tgoop.com/MedinaTube/1029
Last Update:
#ሰለዋት…
የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦
﴿اِنَّ اللّٰهَ وَمَلٰٓٮِٕكَتَهٗ يُصَلُّوۡنَ عَلَى النَّبِىِّ ؕ يٰۤـاَيُّهَا الَّذِيۡنَ اٰمَنُوۡا صَلُّوۡا عَلَيۡهِ وَسَلِّمُوۡا تَسۡلِيۡمًا﴾
“አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡”
📚 አል‐አህዛብ: 56
ረሱልም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إنَّ مِن أفضَلِ أيّامِكم يومَ الجُمعةِ، فأكْثِروا عليَّ الصلاةَ فيه؛ فإنَّ صلاتَكم مَعروضةٌ عليَّ.﴾
“ከቀናችሁ ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። በዚህ ቀን በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድ አብዙ። ሰለዋታችሁ ለኔ ይቀርብልኛልና።”
@medinatube
📚 አቡ ዳውድ ሶሂህ ብለውታል: 1531
በሌላ ሀዲሳቸው ﷺ፦
﴿أكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يومَ الجمُعةِ و ليلةَ الجمُعةِ، فمَن صلّى عليَّ صلاةً صلّى اللهُ عليهِ عَشرًا.﴾
“በጁምዓ ቀንና ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ። በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል።”
@medinatube
BY Medina Tube || መዲና ቲዩብ
Share with your friend now:
tgoop.com/MedinaTube/1029