tgoop.com/MizanInstituteOfTechnology/382
Last Update:
ሰሪወችንና ተስተናጋጁን መሃል ላይ ሆነው ያገናኙት አስተናጋጆች፤ ፍሮንትኢንድንና ባክኢንድን እንደሚያግባባው እንደ API ናቸው። ተጠቃሚው ድረ-ገጽ ላይ "ግባ" የሚለውን በተን ሲጫን፣ Front-End ያንን ጥያቄ በኤፒአይ በኩል ወደ Back-End ይልካል። Back-End መረጃውን አጣርቶ መልሱን በኤፒአይ በኩል ወደ Front-End ይመልሳል።
ልክ አንድን ህንፃ ከመሰረቱ እስከ ጣሪያው ድረስ እንደሚገነባ መሃንዲስ ነው። የድረ-ገጹን ፊት ለፊት (Front-End)፣ ጀርባ (Back-End)፣ እና የመረጃ ቋት (Database) የመስራት ችሎታ አለው። ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ ማስተዳደር ይችላል።
ከላይ አንድ ፉል ስታክ የሚባል ድረ ገፅ ሲሰራ Front-end, Back-end & Database አለው ብለናል። Front-endን ለመስራት ብዙ አማራጮች እንዳሉና ብዙ ፍሬምወርኮች መኖራቸውን ተነጋግረናል። Back-endንም፣ ደታቤዝንም ለመስራት ብዙ አማራጭ እንዳሉ አይተናል።
ስለዚህ ሁሉንም እነዚህን ያሟላ ድረ ገፅ ሲገነባ Front-end ላይ ካሉ አማራጮች እነማንን ይዞ፣ Back-end ላይ ካሉ አማራጮችም እነማንን ይዞ፣ ከደታቤዝም እነማንን ይዞ ማንን ከማን በማጣመር አንድ የተሟላ full stack ድረ ገፅ ያበለፅጋል የሚለውን እንመልከት።
ከላይ እንደተጠቀሰው MERN እና MEAN ብቻ አይደሉም:
ለFront-end የምንጠቀመው Reactን፣ ለBack-end የምንጠቀመው Express.jsን በNode.js፣ ለደታቤዝ የምንጠቀመው MongoDBን ነው።
ሁሉም ቴክኖሎጂዎች (MongoDB, Express.js, React.js, Node.js) JavaScriptን ስለሚጠቀሙ፤ አንድ ቋንቋ ብቻ መማር በቂ ነው። ይህም ሂደቱን በጣም ቀላል እና ፈጣን ያደርገዋል። ጃቫስክሪፕትን ካወቅን ለፍሮንት ኢንድም፣ ለባክኢንድም፣ ለደታቤዝም የምንጠቀማቸው አማራጮች እንደ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ መስታቸው አንድ ስለሆነ ሌላ አድስ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ሲንታክስና ሴማንቲክስ ማወቅ አይጠበቅብንም።
React.js የፌስቡክ ኩባንያ ያበረከተው በጣም ፈጣን እና ዘመናዊ የፊት ለፊት (Front-End) ቴክኖሎጂ ነው። ድረ-ገጾችን እና መተግበሪያዎችን በሚገርም ፍጥነት እንዲሰሩ ያደርጋል።
MongoDB በቀላሉ የሚለዋወጥ (Dynamic የሆነ)የመረጃ ቋት (Database) ነው። አዳዲስ መረጃዎችን በቀላሉ ለማስተናገድ ያስችላል።
በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ያሉ ብዙ ታላላቅ ኩባንያዎች MERN Stackን ይጠቀማሉ። ይህም ማለት የስራ እድሉ በጣም ሰፊ ነው።
MERN ስታክ በአሁኑ ጊዜ በድረ-ገጽ ልማት አለም ውስጥ ካሉት በጣም ዘመናዊ እና ተፈላጊ ቴክኖሎጂዎች አንዱ ነው። ካሉት ፍልስታክን የመስራት አማራጮች በአለም ላይ ግንባር ቀድም የሆነው ይህ መንገድ ነው።
በMizan Institute of Technology (MiT) የፉል ስታክ (MERN) ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች (በዝርዝር):
እነዚህን ስናስተምር HTML ውስጥ ከጀማሪ እስከ አድቫንስድ የሚባሉትን ጭምር እንዳስሳለን። CSS ላይ ለresponsive ድረ ገፅ ያግዘንና ስራችንን ያፋጥንልን ዘንድ ካሉ የ CSS ፍሬምወርኮች ቀዳሚ የሆኑትን Tailwindን እና Bootstrapን እናያለን።
ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር፡ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን አስደግፈን ለእያንዳንዱ ርእስ እንሰጣለን። (Capstone Projects)!
በMiT ስልጠናችን፣ በንድፈ ሃሳብ ብቻ አንወሰንም። የተማራችሁትን በተግባር የምትፈትሹበት፣ እውነተኛ ድረ-ገጾችን እና መተግበሪያዎችን የምትሰሩበት እድል ይኖራችኋል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች (Capstone Projects) መካከል፡