tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3101
Last Update:
🤪እብዱ ደራሲ✍
#ተከታታይ ልቦለድ📖
#ክፍል ሰባት(7)
ትረፊ ያላት ነፍስ አሉ ጋሽ አህመድ ብቻ አልሀምዱሊላህ ተርፏል ባይባልም አልሞተም።የመኪና አደጋ ነበር የደረሰበት ነገር ግን ሹፌሩ አላህ የመረቀው ወጣት ስለሆነ ትቶት አልሄደም እሱ ወድያው ሀኪም ቤት ባይወስደው ኖሮ አይተርፍም ነበር ብቻ አልሀምዱሊላህ ብላ እንባዋን ጠራረገች።እሺ አሁንስ እንዴት ነው ሰሙ ነበረች የጠየቀችው ዶክተሮቹ ሰው የማይገባበት ክፍል አስተኝተውት ማንም አላየውም እነዚ እነማናቸው እዛ ታች የሚቀመጡት ጎረምሶች?እነ ኡስማን ነው ኡሚ?አልኳት አዎ!እነሱም ካላየነው አናምንም ብለው ቢበጠብጡም የባሰ ከሀኪም ቤቱ ተባረሩ አለችን።ሰሙ እና እኔ በረጅሙ ተንፍሰን እኩል አልሀምዱሊላህ አልን በጣም ተጨንቀን እንደነበር የገባት ኡሚ ልጆቼ ለሰው ልጅ መጨነቅ እኮ የኢማን ግማሽ ነው አለችን ኡሚ ሁሌም እኛን ለማስፈራት ሆነ ለማስደሰት በራሷ ሀዲስ እንደምትፈጥር ስለምናውቅ ሳቃችንን ለቀቅነው"ምን ያስገለፍጣቿል"አይ ኡሚዬ ሀዲሶችሽን በዝተውብን እኮ ነው ብለን ተሳሳቅን።ሰው አረ እንኳን ተረፈ እኛኮ በጣም ተጨንቀን ነበር የሲሁ ደግሞ ይባስ ስትል ኡሚ ቀበል አድርጋ አንቺ ከመች ጀምሮ ነው እንደዚ አስተዋይ የሆንሽው እ አለችኝ ሾርኒ መሆኑ ነው።አይ ኡሚዬ ወላሂ ለኔም ግራ የገባኝ እሱ አይደል ከልክ በላይ ነውኮ የተጨነኩት ኡፍ ዋናው እንኳን አልሞተ ደሞ ማን ያውቃል አላህም የኔን ጭንቀት አይቶ ይሆናል ያተረፈው አልኩ በማልገጥም በጉራም አይነት ነገር እሺ የኔ ወልይ ሰላቱን በስርዐቱ በሰገድሽው ወገኛ አለች ኡሚ።ኡሚ ስለ ሰላት ከተነሳ በዛውም የምክር አገልግሎት እንደምትጀምር ስለማውቅ እሷ ከጀመረች ደግሞ አቶ ሰሚራም እንደምትከተላት ስለገባኝ በሉ ደክሞኛል ልረፍ ብዬ ተነሳው🚶♀🚶♀እሺ ሸይጧንሽ ተነሳ አለችኝ ኡሚ ሁሌም እንደዚ ስለማደርግ ለምዳዋለች ሰሙም በቃ ልሂድ ስትል መለስ አልኩ የምን መሄድ ነው ወላሂ እዚ ነው ምታድሪው በጠዋት ተነስተን ማሂርን ጠይቀን ነው ስራ ምንገባው አልኳት ኡሚም እንድትሄድ ስላልፈለገች አዎ ብላ ሰሙን አሳመነቻትና አደረች።
...................
ቀናት ቀናትን እየተኩ ማሂር ሀኪም ቤት ከተኛ 15ቀን ሆኖታል ዶክተሮቹ ከ1ሳምንት ቡሀላ እንደሚወጣ ነግረውናል የሰፈሩ ሰው እኛ ስላለን ነው መሰለኝ ብዙም አይመጡም እነ ኡስማን ወደ ሀኪም ቤት መግባት ስለተከለከሉ እኛን ነው ሚጠይቁት መድሀኒት ምናምን ሲያስፈልገው ገዝተው ያመጡልናል ለነገሩ ማሂርንም የገጨው ሰውዬ ኡሚ እንዳለችው ጥሩ ሰው ነበር እሱ ነበር ሚያድርለት ሁሌም አውፉ በለኝ እያለ የማሂርን እጅ ይዞ ያለቅሳል ማሂር የግራ እግሩ ስለተጎዳ በዊልቸር ይሂድ እንጂ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ደና ነው።ኡሚም ምግብ እየሰራች እሱን መካደም የዘወትር ልማዷ አድርጋዋለች እኔና ሰሙም ወይ ስራ ስንወጣ ወይም ስንመለስ እንጠይቀዋለን መንገዳችን ስለሆነ በቀን አንዴ ሳናየው አንውልም እሱም ደስተኛ ነው አእምሮውም ቢሆን ወደራሱ ተመልሷል ኡሚንም እማ እያለ መጥራት ጀምሯል እሷም ቢሆን አላሳፈረችውም የእናት ያህል ትንከባከበዋለች።ነገር ግን ለሁላችንም ጥያቄ የሆነብን እና ለመናገርም የፈራነው ነገር ቢኖር ማሂር ከሀኪም ቤት ከወጣ ቡሀላ እዛ ማዳበሪያ ውስጥ ነው ሚመለሰው ወይስ ምንድነው ሚሆነው ዶክተሮቹ ደሞ ቢይንስ መድሀኒት እስኪጨርስ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ለአእምሮ ህመሙ ምክንያት ብቸኝነት ሰው ማጣት እና ጭንቀት እንደሆነ ነግረውናል መጀመሪያ አካባቢ ማሂርን የገጨው ሰውዬ እንደሚወስደው አስበን ነበር እሱ ግን ለኡሚ እዚ ሀገር እንደማይኖር እና ለመዝናናት እንዲመጣ ከ15ቀን ቡሀላ ወደ አሜሪካ እንደሚመለስ ነጎሯታል ኡሚም በሰዐቱ እሺ አታስብ እንዳለችው እና የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግ እና በአላህ ስም አደራ እንዳላት ነግራናለች ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ኡሚ ግራ ተጋብታለች ጓረቤቶቿም ቢሆኑ በሀሳቧ አልተስማሙም እንዴት ማታቂውን ለዚያውም እብድ ወደ ቤትሽ ታስገቢያለሽ እያሉ ይወተውቷት ጀምረዋል።ሰዒድም ወደ ሀገሩ ሂዷል ማሂር ከሀኪም ቤት ሊወጣ 3ቀን ብቻ ቀርቶታል።ማን ያኖረው ይሆን?ማን ጋር ያርፍ ይሆን?መልስ የታጣለት ጥያቄ.............
............ይቀጥላል...........✍
https://www.tgoop.com/tesefgna
BY በቁርአን ጥላ ስር
Share with your friend now:
tgoop.com/ONLYFORTRUTHERSJ/3101