tgoop.com/Mebacha/135
Create:
Last Update:
Last Update:
የፍጥረት ውሃ ልክ
--‐----------------
#ሚካኤል_እንዳለ
.
ከሴት ልጅ የፀዳች ፥ ዓለምን ፈጥሬ
ዠርገግ ባልኩባት ፥ ባረፍኩባት ኖሬ
የምትል ቋጠሮ
ቤት መምቻ እሮሮ
. . . አስቤ ልገጥም
ለካስ ሴት ከሌለች እናትም አትኖርም !!
የሚል መደምደሚያ ከባድ ስንኝ ቢያንቀኝ
ሰረዝኩት ሃሳቤን ወንድ የሆንኩበት ሴትነት ቢገባኝ
. . .
እናማ ካዘለች
ፈትላ ካዋሃደች
ከተሰጣት ዘንዳ
መምሰል ጽጌሬዳ
እሾህን ከጣዕም በአድ ላይ ገምዳ
ካስተባበረችው ፥ በተፈጥሮ ፀጋ
መቻል ግዴታ ነው ማሯን እስከላሱ ንቢት ስትዋጋ
. . .
በሚለው እውነታ
ቁጭ አርገው ከግርጌ 'ካውድማው ጉብታ
እንዲ ብለው ነበር ሲመክሩኝ 'የኔታ . . .
ሃላፊውን ችለህ ለመኖር ከፈለክ ዘላለም አብረሀት
በፍጥረት ውሃ ልክ በ'ናትነት ይሁን ሴትን ስትለካት !!!
@mebacha
@mebacha
BY መባቻ ©

Share with your friend now:
tgoop.com/Mebacha/135