Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tgoop/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/ONLYFORTRUTHERSJ/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tgoop/post.php on line 50
በቁርአን ጥላ ስር@ONLYFORTRUTHERSJ P.3096
ONLYFORTRUTHERSJ Telegram 3096
Forwarded from ብዕሬ ስትደማ (crazy girl🤒)
🤪እብዱ ደራሲ

ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል ሁለት(2)

"ሲሁ ሲሀም ተነሺ እንጂ ስራ ረፍዷል፡እንደ ቀልድ ሱብሂ መስገድ ተውሽ አይደል?እሺ አሁን ብድግ በይ ውሀ ሳልገለብጥብሽ"ብላኝ ወደ ኩሽናዋ ሄደች በጠዋት እንቅልፍ ማልደራደረው እኔ ስልኬን ከአጠገቤ ሳብ አድርጌ ሰዐቱን አየሁት ምክንያቱም ኡሚ ሁሌ ሱብሂ ልትቀሰቅሰኝ ስትፈልግ ስራ ረፍዷል ነው የምትለኝ እንዴት እንደምበሳጭባት!አንዴ ከተነሳው እንቅልፍ ስለማይወስደኝ በተነሳው ሰዐት ነው መስገድ ምፈልገው እሷ ግን አትሰማኝም "ሱብሂ መስገድ ቀንሽን ሙሉ ደስተኛ እንድትሆኚ ያደርግሻል" ትለኛለች።ለኔ ደስታ የሚሰጠኝ የጠዋት እንቅልፍ መሆኑን አይገባትም ግን ላለመጨቃጨቅ ስል"እሺ"እላታለው።ኡሚ ግን እሺ ማለቴ የባሰ ያናድዳታል።"ሁሌም እሺ ብቻ እስቲ አንድ ቀን እንኳን ተግብረሽ አሳይኝ ትለኛለች"።አሁን አሁንማ ሰለቻት መሰለኝ በስራ ሰዐት ነው የምትቀሰቅሰኝ ግን ምንም ቢሆን ከ12:40 አታሳልፈኝም ነበር፤ዛሬ ግን ረፍዷል ስልኬን ሳየው1:05 ይላል።ውሀ እንደተረጨ ሰው ብርድ ልብሴን ወርውሬ"ኡሚ ግን ምን ሆና ነው?እስካሁን ያልቀሰቀሰችኝ"እየተነጫነጭኩ ሻወር ለመውሰድ ወጣው።ትላንት ስዞር ስለዋልኩ እና አምሽቼ ስለተኛው ሰውነቴ ዛል ብሏል ሻወር ስወስድ ከለቀቀኝ ብዬ ቀዝቀዝ ባለ ውሀ ሻወር ወሰድኩ ምንም ስራ የመሄድ ሙድ ሊመጣልኝ አልቻለም ግን ደግሞ ግዴታ ነው!ለሰሙ አልነገርኳትም፤ይህን እያሰብኩ ስልኬ ጠራ ሰሙ ነበረች።
"እ አንቺ ጨረሽ" አለችኝ ምን አለ ደና አደርሽ ቢቀድም አልኳት "ትላንት አብረን መስሎኝ ያመሸነው በይ ነይ ውጪ እየደረስኩ ነው"ብላ ስልኩን ዘጋችው።ምን አለ እንዳወራ እድሉን ብትሰጠኝ ኡፍፍ ብዬ ልብሴን መልበስ ጀመርኩ።"አንቺ ልጅ አረ ነይ ውጪ ሻዩ ቀዘቀዘ እኮ ምን ይሻልሻል በአላህ?ሰው አንድ ቀን እንኳን አያልፍለትም?ጓደኛዬ ምን ትለኛለች እንኳን አትይም እንዴ?አረ ተይ ሲሁ ቀልብ ግዢ ተይ"ኡሚ ምክሯን ጀመረች።ጨርሻለው እኮ ቁርስ ደሞ አልበላም፤አራበኝም አልኳት።ከክፍሌ ውስጥ ሆኜ፤አራበኝም ማለት ምን ማለት ነው?ከእንቅልፍ አይደል እንዴ የተነሳሽው?ነይ ውጪና ብይ!"ቁጣ እና ትዕዛዝ የተቀላቀለበት ድምፅ!!መልስ ልሰጣት ስል በር ተንኳኳ"ይሀው ጓደኛሽ መጣችልሽ ስትንከራፈፊ ብላኝ በር ለመክፈት ወጣች"ኡፈይ አልሀምዱሊላህ ተገላገልኩኝ"ብዬ ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ከክፍሌ ወጣው።ጫማዬን እየፈለኩ እያለ ኡሚ መጣች ከሗላዋ ጓረቤታችን ወይዘሮ አኢሻ ተከትለዋት ገቡ።ፊታቸው ልክ አልነበረም መርዶ ነጋሪ ነበር የሚመስሉት፤ኡሚም ተረብሻለች፤አጠገቧ እንደቆምኩ ራሱ ልብ አላለችም ነበር፤"ደሞ ማን ሞተ አይ እኛ ሰፈር አዝራኤል ከገባ ካልጠራረገን አይወጣም አይደል?"እያልኩ ጫማዬን ለብሼ እንደጨረስኩ ሰሙ ደወለች"አረ አንቺ ሴትዬ ነይ ውጪ ጥዬሽ ነው ምሄደው"ብላ ስልኩን ዘጋችው።
እንደተበሳጨች ስለገባኝ ኡሚን"ደና ዋይ ብያት"ልወጣ ወደ ሳሎን ስገባ እሷም ስትወጣ በር ላይ ተጋጨን ግን ትዝም አላልኳት!"ኡሚ ደና ዋይ በቃ ልሄድ ነው"ብዬ እንደለመድኩት ግንባሯን ልስማት ስል አይኖቿ እንደጉድ እንባን አዘነቡ፤በጣም ነበር የደነገጥኩት"ኡሚ ምንድነው የሆንሽው?ማነው የሞተው!ማን ምን ሆኖ ነው!መልሷን አልጠበኩም ነበር"ምንም ምንም አይደል ልጄ ሂጂ በይ ከስራሽ ቶሎ ተመለሺ የግቢውን በር ቆልፈሽ ሱቅ አስቀምጪልኝ።ብላ ጉንጬን ሳም አድርጋኝ ከቤት ወጣች ጨራርሼ ስለነበር ተከትያት ወጣው።አይ የኔ ልጅ፣የኔ የዋህ፣አይ ማሂርዬ የሚሉ ከአንደበቷ የሚወጣ የለቅሶ ድምፅ ይሰማኛል።ጓረቤታችን እትዬ አይሻም "በልጅነቱ እንዲ መሆኑ ሳያንስ አይ የሰው ልጅ መከራ አይ ማሂር"እያሉ ከኡሚ ተከታትለው ወጡ.....ማነው ማሂር ምን ሆኖ ነው ለማወቅ በጣም ፈለኩ።

..........ይቀጥላል........

https://www.tgoop.com/tesefgna

tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3096
Create:
Last Update:

BY በቁርአን ጥላ ስር

Share with your friend now:
tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3096

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

"Doxxing content is forbidden on Telegram and our moderators routinely remove such content from around the world," said a spokesman for the messaging app, Remi Vaughn. According to media reports, the privacy watchdog was considering “blacklisting” some online platforms that have repeatedly posted doxxing information, with sources saying most messages were shared on Telegram. Ng, who had pleaded not guilty to all charges, had been detained for more than 20 months. His channel was said to have contained around 120 messages and photos that incited others to vandalise pro-government shops and commit criminal damage targeting police stations. Write your hashtags in the language of your target audience. How to create a business channel on Telegram? (Tutorial)
from us

Telegram በቁርአን ጥላ ስር
FROM American