tgoop.com/Official_nahi/276
Last Update:
┉••••✽̶»̶̥🌺ከረፈደ!🌺̶̥✽̶••••┉
❣:¨·.·¨: ❣
┈┈••◉❖◉●••┈┄
#❤️በእዉነተኛታሪክላይየተመሰረተ
#🌺🌺ክፍልሰባት (7)
ምን እንደተፈጠረ ሊገባኝ አልቻለም ትዕግስትን ደጋግሜ ብጠይቃትም ጩኸትና ለቅሶዋን አቋርጣ የተፈጠረዉን ልታስረዳኝ አልቻለችም። አብረዋት ሆስፒታል ከመጡት ጥቂት ሰዎች ዉስጥ እንደ እኔ ወጣት የሆነዉን ምን እንደተፈጠረ ጠየኩት?
<<ሔርሜላ በሌቦች ጥቃት ደርሶባት ከፍተኛ ጉዳት ላይ ስለሆነች መትረፏንም እንጃ!>> አለኝ! ምድር በፍጥነት እየዞረች ይመስል የሁሉም ነገር ምስል ጥርት ብሎ አልታይ አለኝ...ብዥዥ አለብኝ...ሁሉም ድምፅ በትንሽ በትንሹ እና ጥርት ብሎ አልሰማህ አለኝ...ወንድነቴም ጉልበቴም ከዳኝ...ዘጭ ብዬ ከመሬት ተዘረርኩ...እንባዬ የት ገባ?...ማልቀስም መጮህም አልቻልኩም! ብቻ ዝም ብዬ ከመሬት እንደተዘረርኩ የተወሰኑ ሰዎች ከበዉ ዉሃ ጭንቅላቴ ላይ ሲያፈሱና ሊያረጋጉኝ ሲሞክሩ ድንገት ከእንቅልፉ እንደባነነ ሰዉ ከተዘረርኩበት ብድግ አልኩ... አዎ! አሁን እዉነቱን በደንብ ተረዳሁ ሔርሜላ በሌቦች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባትና 4 ቦታ በስለት እንደተወጋች ገባኝ! አምርሬ አለቀስኩ! ትዕግስት ድንጋጤና ያለችበት የእርግዝና ሁኔታ ተደራርበዉ ጩኸትዋን ወደ ድካምና ዝምታ ለዉጠዉባታል። ወደ ሆስፒታል ሔርሜላን ያመጧት ሰዎች ጠዋት መጥተዉ እንደሚያይዋትና ፈጣሪ መልካሙን ሁሉ እንዲያደርግላት ተመኝተዉ ወደ ቤታቸዉ ሄዱ እኔና ትዕግስት ብቻ ቃል ሳንለዋወጥ እንደተፋጠጥን ቀረን! የድንገተኛ ክፍል በሩ ተከፈተና በእድሜ ጠና ያለ ዶክተር
<<የተጠቂዋ ቤተሰቦች ናችሁ?>>
<<አዎ!>>
የተመካከርን ይመስል ከእኔና ከትዕግስት አንደበት ቃሉ እኩል ወጣ!
<<ሁኔታዉን ለህግ አካላት ማሳወቅ ይኖርባችሗል!>>
<<እህቴ...ምን...ሆነች...ንገረኝ.. ሞ..ሞ..ተ..ች>>
<<ተረጋጊ እንደሱ አይደለም ግን ያጋጠማት አደጋ ከባድ በመሆኑ ለቀዶ ጥገና ወደ ከፍተኛ ከትትል ክፍል መግባት ይኖርባታል! እራሷንም ስታለች!የፈሰሳት ደም ብዙ ስለሆነ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ለማስረዳት ይከብዳል ብቻ የተፈፀመባት ወንጀል ስለሆነ ለህግ አካላት ማሳወቅ ይኖርባችሗል! አንቺ አረፍ በይ አንተ ግን ከእኔ ጋር ወደ ካርድ ክፍል መምጣት ይኖርብሃል>> ብሎ ወደ ካርድ ክፍል እየወሰደኝ እያለ
<<ት.ተ.ር.ፋ.ለ.ች?>> አልኩት
<<አላዉቅም ግን ሆስፒታላችን የ 24 ሰዓት አገልግሎት መስጠቱ ምናልባት ችግሩን ያቀለዉ ይሆናል በሰዓቱ ህክምና ባታገኝ ነገሩ ከዚህም ይብስ ነበር! በነገራችን ላይ ምኗ ነህ?>>
<<ፍ.ቅ.ረ.ኛ.ዋ!!>>
<<አዝናለሁ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳት ለማድረግ ደሟን ስንጠራርግ ነዉ በሀይል ጭብጥ አድርጋ ስለያዘችዉ ከእጃ ላይ ያገኘነዉ እንደ እዉነቱ ከሆነ ለምርመራ ሊረዳ ስለሚችል ለፓሊስ ማስረከብ ነበረብኝ ነገር ግን ካንተ ጋር የተያየዘ ስለሆነ ነዉ!>> ብሎ እጄ ላይ ያስቀመጠዉን ነገር ተመለከትኩ! 2 የቃልኪዳን ቀለበት ነበር ለካ ሔርሜላ ቤተክርስቲያን ልታገኘኝ የነበረዉ...
❤❤❤❤❤❤❤❤
የመጨረሻው
ክፍል 8 ይቀጥላል 20👍.......
━━━━━━━✦✿✦━━━━━
http://www.tgoop.com/+do0OCDQEx_MzOWY0
BY official_nahi
Share with your friend now:
tgoop.com/Official_nahi/276