tgoop.com/Mahdi_Only_Quran/60
Last Update:
. መፈቀር ስጦታ ነው 😍
ውለታን መመለስ ደግሞ መልካምነት
ነው ተፈቃሪ ብቻ ሳይሆን አፍቃሪን ማፍቀርም ሀቅ ነው 😊
ያገባት በ15 አመት እንደምትበልጠው
አውቆ ነው 🤔 ከእሱ በፊትም ሁለት
ጊዜ አግብታ እንደተለያየችም አረጋግጧል😳 ያገባት ያለፈውን ታሪኳን
በመመዘን ሳይሆን የአሁን ምንነቷን በመለካት ነው😍
እሷም ለእሱ እጅጉኑ ታማኝ ሚስት
ሆነች 😇ስ ድስት ምርጥ ምርጥ ልጆችን
አፈራችለት በችግሩና በከፋው የመከራ
ዘመን በምክሬም በሀብቴም ከጎንህ ነኝ ብላ ከእሱው ጎን በእኩል ተሰለፈች 😌
ዘላለም አይኖርምና ይች ምርጥ ሚስት ሞተችበት 😞 ባልም በሞቷ ክፉኛ
አዘነ እሷን ያጣበት አመት የሀዘን
አመት ተባለ 😓 እሱም ታማኝ አፍቃሪ
ነበርና በተለያዩ አጋጣሚዎች እሷን ከማወደስ ወደኋላ አይልም ፡፡
እሷኮ እንደዚህ ነበረች እንደዚህ ነበረች እያለ ያሞጋግሳታል 😎 ልጆችን
ያፈራችልኝ በችግሬ ዘመን የረዳኝም እሷው ነች ፍቅሯን በሰፊው ተሰጥቻለሁ እያለ ለሌሎች ሚስቶቹም ጭምር ያወራል ☺️
ታማኙ አፍቃሪ የሚስቱን እህቶች አይነት ድምፅ ሲሰማ ሀውላ ትሆን እንዴ!! ብሎ የእንኳን መጣሽ መልእክት ያሰማል 😙
ስጋ አርዶ በሂወት ላሉት ሚስቶቹ ብቻ አያከፋፍልም ለሟች ሚስቱ እህቶችም ድርሻቸውን ይልካል ቀብሯን ይዘይራል
በቅናት ምክንያት 🤩
"ለመሆኑ ለዚያች አሮጌ ሚስት ይሄን ያክል ማውራት ምን ይሉታል!!"
የሚሉ ሚስቶችም ተፈጥረው ነበር።
😔 ከሞተኝም በኋላ በባሏ ልቦና
በፅኑ የተፈቀረች ይች እድለኛ
ሚስት ማን ነች ካላችሁ.......
#ኸዲጃ_ቢንት_ኹወይሊድ
መሆኗን እወቁ።
https://www.tgoop.com/Anush_tube
https://www.tgoop.com/Anush_tube
BY Mahdi_Only_Quran
Share with your friend now:
tgoop.com/Mahdi_Only_Quran/60