tgoop.com/Nuensak/1960
Last Update:
ገፅ:- ፩
አርብ:- ሰው የተፈጠረበት ቀን፡፡
(ዘወትር አርብ ምሽት)
--------/////---------
ሰው አንድም ዛሬ
አንድም ነገ
አንድም ትናንት፡፡
አንድም አሁን በአካል
አንድም ነገ በተስፋ
አንድም ትናንት በትዝታ፡፡
"ትዝታህን ውሰድ ብለሽ የላክሽብኝ
አንቺው ጋር ይቀመጥ እኔም ያንቺ አለብኝ፡፡"
የትዝታ ባሪያዎች ነን፡፡ እወቀታችንም እምነታችንም ምን ቢገዝፍም የትዝታ ባሪያዎች ነን፡፡ በሳይኮሎጅስቶች ነገህን አስብ ትናንት አልፏል ብንባልም፡፡ ሰው የትዝታው ባሪያ ነው፡፡
በጊዜ ብዛት የስሜቱ መጠን ይቀንስ ወይ ይጨምር ይሆናል እንጂ፡፡ መርሳት አይቻለንም፡፡ እንርሳ ብለን ስንሟገት በዛው ቅፅበት ነገሩን እያሰብነው ነው፡፡ ይሄንን ፅሁፍ እንኳን እያነበብን ወደ ብዙ ትዝታ ተስበናል፡፡ በልብ የተኖረ በጭንቅላት መቀመጡ አይቀሬ ነው፡፡ ትዝታን ጠላቴ ብሎ መጥራት ራስን መካድ ነው፡፡ ለተኖረው ትናንት ራስን ማመስገን ትልቅነት ነው፡፡ ክፉም ይሁን በጎ፡፡
የብዙ የአእምሮ በሽታ ተጠቂዎች ፍላጎት ወደትዝታ ተመልሶ ማን እንደነበሩ ማስታወስ ሲሆን የብዙ ጤነኞች ፍላጎት ደሞ ማን እንደነበሩ መርሳት ነው፡፡ ያሳለፍነው ለመርሳት የምንታገለው የሆነውን ማመን መቀበል ስለማንፈልግ ነው፡፡ የትናንት የፍቅር ትዝታችንን ለማጥፋት የምንጥረው የፍቅር ወዳጃችን ስለጠፋ ነው፡፡ ከፍቅረኛ ስንለያይ ከትዝታ ጋር መኖር የጀመርን ይመስለናል፡፡ ግን ትዝታው መጀመሪያም ተቀመጦ ነበር፡፡ለማሰብ እንችል ዘንድ ግን አልቻልንም፡፡ ምክንያቱም የትዝታችን ባለቤት አጠገባችን ነበርና፡፡ ስንለያይ ግን የኖረንው ሁሉ መታሰብ ይጀምረናል፡፡
ትዝታ ህመም አይደለም፡፡ ትዝታ መርገም አይደለም፡፡ ትዝታ ከሰው በተለየን ጊዜ ሰውየውን እኛ ጋር የሚያስቀርልን ከሷ በተለየን ጊዜ እሷን እኛ ጋር የሚያስቀርልን በረከት ነው፡፡
* * * * * * * * * *
BY ኑ እንሳቅ😂😂😂
Share with your friend now:
tgoop.com/Nuensak/1960