Telegram Web
"እናንተ ልምዶቻችሁን ትፈጥራላቹ።ልምዶቻቹ እናንተን ይፈጥራሉ"

መልካም ልምዶችን በማዳበር ዙሪያ የስነ ልቦና ባለሙያው ኤርሚያስ ኪሮስ በ EBS ላይ የነበረውን ቆይታ ይከታተሉ።
https://youtu.be/kkLb9eikmRw
ሐዋሳ ለምትኖሩና ሰውን የመርዳት ልብ ላላችሁ
ስልጠናውን እነማን ይውሰዱ?

እውነተኛ የልብ ሰላምና ደስታን ማግኘት የሚፈልጉ

የተጨነቁ ሰዎችን የመርዳት ልብ ያላቸው

ፍካት በሐገር አቀፍ ደረጃ በሚሰራው የልብ ቁስል ፈውስ አገልግሎት(Trauma Healing Programs) ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ሊወስዱት የሚገባ ስልጠና ነው።

በጣም ጥቂት ቦታዎች ብቻ ስላሉን ፈጥነው ይመዝገቡ።
ርዋንዳ ከ28 አመት በፊት በተፈጠረው የዘር ማጥፋት እልቂት በ100 ቀናት ውስጥ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎቿን አጥታለች።ቃላት ሊገልጡት በማይችሉት ሰቆቃ ውስጥ አልፋለች።አሁን ግን ራዕይ ባላቸው ከበቀል ይልቅ ፍትህና ይቅርታን በመረጡ ልጆቿ አስገራሚ ወደሆነ ሰላምና እድገት ተመልሳለች።ከርዋንዳ ቆይታዬ ሁለት ነገር ተምሬያለው።

1.ጥላቻ ቀኑን ያጨልማል።ፍቅር ጨለማን ያነጋል።

2.ባይመስልም እንኳን ሁሌም ተስፋ አለ!
ኤርሚያስ ኪሮስ(ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)
የፍካት 18ኛ ዙር Bible Based Trauma Debriefing Skills ስልጠና ለ 29 ተሳታፊዎች ከጥቅምት 25-27/2015 በመስጠት በታላቅ ስኬት መጠናቀቁን ስንገልጽ በደስታ ነው።

We are happy to announce that we have successfully completed the 18th round of Fikat's Bible Based Trauma Debriefing Skills training for 29 participants from the 4th to the 6th of November, 2022.

ፍካት የስነ - ልቦና ማማከር አገልግሎት - Fikat Counseling services
የፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመሆንን የመፍራት ህመም( anuptaphobia)

የፍቅር ግንኙነትን መፈለግ ተፈጥሯዊ ስሜት ነው።አንዳንድ ሰዎች ግን  ከፍቅር ግንኙነት ውጪ ወይንም single  መሆንን አጥብቀው ይፈራሉ።እንዲህ አይነቱ ህመም በሙያዊ አጠራሩ anuptaphobia ይባላል።ይሔ ሕመም ያለባቸው ሰዎች ከዚህ በታች የተገለጹት ምልክቶች ይታዩባቸዋል

Ø  የፍቅር ግንኙነት(relationship)ውስጥ ካልሆኑ በጣም ይጨነቃሉ::ይሄ ጭንቀት ሊቋቋሙት  እስከማይችሉ ድረስ ይቆጣጠራቸዋል

Ø  የፍቅር አጋር አላገኝም የሚል ከፍተኛ  ፍርሀት አለባቸው

Ø   ብቻቸውን ላለምሆን ሁሌም ቢሆን የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ለመግባት ብርቱ ጥረት ያደርጋሉ።ብቸኝነትን ከመፍራታቸው የተነሳ ጤናማ ያልሆነና እንደማይቀጥል የሚያውቁትን  የፍቅር ግንኙነት ይጀምራሉ።

Ø  ጤናማ እንዳልሆነ የሚያውቁትን የፍቅር ግንኙነት ለማቋረጥ ይቸገራሉ

Ø  ብቸኝነታቸውን ከመፍራታቸው የተነሳ ያላቸውን የፍቅር ግንኙነት ለማቆየት ሲሉ ሊከፍሉት የማይገባውን ዋጋ ይከፍላሉ

Ø  የፍቅር ግንኙነታቸው ሲቋረጥ ለራሳቸው ጊዜ አይወስዱም።ይልቁኑ በጣም በፍጥነት  ወደ ሌላ የፍቅር ግንኙነት ይሸጋገራሉ።

Ø  ሁሌም ራሳቸውን ከሰዎች ጋር ያነጻጽራሉ

የህመሙ ምክንያት

Ø  ከልጅነት ጀምሮ የመጣ ያለመፈለግ ስሜት

Ø  ለራስ የሚሰጥ ዝቅተኛ ግምት

Ø  በልጅነት ያጋጠመ የስነ ልቦና ቁስል

Ø  ማህበራዊ ተጽዕኖ በጥቂቱ ሊገለጹ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።

መፍትሄ

Ø  ፍርሀቱና ጭንቃቱ ከየት እንደመጣ መለየት

Ø  የፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመሆን ያለመፈለግ መገለጫ እንዳለሆነ መገንዘብና ለራስ ጤናማ ግምት መስጠት

Ø  የፍቅር ግንኙነት ውስጥ አለመሆን ጤናማ የህይወት አንዱ ደረጃ እንደሆነ ማስታወስና ይሄን ጊዜ ራስን ለማሳደግ፣እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነትንና መንፍሳዊ ህይወትን ለማበልጸግ መጠቀም

Ø  ከማህበረሰብ የሚሰነዘሩ ምክንያታዊ ባልሆኑ ሀሳቦች አለመሸማቀቅ

Ø  የስነ ልቦና ምክክር አገልግሎት  መውሰድ ተጠቃሾች ናቸው።

"ሰዎች የሚሉት ሳይሆን እኛ ስለራሳችን የምንለው ህይወታችንን ይወስናል"።

ኤርሚያስ ኪሮስ(ካውንስሊንግ ሳይኮሎጂስት)

ለማንኛውም የስነ ልቦና ድጋፍ ይደውሉልን

0967678832

ፍካት የስነ ልቦና ማማከር አገልግሎት
በህይወታችሁ ሰዎችን የመርዳት: የማማከር ጥሪ እንዳላችሁ ለምታምኑ ሁሉ የተዘጋጀ ስልጠና ነው።

19ኛ ዙር ስልጠና ምዝገባ ጀምረናል።ፈጥነው ይመዝገቡ!

0967678832
+251940594855
በህይወታቸው የልብ ሰላም እንዲኖራቸውና ሰዎች በማማከር መርዳትን የሚሹ የሚወስዱት ስልጠና

8 ቀናት ብቻ ቀሩት።መጋቢት 1-3/2015
ፈጥነው ይመዝገቡ
+251980494342
+2519425236531
በህይወታቸው የልብ ሰላም እንዲኖራቸውና ሰዎች በማማከር መርዳትን የሚሹ የሚወስዱት ስልጠና

6 ቀናት ብቻ ቀሩት።መጋቢት 1-3/2015
ፈጥነው ይመዝገቡ
+251980494342
+2519425236531
Good News!! Erasmus Mundus Scholarship has Organized a webinar on October 17, 2023. On this session there will be a detailed presentation about the scholarship. There is also a Question and Answer session. Don't miss this opportunity!

https://yt.psee.ly/5bu86w
2024/09/30 08:19:11
Back to Top
HTML Embed Code: