tgoop.com/NatnaelMekonnen21/44266
Create:
Last Update:
Last Update:
ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ ዐቅም አሳድጋለች- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎም ወደውጭ የመላክ አቅም ማሳደጓን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሆሚቾ ጥይት ፋብሪካን በጎበኙበት ወቅት፤ ኢትዮጵያ እንደ ታላቅ ሀገር ራስን የመቻል ጉዞዋን በማጠናከር ስሉጥ የሆነ የትውልድ ቅብብሎሽ ማረጋገጥ እንደሚገባት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ጥይቶችን የማምረት ሙከራዎች ብታደርግም፤ እስከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ድረስ ከውጭ በማስገባት ላይ ተመስርታ መቆየቷን አንስተዋል፡፡
አሁን ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ተተኳሽ ከማምረት አልፎ ወደውጭ የመላክ አቅም አሳድጋለች ብለዋል ።
ይህ ርምጃ በምሉዕነት የተገነባ እና በሚገባ የታጠቀ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከማረጋገጥ አንፃር አበረታች ሥራ ስለመሆኑ ጠቅሰዋል፡፡
ከመከላከያ ግብዓቶች ባሻገር ሀገር የራሷን ምግብ ፣ መድኃኒት እና አልባሳት በበቂ ሁኔታ በማምረት እውነተኛ በራስ ምርት መተማመንን ማረጋገጥ እንደሚገባትም ነው ያስገነዘቡት፡፡
BY Natnael Mekonnen

Share with your friend now:
tgoop.com/NatnaelMekonnen21/44266