tgoop.com/Orthodox_picturess/3990
Last Update:
አድዋ!
የነፃነት የድል አምባ
በዕምነት በርኖስ፣ በዕንባ መባ
ፈርሷል ባንቺ ፣ሀገር ሚንድ፣ ታላቅ ደባ
አድዋ
መናገሻሽ እውነት እንጂ፣መች አንግቦ የሀሰት ካባ
ማን ነው ከቶ የሚያፈርስሽ፤
ምን ሀይል ነው የሚንድሽ፤
ቅድስቲቱን የእግዜር አምባ
አድዋ!
የድል ነፀብራቅ እውነቷ
የፅናት ምሥጢር ሕይወቷ
መሰናስልሽ ሰውነት
ሰብሳቢ ያለ ልዪነት
የሰውነትሽ ልኬቱ
አጥንት ያለየው ስሌቱ
ዘውግ ያልናጠው ማንነቱ
በደም የተዋሀደን፣የማንነትሽ ስሪቱ
በዕትብትሽ መሀል ያለፈው፤
ኢትዮጵያዊነት ነው በብርቱ
አድዋ!
ሊቃውንትሽ በያሬድ ዜማ፤በቅኔ አለም ቢናኙ
የጦሩን ስፍራ ለውጠው፤ቅኔ ማህሌት ቢያሰኙ
የጠላት ልቡ ረበደ
ጉልበቱ አቅሉን በመሳት፤
ለኢትዮጵያውየን ሰገደ
ሀይ አድዋ!
ሼሆችሽ የማለሉልሽ፣በወኔ የታገሉልሽ
ኢማም ኡስታዙ በህብረት፣በዱአው በአንድ የቆሙልሽ
አንቺ የድል ተምሳሌት፣የኢትዮጵያዊነት ህብር ነሽ
አድዋ!
ካህንሽ ታቦት አክብሮ፣ፅና ማጥንቱን አብሮ
ቅድመ እግዚአብሔር የሚያሳርግ፤
የዕምነት ማህሌት ወድሮ
ከፊትሽ አስቀድሞታል፣እግዜር ሀያሉን በዕሮሮ
አድዋ! ያቺ የጥንቷ፣ዛሬም በኛ ትውልድ መጥታ
የመከፋፈል ዕብሪትን፣ከእኔነት ጎራ ለይታ
በእኛነት አንድ ታድርገን፣በኢትዮጵያዊነት ረታ።
23/06/2013
ፍፁም ገነነ
@zosemas
BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ_Pictures
Share with your friend now:
tgoop.com/Orthodox_picturess/3990