tgoop.com/OnlyAboutCarsEthiopia/1387
Last Update:
#CarNews
የኔታ ኤሌክትሪክ መኪና ከ 401 ኪሎሜትር ወደ 40 ኪሎሜትር ሬንጅ ሁለት አመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ደረሰ
ቻይና ውስጥ በዝህጂያንግ ግዛት የሁዙ ነዋሪ የሆነችው ወ/ሮ ሂ በሜይ 2023 የኔታ አያ ኤሌክትሪክ መኪና (~10,400 ዶላር) ገዛች :: ይህም 401 ኪሎ ሜትር ይፋዊ ርቀት የሚሄደው ነበር ። ዓመት ከስድስት ወር በኋላ የምትኖርበት ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታን ተከትሎ ወደ 60 ኪሎ ሜትር ከዛም ወደ 40 ኪሎ ሜትር በመቀነሱ መኪናው ከዛ በላይ በፉል ቻርጅ መጟዝ አልቻለም ።
ስለዚህ እርዳታ ፈልጋ ወ/ሮ ሂ ወደ አንጂ የኔታ 4S አከፋፋይ ስትሄድ ቴክኒሻኖቹም High Voltage Battery ላይ ችግር መኖሩን በመለየት እንዲቀየር ሀሳብ ያቀርባሉ። ነገር ግን ባትሪ አልቆ ነበርና አከፋፋዩ የሚቀይርበትን የቀነ ገደብ ሊያስቀምጥ አልቻለም። ጉዳዮን ለማቅለል አከፋፋዩ “ዳይቡቺ” ተብሎ የሚጠራውን ተሽከርካሪ በጊዜያዊ ምትክ ተሽከርካሪ ለወ/ቢያቀርብም እሱ ግን ከእርሷ የኔታ አያ ምቾት እና ተግባራዊነት ጋር ላይጣጣም ችላል::
"ይህ ሁኔታ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪዎችን ለረዥም አመት የመቆየት ጉዳይ በተለይም በቀዝቃዛ እንዲሁም በሞቃት የአየር ሁኔታዎች የሚያሳስብ ሲሆን ከሽያጭ በኋላ የአቅርቦት ችግር ባለበት በእኛ ሀገር ደግሞ ከባድ ያደርገዋል :: ምንም እንኳን በፍጥነት እየተሻሻለ ባለው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ገበያ ላይ ያለውን ፍላጎት ሊቀንስ ይችላል ብዬ አስባለሁ ። ስለዚህ አዲስም ሆነ ያገለገሉ ኤሌክትሪክ መኪኖችን ስትገዙ የባትሪ ጤና(SOH) እና (SOC) ቼክ ማድረግ ይኖርባችሗል:: ይበልጥ ደግሞ ኔታ መኪኖች በአብዛኛው የዲያግኖሲስ ማሽን ቼክ መደረግ አለመቻላቸው ከባድ ያደርጋቸዋል ::" ዮናታን ደስታ
ምንጭ - CarNewsChina
@OnlyAboutCarsEthiopia
BY Only About Cars Ethiopia
Share with your friend now:
tgoop.com/OnlyAboutCarsEthiopia/1387