tgoop.com/Official_nahi/266
Last Update:
┉••••✽̶»̶̥🌺ከረፈደ!🌺̶̥✽̶••••┉
❣:¨·.·¨: ❣
┈┈••◉❖◉●••┈┄
🌺ክፍል 2
✍በ bina
#በእዉነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ከረፈደ
#ክፍል_ሁለት
ሰዉ ሲደነግጥ በየትኛዉ የአእምሮ ክፍል እንደሚያስብ አይገባኝም ብቻ በፍጥነት መሪዉን ወደ ቀኝ ጠምዝዤ መኪናዉን ከአንድ ትልቅ ግቢ አጥር ጋር አላተምኩት። ሁሉም ነገር በፍጥነት የተከናወነ ስለነበር ምን እንደተፈጠረ የተረዳሁት እራሴን ከድንገተኛ ክፍል አልጋ ላይ ሳገኘዉ ነበር። ማን እንደደወለላቸዉ ባላዉቅም አከራዬ ወ/ሮ ሙሉ አቶ እንዳለና ከመገጨት ያዳንኳት ቆንጆ ሴት በታላቅ ድንጋጤና መጨነቅ ከአጠገቤ ቆመዉ ነበር። ዶክተሩ ለጤናዬ አሳሳቢ ነገር አለመኖሩንና እራሴን የሳትኩትም ከድንጋጤ የተነሳ መሆኑን እንዲሁም እረፍት እንደሚያስፈልገኝ ነግሮ አንዳንድ ቁስሎቼ ላይ ፕላስተር ካደረገልኝ በሗላ ወደ ቤት መሄድ እንደምችል ነገረኝ።<<እኔን ለማዳን እራስክን ልታጣ ነበር የሆነ የከፋ ነገር ገጥሞክ ቢሆን በእኔ ስህተት ስለደረሰብህ ነገር እድሜ ዘመኔንን የፀፀት አለንጋ ሲገርፈኝ ይኖር ነበር>> ለማንኛዉም <<ሔርሜላ>> እባላለሁ ብላ እጇን ዘረጋችልኝ <<ቢኒያም>> መናገር የቻልኩት ይሄን ብቻ ነበር። ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ ስለነበርኩ ስሜን ከመናገር ዉጪ ቃል ሊወጣኝ አልቻለም።>>
እንዲህ ባለ እራስን ሰዉቶ የሰዉን ህይወት በማዳን አጋጣሚ ከ ሔርሜላ ጋር ፍቅር ከጀመርን ሁለት አመታትን አስቆጠርን። ያለፈዉን ትዝታና የጠዋቱን ዱካክ ወደ ሗላ ጥዬ <<በአንድ ሰዓት ዉስጥ እደርሳለሁ>> ያለችኝ ፍቅሬን ለመቀበል ከአልጋዬ ላይ ወረድኩ...
እድሜ ለሔርሜላ ቤቴን የቤት ቅርፅ አስይዛልኛለች። እርሷ ወደ ቤቴ መምጣት ከጀመረች ግዜ አንስቶ ቤቴ በየእለቱ በአዳዲሰ ሀሳቦችና እቃዎች ተሟልታለች!
የተኛሁበትን አልጋ አነጣጥፌ እንደጨረስኩ ቤቴ በሀይል ተንኳኳ
<<እንደምን አደርክ? እንኳን አደረሰክ ቢኒያሜ>> ወ/ሮ ሙሉ ነበሩ!
<<እንኳን አብሮ አደረሰን እንደምን አደሩ?>> አልኳቸዉ በሩን በሀይል ሲያንኳኩ ስለነበር በድንጋጤ <<ጎሽ ዛሬ በጠዋት ነቅተሃል እኔማ በሩን ልሰብረዉ የነበረዉ ምናልባት ሌባ መስሎህ ከመከረኛ የእንቅልፍ መዉደድ ስሜትህ በድንጋጤ ትላቀቃለህ ብዬ ነበር>> አሉና የጠዋት ፈገግታቸዉን ቸሩኝ። ወ/ሮ ሙሉ ቀላ ብለዉ ወፈር ያሉ የእናትነት ገፅታቸዉ ከፊታቸዉ ላይ የሚነበብ በሀዘንና በለቅሶ ብዛት ፊታቸዉ ላይ የተወሰነ ማድያት ጣል ጣል ያደረገባቸዉ የ 45 አመት ጎልማሳ ናቸዉ። በስደት ከሀገር ለመዉጣት ሲሞክር ህይወቱ ያለፈ ብቸኛ ወንድ ልጅ ስለነበራቸዉ እሱን እንደምመስል ይነግሩኛል! የልጃቸዉ የ40 ቀን መታሰቢያ ሰሞን ቤቱን ስለተከራየሁ የልጄ ምትክ እያሉ ይጠሩኛል።
መርካቶ ላይ የልብስና የህንፃ መሳሪያ መደብር የሆነ ግዙፍ ሱቅ አላቸዉ። ከሚኖሩበት ባለ አንድ ፎቅ ህንፃ በተጨማሪ ሶስት የሰርቪስ ክፍሎች ሲኖሩ ከሶስቱ አንዱ ሟች ልጃቸዉ ይኖርበት የነበረና አሁን በእኔ ተከራይነት የተያዘ ነዉ። በእርግጥ ቤት የማከራየት ፍላጎት እልነበራቸዉም በስህተት የእሳቸዉን ግቢ አንኳኩቼ <<የሚከራይ ቤት አለ ብዬ ስጠይቅ>> ፊቴ ከሟች ልጃቸዉ ጋር ይመሳሰልባቸዉና ያለምንም ማንገራገር ልጃቸዉ ይኖርበት የነበረዉ ባለ አንድ መኝታ ክፍል አከራዩኝ። የቤት ኪራይ ገንዘብ አልቀበልህም ማለት ከጀመሩ 5 ወር ያህል ሊሞላቸዉ ነዉ ከእናትነት ፍቅራቸዉ በላይ ዉለታቸዉ ስለከበደኝ አልቀበልም በሚሉኝ ገንዘብ የሆነ ስጦታ እየገዛሁ አመጣላቸዋለሁ እሷቸዉ ባይፈልጉትም። ያልገባኝ ነገር ቢኖር ጥሩ እናትና የገንዘብ ችግር የሌለባቸዉ ሆነዉ ሳለ ብቸኛ ወራሽ ልጃቸዉ ለምን ስደትን እንደመረጠ ነዉ?
<<ሔርሜላ መጥታለች በግድ ጎትቼ ወደ ቤት አስገባሗትና አንተን ለመጥራት መጣሁ ቁርስ ሳትበሉ ከቤት መዉጣት የለም>> አሉና እጄን አየጎተቱ የለሊት ልብሴን እንኳን ለመቀየር እድል ሳይሰጡኝ ወደ ሳሎናቸዉ ይዘዉኝ ገቡ...
ይቀጥላል....
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
http://www.tgoop.com/+do0OCDQEx_MzOWY0
BY official_nahi
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/PVX_ir2FQfjlk94f0Sw74hiy7tGcJxzsCPwCNcPRXEkA8-fzXIVj0kTtJwJaxz6T0uvsnjtNuWHMcaY4i-fK_nOrlnDiZe_rDZnDGV2lxrzax14QYN3iuhejEqENhS_Wv17mK-dvmaz4hmQBnyZRNuptWg6El2watAbi0Whhp8m6dzhyYfhhQwHnKB6AY1VjuuLDksROuvgdoeQOmWqBUCrrL24xsv6Y5na1Mj_3MZSjduhip4uS11DG1_JyPZR0Qt8jVQ5-3W5zqHWp_xL2q6xFkpjlWXwwv_pL-Sz20SjXIKobq4NuMXIAfkbjXNLb6lhpfVEFAyEhHN3w5d6XDw.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/Official_nahi/266