tgoop.com/Mgetem/4765
Last Update:
እመ አምላክ አደራ
@Mgetem
ከቤተመቅደስሽ ፣ከፊትሽ ስጠጋ
ምኞቴ እንዲሰምር፣ ሃሳቤ እንዲረጋ
በደሌም እንዲፋቅ ፣ነፍሴም እንዳትሰጋ ።
ይቅር በይኝ ድንግል ፣ሁሉንም ረስተሽ
የበደልኩሽንም፣ ኃጢያተንም ትተሽ
ነይ በይኝ እማምላክ ፣እጅሽን ዘርግተሽ ።
ከካቡ ስር ቁሜ፣ ከመቅደሱ ታዛ
በልጅሽ ፈጣሪ፣ በሕጉ ስገዛ ።
እማምላክ አደራ፣ ፀሎቴን አትርሽኝ
ጉድፈን አንሽልኝ፣ እምባየን አብሽልኝ
እራቁት ገላዬን፣ በረከት አልብሽኝ
ከቤት ውጥቻለሁ ፣ወደቤት መልሽኝ ።
እማምላክ አደራ
ሀጥያት ያረከሳት፣ ነፍሴ እንዳትፈራ
መጫወቻ እንዳትሆን፣ በዲያብሎስ ጭፍራ
እባክሽ መልሽኝ፣ ወደ አባቴ ስፍራ
ድንግል ሆይ አስታርቂኝ፣ ከፈጣሪ ጋራ ።
ስቆም ከመቅደሱ፣ ስጠጋ ከደጅሽ
እማምላክ ዳባብሽኝ ፣የፈጣሪን ገላ፣ በዳበሱት እጅሽ
ምሕረትን አሰጭኝ ፣ከልጅ ከወዳጅሽ።
ብላችሁ ለምኗት
ሁሉን ታሰጣለች፣ ሁላችሁ እመኗት
ፈጣሪም እናቱን፣ እምቢ እይላትም ቅንጣት
መቸም የማይሻር ፣ቃሉን ነው የሰጣት
እስቲ ማን ነበረ፣ ለምኖ ያፈረ
አድርግልኝ ብሎ ፣ስለቱ ያልሰመረ ።
ስለ እማምላክ በሉ፣ ምኑ ያሳፍራል ?
እንክዋን እኛ ቀርቶ፣ ሙሉ ገላ ያለን ፣ስለ ድንግል ብሎ፣ ድሃው ጠግቦ ያድራል ።
ስለ ልጅሽ ድንግል ፣አሁንም አትርሽኝ
እንደቃናው ድግስ ፣ጓዳዬን ጎብኝልኝ፣
እንደ አባ ጊዮርጊስ፣ ሰማያዊ ፅዋ፣ እውቀትን ለግሽኝ
ቤቴ ወና እንዳይሆን፣ በረከት አትንሽኝ ።
በፊት በኋላዬ ፣እናቴ አንቺ ምሪ
ኑሮዬንም አቅኚ ፣ሕይወቴን አስምሪ
መደገፊያ ምርኩዝ፣ ደግ አማላጃችን
በረከትን ስጭን፣ ባዶ ነው እጃችን
ድንግል አትራቂን ፣ኑሪ በደጃችን
ሰላም አድርጊልን ፣ህዝበ ክርስቲያኑን ፣ኢትዮጵያ ሀገራችን ።
ክፋትና በደል፣ ኃጢያትም ላለብን
እንደ በላዔሰብ ፣ጥላ ትጣልብን።
አሜን፫
____
https://www.tgoop.com/Mgetem
https://www.tgoop.com/Mgetem
https://www.tgoop.com/Mgetem
BY መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
Share with your friend now:
tgoop.com/Mgetem/4765