tgoop.com/Nuensak/1985
Last Update:
"ለኢትዮጵያ ካለን ምኞት እንጂ ከኢትዮጵያ ፍቅር የለንም"
የዚህ ዘመን አባል እንደመሆኔ መጠን የሀገር ፍቅር የተባለውን ስሜት ሀገር ይቅር ወደሚባል ስሜት የሚያሻግረኝ ነገር እልፍ ነው፡፡
ልጅነቴን
ወጣትነቴን
ወድቄ የኖርኩባት ሀገር እርጅናዬን አምኜ አልሰጣትም፡፡
"ሀገርና መንግሥት ለየቀል ነው"
ይልሀል ግራ የገባው 'ምሁር'፡፡ ልደታችንም መቃብራችንም ከቤተመንገሥት አይደለምን?
ታሪክ ዛሬን እንደዚህ ከመሆን አላደነንምና ፉርሽ ነን፡፡
ደክሞናል ሰለኢትዮጵያ ማሰብ፡፡ ለሀገር ምኞት እንጂ ፍቅር የለንም፡፡ የምንመኛት ኢትዮጵያን እናፈቅራለን እንጂ ያሁኗንማ እያየናት አይደለ?
ድሮ ድሮ ....
ቲያትር ትምህርት ቤት ላይ እያለን ክብ እንሰራና 'ቮካል' እንሰራለን፡፡
አንዱ መሃል ይገባና "እሰይ" ሲል ክብ የሰራነው ደግሞ "እንኳን" እንላለን፡፡ እሱ ገልብጦ "እንኳን" ሲል እኛ ተገልብጠን "እሰይ" እንላለን፡፡
"ተገልብጠን"ን ያዙልኝ፡፡
አሁን እንደሀገር እዛ ላይ ነን፡፡
"እሰይ" እና "እንኳን" ምን ልዩነት አለው? ብቻ የተቃረንን መስሎን እሱኑ እንደግማለን፡፡
ደርግ "እሰይ" ሲል ኢህአዴግ "እንኳን" ልላል፡፡ ኢህአዴግ እንኳን ሲል ብልፅግና እሰይ ይላል፡፡
አማራ እንኳን ሲል ኦሮሞ .....
ሙስሊም እሰይ ሲል ክርስቲያን ....
ራሱኑ በራሱን የምንደግም ነን፡፡ ያውም ሳናፍር፡፡ ነገሩ በቤታችንም ገብቷል፡፡ በቤታችንም ዘልቋል፡፡ እሰይ ከእንኳን አይሻልም፡፡ ግን እንለዋለን፡፡ በኛ ቤት የተለየ ማለታችን መሆኑ ነው፡፡ የተባለ ነው ደጋግመን የምንለው፡፡ እውነት የምትወደድ ሀገር አለችንስ?
"እንኳን"
"እሰይ"
BY ኑ እንሳቅ😂😂😂
Share with your friend now:
tgoop.com/Nuensak/1985