Telegram Web
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD🇪🇹

" የታላቁ ህዳሴ ግድብ 3ኛውን የውሃ ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ ነው ፤ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ በትኩረት እየተሰራ ነው " - ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ

የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ደስታ አብቼ ፥ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው የምትገኘው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲከናወን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ሌ/ጀኔራል ደስታ " ሠራዊቱ የተሠጠውን ተልኮ ሌት ተቀን በቁርጠኝነት መፈፀም በመቻሉ ለህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውሉ ግብአቶች በሰላም ተጓጉዘው እንዲደርሱ እና ሰራተኞችም ደህንነታቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ ማድረግ ተችሏል " ብለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ #3ኛውን_የውሃ_ሙሌት ለማከናወን በ21 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የምንጣሮ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የገለፁት ሌ/ጀኔራሉ " የግድቡ ግንባታ ሰራተኞች ያለምንም የፀጥታ ስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ በትኩረት እየሰራ ነው " ብለዋል።

አክለውም " የተቀናጀ የፀጥታ ሃይሉ ዕድገታችንን ለማደናቀፍ #ከሱዳን ሰርገው የሚገቡ ኃይሎችን እየተከታተለ ሴራቸውን እያከሽፈው ይገኛል ፤ በቀጣይም ከአካባቢው ማህበረሰብ እና ሲቪል አመራሮች ጋር ተቀናጅቶ ግዳጁን በአስተማማኝ ለመወጣት ዝግጁነቱ የላቀ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

#FDRE_Defense_Force🇪🇹

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
Forwarded from 🌿🌿🌿 መርጌታ ይግዛው 🌱🌱🌱
ለተቃውሟችን ለከት ካላበጀን ሀገራችንን እንጎዳለን!

ዶ/ር ዐቢይ ፋኖን ሊያፈርስ ነው እያሉ ሲያደነቁሩን የነበሩ አሉባልታውያን ዛሬ መንግሥት ፋኖን እውቅና ሰጥቶ በሽልማት ሲያምበሸብሽ ምን ይሉ ይሆን?

#ሰላም_ለሰው_ዘር_በሙሉ
#ኢትዮጵያ #Ethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
🫂 ከጭልጋና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ወደ ቦታቸው እየተመለሱ ይገኛሉ።

በጭልጋና አካባቢዋ ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተነግሯል።

ከትላንት አንስቶ ከአይከል እና በዙሪያዋ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 938 የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ወደ አይከል ከተማ ሲገቡ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተቀብሏቸዋል።

ተፈናቃዮቹ ከዚህ በፊት በአይከል ከተማና በአካባቢዋ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ከማንነት ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቦታቸው ተፈናቅለው በተለያዬ ቦታ ነበሩ። አሁን ላይ በተፈጠረው አንፃራዊ ሰላም ከትላንት አንስቶ ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ መሆኑ ተነግሯል።

ፎቶ ፦ የጭልጋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Update

በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸዉ ተመለሱ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ - ባህር ከተማ በወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው አይከልና ሰራባ ጊዜያዊ መጠለያ የነበሩ የህበረተሰብ ክፍሎች ዛሬ ወደ ቀያቸዉ ተመልሰዋል።

ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ነጋዴ - ባህር ከተማ ሲደርሱ የነጋዴ ባህር ከተማ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል እንዳደረገላቸው ተገልጿል።

Photo Credit : ጭልጋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ተፈትኖ የወደቀው ፌስቡክ

ፌስቡክ ፤ በኢትዮጵያ ሶስት ብሔሮች ላይ ያነጣጠሩ #የጥላቻ_ንግግሮች ያዘሉ ማስታወቂያዎች ይለይ እንደሆነ የተሰጠውን ፈተና መውደቁ ተሰምቷል።

ፌስቡክን የሙከራ ማስታወቂያዎችን በመጠቀም የፈተኑት " ግሎባል ዊትነስ " እና " ፎክስ ግሎቭ " የተባሉ ሁለት ተቋማት ከቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት መምህር ዳግም አፈወርቅ ጋር በመተባበር ነው። 

ምርመራው የተከናወነው የፌስቡክ የጥላቻ ንግግር መለያ ምን ያህል ጥሩ እንደሆነ ለመፈተን እና የኩባንያው የደህንነት መቆጣጠሪያ ስልቶች ሁከት የሚያባብሱ ማስታወቂያዎችን መከላከል ይችል እንደሁ ለመፈተሽ ነበር።

በአማርኛ ቋንቋ በፌስቡክ የተጻፉ 12 የከፉ የጥላቻ ንግግሮችን የለዩት ምርመራ አድራጊዎቹ እነዚሁኑ ይዘቶች ለኩባንያው እንደ ማስታወቂያ በማቅረብ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለመለጠፍ ይፈቅድላቸው እንደሁ ሙከራ አድርገዋል።

የኩባንያውን የቁጥጥር አቅም ለመፈተሽ በምሳሌነት የተመረጡት የጥላቻ ንግግሮች የተካተቱባቸው ማስታወቂያዎች፤ የአማራ፣ የትግራይ እና የኦሮሞ ብሔሮች ላይ እኩል ያነጣጠሩ ናቸው።

በማስታወቂያዎቹ አረፍተ ነገሮች መካከል " ሰዎች እንዲገደሉ፣ እንዲራቡ ወይም ከአንድ አካባቢ እንዲጠፉ በቀጥታ ጥሪ የሚያደርጉ፤ ሰዎችን ከእንስሳት ጋር የሚያነጻጽሩ እና ሰብዓዊነት የጎደላቸው” ገለጻዎች እንዳሉበት ተገልጿል።

አብዛኞቹ የማስታወቂያዎቹ ይዘቶች የዘር ማጥፋት እንዲፈጸም ጥሪ የሚያቀርቡ መሆናቸውም ተገልጿል። ከእነርሱ ውስጥ አንዳቸውም ለመተርጎም ውስብስብ እንዳልነበሩ ተመላክቷል።

ግሎባል ዊትነስ ፤ " የትኞቹንም ማስታወቂያዎች አላተምናቸውም። የሚታተሙበትን ቀን ወደ ፊት እንዲሆን በማድረግ፤ ፌስቡክ ማስታወቂያዎቹን መቀበል እና አለመቀበሉን ካሳወቀን በኋላ አጥፍተናቸዋል " ብሏል።

የጥላቻ ንግግሮቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ለህዝብ ይፋ አለመደረጋቸውን አረጋግጧል።

በምርመራው መሰረት ፌስቡክ የቀረበሉትን 12ቱንም የጥላቻ ንግግሮች በማስታወቂያ መልክ በገጹ እንዲቀርቡ ፈቃድ ሰጥቷል።

ሁሉም ማስታወቂያዎች ፌስቡክ በአጠቃቀም መመሪያው (community standards) የጥላቻ ንግግር ብሎ ከሚበይናቸው ውስጥ የሚካተቱ ናቸው።

በሙከራ ደረጃ ፌስቡክ የተፈተነባቸው ማስታወቂያዎች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው ላይ ለዕይታ ቢበቁ ኖሮ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከ57 አመታት በፊት የጸደቀውን ስምምነት የሚጥሱ ነበሩ።

ስምምነቱ ማናቸውም አይነት የዘር መድሎዎ ለማስወገድ የጸደቀ ነው።  

በድርጅቶቹ ምርመራ የተገኘው ውጤት በስተመጨረሻ የቀረበለት ፌስ ቡክ፤ ማስታወቂያዎቹ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴው እንዲታተሙ መፈቀድ እንዳልነበረበት ማመኑን ግሎባል ዊትነስ አሳውቋል።

ፌስቡክ ለኢትዮጵያ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የደህንነት ቁጥጥሩን ለማጥበቅ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን መግለጹንም ምርመራውን ካከናወኑት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ግሎባል ዊትነስ አመልክቷል።

Credit - www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ቅናሽ ካለማ…
አዲሱን የአቢሲንያ ባንክ አፖሎ የዲጂታል መተግበርያ ሲጠቀሙ በሲኒማ ትኬት፥ በምግብ እና መጠጥ ትዕዛዝዎ ላይ ቅናሽ ያገኛሉ። አፖሎን አውርደው ዛሬውኑ ይጠቀሙ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።

https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo
#Apollo #OurNewProduct #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank, #poweredbybankofabyssinia, #thechoiceforall
Ethiopia
August 4, 2024
IMF ዓለማው ምንድነው ? ቢሊዮን ዶላሮች ደግፎ / አበድሮ ምን ይጠቀማል ?
(በኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ)
የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ፥ 190 አባል ሀገራት ያሉት የጋራ ድርጅት ነው። ትልልቅ ሼር ያላቸው ሀገራት አሉ። የድርጅቱ ገንዘብ በነዚህ ሼር ካላቸው ሀገራት የሚገኝ ነው።
- አሜሪካ 17.43%
- ቻይና 6.4%
- እንግሊዝ 4.23% ...አላቸው። ሌሎችም ሁሉም ገንዘብ አላቸው በድርጅቱ።
ኢትዮጵያም የIMF አባል ናት።
IMF የተቋቋመው በዓለም ላይ የተረጋጋ የፋይናንስ ስርዓትን ለመገንባት ነው። ለዚህም ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ድጋፍ ለማድረግ ነው የተመሰረተው።
በዚህ ምክንያት በየሀገሩ ሪፎርም እያዘጋጀ ይቀርባል ' ይሄን ይሄን አድርጉ ' እያለ ወይም የቀረበለትን እየገመገመ ' ይሄን አድርጉ ይህ እንዲሆን ' ይላል። ትክክል ሲመስለው ያጸድቃል ካልሆነ ውድቅ ያደርጋል።
ኢትዮጵያም ወደ IMF የሪፎርም አጀንዳ ሰንድ ይዛ ቀርባለች። 3 ዓመታት ያህል ሰነዱን ሲገመግም ቆይቶ አሁን አጽድቋል። ሲያጸድቅ ግን ይሄ ይሄ መሆን አለበት ብሎ ነው ወደ ተግባር የገባው።
የIMF ስም ከfloating exchange rate ጋር የሚነሳውም ለዚህ ነው።
IMF ለኢትዮጵያ 6 ዓመት የእፎታ ዘመን ያለው ብድር ነው የሰጠው ይህ ማለት ለቀጣይ 6 ዓመታት ምንም ክፍያ አይፈጸምም ፤ 0 ምንም ወለድ የሌለበት ነው።
እውነት IMF ለሀገራት ስለሚያስብ ነው ? ወይስ በእጅ አዙር ሌላ አላማ አለው ? ይህ ነው ትልቁ መከራረከሪያ ነጥብ።
IMF ስለ እራሱ የሚለው ምንድነው ? ስራዎቹን በመልካም ጎኑ የሚያዩት አካላት የሚሉት ምንድነው ?
- ዓለም ላይ ባሉ ሀገራት ተወዳዳሪነት ያለበት የኢኮኖሚ ስርዓት እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ የንግድ ስርዓት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- ጤነኛ ኢንቨስትመንት እንዲኖር እፈልጋለሁ።
- የዓለም ኢንቨስትመንት ያለምንም እንቅፋት እንዲንቀሳቀስ ነው የምፈልገው።
- ገንዘብ በመላው ዓለም በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ እፈልጋለሁ። ... ይላል።
በዚህም ፤ " ምቹ ኢንቨስትመንት እና ንግድ ያለበት ሀገር መፍጠር ነው የምፈልገው በየሀገራችሁ ይህን ፈጥርላችኋለሁ " ነው የሚለው።
ጣልቃ እየገባ መቆጣጠሩን ያቁም
የግል ሴክተሩን መቆጣጠር ያቁም
ኢምፖርት ላይ የሚወጣው ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ይቀንስ
ኤክስፖርት ላይ ያለ ቁጥጥር ይቀንስ
አሳሪ ህጎችን አላሉ
ፕራቬታይዤሽን እንዲኖር አድርጉ
ሊባራይዜሽን ይጠናከር / በሞኖፖል የተያዙትን ዘርፎች ክፍት አድርጉ (ለምሳሌ ፦ ቴሌ ሊሆን ይችላል)
ማንም ከውጭ አይገባም የሚለውን ቀንሱ ፤ ፉክክር ይኑር
የዋጋ ንረት መቆጠር አለባችሁ
የበጀት ጉድለት አስተካክሉ
መልካም አስተዳደር እና ጠንካራ ኢኮኖሚ ተቋማት ይገንባ
ስለዚህ ለናተው ሲባል " በኢኮኖሚ እንድታድጉ ፣ የተረጋጋ ኢኮኖሚ እንዲኖራችሁ " ነው ይህን ማድረግ ያለባችሁ የሚለው።
በኢኮኖሚ መርህ ተመሩና ሀገራችሁ እዲያድግ እፈልጋለሁ ነው የሚለው።
የሀገራት የእድገት አቅጣጫ እንዲስተካከል ይፈልጋል። በዚህም ከድህነት የወጣ ሀገር ይመሰረታል፣ ሁሌ የማይበደር ሀገር ይፈጠራል፣ ኢንቨስትመንት ጤነኛ የሆነበት፣ ምቹ ሀገር መፍጠር ይቻላል የሚል ሐሳብ አለው።
በመሆኑም ፦ የማክሮ ኢኮኖሚውን የመምራት አቅማችሁ ደካማ ከሆነ የምትመሩበትን ሁኔታ ይዤ መጣለሁ፣ የገንዘብ ፖሊሲው ጤነኛ ካልሆነ እኔ አግዛለሁ ፦
• ብድር በማራዘም አግዛለሁ ይላል።
IMF ይሄን ያደርጋል ብሎ የሚከራከሩለት አሉ።
IMF የሪፎርም ሰነዶቹን ለተለያዩ ሀገራት ነው የሚያቀርበው።
IMF ያደጉ ሀገራት ያሉበት ሼር ነው። ስለዚህ ያደጉ ሀገራት ድሃ ሀገራት ላይ ፍላጎታቸውን መጫን ይፈልጋሉ።
ብዙ ብድር በመስጠት የሚፈልጓትን ሀገር ተቆጣጥረው መያዝ ይፈልጋሉ።
እዳ ውስጥ እንድትቆይ በማድረግ መያዝ። በብድር ሰብሰብ መያዝ።
ብድር እና ድጋፍ እንደ ፖለቲካ መሳሪያ አድግጎ መጠቀም ይፈልጋል።
በየሀገሩ እየሄደ ልርዳችሁ የሚለው በብድር ሰበብ ረጅም አመት በእዳ መያዝ ይፈልጋል።
ለአንድ ሀገር ብዙ ብድር ከእፎታ ዘመን ጋር ፣ ከዛም ምንም ወለድ የሌለበት ብድር ሲሰጥ ረጅም ዓመት ሀገሪቱ በእዳ ውስጥ እንድትቆይና በዛ ሀገር የፈለገውን ነገር ለመጫን እድል እንዲሰጠው ነው።
በእዳ የሚይዘው ያደጉት ሀገራት የድሃ ሀገራትን ማዕድን፣ ገበያውን ለምዕራባውያን መስጠት ስለሚፈልግ ነው።
ፊት ለፊት ከሚያደርጉት ስምምነት በተጨማሪ ከጀርባ የሚያደርጉት ስምምነት አለ። ያደጉ ሀገራት ድርጅቶቻቸው ያላደጉ ሀገራት ሄደው ፦
° ማዕድን እንዲያገኙ
° ገበያ በቀላሉ እንዲያገኙ እድል እና ጫና የመፍጠር አዝማሚያ አለው።
እዳ ውስጥ ያለ ሀገር በፖለቲካው በኩል የሚመጣለትን መከራከሪያና ጫና ሁሉ እንዲቀበል የማድረግ መሳሪያም ነው። ብድር እና እርዳታ በመስጠት። አንዳንድ ሀገራት ግጭት ውስጥ ሲገቡ (እልውናቸውን ለማስጠበቅ ቢሆን እንኳ) ፣ ሰላም እና መረጋጋት ሲርቃቸው እርዳታ እና ብድር ይይዛል። አይሰጣቸው።
ዓላማው እድገት ብቻ አይደለም።
ተመሳሳይ ሪፎርም ለብዙ ሀገራት ይሰጣል። ይህ የሀገራቱን ሁኔታ ያላገናዘበ ነው። ለግብጽም፣ ለናይጄሪያም፣ ለኢትዮጵያም የሚመክረው ተመሳሳይ ነው። ብዙ ድሃ ላለበት ሀገር እና ትንሽ ድሃ ላለበት ሀገር ተመሳሳይ ምክር ይሰጣል።
ምሳሌ ፦ IMF ድጎማ እንዲቀንስ ያበረታታል። በደካማ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለ ሀገር ላይ መንግስት ከድጎማ ወጥቶ ገበያው በራሱ እንዲንቀሳቀስ ይመክራል። ይሄ ደግሞ በርካታ ሰዎች ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ውጭ ይሆናሉ።
ነጻ ገበያ እያለ ያውጃል ግን ያላደጉ ሀገራት እሱን ሲሞክሩ ብዙ የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ የሚገቡ ማህበረሰቦች ይፈጠራሉ።
የሀገር ውስጥ አምራቾችን ለመጠበቅ እንኳን መንገድ እንዳይኖር ልቀቁት ይላል። በዚህም ትንንሽ አማራቾች ከውጭ በሚመጣ ምርት እና አምራች ጋር መፎካከር አቅቷቸው ከንግድ ውጭ ይሆናሉ።
ምክሮቹ ድህነትን የሚያበረታቱ የመሆን እድል አላቸው።
በሚል የሚከራከሩ አሉ።
IMF ግን አንዳንድ ሪፎርሞች ወዲያው ለውጥ እንደማያመጡ ያምናል።
ለምሳሌ ፦ ብድር እና እርዳታ ከIMF ስለመጣ ብቻ ሀገር ውስጥ ያለ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጠንካራ ካልሆነ፣ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ተቋማት አፈጻጸማቸው ጠንካራ ካልሆነ በብድር እና ድጋፍ ብቻ የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ያድጋል ብሎ አያምንም።
ሪፎርም ሲመጣ ችግር እንደሚመጣም ያውቃል። ከሪፎርም በኃላ የዋጋ ንረት ሊኖር እንደሚችልም እራሱ ይተነብያል መጀመሪያ ላክ ሾክ / መናጋት ይኖራል ግን ሪፎርሙ እግር ሲይዝ የዋጋ ንረት ይቀንሳል ነው የሚለው።
ከIMF ድጋፍ በኃላ የወደቁ ሀገራት ካሉ የወደቁበት ምክንያት የIMF ጣልቃ ገብነት ስላለ ሳይሆን በሀገር ውስጥ ያላቸው የተቋማት አፈጻጸም አቅምና የኢኮኖሚ ፖሊሲ የመፈጸም ሁኔታዎች ናቸው የሚል መከራከሪያ አለው።
IMF ድጋፍ እና ብድር ሲሰጥ እሱን መቋቋም የሚችል የኢኮኖሚና የፖለቲካ ተቋም ያስፈልጋል። ይህም ፦
- የመፈጸም አቅም ያለው።
- መልካም አስተዳደር መትከል የሚችል መንግሥት ያስፈልጋል።
ሀገር ውስጥ ያለውን የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ማረጋጋት ያስፈልጋል። እዳ ለመክፈል ኤክስፖርት ጠንካራ መሆን አለበት። አምራች ሴክተር ጠንካራ መሆን አለበት። አምራች ሴክተር መደገፍ ባልተቻለበት የተገኘውን የውጭ ምንዛሬ በትክክለኛ ምርት እና ምርታማነት የሚያሳድግ ፣ገበያን የሚያረጋጋ ሴክተር ላይ ማሳረፍ አቅቶት ኢኮኖሚ ከተዳከመው IMF ስለረዳ ብቻ አይደለም የተዳከመው። የመፈጸም አቅም ደካማ ስለሆነ ነው።
ሪፎርም ሲመጣ የሚመጣውን ሾክ እንዴት መምራት እንደሚቻል ማወቅ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ፦ ገበያው float ሆኗል። ምንዛሬ float በመሆኑ ገንዘብ devaluate መሆኑ አይቀርም። ገንዘብ ከብላክ ማርኬት ጋር ማቀራረብ በሌላ መንገድ devaluate ነው።
መንግስት ድጎማም አደርጋለሁ ብሏል፣ ብዙ ያስወጣዋል ስለዚህ እንዴት ነው ኢኮኖሚው የሚሸፍነው ብሎ ማሰብ አለበት። የበጀት ጉድለት ያለበት ኢኮኖሚ ነው ስለዚህ ይህን ጉድለት ፣ የድጎማ በጀት እንዴት ነው የሚሸፍነው ኢኮኖሚው ተጨማሪ ብር ሰርቶ እንዲከፍል ነው ? ወይስ መቋቋም የማይችል ከሆነ money print እያደረገ ነው የሚሞላው ? ወይስ የተለጠጠ የበጀት ጉድለቱን ይዞ ይቀጣላል ? ይሄን በጥናት እና በጥንካሬ መመልስ ያስፈልጋል።
(የኢኮኖሚ ባለሙያው ዋሲሁን በላይ)
2025/01/08 17:37:22
Back to Top
HTML Embed Code: