ONLYFORTRUTHERSJ Telegram 3097
Forwarded from ብዕሬ ስትደማ (crazy girl🤒)
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል ሶስት(3)

ሰዐቱ አምስት ሰዐት ሆኗል ሰሙ ጠዋት ስላረፈድኩባት እንደተኮፈሰች ኮምፒውተሯ ላይ አፍጥጣለች።እኔም የማሂር ነገር ስላሳሰበኝ ቢሮ ከገባው ጀምሮ ከማንም ጋር አላወራሁም እሷንም ቢሆን እንደ ሌላ ቀኑ አልተለማመጥኳትም።ሰሙ ልምምጥ ትወዳለች፤ዛሬ ግን ምንም አላልኳትም ቁርስ አለመብላቴን ራሱ ረስቼዋለው።
ሰሙም እንደደበረኝ ገብቷታል፤አስር ጊዜ ስልክ ስደውል በቆሪጥ ታየኛለች፤አጠገቤ መታ ልታወራኝ ፈልጋለች፤ሄጄ አንዴ እንኳን ሰሙ sorry ብላት እንደምትመለስ አውቃለው፤ግን በቃ ዛሬ ሙዴ አይደለም!የማሂር ነገር አስጨንቆኛል፤ምን አለ ባልመጣ?እቤቴ ሆኜ በነበር ምን እንደተፈጠረ አውቄ ነፍሴ ትረጋጋ ነበር!
"የኡሚ ስልክ አለማንሳት ደግሞ የባሰ ጭንቀቴን ጨመረው"ማሂር ምን ሆኖ ይሆን?መኪና ገጭቶት ይሆን?ሞቶ ይሆን?ይህንን እያሰብኩ እንባዬ ፈሰሰ።ሰሙ እያየችኝ እንደሆነ እንኳን አላስተዋልኩም።
"አሀ ሲሁ እያለቀሽ እኮ ነው"ብላ ከወንበሯ ላይ ተስፈንጥራ አጠገቤ ተቀመጠች።እንባዬን ጠራርጌ"sorry ሰሙ"አልኳት።አሁን እሱን ተይውና ምን ሆነሽ ነው?ኡሚዬ ደና አይደለችም እንዴ?ከገባን ጀምሮ ልክ አልነበርሽም!"ምንም ሰሙ ዝም ብዬ ነው" "ኡፍፍ አንቺ ደግሞ ችግር አለብሽ ወይስ ሰውዬሽ ናፍቆሽ ነው?"ስትል ሳቄን ለቀቅኩት።

..................

ሰሙ የሳቄ ምንጭ፤የጭንቀቴ ማቅለያ ነች።ትውውቃችን የቅርብ ጊዜ ቢሆንም ለሚያየን የልጅነት ጓደኛሞች እንጂ የአመት ከ6ወር ትውውቅ አይመስልም።ያወኳት እዚሁ መስሪያ ቤት ልቀጠር ሲቪ ላስገባ ስመጣ ነው እሷም ልትቀጠር መሆኑ ነው።ድርጅቱ የሚፈልገው 2ሴት ብቻ ነው።እንደኛ ሊቀጠሩ የመጡት ግን ከ50 ይበልጣሉ፤ድርጅቱ የሙስሊም ስለሆነ ግማሽ ያህሉ ሙስሊም ናቸው።እኔና ሰሙ ወረፋችን ፊት እና ሗላ ስለነበር ለመግባባት አልተቸገርንም፤የት/ት ማስረጃችን የሚቀበለን ሰው 4ሰዐት ቢሆንም የሚገባው እኛ ግን ወረፋ ለመያዝ ስንል ጠዋት 1ሰዐት በቦታው ተገኝተናል።ከሰሙ ጋር ብዙ አወራን፤እዛ ቦታ ላይ የተገናኘን ሳይሆን አብረን የመጣን ነበር የምንመስለው፤ሰሙን ስላወኳት ደስ ብሎኛል፤የሚገርመው ደሞ ሁለታችንም የAccounting ተመራቂ መሆናችን እና የተማርንበት ት/ቤት መገጣጠሙ ነው ያልተዋወቅነው ሰሙ የማታ ተማሪ ስለሆነች እኔ ደሞ የቀን ተማሪ ስለሆንኩ ነበር።"እራሴ እየከፈልኩ ስለሆነ የምማረው የማታ ነበር"አለችኝ።"ዋናው መማርሽ ነው ባክሽ" አልኳት።እንደዛ እንደዛ እያልን ብዙ ነገር አወራን፤ሲበዛ ግልፅ መሆኗ አስገረመኝ፤ብዙ ጓደኞች ቢኖሩኝም አብሪያት መሆንን ተመኘው፡አሁን ወረፋችን ደርሷል፤ሁለታችንም ገብተን ወረቀታችንን አስገብተን ተያይዘን ወጣን።"ሁለታችንም አልፈን አብረን ብንሰራ ደስ ይለኛል" አለችኝ።የኔም ፍላጎት ነበርና"ኢንሻአላህ"አልኳት።ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን።ከሰሙ ጋር ቅርርባችን በጣም ጠብቋል እቤት ትመጣለች ኡሚም ወዳታለች የት/ት ማስረጃ ያስገባንበት መስሪያ ቤት ለፈተና ስንጠራ አብረን ነበር የሄድነው ውጤቱ ግን በጣም ዘግይቷል ሁለታችንም ተስፋ ቆርጠናል፤ቢሆንም ግን አልደበረንም፤አብረን እንውላለን፤አንዳንዴ ሰሙ እኛ ቤት ታድራለች።የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ወደቤቷ የምትሄደው ለአዳር ብቻ ነው።ቤተሰቦቿ እንደሞቱ እና ከአያቷ ጋር ክፍለ ሀገር እንደኖረች፤የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በአጎቷ ልጅ እገዛ አ.አ እንደመጣች እና ከሱ ጋር እንደነበር ምትኖረው፤ነገር ግን ሚስቱ ክፉ ስለነበረች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደመጣላት ስታውቅ ከሱ ጋር አጣልታ ከቤት እንዳባረረቻት ሆኖም እሱ ከሚስቱ ደብቆ እንደሚረዳት፤ስራ እንዳስጀመራት፤የቤት ኪራይ ይከፍልላት እንደነበር፤የማታ ት/ት ያስመዘገባት እሱ እንደነበር፤ከአመት በፊት ግን በልብ ህመም እንደሞተ ሁላ በመጀመሪያ ቀን ነበር የነገረችኝ።ይህንን ሁላ ስቃይ በልጅነቷ ስለተሸከመች ታሳዝነኛለች ጥንካሬዋ ብርታቷ በጣም ይገርመኛል።

አንድ ቀን እንዲ ሆነ ሰሙ እኛ ቤት ነበር ያደረችው በጠዋት ስልኬ ጠራ ሳየው ባለፈው የተፈተንበት ድርጅት ቁጥር ነው ምን አልባት ሰሙ ካላለፈች እንዳትሰማኝ ብዬ ኔቶርክ እንደተቆራረጠበት ሰው ሄለው እያልኩ ከክፍሌ ወጣው.......

.........ይቀጥላል..............

https://www.tgoop.com/tesefgna

tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3097
Create:
Last Update:

BY በቁርአን ጥላ ስር

Share with your friend now:
tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3097

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Deputy District Judge Peter Hui sentenced computer technician Ng Man-ho on Thursday, a month after the 27-year-old, who ran a Telegram group called SUCK Channel, was found guilty of seven charges of conspiring to incite others to commit illegal acts during the 2019 extradition bill protests and subsequent months. On June 7, Perekopsky met with Brazilian President Jair Bolsonaro, an avid user of the platform. According to the firm's VP, the main subject of the meeting was "freedom of expression." Just as the Bitcoin turmoil continues, crypto traders have taken to Telegram to voice their feelings. Crypto investors can reduce their anxiety about losses by joining the “Bear Market Screaming Therapy Group” on Telegram. The visual aspect of channels is very critical. In fact, design is the first thing that a potential subscriber pays attention to, even though unconsciously. Public channels are public to the internet, regardless of whether or not they are subscribed. A public channel is displayed in search results and has a short address (link).
from us

Telegram በቁርአን ጥላ ስር
FROM American