tgoop.com/MekuriyaM/9358
Last Update:
ደስ የሚል ነገርን አንብቡ! መልካም ቆይታ👌
#የሚገርመው ነገር ለብዙዎች ግራ አጋብቷል። “ፍልስፍና ጀመርክ እንዴ?” ያሉም አልጠፉም😍 ፍልስፍናማ ከጥያቄ አይጀምርም'ኮ፤ “ከማድነቅ ነው የሚጀምር።” ከዚያ በኋላ ነው ወደ ጥያቄ/መመራመር/መፈላሰፍ የሚኬድ።
#በጣም_የሚገርመው ደግሞ የብዙዎቹ ጓደኞቼ ምላሽ 'Emoji' መሆኑ ነው።
ታድያ ይሄ ጥያቄ ምንድር ነው? ዲ/ን መኩሪያ(ማርመድሕ) ነኝ ተከተሉኝና በአንድ ርዕሰ ጉዳይ ውስጥ ብዙ ቁም ነገርን ጨብጡ።
🛑 ሰው ነህ⁈ || ሰው ነሽ⁈ ነው ጥያቄው! ሰው ናችሁን?
● “እግዚአብሔር ሙሉ ሰው አድርጎ ነው የሠራኝ። በኦሪት ዘልደት ሥላሴ ሰዉን በመልካቸው በ አርአያቸው ፈጥረውታል። ማለት፦ ንጽሕና፣ ቅድስና የባሕርይ ገንዘባቸውን ለሰዉም ፀጋ ተደርጎ ገንዘብ ተደርጎ ተሰጥቶን ነበር። በዚያ ላይም በገነት ነበር የምንኖረው።
ይህን ጸጋ አጣነው። ማለት፦ ከሰዉነት ዝቅ አልን። እና ይህን ሰዉነት አባቶቻችን ነበራቸው። ቅዱስ ዳዊት ልጁን ሶሎሞንን ሲመርቅ “ልጄ ሆይ ሰው ሁን” ይላል።
እሱ ሰው ሆኖ!! ምን ማለት ነው? ዳዊት በጽዮን ከተማ :ንጉስ ሲሆን :ፍርድ አይጕደል: ደሃ አይበደል: የሚል: ንጉሥ ነው። ይህ ብቻ አይደለም ከእግዚአብሔር ሲርቅ ካንተ ተጣልቼማ እንደማይሆን ነው ብሎ ንስሐ የሚገባ... ይህ ሰው ነው። ልጁንም የመረቀዉ ይህንኑ ነው:: ሰው እንዲሆን እና እኔ ይህን ነገር አለኝ ለማለት ይቸግረኛል... በዝርዝር...ከተለካሁ ነኝ ለማለት ይከብደኛል።
ግን እንዲሁ ዝም ብሎ በቁሙ ሰው ነህ ወይ ካልከኝ ?!! አዉሬ አይደለሁም፣ እንስሳም አይደለሁም። ስለዚህ ጥሩ ሥራ ቢኖረኝ የምጸድቅበት፤ ባይኖረኝ የምኮነንበት ሰውነት ያለኝ #ሰው_ነኝ።
◎ ዲ/ን ጸአዳ ከወልቂጤ
● “ሰላምህ ብዝት ይበል እያልኩ 🙏
እኔም አልኳት፥ የአንቺም ሰላም ይትረፍረፍ!
ቀጠለች...
ሰው ነሽ ወይ ? ላልከኝ ጥያቄ አዎ ነኝ እላለሁ። ሰው የሚለው 'ሰው ምንድነው?' የሚለው በመጀመርያ ስለሚጠይቅ እነሆ፦
1 እኔ ማን ነኝ ?
2 እኔ ከየት መጣሁ ?
3 ምንድነው ምሠራው?
4 መጨረሻዬ ምንድነው?
የሚሉትን ይኖሩታል ሰው የባህር አውሬ ነው ይላል ከእዮብ መጽሐፍ ላይ የተወሰደ።
ሌላኛው የአሜርካው ኖቭሊስት ደሞ ሰው ማሽን ነው ይላል ከምንም በላይ ደሞ ታላቁ ቅዱስ መፅሐፍ ደሞ ሰው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ነው ይለናል ሰው ክቡርም ነው ለዚህ ነው #ሰው_ነኝ የምልህ !
ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነውና🙏”
◎ገጣሚት መቅደስ(ከብዕር አንደበት) ከወልቂጤ
● “እርግጥ ነው ሰው ስውነቱን ክብሩን የተወበት(የረሳበት)ክፉ ጊዜ ላይ ደርሰናል። ነገር ግን የሰውነት ውሃልክ የሆኑ፣ ሰው ሆነው እንደ መላዕክት የሚኖሩ፣ ከኪሩቤል ጋር የሰማይን መቅደስ ያጠኑ፣ ከዋክብተ ሰማይ የሆኑ ቅዱሳን፣ የእውነተኛ ትሕትና መምህራን የሆኑ፣ በጸሎትና በጾም ተወስነውና በዋሻ ውስጥ የሚኖሩ አበው ባሉበት ዓለም ነው የምንኖረው። ሰለዚህ ሰው ነን ለማለት ምስክሮች አሉን ማለት ነው። አሁን ከክብር የጎደልን ልቦና አግኝተን ወደ ቀደመው ነገራችን እስክንመለስ ድረስ።
#አዎ_ሰው_ነኝ#
ምክንያቱም ከ3ቱ ባሕርያተ ነፍስ ከ4ቱ ባሕርያተ ሥጋ የተፈጠርኩ፣ በአርአያ(በአምሳለ)#ቅድስት_ሥላሴ የተፈጠርኩ፣ ሀገሬ ሰማይ፣ መኖሪያዬ ክርስቶስ የሆነ፣ ብቸኛ የክብሩ ቀዳሽ፣ የመንግሥቱ ወራሽ የሆንኩ እስትንፋሰ ክርስቶስ #አዎ_ሰው_ነኝ።”
◎ ዮሴፍ ሺፈራው ከወናጎ
●“እኔ የሰውን ልጅ ባሕርይ ወይም ምግባር ባይኖረኝም፣ ሰው ለመባል ሁሉን ባላሟላም እንኳ፤
“እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤...።”
— ዘፍጥረት 1፥26
ብለው ስለፈጠሩኝና እኔም የሥላሴ አገልጋይ ስለሆንኩኝ #አዎ_ሰው_ነኝ!”
◍ዲ/ን መኩሪያ ገብሩ(ከጉራጌ ዞን)
●“ነኹም አይደለኹምም!
አፈጣጠረ መልከ ሰብእ ቢሆንም በግብሬ ግን ሰው አይደለኹም።”
◎ዲ/ን ጌታቸው ከጉራጌ ዞን
● «በእርሱ አምሳል የተፈጠርኩ...
ሰው፦ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ውስጥ ለየት የሚያረገው #ሰው የሚያስብ፣ የሚያምን፣ የሚያወራ ከእግዚአብሔር በታች ምንም ነገር ላይ መወሰን የሚችል ሰው ነው......። ስለዚህ #አዎ_ሰው_ነኝ!»
◎መዓዛ ከአዲስ አበባ
● ❝እግዚአብሔር በመልኩና በአምሳሉ፤ በእጁ አቡክቶ፣ እስትንፋሱን እፍ ብሎ የፈጠረኝ፣ በመስቀል ተሰቅሎ ነጻ ያወጣኝ ፍጡር ስለሆንኩ #አዎ_ሰው_ነኝ
◎ዘማሪት ምሥራቅ ከጉራጌ ዞን
● ❝አዎ_ነኝ! ...
ለዚያውም በ አምላኬ ምስል የተሳልኩኝ ፍጡር!!!
#ሰው_ነኝ!❞
◎ዳኛቸው ያቦነህ ከቡታጅራ
●❝ #አዎ_ሰው_ነኝ!
ያውም በአምሳሉ የፈጠረኝ!❞
◎ቴዲ ከዲላ
●❝ #አዎ_ሰው_ነኝ!
ሰው የሆንኩት በአምሳሉ ስለተፈጠርኩኝ ነው።❞
ዘፍጥረት 1÷26 ❞
◎ንጉሤ በላይ ከዲላ
◉"በሥጋ ሰው ነኝ። "ሰው ሁን" በተባለበት ሐሳብ ራሴን ስመለከተው ግን ሙሉ ሰው አይደለሁም።🙏"
◎ዲ/ን ኤርምያስ(ሰፋኒት ሚዲያ) ከወልቂጤ
◉"መልካም መልሴ ግር ሊል ይችላል ሆኖም
#ሰው_ነኝ_ደሞም_አይደለሁም
(ሰው ነኝ ስል):- በአምሳሉ የተፈጠርኩኝ
የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ እያልኩ ነው
(ሰው አይደለሁም ስል ደሞ):- ምግባሬ ሰው ሰው አይሸትም ምግባሬ ወድቋል
እያልኩኝ የሰው ምግባር እንዲኖረኝ ፀልዩልኝ (ፍቅረ ጻድቅ)"
●ገጣሚ በረከት ግዛው(ታላቁ መጽሐፍ) ከዲላ
🛑Join/Follow us on
◎ Telegram
www.tgoop.com/MekuriyaM
◎ Ttiktok
http://tiktok.com/@mekuriya19
◉ Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=61570329701398
ከ9,500 አልፈናል 10,000 Members ላይ አድርሱኝ👌
#Share ይደረግ!
BY እምዝ-ዓለም | From this world
Share with your friend now:
tgoop.com/MekuriyaM/9358