tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3041
Last Update:
አሏህን መች እናስታውስ?
.
.
.
አብዛህኛዎቻችን አሏህን የምናስታውሰው የችግራችን ጊዜ ነው። አሏህን ጠይቄው ሰማኝ፣ በአሏህ ተመክቼ ዳንኩኝ፣ ጠይቄው ሰጠኝ፣ በሱ ተጠብቄ ጠበቀኝ። እንል እንደሆነ እንጂ በተሰጠን ነገር ከማመስገን ባሻገር የሰጠንን ነገር እንዲያዘልቅልን ዱዓ የምናደርገው ጥቂቶች ነን። አብዛህኛው አይደለም ሀጃ ሳይኖረው ዱዓ ሊያደርግ ቀርቶ ለተቸረው ውለታ ምስጋና ማድረሱንም እንጃ! ለዚህም ይመስላል በችግር ሰዓት መፈናፈኛ እስኪታጣ ድረስ በባለ ጉዳዮች የተጨናነቁት መሳጅዶች በአማን ጊዜ ጭር ማለታቸው። አብዛህኛዎቻችን አሏህን ባጣ ቆየኝ አድርገነዋልና!
ዱዓ ልታደርጉ አስባችሁ ምን ብላችሁ ዱዓ ማድረግ እንዳለባችሁ ጠፍቶባችሁ አያውቅም? ምክኒያቱም ዱዓ ሁለት አይነት እንደሆነ አናውቅማ! አዎ! ዱዓ ሁለት አይነት ነው፦ #የአምልኮ_ዱዓ እና #የጥያቄ_ዱዓ። የጥያቄ ዱዓ ሁላችንም ሲቸግረን የምናደርገው የዱዓ አይነት ሲሆን፤ የአምልኮ ዱዓ ደግሞ ምንም ጉዳይ ባይኖረንም እንኳ ከአሏህ ተብቃቂ አለመሆናችንን፣ ከሱ ሀጃ ኖረንም አልኖረን እሱን ችላ አለማለታችንን የምንገልፅበት፣ ከዚህ በፊት ስለሰጠን ፀጋ የምናመሰግንበት፣ የሰጠንን እንዲያዘወትርልን የምንማፀንበት የዱዓ አይነት ነው።
በጥቅሉ #አልሐምዱሊላህም ዱዓ ነው ለማለት ነው። አዎ! ለኛ ለሙስሊሞች የኦክስጅን ያህል ዱዓም ያስፈልገናልና ከርሱ አንዘናጋ! የነብዩላህ ሱለይማንን ፈለግ እንከተል እንዲህ እንበል፦
«ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አግባኝ»[ ሱረቱ አል-ነምል - 19 ]
.
@ONLYFORTRUTHERSJ
BY በቁርአን ጥላ ስር
Share with your friend now:
tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3041