Telegram Web
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አመራር ቦርድ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የስራ አመራር ቦርድተወካዮች ጋር የተካሄደ አጠቃላይ ስብሰባ ላይ የተያዘ የአቋም መግለጫ


በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
★★★★★★★★★★

እኛ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በሀገራችን ውስጥ ለዘመናት ብዙ ጭቆናዎችንና የመብት ጥሰቶችን ስናስተናግድ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ በሀገራችን ውስጥ እንደ አንድ ዜጋ ሙሉ መብት እንዲኖረንና ህገ መንግስቱ ባጎናፀፈን የሀይማኖት እኩልነት መሰረት ሀይማኖታችንን የምናራምድበት የሙስሊሙን መብት የምናስከብርበት፣ የሀይማኖታችን ምድራዊና ሰማያዊ ዓላማ የምናሳካበት የራሳችን ተቋም ይኑረን በማለት ለዘመናት ሠላማዊ ትግል ስናደርግ ቆይተናል፡፡ ያለፉት ቅርብ ዓመታት የሙስሊሙ ሠላማዊ እንቅስቃሴ በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን ለስደት፣ ለሞትና ለእስር የዳረገው ቢሆንም ለሙስሊሙ ብሎም ለሀገራችን ህዝብ ትልቅ ሀገራዊ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡

በሀገራችን ፓለቲካዊ ለውጥ በመጣ ማግስት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የሙስሊሙን ዑማህ የዘመናት በደልና ሠቆቃ እንዲሁም ዓመታት የነበረውና የሠላማዊ ትግል ጥያቄ በአግባቡ በመረዳት ይሄን ችግር ለመፍታትና ሙስሊሙ ዑማህ በቅርብ የራሱ ተቋም እንዲኖረው ለማድረግ ፅኑ አቋም በመያዝና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ በፍጥነት በማዋቀርና ኮሚቴውም በአጭር ጊዜ ውስጥ የመፍትሄ ሀሳቦችን ይዞ እንዲመጣ አቅጣጫ ሠጥተዋል፡፡ በዚሁ መሠረትም የተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ለወራት ያህል ሲለፋ ቆይቶ የኢትዮጵያ ሙስሊም የተቋም ባለቤት ሊያደርግ የሚያስችለውንና አንድነቱን አስጠብቆ በሀገሪቱ ውስጥ እንደ አንድ ሙሉ ዜጋ መብቱ ተረጋግጦለት መኖር እንዲችል ሦስት ሠነዶችን አዘጋጅተው በሚያዚያ 23 ቀን 2011 የሽራተን አዲስ ጉባኤ ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩና ክብርት የሠላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪሃት እንዲሁም ሙስሊሙን ዑማህ ሊወክሉ የሚችሉ ዑለማዓዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ምሁራን፣ ወጣቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሦስቱ ሠነዶች ቀርበው ነበር፡፡

በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይም የሙስሊሙን ተቋም ያሻግራሉ የተባሉ 26 ዑለማዓዎችና ሠባት ምሁራን ተመርጠው ወደ ስራ እንዲገቡና የሙስሊሙን አንድነት አስጠብቀው ዑማውን የተቋም ባለቤት አድርገው እንዲመሩ ትልቅ አደራ ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነሱም በህዝብ ፊት በጋራ ቃል ገብተዋል፡፡ እነሆ ዛሬ ድፍን ሁለት ዓመት ሊሆን ሁለት ወር ያህል ቀርቶታል፡፡ በዚህ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ 26ቱ ዑለማዓዎችና ሠባቱ የስራ አመራር ቦርድ አባላት በሽራተን አዲስ የወሰዱትን ሦስቱን ቁልፍ ተግባራት ማለትም የመጅሊሱን አዲሱን ህገ-መጀሊስ በመጠቀም ሪፎርም ማድረግና በአዲስ መልክ መጅሊሱን በማደራጀት በህዝብ ለተመረጠ አካል ማስረከብ፣ የዑለማዓዎች የአንድነት ሠነድ ተግባራዊና ተፈፃሚ በማድረግ የኢትዮጵያን ሙስሊም አንድነት ፅኑ መሠረት ላይ ማቆምና ሦስተኛው የሙስሊሙ ተቋም የሆነው መጅሊስ በአዋጅ እንዲቋቋም ማድረግ ናቸው፡፡

ከሦስቱ ዋና ዋና ሥራዎች መካከል በመንግስት በኩል የሚጠበቀው ኃላፊነት መጅሊሱን በአዋጅ እንዲቋቋም ማድረግ ሲሆን መንግስታችን ሙሉ በሙሉ ኃላፊነቱን ተወጥቷል፡፡ ለዚህም መንግስታችን ታላቅ ምስጋናና እክብሮት ይገባዋል፡፡ ሆኖም ግን የቀሩት ሁለቱ አብይ ጉዳዮች እስስ አሁን ድረስ መሬት መውረድ አልቻሉም፡፡ ሁለቱ ጉዳዮች ተግባራዊ ያለመሆን ቁልፍ ችግርም የዑለማዓዎችና የቦርዱ በጋራ ስምምነትና ኃላፊነት ወደ ስራ ያለመግባት ጉዳይ ነው፡፡ የዚህም ዋናው መንሰኤ የሙስሊሙን አንድነት የማይፈልጉና ለውጡን ለመቀልበስ የሚተጉ አፍራሽ ግለሰቦች በዑለማዓዎችና በቦርዶች መሀከል አለመተማመን እንዲፈጠር በማድረጋቸው ነው፡፡ የፌደራል ቦርድ በሽራተን አዲስ ጉባኤ ላይ የተሠጠውን በአዲሱ ህገ-መጅሊስ መሠረት መጅሊሱን በአዲስ መልኩ የማዋቀርና የማደራጀት ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ ጥረትና ረጅም ርቀት ቢጓዝም ሊሳካ አልቻለም፡፡ ስለሆነም በዛሬው ዕለት የተደራጁ ክልሎችን የቦርድ አባላት በመጥራትና የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ በማድረግ፣ የተፈጠሩ ችግሮችንና መንስኤዎችን በመለየት እንዲሁም የወደፊት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ የሚከተሉትን ባለ 17 የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡

1ኛ. የስራ አመራር ቦርዱ ኃላፊነቱን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ብዙ እንቅፋቶችና የስራ ማነቆዎች ሲያጋጥሙት ቆይተዋል፡፡ ይሁንና ያጋጠሙትን ችግሮች ሁሉ ለሙስሊሙ አንድነት ብሎ በሆደ-ሠፊነትና በታላቅ ትዕግስት ተሸክሞ ሲያሳልፍ ቆይቷል፡፡ ይህን በማድረጉም የሙስሊሙ አንድነት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ ለማድረግ ችሏል፡፡ በዚህም ምክንያት በሚፈለገው ደረጃ ባይሆንም ውጤቶች ታይተዋል፡፡ ከዚህም ውስጥ የመጅሊሱ ህጋዊ ሰውነት በአዋጅ እንዲታወጅ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ ይሁንና፣ በዚህ በኃላ በዚህ ትዕግስት መቀጠል የህዝበ ሙስሊሙን ታሪካዊ እድል ማጨናገፍ ስለሚሆን በነበረው መልኩ መቀጠል ስለማንችል የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ እንደምንወጣ ለህዝባችን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

2ኛ. በተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ የተዘጋጀውና የፀደቀው ህገ-መጅሊስ በሽግግር መጅሊሱ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲፀድቅና የመጅሊሱ የሪፎርም ማስተባባሪያ ሠነድ እንዲሆን እናደርጋለን፡፡ ህገ-መጅሊሱ በጠቅላላ ጉባኤው በአጭር ጊዜ ውስጥ የማይፀደቅ ከሆነ ቦርዱ የቦርዶች ጠቅላላ ጉባኤ በመካሄድ ህገ-መጅሊሱን የማፀደቅ ግዴታ ይኖርበታል፡፡

3ኛ. እስከ አሁን ያልተደራጁ ክልሎች አደራጁን በማለት ተደጋጋሚ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ በተለይ የአማራ ክልል ሙስሊሞች በሺዎች የሚቆጠሩ ሠዎች ፒቲሽን በማቅረብ ጭምር አደራጁን በማለት የፌደራል መጅሊስ ደጅ መጥናት ከጀመሩ ሠነባብተዋል፡፡ ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የመንግስት አካላት ጭምር አቅርበዋል፡፡ በመሆኑም፣ ለጥያቄያቸው አስፈላጊውን ትኩረት በመስጠት ከሚመለከተው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያልተደራጁ ክልሎች በአስቸኳይ እንዲደራጁ እናደርጋለን፡፡

4ኛ. ትላንት ሀገሪቱን ሲበዘብዙና የሀገሪቱን ህዝብ መብት ሲረግጥ ከነበረው አካል ጋር በመሆን የሙስሊሙ ተቋም አቅም እንዳይኖረው በተቋሙ ውስጥ ተሰግስገው ተቋሙን ሲያመክኑና የሙስሊሙ መብት እንዲጨናገፍ ሲያደርጉ የነበሩ አካላት ዛሬም የመጀሊሱን ስልጣን ለመቆናጠጥ ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት የዲን ካባ በመልበስ አንዱ ወገን ተጎድቷል በማለት ራሳቸውን ተቆርቋሪ በማስመሰልና ሽግግሩ ሀዲዱን ስቷል በማለት ህብረተሰቡን እያዋከቡ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ አካላት የሙስሊሙን አንድነት ከማናጋት እንዲቆጠቡ ጥሪ እያቀረብን ከድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ ለህግና ለፍትህ እንዲቀርቡ እናደርጋለን፡፡ በሠሩትም ወንጀል ተጠያቂ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ክትትል እናደርጋለን፡፡

5ኛ. አንዳንድ ግለሰቦች በተለይም የሽራተን አዲስ ጉባኤ ስኬታማ እንዳይሆንና ሙስሊሙ በዚች ሀገር ውስጥ ለሁለት ተከፍሎ ሁለት የተለያየ ተቋም እንዲኖረው ሲያልሙና ሲመኙ የነበሩ ሠዎች ከሽራተን አዲስ ጉባኤው ማግስት ጀምሮ የሙስሊሙን አንድነት አደጋ ላይ ለመጣል ወደ ስራቸው ገብተዋል፡፡ ይህንንም አጀንዳቸውን ዑለማዓዎቻችን ዘንድ በመልካም ገፅታና ራሳቸውን ለአንድ ወገን ተቆርቋሪ በማስመሰል ትላልቅ መሪዎቻችንን እያሳሳቱ ይገኛሉ፡፡ መሪዎቻችን እርስ በርስ እንዳይተማመኑና በወሰኑት ጉዳይ ሁሉ የጋራ አቋም ይዘው ወደ ፊት እንዳይሄዱ ትልቅ ሳንካ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ከዚህም ባለፈ
በመጅሊሱ ዑለማዓዎችና ሥራ አስፈጻሚ ቦርዶች ላይ ዛቻ ጭምር በመስጠት የመጅሊሱ አመራር (የክልል መጅሊሶችን ጨምሮ) የጋራ አቋም እንዳይኖረውና እንዲከፋፈል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም ይህን ተግባር በፅኑ እናወግዛለን፡፡ የመጅሊሱ ዑለማዓዎችና የቦርድ አመራሩም ለእነዚህ አፍራሽ አመለካከት ያላቸው ጥቂት ግለሰቦች ሴራ እንዳይንበረከክ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

6ኛ. አንዳንድ የመጅሊስ አመራሮች ያለ ዑለማዓዎችና ቦርዶች የጋራ ውሳኔና እውቅና የሙስሊሙን አንድነት አደጋ ውስጥ የሚያስገባና ትላንት ሙስሊሙን ሲዘርፉ፣ ሲያሳስሩና ሲያስገድሉ ለነበሩ ሠዎች ደብዳቤ እየፃፉ በመጅሊሱ ማህተም ወጭ በማድረግ በየደረጃው ላለው ለመጅሊስ መዋቅር ሳያሳውቅና የስልጣን ተዋረዱን ሳይጠብቅ ወደ ወረዳ፣ ቀበሌና መስጂድ ደብዳቤ ይልካሉ፡፡ ግለሰቦቹም ከፌደራል መጅሊስ ዳብዳቤ ተሰጥቶናል በማለት ሙስሊሙን ህብረተሰብ እየከፋፈሉና እያተራመሱ ብሎም የሠላምና የፀጥታ ችግር እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም፣ ይሄን ህገ-ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ የፌደራል አመራሮች ከዚህ ከተቋማዊ አሰራር ሥርዓት ውጭ ከሆነ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡

7ኛ. በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ላይ ውስጣዊና ውጫዊ የሆኑ አደጋዎች ተጋርጠውበታል፡፡ መንግስታችን አደጋውን ለመቀልበስና የሀገሪቱን ለውጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ከፍተኛ የሆነ እልህ አስጨራሽ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡ መጅሊሳችን ለሀገራችን ሠላምና እድገት መሣካት ከፍተኛ ሚናና አስተዋፅዖ ማድረግ የሚችል የሠፊው ህዝብ ተቋም ነው፡፡ በመሆኑም፣ መጅሊሱ በተለይም የሥራ አመራር ቦርዱ ከምን ጊዜውም በላይ ከመንግስታችን ጎን ለመቆም ቆርጦ ተነስቷል፡፡ ስለሆነም፣ ከሚመለከተው የመንግስት ቷቋማትና ባለ ድርሻ አካላት ጋር እጅና ጓንት በመሆን ለሀገሪቱ ሠላምና ፀጥታ፣ እድገትና ልማት ቆርጦ ይሠራል፡፡

8ኛ. የሥራ አመራር ቦርዱ የተጣለበትን አስተዳደራዊና የልማት ሥራዎች ላይ በሚያደርገው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ፣ የሙስሊም ምሁራን እያደረጋችሁልን ላለው ሙያዊ ድጋፍ ምስጋናችንን እያቀረብን ለወደፊቱም አሁን ከገባንበት ችግር ለመውጣት በምናደርገው ጥረት ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን::

9ኛ. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤትን ህጋዊ ሰውነት በአዋጅ እንዲቋቋም የጸደቀውን አዋጅ መነሻ በማድረግ ማስፈጸሚያ ደንብ እና መመሪያ በማዘጋጀት ወደ ሙሉ ትግበራ እንዲገባ በጋራ እሰራለን::

10ኛ. የተዘጋጀውን ዘመናዊ አደረጃጀት እና የአሠራር ሥርዓት መመሪያዎች እና ማኑዋሎች ተግባራዊ በማድረግ ተቋማችንን ለሁሉም ሙስሊም ህብረተሰብ ያለ አድሎ የሚጠበቅበትን አገልግሎት በቅልጥፍናና በፍትሃዊነት አገልግሎት እንዲሰጥ እናደርጋለን::

11ኛ. የሥራ አመራር ቦርዱ የተሰጠውን አስተዳደራዊ እና የልማት ሥራዎችን የማስተባበር ሚና በሚገባ እየተወጣ ባለመሆኑ በቀጣይ አስተዳደራዊና የልማት ሥራዎችን ሙያውን ተጠቅሞ በብቃት በመምራት ሙስሊሙ ህብረተሰብ ያለበትን ዘርፈ ብዙ ችግሩች እንዲቀረፉ በጋራ እንሰራለን::

12ኛ. ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተረከብነው አፍሪካ ህብረት አጠገብ የሚገኘው ቦታ አለም አቀፍ ኢስላማዊ ማዕከል ፕሮጀክት ግንባታውን ለማሳካት ሙስሊሙን ህብረተሰብ በማስተባበር ያለብንን ኃላፊነት በጋራ እንወጣለን::

13ኛ. የ1440 ዓመተ ሂጅራ የሃጅ ሥነ-ሥርዓት ለማከናወን ክፍያ ፈጽመው ነገር ግን ኮታ በመሙላቱ ምክንያት መሄድ ያልቻሉ ምዕመናንን የከፈሉት ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፣ ገንዘቡ በወቅቱ ሊመለስ ያልቻለው ወደ ሳውዲ አረቢያ የመጅሊሱ የሐጅ የባንክ ሂሳብ የተላከው ገንዘብ ወደ ሀገር ተመላሽ እንዲደረግ በተደጋጋሚ በስራ አመራር ቦርዱ ጥረት የተደረገ ቢሆንም እንዲመለስ የማይፈልጉ አመራሮች ምክንያት ሊሳካ ባለመቻሉ ነው፡፡ ይሁንና፣ አሁንም ቢሆን የሙስሊሙን ገንዘብ በአስቸኳይ ተመላሽ እንዲሆን በማድረግ ለባለቤቱ እንዲመለስ የሚመለከተው ሁሉ አስፈላጊውን ጥረት እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

14ኛ. እኩል ኃላፊነት ተሰጥቶት ወደ ሥራ የገባው የቦርድ አመራር ዋና ጸሐፊ የጋራ ስምምነት ባልተደረሰበት፣ ምንም አይነት የአሰራር ክፍተት ባልታየበት እና የተቋሙን የአሰራር ሥርዓት ባልተከተለ ሁኔታ ከስራ እንዲታገድ በማለት የተፃፈው ደብዳቤ የምናወግዝ መሆኑን እየገለጽን በቀጣይ ዑለማዕ እና ቦርዱ መካከል ያለውን መጓተት በመተው የጋራና የተናጠል ኃላፊነታችንን እንድንወጣ የበኩላችንን ጥሪ እያቀረብን ይህን ድርጊት የፈፀሙ አካላት ከመሰል ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እናሳስባለን፡፡

15ኛ. ሙስሊሙ ህብረተሰብ ከመጅሊሳችን ጎን በመቆም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተጎዱ አካላትን በመደገፍ፤ በሞጣ ጥቃት ድጋፍ ማሰባሰብ፣ በአወሊያ መልሶ ማልማት በተካሄደ የገቢ ማሰባሰብ፣ እንዲሁም በሌሎች የልማት እንቅስቃሴዎች ላይ እያደረገ ላለው ተሳትፎ ያለንን ከፍተኛ ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን፡፡

16ኛ. በትግራይ ክልል የሚገኘው የነጃሺ መስጂድ ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሙስሊሙ ላይ ብቻ ሳይሆን በአገራችን ላይ የተቃጣ ጥቃት መሆኑን በመገንዘብ ጥቃቱን እያወገዝን ጉዳቱን ያደረሰው አካል ለህግ እንዲቀርብ እየጠየቅን መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ታሪካዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ጥገናው እንዲደረግ እንጠይቃለን::

17ኛ. በአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች በሠላማዊ ዜጎች ላይ ማንነትንና እምነትን መሰረት አድርጎ እየተፈጸመ ያለውን ጥቃት እናወግዛለን፡፡ በድርጊቱ ላይ የተሳታፉ አካላትም በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርቡ እየጠየቅን ህዝባችን ከምን ጊዜውም በላይ ለአብሮነት ቅድሚያ በመስጠት በሀገራዊ ግንባታ ላይ ንቁ ተሳትፎና ሚናውን አንዲወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

★ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አመራር ቦርድ እና የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የስራ አመራር ቦርድ ተወካዮች
★ ጥር 09 ቀን 2013
★ አዲስ አበባ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አመራር ቦርድ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የስራ አመራር ቦርድተወካዮች ጋር የተካሄደ አጠቃላይ ስብሰባ ላይ የተያዘ የአቋም መግለጫ

T.me/ahmedin99
አንዳንዶች አፍሪካ ኅብረት አጠገብ የሚሠራውን መስጊድ መቃወማቸው ብዙዎችን አስቆጥቷል። ለመሆኑ የተቃውሟቸው ትክክለኛ ምንጭ ምንድነው? ሐሳባቸውስ ምን ያክል ሚዛን ይደፋል? ከአ/አ መጅሊስ ም/ቦርድ ሰብሳቢ ኡስታዝ ሙሐመድ አባተ ጋር አውርቻለሁ!
.
ለበርካታ ሰው እንዲደርስ ላይክ እና ሼር በማድረግ ያግዙ... የምሠራው እንዲደርሳችሁ ቻነሉን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ የደወል ምልክቷን አብሩ!
.
https://www.youtube.com/watch?v=vdYpxAKbpVw&list=PLcjkEiF9HhE9JpVPrJ_AqU_k5cR5Yco1r&index=6 
.
#ነጃሺመስጊድ #አፍሪካኅብረት #የመስጊድችግር #መጅሊስ #ፌደራልመጅሊስ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC
የፌደራል መጅሊሱ ችግሮች ምንድናቸው? እንዴትስ ሊስተካከል ይችላል? በአ/አ መጅሊስ የቦርድ አመራርና የሕግ ክፍል የበላይ ጠባቂ መምህር ሱፍያን ዑስማን (Cush Land) ጋር ላይቭ ተወያይተናል! የተመልካች አስተያየትም ተቀብለናል!
.
https://www.youtube.com/watch?v=1bCOVYim5DE&list=PLcjkEiF9HhE9JpVPrJ_AqU_k5cR5Yco1r&index=7
.
ለበርካታ ሰው እንዲደርስ ላይክ እና ሼር በማድረግ ያግዙ... የምሠራው እንዲደርሳችሁ ቻነሉን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ የደወል ምልክቷን አብሩ!
.
#መጅሊስ #ፌደራልመጅሊስ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC
ከሥራ አመራር ቦርዱ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብቶ የቆየው ፌደራል መጅሊስ ችግሮች ምንድናቸው? መፍትሄውስ  ምንድነው? ቦርዱ ምን ለማድረግ ያስባል? የመጅሊስ የሥራ አመራር ቦርድ አባል ከሆኑት ኢ/ር አንዋር ሙስጠፋ ጋር ተወያይቻለሁ። የተመልካች አስተያየትም ተካትቷል!
.
https://www.youtube.com/watch?v=Rmc4el7hPIo&list=PLcjkEiF9HhE9JpVPrJ_AqU_k5cR5Yco1r&index=8
.
ለበርካታ ሰው እንዲደርስ ላይክ እና ሼር በማድረግ ያግዙ... የምሠራው እንዲደርሳችሁ ቻነሉን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ የደወል ምልክቷን አብሩ!
.
#መጅሊስ #ፌደራልመጅሊስ #የመጅሊስቦርድ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC
Forwarded from Nejashi Printing Press via @vote
ነጃሺ ማተሚያ ቤት ለአንባቢያን ይበልጥ ተደራሽ ለመሆን መርካቶ ካለው መጽሐፍ መደብር በተጨማሪ በአ/አ ለአንባቢያን ምቹ የሆነ ቦታ ላይ መደብር መክፈት ይፈልጋል፡፡ አዲሱ መደብር የት አካባቢ ቢሆን ለአብዛኛው ተጠቃሚ ምቹ ይሆናል የሚለውን ለመወሰን የደንበኞቻችንን ፍላጎት ማወቅ አስፈላጊ በመሆኑ ከታች ከተጠቀሱት አካባቢዎች ይበልጥ ምቹ የሆነውን በመምረጥ እንድትተባበሩን እንጠይቃለን፡፡
public poll

ቤተል – 4
👍👍👍👍👍👍👍 57%
@lawen7, @Ahbabu, @AbdellaS, Shehabudin

ፒያሳ – 2
👍👍👍👍 29%
@Endovsiky, @Emranium

ሜክሲኮ – 1
👍👍 14%
@DUJDEMMAHOM

ፍልውሃ
▫️ 0%

👥 7 people voted so far.
ዘላቂ ተቋም የመምስረት ህልሙ ስልጣን ላይ ባሉ ሰዎች አማካኝነት መክኗል።


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮችን በሽግግር ጊዜ በመምራትና ሰነዶችን በማስጸደቅ ኃላፊነትን አብረው በጋራ ኃላፊነት የተቀበሉት የ26ቱ ዑለሞችና 7 የቦርድ አባላት የጋራ ጠቅላላ ጉባኤ በተባበሩት ዐረብ ኢምሬት ተጠርተው በኢምሬትስ ሰዎች ዘንድ ካደረጉት አንድ ስብሰባ በቀር በ2 ዓመት ገደማ ጊዜ ዉስጥ አንድ ጊዜ ተሰብስበው አልመከሩም።ተቋሙ የሚመራበትን ዘላቂ መተዳደሪያ ደንቡም እስካሁን የለውም።

እንኳንስ የሀገሪቱን ግማሽ ህዝብ የሚመራ ተቋም ቀርቶ አንድ ተራ ድርጅት እንኳን ዓመታዊ እቅድ አውጥቶ በጠቅላላ ጉባኤ አስጸድቆና በጀት መድቦ ወደ ትግበራ ይገባል።ተግባሩንም በዓመት ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብስቦ ይገመግማል። ክትትል ያደርጋል። መጅሊስ ላይ ያሉት ደግሞ እንኳንስ ይህን ሊያደርጉ ቀርቶ ጠቅላላ ጉባኤው በተቋሙ ጉዳይ እንዳይመክር እንቅፋት የሆነ፣ ይባስ ብሎ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ይደረግ በሚል ከ26ቱ ዑለሞች አባላት መካከል ከፊሎቹ ተፈራርመው የጠየቁበትን ጥያቄ «አልቀበልም» ከባልደረቦቹ ዑለሞች ጋር መምከርን እምቢ ብሎ ከጠቅላይ ሚኒስተር እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር፣ ከደህንነት ቢሮ እስከ ሰላም ሚኒስተር፣ ከፖሊስ እስከ ጸጥታ ዘርፍ ጽ/ቤት፣ከብልጽግናው አቶ ብናልፍ አንዷለም እስከ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አገኘሁ ተሻገር፣ከአቡደቢ ሰዎች እስከ በአዲስ አበባ ለረብሻ ያዘጋጁዋቸው ጥቂት ወመኔዎች ጋር በመመላለስ «አደራ ተቀብለን የመጣንበትን የመጅሊስ ህገ ደንብ ጸድቆ ወደምርጫ ይገባ» እያለ በመወትወት እንቅልፍ የነሳቸውን የፌደራል መጅሊስ የሥራ አመራር ቦርዱን ለማስባረር «አግዙኝ»፣ «ቦርዱ የማይባረር ከሆነ በቃ እኔ ጥዬ እሄዳለሁ።» እያለ ምንም ሳያፍር በስራ በሌሎች ዑለሞች ፊት ጭምር በግልጽ በማስፈራራት ድጋፍ ለማግኘት ተግተው ቀጠሉ።

በተለያየ ስፍራ ህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለሚደርሰው ጥቃትና እንደሀገር በሚፈጠሩት ችግሮች እርስ በእርስ፣ከህዝቡና ከመንግስት በጋራ መክሮ መፍትሄ ፍለጋ ይተጋል ብለህ ስታስብ ከዚህ ይልቅ ከፊሉ «እንዴት የምርጫን ነገር አረሳስተን ያለምርጫ በመጅሊስ መሪነት በስፍራው እንቆይ?» ከሚል መነሻ ከፋፋይና ችግር ለመፍጠር ሲጥር ታየዋለሀ።

በሽግግር ጊዜ እንዲሰሩት የተሰጣቸውን በዘጠኙ ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ተረቆ የተሰጣቸውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብና የአንድነት ሰነድን በ6 ወራት ዉስጥ የማስጸደቅና በነርሱ አማካኝነት ምርጫ በማስደረግ በህዝቡ ፍላጎት አዳዲስ አመራሮችን አስመርጦ ለነርሱ የማስረከብ ጉዳይን ወደ ጎን ትተው ስልጣን የማደላደል ስራ ዉስጥ ገቡ። አሁን ደግሞ ይባስ ብለው «ለስድስት ወር የሚባልና የሽግግር መጅሊስ የሚባል ነገር የለም ቋሚ ነን።» ቋሚ ነን ብለው አረፉ።

የሚተጋ የመጅሊስ አመራር ወደ ስልጣን ሲወጣ የተቀበለውን አዲሱን የመጅሊስ መተዳደሪያ ደንብና የአንድነት ሰነድ የማስጸደቅና ሕዝቡ የሚጠብቀውን የመጅሊስን ምርጫ የማስደረግ አማና በራሱ ጊዜ ይወጣል ብሎ መጠበቅ ዘበት ሆኗል።አደራው በተሰጣቸው ሰዎች አማካኝነት ዘላቂና በህዝቡ ፍላጎት የሚመረጥ ተቋም የመመስረት ተስፋው መክኗል።

ችግሩ የሚያስከትለውን መዘዝ በጋራና በተናጠል ነግረህ ፣መክረህና አስመክረህ፣በትዕግስት ከጎን ቆመህ አግዘህና ጊዜ ሰጥተህ፣ ነገሮች በዉይይትና በሽምግልና ጭምር እንዲፈቱ ለወራት ተጥሮና ተደጋጋሚ እድል ተሰጥቷቸው፣ ሀገር በአጣብቂኛ ሁኔታና ዘርፈ ብዙ ፈተናዎች በተወጠረችበት በዚህ ጊዜ ጭምር በዚያው የጥፋት መንገድ ለመቀጠል የመረጠና አብሮ አደራ የተቀበላቸውን ዑለሞችና የቦርድ አባላትን አቤቶታ፣ልመናና ዉትወታ፣ የሽማግሌዎችን ልመና ከቁብ ሳይቆጥር ሁሉንም ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ህዝበ ሙስሊሙን ለሌላ ዙር ትግልና መስዋዕትነት ለመዳረግ «ከማን ተልዕኮ ተቀብሎ ይሁን?» ብለው ባልደረቦቻቸው ጭምር እስኪጠይቁ ድረስ የደረሰ አመራር ህገወጥ ከመባል ዉጭ ሌላ ስም የለውም።

ስንት ዋጋ የተከፈለበትን ጉዳይ መና ለማሰቀረት በዚያው ከቀጠሉና ስታከብራቸው በተከበሩበት ካልተገኙ ቀጥሎ ያለው ያንተ ጥፋት አይደለም። ስለሆነም የተቋሙ ባለቤት ህዝበ ሙስሊሙ ተቋሙ የርሱ እንጂ የጥቂት ግለሰቦች፣ ታግሎ ወጋ ከፍሎ ለዚህ ለውጥ መነሻ የሆነው በተቋሙ ላይ በነጻነት የሚፈልጋቸውን መሪዎችን በመምረጥና ለመገልገል እንጂ እንዲህ መቀለጃ እንዲደረግበት አይደለም። ለዓመታት ያ ሁሉ ዋጋ የከፈለንና በብዙ ተስፋና ትዕግስት እየጠበቀ ያለን ህዝብ መናቅ ለዉርደትና ዋጋ ለመክፈል ይዳርጋል።

ይህ ሁሉ ጊዜ በትዕግስት የጠበቅነው ወደ ቀልባቸው ተመልሰውና ተማክረው ከአንድ ቁም ነገር ይደርሳሉ ከሚል ተስፋም ነበር። አሁን ደግሞ ተቋሙ ላይ እንኳንስ ህዝብ የኔ ብሎ ሊወስንበት ቀርቶ በጊዜያዊነት ለሽግግር ጊዜ በኛ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ የጋራ(9ኙ) ኮሚቴ የተመረጡትን ሀገር በዉጥረት ላይ ባለችበት ሰዓት ነባራዊ ሁኔታን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በስፍራው የተቀመጡትን ዑለሞችና የቦርድ አባላት በማባረር ተቋሙን የማፈራረስ ተግባር ዉስጥ ሲገቡ ከዚህ በላይ በተስፋ መጠበቅና የዉስጥ ችግር አደባባይ እንዳይወጡ አፍኖ በመያዝ እውነቱን ከህዝብ መደበቅና ዝም ብሎ ማየት ይበቃል። አምና ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የተቀጠረው ዋና ስራ አስኪያጅ አብዱል አዚዝ አሎ በጥፋት ቡድኑ በተደረገበት ጫና ዛሬ ጠዋት የስራ መልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቷል።

የተቋሙ መሪ ከዚህ በፊት አብረው ከተመረጡት ዑለሞች መካከል አንደኛውን ዓሊም «ሁለተኛ በዚህ ግቢ እንዳላይህ» ብለው የተናገሩት ስህተት መሆኑን እንዳልተቀበሉ ዛሬ ደግሞ ለፖሊስ ደብዳቤ ጽፈው የፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ስላገድናቸው ወደ ተቋሙ እንዳይገቡ ቆማችሁ ጠብቁልን ሲሉ እስከመጠየቅ ደረሱ። በአደባባይ የዋህ መስለው በሴራ ግን በ2004 ህዝበ ሙስሊሙ የታገላቸውን የቀድሞ የመጅሊስ መሪዎችን ተንኮልና ሴራ በሚያስንቅ መልኩ ሴራውን ቀጥለዋል።በነዚህ ሰዎች ምክንያት ዘላቂ ተቋም የመምስረት ህልሙ መክኗል።

ይህን ያክል አብረዋቸው ያሉትን የ26 ዑለሞችን አባላትንና የቦርድ አባላትን፣የየክልል የእስልምና ጉዳዮችን፣ ብሎም ህዝበ ሙስሊሙን ንቀው በድፍረትና በስርዓት አልበኝነት እንዲህ እየሆኑ ያሉት ማን አይዟችሁ ብሏቸው ይሆን? ህዝበ ሙስሊም ሆይ! እውነቱን አውቀህ ስትፈልግ ለእምነት ነጻነትና ለተቋምህ ከዚህ በፊት ለዓመታት በጽናት ስታደርገው በነበረው አልያም በሌላ በአመንክበት መንገድ በአንድነት ታግለህ መብትህን ማስከበር ያንተ ምርጫ ነው።

ለዓመታት ህዝቡን ስበዘብዙ የነበሩ፣ሲያሳስሩና የሀሰት ምስክር ሆነው ሲመሰክሩ የነበሩ የመጅሊስ አባላት እርቅና ይቅርታ ይሻላል ተብለው በይቅርታ ሲታለፉ ከእንደገና ከስር ፎቶ ግራፋቸውን ከምትመለከቷቸው ጠበቃ ቃሲም ታጁዲንና የብሄረ ጽጌው መሀመድ ሲራጅ ከሚባሉት የመጅሊስ አባላት ጋር ገጥመው ዳግም ለሌላ የጥፋት ተግባር ሲነሱ፣በተሰጣቸው የይቅርታ እድል ስላተጠቀሙ የየክልል መጅሊሶች ከፍርሃታቸው ነፃ ወጥተው ህዝባቸውን ይቅርታ ጠይቀውና ከጎኑ በሚቆም መጅሊስን እስከ ታችኛው እርከን ድረስ ከቀድሞዎቹና የአሁኖቹን የጁንታውን ተላላኪዎች የሚያፀዱበት ብሎም ለህግ የሚያቀርቡበት ጊዜው አሁን ነው!
መጅሊሱን ለማስተካከል በሚያዝያ 23ቱ ጉባዔ አደራ ከተቀበሉት ዑለሞች አብዛኞቹ በዘዴ ተገፍተዋል። አሁን ላይ ዑለሞቹ ስለሁኔታው ምን ይላሉ? በዚህ የ"አብረን እንየው" ፕሮግራሜ ንግግራቸውን እያየን ስለአንድምታው እንወያያለን! የዋትሳፕ አስተያየትም አለን!
.
https://www.youtube.com/watch?v=jimpuRncm6E&list=PLcjkEiF9HhE9JpVPrJ_AqU_k5cR5Yco1r&index=9
.
ለበርካታ ሰው እንዲደርስ ላይክ እና ሼር በማድረግ ያግዙ... የምሠራው እንዲደርሳችሁ ቻነሉን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ የደወል ምልክቷን አብሩ!
.
#መጅሊስ #ፌደራልመጅሊስ #የመጅሊስቦርድ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC
ለሕዝበ ሙስሊሙ ያለው ንቀትና ሕገ ወጥነቱ ቀጥሏል።
Tuffannaa ummata Muslimaa fi seeraan alumaan itti fufeeera.


የስልጣን ጥማት ምን ያክል ወደ ጥፋት ጥግ እንደሚወስድ በአንዳንድ የፌደራል መጅሊስ ሰዎች ላይ በተግባር እያየን ነው። የተረቀቀው የመጅሊስ መተዳደሪያ ደንብ እንዳይጸድቅ እና የመጅሊስ ምርጫም እንዳይደረግ የሚሻው ይህ የጥፋት ቡድን በዘላቂነት መጅሊስን ተቆጣጥሮ ለመቆየት ሲል «የሽግግር ጊዜ ብሎ ነገር የለም» በሚል የህዝበ ሙስሊሙን አማና መብላቱ ይፋ አደረገ።

አሁን ደግሞ ከአይዞህ ባዮቹ አካላት በተሰጠ አቅጣጫ መሠረት «ቶሎ የመጣንበትን ዓላማ ፈጽመንና ምርጫ አስደርገን ስፍራውን ህዝብ ለመረጠው አካል አስረክበን እንሂድ» በተደጋጋሚ ሲሉ የነበሩትን የመጅሊስ የቦርድ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት «ሲታገዱ ህዝቡ በዝምታ ስላለፈን የሚያሰጋን ነገር የለም።ዓላማችንንና አካሄዳችንን የሚደግፉት አዳዲስ የቦርድ አባላትን መልምለን እንሾማለን።» በሚል እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

ከዚህ በፊት በ26ቱ ዑለሞች መካከል ያልተመረጡና በቀድሞ በህወሃት መራሽ መጅሊስ ዘመን የሀጅና ዑምራ ሊቀመንበር ሆኖ የቆየና በብዙ የሙስና ክስና ሁጃጆችን በማንገላታት ክስ የሚቀርብበትና የሚወቀስ ሼህ አህመድ የተባለን ሰው የሚቀርብበት የሙስና ዉንጀላ ክስ በሚገባ ኦዲት ከማስደረግና ክስ ከመመስረት ይልቅ በሰላም ሜኒስቴር ትዕዛዝ ወደ ፌደራል መጅሊስ የዑለማ ምክር ቤት መመደቡ ይታወሳል።ሰሞኑን ቦርዱን «አገድነው» ባሉት ህገወጥ ዉሳኔያቸው አንዱ ድምጽ ሰጪ ይህ ግለሰብ ነበር። ይኸው ለህዝበ ሙስሊሙ ያለው ንቀትና ሕገ ወጥነቱ ቀጥሏል።

✿✿✿✿✿
Tuffannaan ummata Muslimaa fi seeraan alumaan itti fufeeera.
❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆❆

Dheebonnaan taayita hagam akka nama gara badiitti akka geesu namoota majlisa feederaala tokko tokko irratti argaa jirra.

Seerri ittin bulmaata majliisa kan qophaahee itti kennamee mirkanaaheea akk hoji irra hin ollee fi filannoon majlisa akka hin taasifamnee kan fedhuufi taayitaa majlisaa feedaraalaa toowatee itti fufuuf jecha "Majlisa cee'umsaa kan jedhamu hin jiru" jechun amaana ummataa nyaachu ifa godhe.

Amma immo kallatti warra abshir jaraan jedhun boordi "Kaayyoo ittin as dhufneef xumurre, filannoo goosiifnee taayitaa qaama ummani filateetti kenninee ademnaa" jedhaa warra turan boordoota majlisa feedaraala yeroo jarri ari'aman ummani waan calliseef wanni nu sodaachisu hin jiru jechuudhaan "boordi kaayoo keenyyaan adeemuu fi kan nu fakkaatu haaraa tolfannaa" jedhani sochi jalqaban.

Ulamoota 26 kessaa heddu jara akka majlisa federaala hin dhihaannee yeroo godhamanu, ulamoota 26 kessaatti kan hin filatamnee nama Gaafa Majlisaa majlisa wayyaaneen hoganamu kessaatti itti gaafatamaa Hajji fi umraa kan turee fi malaamaltumaa fi midhaa ummata irratti geesisuun kan heddu himatamu nama sheh Ahmad jedhamu ajaja ministeera nagaatin gara mana mari ulamoota majlisa feedaraalaatti dabalamuun ni yaadatama. Silaa namicha kan irratti qoranno gagessani himannaa itti banuu malee seeraan alumaan majlisa kessatti mudu hin turre. Gidu kana boordi majlisaa fedaraala yeroo seeraan alaan ar'ine jedhanu warra sagalee kennan kessa nama tokko. Tuffannaa ummata Muslimaatif qabanuu fi seeraan alumaan itti fufeeera.
Forwarded from Zawya Tv
ውድ የዛውያ ቴሌቪዥን ተከታታዮች እና ቤተሰቦች ቀደም ሲል ባሳወቅነው መሰረት የዛውያ ቲቪ የፌስቡክ ገፅ በማይታወቁ አካላት ቁጥጥር ስር መሆኑን እና ምንም አይነት ነገር መለጠፍም ሆነ የተለቀቁትን አልባሌ ልጥፎች ለማጥፋት እንዳንችል የተደረግን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጉዳዩን ለማስተካከል ከፌስቡክ ድርጅት ጋር የተፃፃፍን ቢሆንም በተደጋጋሚ የተሰጠን ምላሽ የተሰረቀብንን የፌስቡክ ገፅ ባለቤትነት ማስመለስ እንደማንችል ያሳያል፡፡ በመሆኑም በዚህ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በተቋማዊ ጥያቄ ውስጥ ባለበትና ሀገራዊ ወሳኝ ኩነቶች ከፊት ለፊቱ በሚጠብቁት ጊዜ ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ተከታይ ያለውንና ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነውን የዛውያ ቴሌቪዥን የፌስቡክ ገፅ ማጣት የሚፈጥረውን ማህበረሰባዊ ክፍተት በማሰብ አዲስ ደህንነቱ የተጠበቀ የፌስቡክ ገፅ ለማስተዋወቅ ተገደናል፡፡

ትላንትም አሊፍ ብለን ስንነሳ ጀምሮ በአላህ እገዛ ለየትኛውም አጥፊና አምባገነን አካል እጅ ሳንሰጥ እዚህ ደርሰናልና ዛሬም ሰርተው መኖር ተወያይተው ሐሳብ መሸጥ በማይችሉ ሰነፎች ጉዞአችን በስንዝር አይገታም!

መላው ሙስሊም ማህበረሰብ ክስተቱን ከለሊቱ 7፡47 ካስተዋለ ጀምሮ በፍፁም ቀናነት እና የትብብር መንፈስ ከሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ጉዳዩን ለማተካከል ሲለፉ የነበሩ ወንድሞችን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ በዚሁ አንድነት እና ትብብራችንም የዛውያ ቲቪ የፌስቡክ ገፅን ወደነበረበት አቋም እንመልሰዋለን ብለን በአላህ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ሌሎች የሀገራችን ሙስሊም ሚድያዎችም ብዙ የደከማችሁበትና ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አንዱ መዳረሻ የሆኗችሁን የማህበራዊ ድህረ ገፆች ደህንነታቸው እንዲጠበቁ የሚረዷችሁን መንገዶች ከባለሙያዎች ጋር በመነጋገር ከመሰል ዝርፍያ ራሳችሁን እንድታድኑ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡
*
አዲስ የዛውየ ቲቪ የፌስቡክ ገፅ ሊንከን ከስር ያገኙታል!
https://www.facebook.com/%E1%8B%9B%E1%8B%8D%E1%8B%AB-%E1%89%B2%E1%89%AA-Zawya-TV-101376215334211

ዛውያ ቲቪ
ተግባራዊ ዳዕዋ!
ሙሉ ክፍያ የፈጸሙ 400 ሐጃጆች ሐጅ ሳይሄዱም እስካሁን ገንዘባቸው አልተመለሰላቸውም። ገንዘቡ ያለው የት ነው? ያልተመለሰላቸውስ ለምንድነው? ከሰዎቹ መጉላላት ጀርባ ማን አለ? ያለኝን መረጃ አካፍያለሁ! የእናንተንም አስተያየት በቴሌግራም ተቀብያለሁ!
.
https://www.youtube.com/watch?v=xqZTmUFNLAA&list=PLcjkEiF9HhE-blvGBAnZ5hUJvK_xC-V-d&index=10
.
ለበርካታ ሰው እንዲደርስ ላይክ እና ሼር በማድረግ ያግዙ... የምሠራው እንዲደርሳችሁ ቻነሉን ሰብስክራይብ አድርጋችሁ የደወል ምልክቷን አብሩ!
.
#40ሚሊዮኑ #ሐጅ #ሐጅ2011 #26ቱዑለሞች #መጅሊስ #ፌደራልመጅሊስ #የመጅሊስቦርድ #አዲስአበባመጅሊስ #እስልምናጉዳዮች #EIASC
እንኳን ደስ አላችሁ!
| *አስደሳች ዜና ለኢትዮጵያዊያን በሙሉ* |

¦ አፍሪካ አካዳሚ ¦

📲የትም ቦታ በመሆን ፕሮግራሙን ይተከታተሉ 🤗
💡አፍሪካ አካዳሚ ከአፍሪካ ቲቪ ጋር በመተባበር ልዩ ዲናዊ የርቀት ትምህርት ስልጠና

*"ኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት"*

በሚል ርዕስ ሥልጠና (6) ማዘጋጀቱን ሲያበስር በታላቅ ደስታ ነው🎉

ሁሉም ሙስሊም ማወቅ ያለበት
[ *ኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት*]

*በክቡር ሼኽ ሓሚድ ሙሳ*
የሚቀርብ

*ፕሮግራሙን ለየት የሚያደርጉ ነገሮች፡*
💸ያለ ምንም ክፍያ የነፃ ስልጠና!
📆የፕሮግራሙ ጊዜ ለ6️⃣ ቀናት ብቻ የሚቆይ ነው።

*አቀራረቡ*
🧭በየቀኑ ለ1 ሰዓት ብቻ የሚቀርብ ሲሆን፣

🧾ፕሮግራሙን ካጠናቀቁ ነፃ የምስክር ወረቀት ያገኛሉ።

በየቀኑ ትምህርቱን መረዳትዎን ለመገምገም ጥያቄዎች የሚቀርቡ ይሆናል።

📉🎥 ትምህርቶቹን በፈለጉት ጊዜ በቪዲዩ፣ በድምፅ እና በፅሁፍ PDF ሊከታተሉ ይችላሉ።

🟥ሥልጠናው የሚጀመርበት ቀን፡
*ቅዳሜ ረጀብ 22/ 1442 ሒጅሪ*
(March 6/ 2021 እ'ኤ'አ')
ይሆናል።

*የኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት ኮርስ መመዝገቢያ ቅፅ*፡
📎[http://bit.ly/3cBMfED]

ከተመዘገቡ ቡኋላ ወደ አፍሪካ አካዳሚ ሥልጠና ለመግባት ይህን የቴሌግራም ሊንኩን ይጫኑ፤📍
📎https://www.tgoop.com/Africa_Academy1

ጊዜዎን በዚህ ልዩ ፕሮግራም ያሳልፉ፣ በአሏህ ፍቃድ በጣም አንገብጋቢ እና በጣም አስፈላጊ ኢስላማዊ ቤተሰብ ህግጋት ተረድተው ይመረቁ።

ለሌሎችም እንዲደርስ የፕሮግራሙን ማስታወቂያ SHARE ያድርጉ🌹
2025/07/13 11:24:04
Back to Top
HTML Embed Code: