tgoop.com/LoveAndTruth/1514
Last Update:
Ethiopia
August 4, 2024
IMF ዓለማው ምንድነው ? ቢሊዮን ዶላሮች ደግፎ / አበድሮ ምን ይጠቀማል ?
(በኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ)
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ 190 አባል ሀገራት ያሉት የጋራ ድርጅት ነው። ትልልቅ ሼር ያላቸው ሀገራት አሉ። የድርጅቱ ገንዘብ በነዚህ ሼር ካላቸው ሀገራት የሚገኝ ነው።
- አሜሪካ 17.43%
- ቻይና 6.4%
- እንግሊዝ 4.23% ...አላቸው። ሌሎችም ሁሉም ገንዘብ አላቸው በድርጅቱ።
ኢትዮጵያም የIMF አባል ናት።
IMF የተቋቋመው በዓለም ላይ የተረጋጋ የፋይናንስ ስርዓትን ለመገንባት ነው። ለዚህም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ድጋፍ ለማድረግ ነው የተመሰረተው።
በዚህ ምክንያት በየሀገሩ ሪፎርም እያዘጋጀ ይቀርባል ' ይሄን ይሄን አድርጉ ' እያለ ወይም የቀረበለትን እየገመገመ ' ይሄን አድርጉ ይህ እንዲሆን ' ይላል። ትክክል ሲመስለው ያጸድቃል ካልሆነ ውድቅ ያደርጋል።
ኢትዮጵያም ወደ IMF የሪፎርም አጀንዳ ሰንድ ይዛ ቀርባለች። 3 ዓመታት ያህል ሰነዱን ሲገመግም ቆይቶ አሁን አጽድቋል። ሲያጸድቅ ግን ይሄ ይሄ መሆን አለበት ብሎ ነው ወደ ተግባር የገባው።
የIMF ስም ከfloating exchange rate ጋር የሚነሳውም ለዚህ ነው።
IMF ለኢትዮጵያ 6 ዓመት የእፎታ ዘመን ያለው ብድር ነው የሰጠው ይህ ማለት ለቀጣይ 6 ዓመታት ምንም ክፍያ አይፈጸምም ፤ 0 ምንም ወለድ የሌለበት ነው።
እውነት IMF ለሀገራት ስለሚያስብ ነው ? ወይስ በእጅ አዙር ሌላ አላማ አለው ? ይህ ነው ትልቁ መከራረከሪያ ነጥብ።
IMF ስለ እራሱ የሚለው ምንድነው ? ስራዎቹን በመልካም ጎኑ የሚያዩት አካላት የሚሉት ምንድነው ?
- ዓለም ላይ ባሉ ሀገራት ተወዳዳሪነት ያለበት የኢኮኖሚ ስርዓት እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- የዓለም ኢንቨስትመንት ያለምንም እንቅፋት እንዲንቀሳቀስ ነው የምፈልገው።
- ገንዘብ በመላው ዓለም በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ እፈልጋለሁ። ... ይላል።
በዚህም ፤ " ምቹ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ያለበት ሀገር መፍጠር ነው የምፈልገው በየሀገራችሁ ይህን ፈጥርላችኋለሁ " ነው የሚለው።
☑ ጣልቃ እየገባ መቆጣጠሩን ያቁም
☑ የግል ሴክተሩን መቆጣጠር ያቁም
☑ ኢምፖርት ላይ የሚወጣው ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ይቀንስ
☑ ኤክስፖርት ላይ ያለ ቁጥጥር ይቀንስ
☑ አሳሪ ህጎችን አላሉ
☑ ፕራቬታይዤሽን እንዲኖር አድርጉ
☑ ሊባራይዜሽን ይጠናከር / በሞኖፖል የተያዙትን ዘርፎች ክፍት አድርጉ (ለምሳሌ ፦ ቴሌ ሊሆን ይችላል)
☑ ማንም ከውጭ አይገባም የሚለውን ቀንሱ ፤ ፉክክር ይኑር
☑ የዋጋ ንረት መቆጠር አለባችሁ
☑ የበጀት ጉድለት አስተካክሉ
☑ መልካም አስተዳደር እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ተቋማት ይገንባ
ስለዚህ ለናተው ሲባል " በኢኮኖሚ እንድታድጉ ፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖራችሁ " ነው ይህን ማድረግ ያለባችሁ የሚለው።
በኢኮኖሚ መርህ ተመሩና ሀገራችሁ እዲያድግ እፈልጋለሁ ነው የሚለው።
የሀገራት የእድገት አቅጣጫ እንዲስተካከል ይፈልጋል። በዚህም ከድህነት የወጣ ሀገር ይመሰረታል፣ ሁሌ የማይበደር ሀገር ይፈጠራል፣ ኢንቨስትመንት ጤነኛ የሆነበት፣ ምቹ ሀገር መፍጠር ይቻላል የሚል ሐሳብ አለው።
በመሆኑም ፦ የማክሮ ኢኮኖሚውን የመምራት አቅማችሁ ደካማ ከሆነ የምትመሩበትን ሁኔታ ይዤ መጣለሁ፣ የገንዘብ ፖሊሲው ጤነኛ ካልሆነ እኔ አግዛለሁ ፦
• ብድር በማራዘም አግዛለሁ ይላል።
IMF ይሄን ያደርጋል ብሎ የሚከራከሩለት አሉ።
IMF የሪፎርም ሰነዶቹን ለተለያዩ ሀገራት ነው የሚያቀርበው።
➡ IMF ያደጉ ሀገራት ያሉበት ሼር ነው። ስለዚህ ያደጉ ሀገራት ድሃ ሀገራት ላይ ፍላጎታቸውን መጫን ይፈልጋሉ።
➡ ብዙ ብድር በመስጠት የሚፈልጓትን ሀገር ተቆጣጥረው መያዝ ይፈልጋሉ።
➡ እዳ ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ መያዝ። በብድር ሰብሰብ መያዝ።
➡ ብድር እና ድጋፍ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አድግጎ መጠቀም ይፈልጋል።
➡ በየሀገሩ እየሄደ ልርዳችሁ የሚለው በብድር ሰበብ ረጅም አመት በእዳ መያዝ ይፈልጋል።
➡ ለአንድ ሀገር ብዙ ብድር ከእፎታ ዘመን ጋር ፣ ከዛም ምንም ወለድ የሌለበት ብድር ሲሰጥ ረጅም ዓመት ሀገሪቱ በእዳ ውስጥ እንድትቆይና በዛ ሀገር የፈለገውን ነገር ለመጫን እድል እንዲሰጠው ነው።
➡ በእዳ የሚይዘው ያደጉት ሀገራት የድሃ ሀገራትን ማዕድን፣ ገበያውን ለምዕራባውያን መስጠት ስለሚፈልግ ነው።
➡ ፊት ለፊት ከሚያደርጉት ስምምነት በተጨማሪ ከጀርባ የሚያደርጉት ስምምነት አለ። ያደጉ ሀገራት ድርጅቶቻቸው ያላደጉ ሀገራት ሄደው ፦
° ማዕድን እንዲያገኙ
° ገበያ በቀላሉ እንዲያገኙ እድል እና ጫና የመፍጠር አዝማሚያ አለው።
➡ እዳ ውስጥ ያለ ሀገር በፖለቲካው በኩል የሚመጣለትን መከራከሪያና ጫና ሁሉ እንዲቀበል የማድረግ መሳሪያም ነው። ብድር እና እርዳታ በመስጠት። አንዳንድ ሀገራት ግጭት ውስጥ ሲገቡ (እልውናቸውን ለማስጠበቅ ቢሆን እንኳ) ፣ ሰላም እና መረጋጋት ሲርቃቸው እርዳታ እና ብድር ይይዛል። አይሰጣቸው።
➡ ዓላማው እድገት ብቻ አይደለም።
➡ ተመሳሳይ ሪፎርም ለብዙ ሀገራት ይሰጣል። ይህ የሀገራቱን ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ለግብጽም፣ ለናይጄሪያም፣ ለኢትዮጵያም የሚመክረው ተመሳሳይ ነው። ብዙ ድሃ ላለበት ሀገር እና ትንሽ ድሃ ላለበት ሀገር ተመሳሳይ ምክር ይሰጣል።
ምሳሌ ፦ IMF ድጎማ እንዲቀንስ ያበረታታል። በደካማ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለ ሀገር ላይ መንግስት ከድጎማ ወጥቶ ገበያው በራሱ እንዲንቀሳቀስ ይመክራል። ይሄ ደግሞ በርካታ ሰዎች ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ውጭ ይሆናሉ።
➡ ነጻ ገበያ እያለ ያውጃል ግን ያላደጉ ሀገራት እሱን ሲሞክሩ ብዙ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ የሚገቡ ማህበረሰቦች ይፈጠራሉ።
➡ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመጠበቅ እንኳን መንገድ እንዳይኖር ልቀቁት ይላል። በዚህም ትንንሽ አማራቾች ከውጭ በሚመጣ ምርት እና አምራች ጋር መፎካከር አቅቷቸው ከንግድ ውጭ ይሆናሉ።
➡ ምክሮቹ ድህነትን የሚያበረታቱ የመሆን እድል አላቸው።
በሚል የሚከራከሩ አሉ።
IMF ግን አንዳንድ ሪፎርሞች ወዲያው ለውጥ እንደማያመጡ ያምናል።
ለምሳሌ ፦ ብድር እና እርዳታ ከIMF ስለመጣ ብቻ ሀገር ውስጥ ያለ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጠንካራ ካልሆነ፣ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተቋማት አፈጻጸማቸው ጠንካራ ካልሆነ በብድር እና ድጋፍ ብቻ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ያድጋል ብሎ አያምንም።
ሪፎርም ሲመጣ ችግር እንደሚመጣም ያውቃል። ከሪፎርም በኃላ የዋጋ ንረት ሊኖር እንደሚችልም እራሱ ይተነብያል መጀመሪያ ላክ ሾክ / መናጋት ይኖራል ግን ሪፎርሙ እግር ሲይዝ የዋጋ ንረት ይቀንሳል ነው የሚለው።
ከIMF ድጋፍ በኃላ የወደቁ ሀገራት ካሉ የወደቁበት ምክንያት የIMF ጣልቃ ገብነት ስላለ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ያላቸው የተቋማት አፈጻጸም አቅምና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የመፈጸም ሁኔታዎች ናቸው የሚል መከራከሪያ አለው።
IMF ድጋፍ እና ብድር ሲሰጥ እሱን መቋቋም የሚችል የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተቋም ያስፈልጋል። ይህም ፦
BY NOTHING ...💞
Share with your friend now:
tgoop.com/LoveAndTruth/1514