tgoop.com/OrthodoxAmero/17271
Last Update:
+ ምሕረቱና ፍርዱ +
እግዚአብሔር መሐሪና ታጋሽ ቢሆንም የማይፈርድ ግን አይደለም ። እግዚአብሔር ፈታሒ በጽድቅ ኮናኒ በርትዕ ነውና ምሕረቱንና ፍርዱን ነጣጥሎ ማየት አይቻልም ። ሊቁ አግስጢኖስ "ወደ ኃጢአት መውደቅ ተገኝቶብህ ቢሆን ገደብ የሌለው ምሕረቱን ተስፍ አድርግ ፣ ኃጢአት ለመሥራት ፈተና ሲመጣብህ ደግሞ እግዚአብሔር ፈራጅ መሆኑን አስበህ ፍራ ። ምክንያቱም "እግዚአብሔር መሐሪ ነው " በማለት እርሱን መበደል ራስህን ለምሕረት ያልተገባ ማድረግ ነው " ያለው ለዚህ ነው ። ሌላም ሊቅ እንዲሁ፦ "የበደለ ማንም ቢሆን ምሕረትን መለመን ይቻለዋል ፣ በምሕረት ላይ የሚበድል ግን ወደ ማንም ሊማፀን አይቻለውም በሏል ።
የእግዚአብሔር ምሕረት የመብዛቱን ያህል በንስሐ በማይመለሱ ላይ ደግሞ በታገሠ መጠን ቅጣቱ እየከፍ ይሄዳል ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ፦ " እግዚአብሔር ልበ ደንዳና የሆነውን ኃጥእ ከመቅጣት በታገሠ መጠን አብዝቶ መፍራት ይገባል " ሲል ተናግሯል ። ምክንያቱም በታገሠ መጠን ቅጣቱ እየከበደ ይሄዳልና ። ፈርኦንን ከነ ሠራዊቱ በባሕር ያሰጠመው ፣ ናቡከደነፆርን ለሰባት ዓመታት ያህል ከሰው ተለይቶ በምደረ በዳ ከዱር አራዊት ጋር እንዲኖርና እንደ በሬ ሣር እንዲበላ ያደረገው ብዙ ስለታገሣቸው ነው ። ዳን 4፡31-33 ( ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ ገጽ 51-52)
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ
BY ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
Share with your friend now:
tgoop.com/OrthodoxAmero/17271