tgoop.com/Mgetem/4769
Create:
Last Update:
Last Update:
ለፃድቃን ከጻፍኳቸው የመዝሙር ግጥሞች በብዙ ቁጥር በመመዝገብ የአቡዬ ሥራዎች ግንባር ቀደሙ ነው። ወደ 10 አይጠጉም ብላችሁ ነው? ስላሳደጉኝ ነው መሰል ለአቡየ አደላለሁ። እሳቸው እሳቸውንም የጠየቅኋቸውን ሲሰሙ አይጣል ነው። በተለይ እሄዳለሁ ብዬ ባላሰብኩበት ሁኔታ መካነ መቃብራቸው ምድረ ከብድ ዕለተ እረፍታቸውን እዚያ እንዳከብር በአንዳች ተአምራዊ መንጀድ እንድሄድ ባደረጉበት 2015 እና 2016 የሚታይና የሚዳሰስ ተአምራትና ድንቅ በሕይወቴ ሲያደርጉ ነበር ብዬ እመሰክራለሁ። የፃድቁንም ሆነ ለሌሎች ቅዱሳን የተጻፉ ሙሉ ሥራዎቼን የ"እዩት" የመዝሙር ግጥም መድብል ቅጽ ሁለት የሆነው "ጉባኤያችን ማርያም" መጽሐፍ የፍልሰታ ሰሞን ሲወጣ አስነብባችኋለሁ። ለዕለተ ቀኑ ፣ ለበረከት ከዘማሪት ሕይወት ወልዴ ጋር አምና የሠራነውን ቆንጆ ሥራ ጋበዝኳችሁ።
ዝክረ ፃድቅ ለዓለም ይሄሉ!
https://youtu.be/YXEbsNVBKN0?si=w9is8WAEhdDH32eQ
BY መንፈሳዊ ግጥም ብቻ

Share with your friend now:
tgoop.com/Mgetem/4769