tgoop.com/Orthodoxbiblestudy/392
Create:
Last Update:
Last Update:
አጭር የምሳ መልዕክት
ጌታችን ሲወለድ በጎችን ይጠብቁ የነበሩት እረኞች በዚያ ሌሊት በጎችን የመጠበቃቸው ምክንያት ለኦሪት መስዋዕት ሊቀርቡ የሚያስፈልጉ ስለሆኑ አውሬ እንዳይበላቸው ነው። ለኦሪት መስዋዕት የሚሆኑትን በጎች በሚጠብቁበት በዚያች ሌሊት ግን የሐዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት እውነተኛው [አማናዊው] በግ ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ።
ተወዳጆች ሆይ! እኛስ ጌታ በተወለደበት በዚህ ዕለት ስንቶቻችን ነን ሕይወት የማናገኝባቸውን በጎቻችን እየጠበቅን እየተንከባከብን ያለነው? በዓሉን በጭፈራ በዝሙት በስካር ለማክበር ያቀድን ስንቶቻችን ነን? ዛሬም የጌታን ልደት አስበን ከመላዕክት ጋር እንድንዘምር ቤተ ክርስቲያን ኑ ልጆቼ ብላ ትጠራናለች።
በቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ በምትሰሙትና በምታዩት ሁሉ ደስ ተሰኝታችሁ እንደ እረኞቹ እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ትመለሳላችሁ!
"እረኞችም እንደ ተባለላቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ ተመለሱ።" ሉቃ.2:20
አደራ የጌታን ልደት እንድንዘነጋ በሚያደርግ የዘፈን የስካር የጭፈራ የዝሙት በሆነው የሰይጣን ወጥመድ ውስጥ አንውደቅ!
"የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ" ማር.4:23
ለሌሎችም እንዲዳረስ Share አድርጉ።
BY ኦርቶዶክሳዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት [The Orthodox study bible]
Share with your friend now:
tgoop.com/Orthodoxbiblestudy/392