ONLYFORTRUTHERSJ Telegram 3094
እብዱ ደራሲ
# ክፍል አንድ(1)

# አዲስ ተከታታይ ልቦለድ ተጀመረ!!

..........

ለመኖርም ለመሞትም አልታደለም በመኖር ውስጥ የሞተ፣ሞተ እየተባለ የኖረ፣ምስኪን ፍጡር ነው።የማያውቁት ሰዎች ከሩቅ ሲያዩት በፍርሀት ልባቸው ጥለው ይሮጣሉ።ከፊሉ እያዘነለት፣ከፊሉ እያዘነበት በአጠገቡ ያልፋሉ።ሁሌም ከእጁ ላይ የማትለየዋ ቡኒ ተስቢህ የማሂር መታወቂያ ነች።ሲቀመጥ ሲነሳ ሲተኛ ሲበላ ሁሌም በእጁ ላይ አለች።ሲዞር ሳንቲም ሲለቅም ይውል እና የሰፈሩ ወጣቶች በሸራ እና በማዳበሪያ የሰሩለት ቤት ውስጥ ገብቶ ይተኛል።የተቦጫጨቀ ልብሱ እላዩ ላይ ሊያልቅ ትንሽ ቀርቶታል።የማይታየው የሰውነት ክፍሉ የሚታየው ይበዛል።ያለፈ ያገደመውን ሳንቲም ይጠይቃል።ግማሹ በሀዘኔታ ግማሹ ብከለክለው ይመታኛል በሚል ፍራቻ ይሰጡታል።አንድ አንድም አለ ሂድ ከዚ!ብሎ ቀልቡን ቀፎ የሚያባርረው፡ለነገሩ ማሂር ቀልብ የለውም!ቀልብ ቢኖረውማ የተቦጫጨቀ ልብሱን በቀየረ፣መንገድ ማደሩን ትቶ ወደ ቤቱ በገባ፣ግን የት ነው ቤቱ?ከየትስ ነው የመጣው?እንደዚ ሲሆን ጠያቂ የለውም?ለምንድነው አብዛኛው ጊዜ እዚህ ሰፈር የሚኖረው?ና ልጄ ብላ የምትሰበስብ እናት ወይም የሚሰበስብ አባት የለውም።ቤተሰቦቹስ?ዘመዶቹስ?የማን ልጅ ነው?ወደ ሰፈሩ የመጣ አዲስ ነዋሪ፤ለእንግድነት የመጣ ሳይቀር የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፤ግን መልስ የለም።ማሂር እዚህ መንደር መቶ መዋል ማደር ከጀመረ አምስት አመታትን አስቆጥሯል።አንዳንዴ ለተወሰነ ቀናት ከሰፈሩ ይጠፋል።ግን እሰይ ተገላገልን የሚለው የለም።ሁሌም አንድ ሳምንት ቆይቶ ይመጣል።የት ይሂድ?ለምን ይሂድ?የሚያውቅ የለም!የመንደሩ ሰው እንደ ጎረቤቱ ለምዶታል!ከአይናቸው ሲጠፋ ባይፈልጉትም ይጠይቃሉ።የት ሄዶ ይሁን?ብለው ይጨነቃሉ!መኪና ገጭቶት ይሆን?እብድ ነው ብለው ቀጥቅጠውት ይሆን?ማሂር እኮ ግን እብድ አይደለም!ሰው አይነካም።የጫት ሱስ የለበትም፣ሰው አያስቸግርም አይጮህም እንደ እብድም አይለፈልፍም!ትልቅ ሰው ይወዳል።እቃ ተሸክመው ካየ ተቀብሏቸው የሚፈልጉት ቦታ ያደርስላቸዋል።አሁን አሁንማ እነሱም ና እስቲ የኔ ልጅ እቺን እቃ አድርስ!እያሉ ይልኩት ጀምረዋል።እንቢ አያውቅምአንገቱን እንዳቀረቀረ የተባለበት ቦታ ያደርሳሉ።የሰፈሩ ጎረምሶች #እብዱ ደራሲ ይሉታል፤ያገኘው ላይ ይፅፋል።ለሰው የማይገባ ለሱ እረፍት የሚሰጠው አይነት ፅሁፍ!ወጣቶቹ ይወዱታል እሱም ሳንቲም እንዲሰጡት ስለሚፈልግ ሲያዙት ይታዘዛል።እነሱም እጃቸውን ለሱ ይዘረጋሉ።ደሞ ብር አይቀበልም ሳንቲም ብቻ፣ለሊት በሱ አጠገብ ያለፈ ሰው ሳንቲም ሲቆጥር ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል።ምን እንደሚያረግለት ባያውቁም ይሰጡታል።እሱም ይሰበስባል።ህፃናት የሚጫወቱበት ቦታ ላይ አይጠፋም።አንድ ሰሞን ሲመጣ ይሮጡ ነበር።አሁን ይቀርቡት ጀምረዋል።አንዳንዴ አብሯቸው ይጫወታሉ።አብሯቸው ይስቃል በሳቁ ውስጥ ግን ሁሌም እንባ አለ።ቶሎ የማይደርቅ እንባ ሀዘን፣ስብራት እንዳዘለች የምታስታውቅ እንባ ያነባል።ተስፋ የቆረጠ ናፍቆት ያጠቃው ብቸኝነት ያጎሳቆለው ሰው የሚያፈሰውን እንባ እንደ ጎርፍ ያፈሰዋል።ማልቀስ ከጀመረ አያቆምም ግን እሱ እየሳቀ ነው ሚያለቅሰው!ሳቁ ደሞ ከጣራ በላይ ይሰማል፤ሰዎች ሲያለቅሱ ደግሞ ይስቃል፤ሰፈር ውስጥ ለቅሶ ካለ በአካባቢው አይጠፋም ሰዎች በሀዘን እንባቸውን ሲያወርዱ እሱ ግን በደስታ በሚመስል መልኩ ይስቃል፤በደስታ እንደሚቦርቅ ህፃን ይፈነድቃል እንግድነት ለመጣው ሰው አዲስ ነገር ቢሆንም መንደሩ ግን ለምዶታል ተዉት #እብድ ነው ይባላል።

ሰዎች እብድ ነው የሚሉት ማሂር ዛሬ የለም።እናቶች እንደ ህፃን የሚልኩት የህፃናቶች የጨዋታ ማድመቂያ ወጣቶቹን ሳንቲም እያለ የሚለምናቸው የፈለጉት ቦታ የሚልኩት ማሂር ዛሬ ቦታው የለም።እንደለመደው አንድ ሳምንት ቆይቶ ይመጣል።ሁሉም እየጠበቀ ነው።እሱ ግን እናት ልጇ ወቶ እንደቀረባት ልጅ ከስራ ሲመጣ ብስኩት ገዝቶ እንደሚያመጣለት አባት ደጅ ደጁን እያዩ ነው።አረ ባካቹ #እብዱ ደራሲ እኮ ከጠፋ ሳምንት አለፈው።እያሉ የወንድማቸው ያህል የሚጨነቁለት ጎረምሶች ፍለጋ ከጀመሩ ቆይተዋል።ማሂር ግን የለም.....

............ይቀጥላል..........
https://www.tgoop.com/tesefgna

tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3094
Create:
Last Update:

BY በቁርአን ጥላ ስር

Share with your friend now:
tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3094

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

5Telegram Channel avatar size/dimensions How to Create a Private or Public Channel on Telegram? 2How to set up a Telegram channel? (A step-by-step tutorial) For crypto enthusiasts, there was the “gm” app, a self-described “meme app” which only allowed users to greet each other with “gm,” or “good morning,” a common acronym thrown around on Crypto Twitter and Discord. But the gm app was shut down back in September after a hacker reportedly gained access to user data. Earlier, crypto enthusiasts had created a self-described “meme app” dubbed “gm” app wherein users would greet each other with “gm” or “good morning” messages. However, in September 2021, the gm app was down after a hacker reportedly gained access to the user data.
from us

Telegram በቁርአን ጥላ ስር
FROM American