tgoop.com/MedinaTube/877
Last Update:
ዳና .....በ1ጀምበር 2 ጠሃይ
የ2 የሐበሻ ሸምስይ ሙሐመድይ መደድ ገንባሪዎች ኸልዋ
በሳር ጎጆ የሚታየው የገንደጎራው ሳተኔ የዘቡራው ሰይድ ጫሌ የኢባዳ ኸልዋ ነው
መገን ጎረቤቱ! ከሰሜን ኑር ቀባብሶ ወርዶ ደቡብ ላይ ያስገበየው
አቡ ሙሐመድ ሱልጣን ቀጥበርዩ ሳዳተል ኪራሙ!
2ቱም ኸልዋዎች ፈርሰው ታድሰዋል ' የገረመኝ የቀጥበርዩ ኸልዋ የኺድማ ክፍል መሆኑ ነው....ሩህ ትላለች" አደብ ጥሼ ገብቼ ረክዐተይን ልስገድ ወይስ በሩቁ ሰላምታዬ ይብቃኝ?'
አይ ረሱለላሁ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም
ያንን ሁላ ጭፍራ የከመለው ቀላሴው የአንይ ልጅ ከሙስጦፋው ክንድ ተውሶ እንጂ እንዴት ቻለው ' ሰይዲ ያ ዐሩሰ ዳና
ኦሆሆይ ብዙ ነበር ሚያስብለው ግርግሩ አልተመቸም
መገን አህመድ የዳናው ሙሽራ የዘረኝነትን ሆሳ አይኑን ያጠፋው ቀላሴ....ቀጥበርዩ የመተናነስ ውቅያኖስ ነበሩ ነገር ዐለማቸው ኻዲም መስሎ መቅረብ ነው'' የምርም ኻዲም የምርም ሰይድ
በውስጥዎ የደበቁትን የማዕሪፋ ጀበል ቢያዩት ጫልዪ በአቡል ጀበል መሃባ ተያዙ ' ተላቅሰው ከዳና ዐለም እስኪለያዩ ድረስ 'ጦይባን ተፈጋፈጉ
እንዲህ ነው የኢማን ብርሌ እንዲህ ነው የማወቅ ጥጉ
ሳያንስ ያንዱ እድያ ተጎራ ተገደል ያሉት ከጎረቤትዎ ጀምረው ነው ብንለውሳ?
መውሊዱል ሙከረም!
ሰላም ይድረሶት ሆዴ
@medinatube
BY Medina Tube || መዲና ቲዩብ
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/r4e-erL39Vdkxixbfzdmo077WEVZO6FFEU56W_jdViWspEewfVxVSUBK-T0l0Hj82yEXUMh8wJYqKpOZYC65hphsGr_WDfCAkiPdKbx0P462N175AR4Lj7LNe2dD8ygjKGkWpH3O80kTs8wHyzaUSjPqQuaV__Ge6zABTxOnDNrlhdAwvbvvTOgxixn7-EIQJ_1FvX-ROvAGxVb5RDazSxjj-6NCfj2M9TfhpjnhAapp5PWadmle38KzlKFfRNVWHHvRCo2E0hSeGba_0fzJNKDD2q2b2T0iHSd61KsnujXe59Asi-S10EhRc32QqKQGxVP0jjn3qjYERsa48zJpdQ.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/MedinaTube/877