tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3083
Last Update:
🥺 አልፋና ከሪማ ❤️😭
ክፍል አንድ .1⃣
( ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)
የገዘፈው ሁኔ ከመቸው ረገደ
አንቺን አንቺን ሲል በሀሴት ነደደ 😭
ከዋክብት ብቅ ሳይሉ ጨረቃ ቀደመች ቀኑን ሙሉ ሀይሏን ዝቅ እያረገች እየጨመረች ስትንበለበል የነበረችዋም ፀሀይም ሰማዩ ላይ ሌላ ምህዋር በመተካት ተሰለበች ታችኛዋ ምድር ላይ ያለሁት እኔ ግን ቢመሽም ቢነጋ ሂወቴ ይቀጥላል 😊😊
በተፍጥሮየ ከየዋህነት ባህሪ ፍፁም የራቅኩ ነኝ ራሴን ከሁሉም በላይ በመውደዴ የብዙወችን ጥላቻ ባተርፍም ለማንም ግድ አለመስጠቴ ኩራት ሚሉትን ባህሪ እንዲለጥፉብኝ አስገድዷቸዋል 😐 ከማንም የውጭ ሰው ጋር የሳቅም የጨዋታም ምሳሌ አይደለሁም ጭምት ማይፈታ ሰው እንጂ
ምናልባት በሂወቴ ቅርብ ከሆኑ ሰወች ጋር እንጂ ፍፁም ሌሎች ጋር ቀረቤታ የለኝም !!
የሳምንቱ የመጀመሪያ እለት ላይ ነኝ በእሁዱ የእረፍት ቀን ገና በማለዳው ፀሀይ እንኳን በቅጡ ሳትወጣ በሩ እየተንጋጋ ሰሚር የሚል ድምፅ ይሰማል ልክ በሩን ሲከፍቱት ይህ ቀውስ የሆነ ልጅ ነው የሰው ልጅ እንዴት በዚህ መልኩ አእምሮውን እስኪስት እብድ ብሎም ኬር ይሆናል ሲፈጥረው ለሰው አትጨነቅ የልብህን ስራ ብሎታል በዛ ላይ ምንገድ ላይ እየጮሀ ሲያወራ ሽምቅቅ ያረገናል ከጉሮሮ በታች ማያስቅ ቀልዱን እየቀለደ ለብቻው ይስቃል ማሜ እና አብዱ ለሞራሉ ቢስቁም እኔ እንኳን ጥርሴ ሊከፈት ፊቴ ላይ (ምንድነው ሚጃጃለው) አይነት ስሜት ይነበባል አይ ማሂር
ቶሎ በሩ እንደተከፈተለት ገባና ግቢ ፀጉሬን እየታጠብኩ እያለ ሰሚር ሰሚር 😳 ዛሬ የአብዱ አክስት ብር ልካለች ቶሎ ለባብስና ፈታ ስንል እንውላለን እየጠበቁን ነው አለኝ ☺️
ሳምንቱ የተመታ ሳምንት ስለነበ ነው መሰለኝ በጣም ደስ አለኝ ምንም ሳልመልስለት ክፍሌ ገባሁ ልለባብስ ስዘገጃጅ እንደድንገት አባየ ( ጋሽ አህመድ )ሰሚር የት ልትሄድ ነው አለኝ ?
እኔም ማሂ ጋር መሆኔን ነገርኩት አባየ ሲበዛ ጠርጣራ እና የተረጋጋ ሰው ነው በኢስላሚክ ተርቢያ ልጆችን ለማሳደግ ሁሌም ይጥራል ነገር ግን እንደአዋዋልህ እንጂ እንደምትመከረው አይደለም መቼስ🤷♂
ልክ ለባብሼ እንወጣሁ ያየሁትን ማመን ከበደኝ ማሜ ቪትዝ መኪና ይዞ
አብዱ ጋቢና ነበረ ዛሬማ ልዩ ቀን ነው ብየ እየሮጥኩ ገባሁ አንተ ቀውስ ከየት አባህ አመጣህ ስለው ማሂሩ ፈጥኖ ትናንት ተከራይቷት ነው አለኝ እና ትንሽ ሁላችንም ዝም ካልን በኋላ አንድ ላይ ጋቢና ወዳለው አብዱ ዞርን ከዛም ማሜ የዛሬው ሙሽራችን አብዱ ነው አክስቱ ብል ልካለች አለ ስንት አስገባች ስለው አብዱን ትከሻውን እየመታሁ ብሩን ሳይነግረኝ ሰሚርየ ዛሬ በአል ነው በቃ አለኝ
ውይ ሳልነግራችሁ ስሜ ሰሚር አህመድ ይባላል ሰሙ እያሉ ሲጠሩኝ ያመኛል🙄 ምክኒያቱም ሰሚራንም ሲያቆላምጧት ሰሙ ነው 😏 ማሜ አብዱ ማሂሬ ፉአድ የሌለ ሚጃለሱኝ ጓደኟች ናቸው ፉአድ እንኳ ድሬ ዩኒቨርስቲ ሂዷል አሁን እሱ የለም
ለማንኛውም በማሜ ጊዜያዊ መኪና መሄድ እንደጀመርን ማሂ ከተፍ ብሎ የቪትሷን ብሉትዝ አገናኘው እና የሆነ በደንብ ማይሰማ እንጉርጉሮ ከፍቶ እናሽቅ እያለ ጭንቅላቱን ማወዛወዝ ጀመረ እኔና አብዱ ወዲያውኑ ጮህንና አቦ አታላዝንብን ቀይረው አልነው ማሂሬ የሀድራ ሰው ነች አረንጓዴ ልብስ ለብሳ ማበድ ነው ስራዋ ከኛ ውስጥ የዲን አዋቂው አብዱ ነው ከሱ ጋር ሁሌ ይከራከራሉ ይጨቃጨቃሉ እኔ ብዙም አይገባኝም ብቻ ሁሌም ክርክራቸው ሚያልቀው በማሂር አንተ የነቢ ፍቅር ገና መች ገባህ በሚል ትችቱ ነው
እንደምንም በማላዘኑ አሳምኖት ድቤ እንኳን በሌለው እንጉርጉሮ እያዛጋን ደረስን ማሜ እንኳን ኤርፎኑን ሰክቶ ለራሱ የፈረንጅ ዘፈን ይሰማል እሱ ምን ግድ ሰጠው 🙄
የት እንደምንሄድ ሳይነግሩኝ የሆነ ቦታ ላይ ወረድን ምን የመሰለ ቦታ ገባን ውስጡ ሜዳ ነው ስክሪን ተገጥሞ ፊልም ሚያይ አለ ሚዝናናም አለ ድንቅ ቦታ ነው እዛ ቀኑን ሙሉ ስንዝናና ቆይተን አምሽተን ተመለስን እንደተመለስኩ ጫማየን አውልቄ ለጥ ነው ያልኩት
ማይነጋ የለምና ለሊቱ ተሰውሮ በንጋቱ ተቀሰቀስኩ ልክ ከእንቅክፌ ስነቃ ፊትለፊቴ አባየ ቀጥ ብሏል ትናንት ለምን አመሸህ? ሚል ጥያቄ ሰነዘረ ዛሬ ፈጅር ለምን አልመጣህምም አለኝ ? እኔም በቴ ልስገድ ብየ ነው ብየ ዋሸሁት ሰላት ላይ ያለኝ አቋም ቀጥ ያለ ባይሆንም ፈጅር ከፋዘር ጋር ሁሌ ነው ምወጣው ፈዘዝ እንዳልኩ ልብሴን ቀያይሬ ወደ ትምርትቤት አቀናሁ ክላሰ ውስጥ ኮስታራ ነኝ አረ ሂወቴ መኮሳተር በሉት ከጓደኞቼ ፊት ካልሆነ ለማንም ፈገግ እንኳን አልልም ወንዶቹ በዚ ባህሪየ ቀና ብለው አያዩኝም ሴቶቹ ብዙወቹ እንደምመቻቸው እና ወንድ ማለት እንደኔ እንደሆነ ይገልፃሉ በፍፁም ዞር ብየ አይቻቸውም አላውቅም ለቤታችን ብቸኛ ልጅ ስለሆንኩ ብዙም የእህትነት የወንድም ትርጉም አልገነዘብም ድርቅ ያለ ልቦና መገለጫየም ነበር መልኬ ጠየም ብሎ ፀጉሬ የበዛ ብዙም ያልደረቀ ሉጫም ያልሆነ ሚያምር ፀጉር ከደስ ደስ መልክ ጋር ተሰጦኛል ከክፍላችን ልጆች አረ ከትምርትቤቱ የወንዳወንድ መገለጫ የውበት ምሳሌ ነኝ ግን እኔ ብዙም ለዚ ግድ አይሰጠኝም🤷♂ የሰው ልጅ ብዙ ሚያዝናናው ነገር አያስደስተኝም
ዛሬ መክሰስ አብዱ ልጋብዛቹህ ብሎ ቤቱ ሂደናል ልክ ቤቱ እንደገባን ትንሿ ኢልሃን ማሜ እና ማሂር ላይ ተጠመጠመች እኔ ላይ ብዙም የደስታ ስሜት አላሳየቺም ትንሽ ቅናት ቢጤ ፈጠረብኝ ግን ወዲያውን ረሳሁት ኢልሃን የአብዱ ብቸኛ እህቱ ናት በጣም ደስምትል ተግባቢ ምላሳም ህፃን ልጅ ናት እነ አብዱ ከእናታቸው ጋር ነው ሚኖሩት ያው እናታቸው በንግድ ታስተዳድራቸዋለች ከመካከላኛ ትንሽ ዝቅ ያለ ኑሮ ይኖራሉ ፍቅራቸው ደስ ይላል አብዱ እኛጋ አይማርም ኢስላማዊ መድረሳ ሚሉት የሆነ ሀይማኖታዊ ቦታ ነው ሚማረው እዛ ትምርትቤታቸው ሁሉም ይወደዋል ጎበዝ ተማሪም ነው የዲን እውቀት ላይ ጎበዝ ነው ብር ዘመዶቹ ይልካሉ ማሜም ማሂም በሆነ ምንገድ ብር ያገኛሉ እኔ ግን ብዙም አይደለሁም ድንገት ግን ወደቤት ስመለስ ስራ ምሰራበትን ምንገድ ቤት ላማክር አሰብኩ ምክኒያቱም በገንዘብ እጥረት በጣም ብዙ ነገር ሚስ እያረኩ ስለሆነ
በዛሬው እለት ምሽት ሁሌ አእምሮየ ላይ ያለ ጥያቄ ለአባየ ልጠይቀው ወስኜ ነበር ምንም ብፈራው ምላሹ ምን ቢሆን መች ስራ መጀመር እንዳለብኝ ልነግረው ወሰንኩ አባየ ጋር ማታ ራት እየበላን አባየ አልኩት በለዘበ ድምፅ ወየ ልጄ አለኝ አባየ ስራ መስራት እፈልጋለሁ አልኩት
ቀጥታ እሱም አፍጦ ካየኝ በኋላ ለምን አለኝ ትንሽ ግራ አጋባኝ ድንግጥ ብየ አረ ለምንም ብየ ክፍሌ ገባሁ
ትንሽ ክፍሌ ውስጥ ማሰብ እንደጀመርኩ በሩ ተንኳኳ አባየ በመቆጣቴ መጦ ነው ብየ ስከፍት አሚ ናት እናቴ ከሁሉ በላይ ትረዳኛች ለኔ መሸፈን እንጂ ፈፅሞ ጫና አታበዛብኝም አትቆጣኝምም ጭምር ትከሻየን እያሸች እንዴት ይህን ጥያቄ አነሳህ ሰሚሬ አለቺኝ
ከዛም በመገረም
የራሴ የሂወት ምእራፍ እና ጎዳና የለኝምን ? እኔስ ወደፊት ሂወትን መኖር ገንዘብ ማግኘት አያምረኝም አልኳት ከዛም ትምርት ሳጨርስ ምን አይነት ችኩልነት ነው ከየት አመጣሀው አለቺኝ እኔም እየሰራሁም መማር እንደምችል ያለሁበት ሁኔታ ብር ሚያስፈልገኝ ዋና ሰአት ላይ እንደሆንኩ ነገርኳት ትምርቱም ላይ ሁላችሁም ፍላጎት እንደሌላችሁ አውቃለሁ አልኳት ከዛም መጀመሪያ ስራ ለመስራት ከሰው ጋር መግባባት አለብህ ብላኝ ሄደች ይቺ ቃሏ ለሊቱን ስትረብሸኝ አደረች ራሴን ዝቅ ማድረግ ሚመስሉኝ
BY በቁርአን ጥላ ስር
Share with your friend now:
tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3083