tgoop.com/Mgetem/4775
Last Update:
#ውሸት_እናተንኮል
@Mgetem
ውሸትና ተንኮል ፣ ጓደኞች ነበሩ ፣
እውነትን ለማጥፋት ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
እውነት የተባለው ፣ ይሄ ጠላታችን ፣
መጥፋት አለበት ፣ ጭራሽ ከዓለማችን ።
እኛ እየተጠላን ፣ እሱ እየተወደደ ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ ፣ ዘመንም ነጎደ ።
የኛ ብቻ ይሁን ፣ መላው ሀገር ምድሩ ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ፣ ተንኮል እያደባ ፣
ከውሸት ጋር ሆኖ ፣ ከእውነት ቤት ገባ ።
እውነት ከጓደኞቹ ፣ ሠላምና ፍቅር ፣
በደስታ በሀሴት ፣ ይጫወቱ ነበር ።
ተንኮልም በድንገት ፣ እውነትን ተማታ ፣
ፍቅርም አዘነ ፣ ሠላምም ተቆጣ ።
ውሸት ብቅ አለና ፣ ከተደበቀበት ፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ ፣ እውነትን ገደሉት ።
ሠላምና ፍቅር ፣ እጅግ እያዘኑ ፣
እንቅበረው ዘንድ ፣ ስጡን አስከሬኑን ።
ብለው ተማጸኑ ፣ ውሸትን በእምባ ፣
እውነት ተቀበረ ከመቃብር ገባ ።
ዓለምን የመግዛት ፣ ብርቱ ዓላማችው ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ ሞላ የልባቸው ።
አንድ ቀን ፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት ፣
የሰፈሩን ሰዎች ፣ ደስታ ሲመለከት ።
ተጠራጠረና ፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ ፣
ልክ እንደደረሰ ፣ በጣም ደነገጠ ።
እውነት ተፈልጎ ፣ መቃብሩ ሲታይ ፣
ምንም ነገር የለም ፣ አንዳችም የሚታይ ።
አወይ ልፋታችን ፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ ፣
እውነት ከቶ አልሞተም ፣ ዓርጎ ነው ሰማይ ።
እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው ✔
https://www.tgoop.com/Mgetem
https://www.tgoop.com/Mgetem
https://www.tgoop.com/Mgetem
BY መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
Share with your friend now:
tgoop.com/Mgetem/4775