tgoop.com/MizanInstituteOfTechnology/312
Last Update:
የዱቤ አገልግሎታችንን በተመለከተ ማብራሪያ:
ለምሳሌ እኛ ጋ የምትወስዱት ኮርስ ወርሃዊ ክፍያው 4 ሺ ብር ከሆነ እና ኮርሱ የሚፈጀው ጊዜ 3 ወር ከሆነ አጠቃላይ ኮርሱን ለማጠናቀቅ 12 ሺ ብር ያስፈልጋል:: ይህን ብር ወደማንኛውም ዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ በማቅናት የመንግስት ሠራተኛ ወይንም የባንክ ሰራተኛ ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ወይንም የአየር መንገድ ሰራተኛ የሆነን ሰው ተያዥ ይዛችሁ በመሄድ ሙሉውን ይከፍሉላችሗል:: ወይም ለራሳችሁ ደመወዛችሁን በዳሽን ባንክ የሚከፍል ተቋም ተቀጣሪ ሰራተኛ ከሆናቹህ ተያዥ አያስፈልጋችሁም:: እናንተ ይህንን ገንዘብ በ3 ወራት ውስጥ ለኛ ከመክፈል በ6 ወይም በ12 ወራት ውስጥ በየወሩ ትከፍሏቸዋላችሁ:: ነገር ግን ለ3 ወር ከሆነ ያበደሯችሁ 2.5%፣ ለ6 ወር ከሆነ 4%፣ ለ12 ወር ከሆነ 8% የአገልግለለት ክፍያ ያስጨምሯችሗል:: ይህ ወለድ ሳይሆን የአገልገሎት ክፍያ ነው:: ይህም በየወሩ 1 ሺ ብር እና 8% ጭማሪ (80 ብር) በድምሩ በየወሩ 1,080 ብር እየከፈላችሁ በ12 ወራት ውስጥ ታጠናቅቃላችሁ:: በየወሩ ለነርሱ መክፈል የምትጀምሩት አገልግሎቱን በሰጧችሁ ከ1 ወር ቡሃላ ነው:: በ12 ወሩ መጨረሻ 12,960 ብር ትከፍላላችሁ:: ይህም በአመት 960 ብር ብቻ ጭማሪ ለአገልግሎት ከፈላችሁ:: ይህ ደግሞ በትክክል ከተማራችሁ የ3 ወር ኮርሱን እንዳጠናቀቃችሁ በ15 ሺህ ብር ደመወዝ ብትቀጠሩ ወይም የ30 ሺ ብር ፕሮጀክት ብትሰሩ መዝጋት ትችላላቹህ::
ዳሽን ባንክ ከመጠየቃችሁ በፊት የምትማሩት ኮርስ ምን እንደሆነ አውቆ መምረጥ፣ የጊዜና የክፍያ መጠኑን ማወቅ ይቀድማል:: የምታናግሩት የዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ ካልተረዳችሁ ለራሳቸው ሰው 0910267170 ዳዊት ዮሐንስ ብላችሁ ደውሉና አገናኟቸው:: አድስ አበባ ያላችሁ ቤተል ሰፈረ ኢዮር ቅርንጫፍ ብትመጡ ያለ ተጨማሪ ማብራሪያ ያስተናግዷችሗል::
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጋችሁ በውስጥ ጠይቁን:: ስንመልስ የምንዘገይባችሁ ከይቅርታ ጋር ታገሱን::
BY Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹

Share with your friend now:
tgoop.com/MizanInstituteOfTechnology/312