tgoop.com/Nuensak/1973
Last Update:
እናቴ
"ፌስቡክ ክፈትልኝ"
ደገጥኩ ፡፡ የቀልዷን ቢሆንም ቢሆንም ክው አልኩ፡፡ "ለምንሽ?" ልላት ነበር ተውኩት፡፡
እናቴ ፌስቡክ የላትም!!! ስለዚህ ምርጥ እናት አለኝ፡፡
፡
በውስጤ ስንቱን አወጣሁ አወረድሁ....
:
ታድለሻል አንቺስ ባለሽበት አለሽ፡፡
በነበርሽበት፡፡ ሽበት ጨመርሽ እንጂ፡፡ ንቀት አልጨመርሽም፡፡ ታድለሻል፡፡
፡
፡
የእናትነት በረከት ስለልጇ ምንም መረጃ አለመስማቷ መሰለኝ፡፡ ዘላለም የፍቅር ሀውልቷን የሚንድባት ምንም ነገር አታውቅም፡፡
፡
፡
ከሰው
ከሴት
ከመጠጥ ቤት ዳታ የላትም ስለልጇ፡፡ ምን እንደተባለ ምን እንደሚባል አታውቅም፡፡
፡
፡
እናቴ ፌስቡክ የላትም!!!
ያው ነች ለልጇ እንደነበረችው፡፡ እንደስላሴ ቁጥር፡፡ አልጨመረችም አልቀነሰችም፡፡
፡
የልጇን ጉድ የስሙን ብዛት እንደመልዕክት ዩሀንስ ቃላት አንዴ የሚጣል አንዴ የሚነሳ ልጅ እንዳላት አታውቅም፡፡ ታድላ!!!
፡
"ይቅርብሽ አልኳት" በደፈናው፡፡
:
ካህን ከነታቦቱ የሚታማበት ሰፈር ነው ፌስቡክ
አልኳት::
ገጣሚ ከነውርደት አጋጣሚው የሚዘረገፍበት
ማርያም ከነልጇ የምትሰደብበት
አንዳንዱ "እናትህ እንዲህ ትሁን" ብሎ ለእናት ያለውን ክብር የሚያስረዳበት ..የሚከራከርበት፡፡
ጁመዓ ከነሼኹ የሚዋረድበት
ጠቅላይ ሚንስትሩ ተከታይ ለማፍራት ከሀበሻ ሜም ጋር የሚፎካከሩበት
በሰባት ሥላሴ ናቸው ብሎ ሰባት ላይክ ለማግኘት ሰባቴ ጥቅስ የሚለጥፍ ሰው የሞላበት
ባለዜና
ባለዜማ
ባለሀገር
ባለሸገር
ባለ በሌለ ነገር ሁሉ የሚዘባረቅበት...
ኢንተርኔት አይደለም አምፖል ለሌላቸው ገበሬዎች በኢንተርኔት ትግል የሚካሄድበት የሆነ ነገር ነው ፌስቡክ፡፡
" ይቅርብሽ " አልኳት በደፈናው፡፡
፡
፡
፡
እናቴ ፌስቡክ የላትም!!! ስለዚህ እናት አለኝ፡፡
BY ኑ እንሳቅ😂😂😂
Share with your friend now:
tgoop.com/Nuensak/1973