ይሰማኛል። ወይ የባልነት ወይ የአባትነት ሀላፊነቱን እማይወጣ ሰው ከሰው ሊቆጠር አይገባውም። ልጆቹም ከየአማን በስተቀር እንደሱ ቀንቱዎች ናቸው እንኳን ለሰው ለራሳቸው እንኳን እማይሆኑ እርባናቢሶች። ስልችት ብሎኛል የሊድያንና የየአማንን ትምህርት ቤት ፣ የመብራት ፣ የውሀ ፣ አስቤዛ ስንቱን ልቻለው የራሴም ወጪዎች አሉብኝ አሁን ትምህርት ተጀምሯል ስንት ነገር ያስፈልገኛል የቀን በቀን የታክሲ ወጪ በምኔ ይሄን ሁሉልሸፍነው ? ከየት ላምጣ ደመወዜ የየአማንን ትምህርት ቤትና የመብራት ብቻ ነው እሚችልልኝ የበፊቱ ስራዬ ይሻል ነበር እሱን ደሞ እድሜ ለእነ ሳቢ መተዌ ግድ ሆነ። አሁን የትምህርታቸውም የመብራት ክፍያም ደርሷል ኧረ ሳያልፍ አይቀርም ማታ ትቻቸው ብገባም ሊድያ ብር ስትላት ሰምቻለው። ስለ ሁሉም እግዚአብሄር ያውቃል በፊት በፊት ሳቢዬ ታግዘኝ ነበር ዛሬ ግን እሷም የለችም። ድንገት ከኋላዬ ማይለፍ መቶ ከገባሁበት ሀሳብ አባነነኝ....


"ምንድነው እንደዚህ በሀሳብ ጭልጥ ማለት ?"
"ይቅርታ አላየሁክም ነበር ብዙ ቆየህ ?"
"ለነገሩ ተሳልሜ ነው የመጣሁት። ከጨረስሽ እንሂድ" አለኝ
"ጨርሻለው" ብዬው ወጣን።
"ወደየት እንሂድ ?"
"እኔ እንጃ አንተን ደስ ወዳለህ ቦታ" አልኩትና ወደሚያቀው ቁርስ ቤት ሄድን። ያዘዝነው ቁርስ እስከሚመጣ ማይለፍ...
"አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ ?" አለኝ...
"ትችላለህ"
"ማለት በሌላ መንገድ አትይው እና እውነት ታፈቅሪኛለሽ ስልሽ እኔ እንዳፈቀርኩሽ ስለነገርኩሽ ነው እሺ ያልሽኝ ወይስ ፈልገሽው ነው ?"
"ለምን ጠየከኝ ?"
"አለ አደል ደስተኛ የሆንሽ አይመስለኝም ከእኔ ጋር ሆነሽ እንኳን ሀሳብ ሌላ ቦታ ነው ምናልባት ለእኔ አዝነሽ ከሆነ እሺ ያልሽኝ ብዬ አስቤ ነው" አለኝ። በእርግጥ መጠየቁ ልክ ነው እንደ ሁኔታዬ እንለያይ አለማለቱም እሱ ሆኖ ነው...
"እዮልህ ማይለፍ ይገባኛል ግን አንተን አለመፈለግ ሳይሆን ያለሁበት ሁኔታ ትክክል ስላል ሆነ ነው ብትረዳኝ ደስ ይለኛል የእውነት አፈቅርሀለው" ብዬ መለስኩለት.....
"እንደዛ ከሆን እሺ" አለኝና ያዘዝነውን ቁርስ አብረን በላን። እሱ ስብሰባ ስለነበረው እምትሄጂበት ከሌለሽ ስራ ቦታ አብረን እንሂድ ብሎኝ አብረን ሄድን። እሱ ከስብሰባ እስኪወጣ እዛው መስሪያ ቤት ካሉት ሌሎች ሰራተኞች ጋር ደስ እሚል ጊዜ አሳለፍኩኝ። ስለምን እንደሆነ ባላውቅም ከሁለት ሰዓት በኋላ ከስብሰባ ወጡ። ከተሰብሳቢዎቹ መሀል ከእነ ሳቢ ጋር ለመዝናናት ስንወጣ እምናገኛቸው ቱጃሮችም አሉ...ምነው ባላስተዋልኩኝ እያልኩ አንጋጥቼ ፈጣሪዬን ተማፀንኩት። በእርግጥ ያደረኩት ምንም አይነት አሳፋሪ ተግባር ባይኖርም ግን ደግሞ ስለ አቶ መላኩ እንዲሰማ አልፈልግም..... በእዛ ላይ ለብዙ ሰዎች ዳይመንድ እሚሄዱ ሴቶች ከባለሀብቶቹ ጋር አብረው ተኝተው ገንዘብ ለማግኘት እንድሆነ አድርገው ነው እሚያስቡት። ምናልባት እሱም እንደዛ ካሰበ ለማሳመን ይከብደኛል....ደሞም ከአንዳንዶቹ ጋር ከዳይመንድ ውጪ አብሮ ምሳ እና እራት እስከመብላት ከውጪ እቃ እስከማስመጣት እሚያደርስ ግንኙነት ነበረኝ። እዚህ ካሉት ከአቶ ሰሎሞን እና ከአቶ እስክንድር ጋርም በተለይ ከአቶ እስክንድር ጋር ጥሩ ቀረቤታ ነበረኝ ፤ ለዚህ እንጂ ሌላ አይደለም። ከስብሰባው በኋላ የምሳ ግብዣ ስለነበር ወደዛ እንድንሄድ ጠየቀኝ.....እኔ ይቅርብኝ ብለውም ካልሄድሽ እኔም እቀራለው ብሎ ድርቅ ሲል እያቅማማሁም ቢሆን እሺ ብለው ሄድን። ትልቅ ሆቴል ነበር ግብዣው የለበስኩት ቀሚስም ያን ያህል ደባሪ አልነበረም....ምሳ ተበልቶ ከተጨረሰ በኋላ ነይ ሰዎችን ላስተዋውቅሽ ብሎኝ በእየ ጠረጴዛው እየዞርን ሰላም እያልን አቶ ሰሎሞን እና አቶ እስክንድር ጋር ደረስን......




​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​​ይቀጥላል....

ቀጣዩ ክፍል 150❤️ ሲደርስ ይለቀቃል እያነበባችሁ አስተያየታችሁን አድርሱኝ....



ለአስተያየት - @Yetomah_Bot


✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
@Ketbeb_Mender
@Ketbeb_Mender
✯┄┅┅✿❀♥️❀✿┅┅┄✯
Order ur necklace only 300 birr
Contact @yohabi_24
Order ur zodiac sign hoodies and custom made as u wish
Contact @yohabi_24
ሚካኤል ስለው ስሙን ስጠራ
የአምላኬ ብርሃን በእላዬ በራ
አዛኝ ነው በእውነት ፍፁም አዛኝ
የሚጠብቀኝ የሚያፅናናኝ

እንኳን አደረሳችሁ
ወተት ፕሮቲን ነው ሰውነት ያፋፋል..
💪👍🐮🐮🥛
አረቄ ጥሩ ነው ኑሮህን ያስረሳል..!!!
🥃🍸🤔🤕😴😰
# ከወዳጃችን #wda👏

@ilovvll
@ilivvll
Forwarded from Safaricom Ethiopia
🎁Safaricom ethiopia ሽልማት🎁
በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል
በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።
🎁ያልተገደበ የአንድ ወር ኢንተርኔት
🎁smart phone( s21 ultra)
🎁Asus personal computer
ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ

ማሳሰቢያ! ይህ ሊንክ የሚያገለግለው ለ 𝓵𝓪𝓷𝓲 ብቻ ነው

https://www.tgoop.com/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0629313048
ሰላም እንደምን ቆያችሁን ፤ ውድ የቻናላችን ተከታታዮቻች ። ያው እንደ ሚታወቀው በጣም ለረጅም ጊዜ ጠፍተናል ለሱም እጅግ በጣም ይቅርታ እንጠይቃለን እንደበፊቱ ፅሁፎቻችንን ወደ እናንተ ለማድረስ እማንችልበት ሁኔታ ውስጥ ስለ ነበርን ነው ፤ በተደጋጋሚም እዮሪካ የሚለውን ድርሰት እንድንቀጥለው ብዙዎቻችሁ ጠይቃችሁናል ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ወደ እናንተ ማድረስ አልቻልንም ነበር ለሱም ይቅርታ እንጠይቃለን ። እናም አሁን ላይ እዮሪካ እሚለውን ድርሰታችንን በድጋሚ ወደ እናንተ ለማድረስ ስላሰብን ወደ ቻናላችን ተመልሰናል። ይቀጥል አይቀጥል እሚለውን እናንተ እንድትወስኑ ስለፈለግን ነው።

እንዲቀጥል ፍላጎቱ ካላችሁ 👍 ምልክቱን ተጫኑ።

ለሀሳብ አስተያየት - @Yetomah_Bot ላይ አድርሱን
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ለሆናችሁ ቤተሰቦቻችን በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🙏

መልካም በዓል ለሁላችን
Forwarded from የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ (መክሊት የ16ቷ)
እንኳን አደረሰን

@ilovvll
@ilovvll
Forwarded from የግጥም ቃና በ መክሊት የ16ቷ (መክሊት የ16ቷ)
ነፍስ ይማር አይባል ነፍስን አላወቁ
ሁለት ፍሬ አበባ ተቀጥፈው ደረቁ
ያፅናናችሁ አይባል መፅናናት ይከብዳል
እንዲህ አይነት ሀዘን በምን ቃል ይበርዳል።

በሰዎች የማይቻል ነውና መላእክቱን ልኮ ያፅናናችሁ 🙏😔

@ilovvll
@ilovvll
2024/11/12 01:18:46
Back to Top
HTML Embed Code: