NEJASHIPP Telegram 822
የሐጅ ዚክሮች

ከኢማም አን-ነወዊ አል-አዝካር መጽሐፍ የተወሰደ
ትርጉም - ሙሐመድ ሰዒድ (ABX)
*******
የሐጅ ዚክሮችና ዱዓኦች እጅግ በጣም ብዙ ናቸው፡፡ ነገር ግን እዚህ ላይ በዋናነት እጅግ አስፈላጊዎቹንና የተደነገጉበትን ዋና ዓላማ ለማየት እንሞክራለን፡፡ ዚክሮቹን በሁለት መልኩ መመልከት እንችላለን፡፡ ወደ ሐጅ በሚደረግ ጉዞ ላይ የሚደረጉ ዚክሮች እና በሐጅ ሥራ ላይ የሚደረጉ ናቸው፡፡
 
አንድ ሰው ለሐጅ ኢሕራም በሚፈልግበት ጊዜ ገላውን ታጥቦ ዉዱእ በማድረግ ሽርጡንና ኩታውን መልበስ ይኖርበታል፡፡ ዉዱእ የሚያደርግና ገላውን የሚታጠብ ሰው የሚላቸውን ዚክሮች ማለትም ይኖርበታል፡፡ ከዚያም ሁለት ረከዐህ ይሰግዳል፡፡ የሶላት ዚክሮችንም ያደርጋል፡፡ በመጀመሪያው ረከዐህ ከፋቲሓ በኋላ ‹ቁል ያ አዩሀ-ልካፍሩን›ን በሁለተኛው ‹ቁል ሁወሏሁ አሐድ›ን ቢያነብ ይወደዳል፡፡ ሶላቱን ባጠናቀቀ ጊዜም በፈለገው ነገር ዱዓእ ማድረግ ይወደዳል፡፡ ከሶላት በኋላ የሚደረጉ አጠቃላይ የሆኑ ዚክሮችና ዱዓኦችንም ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ለሐጅ ኢሕራም የፈለገ እንደሆነ በቀልቡ ይነይታል፡፡ በምላሱ ቀልቡን ቢያግዝ ደግሞ ይወደድለታል፡፡ ‹ሐጅን ነይቼ ለሀያሉና የተከበረው አላህ ብዬ ኢሕራም አድርጌያለሁ፡፡ ለበይከ አልላሁምመ ለበይከ /አላህ ሆይ! ጥሪህን ተቀብዬ እዚህ ተገኝቻለሁ  …. እስከ ተልቢያው መጨረሻ ይላል፡፡ በቀልብ ኒያ /ውስጥ ሀሳብ/ ማድረጉ ግዴታ  ነው፡፡ መናገሩ ግን ሱንና ነው፡፡ በልብ ላይ ብቻ ቢወሰንም በቂ ነው፡፡ በምላስ ላይ ብቻ መወሰን ግን አይበቃም፡፡ አል-ኢማም አቡልፈትሕ ሱለይም ኢብኑ አዩብ አርራዚይ ‹አልላሁምመ ለከ አሕረመ ነፍሲ፣ ወሸዕሪ፣ ወበሸሪ፣ ወለሕሚ፣ ወደሚ፡፡› ቢል መልካም ነው፡፡›› ብለዋል፡፡
ትርጉሙ -አላህ ሆይ! ላንተ ነፍሴ፣ ፀጉሬን፣ ሰውነቴ፣ ሥጋዬ፣ ደሜ ላንተ ኢሕራም አድርዋል፡፡  
ሌሎች ደግሞ ‹አልላሁምመ ኢንኒ ነወይቱ-ልሐጀ ፈአዒንኒ ዐለይህ ወተቀብበልሁ ሚንኒ፡፡› / አላህ ሆይ! እኔ ሐጅን አስቤያለሁ፡፡ እርዳኝ፡፡ ተቀበለኝም፡፡/ ማለት ይኖርበታል፡፡› ያሉም አሉ፡፡
 ከዚያም ‹ለበይከ-ልላሁምመ ለበይከ፤ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይከ፤ ኢንነ-ልሐምደ ወንነዕመተ ለከ ወልሙልኩ ላ ሸሪከ ለከ፡፡› ይላል፡፡
ትርጉሙ -/አላህ ሆይ! ጥሪህን ተቀብዬ እዚህ ተገኝቻለሁ፡፡ ጥሪህን ተቀብዬ እዚህ ተገኝቻለሁ፡፡ አጋር የለህም፡፡ ጥሪህን ተቀብዬ እዚህ ተገኝቻለሁ፡፡ ምስጋና፣ ጸጋ፣ ንግስና ላንተ ነው፡፡ አጋር የለህም፡፡/
ተልቢያ ሱንና ነው፡፡ ቢተው ሐጁም ሆነ ዑምራው ትክክል ነው፡፡ ምንም ማካካሻ አይጠበቅበትም፡፡ ነገር ግን ትልቅ ትሩፋት እና የአላህን መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) መንገድ መከተል ነው ያመለጠው፡፡ አንዳንድ ወዳጆቻችን ግዴታ ነው በማለት ለሐጅ ትክክለኛነትም እንደ መስፈርት አድርገው ቢያቀርቡም የኛም ሆነ አብዛኞቹ ዑለሞች አቋም የመጀመሪያው (ሱንና የሚለው) ነው፡፡ ለሁሉም ከልዩነት ለመውጣትና የአላህን መልእክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) መንገድ ለመከተል ሲባል መጠንቀቁ ተገቢ ነው፡፡ አላህ እጅግ አዋቂ ነው፡፡
  አንድ ሰው ለሌላ ሰው ኢሕራም ማድረግ ቢፈልግ ‹ሐጅ ነይቼ የልእልና ባለቤት ለሆነው አላህ ለእገሌ ብዬ ኢሕራም አድርጌያለሁ፡፡ አላህ ሆይ! ለእገሌ ለበይክ... በማለት ለራሱ የሚላቸውን ነገሮች በሱ ሥም ማለት ይኖርበታል፡፡
 
ይቀጥላል ….

https://www.tgoop.com/NejashiPP

https://bit.ly/3r4948i

tgoop.com/NejashiPP/822
Create:
Last Update:

BY Nejashi Printing Press

Share with your friend now:
tgoop.com/NejashiPP/822

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

With Bitcoin down 30% in the past week, some crypto traders have taken to Telegram to “voice” their feelings. Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp. For crypto enthusiasts, there was the “gm” app, a self-described “meme app” which only allowed users to greet each other with “gm,” or “good morning,” a common acronym thrown around on Crypto Twitter and Discord. But the gm app was shut down back in September after a hacker reportedly gained access to user data. best-secure-messaging-apps-shutterstock-1892950018.jpg Although some crypto traders have moved toward screaming as a coping mechanism, several mental health experts call this therapy a pseudoscience. The crypto community finds its way to engage in one or the other way and share its feelings with other fellow members.
from us

Telegram Nejashi Printing Press
FROM American