tgoop.com/Qureankeriim/1457
Last Update:
📌ክፍል 1
የዒልሙ ባህር #ኢማም_አን_ነወዊይ
ሠዎች እነሡን ሸይኽ፥ዒማም፥ዐለም፥ዓላመህ፥ፈቂህ፥ዓቢድ፥ዛሂድ ብለው ይገልፆዋቸዋል!!(ይህ ሁሉ የሲፋ/ፀባይ/ መጠሪያ ግን ሲያንስባቸው ነው እንጂ መቼም አይመጥናቸውም) ሙሉ ስማቸው አቢ ዘከርያ ሙህዪዲን የህያ ብኑ ሸረፍ ቢን ሙሪ ቢን ሀሠን ቢን ሁሠይን ቢን ሙሀመድ ቢን ጁሙዓህ ቢን ሂዛም አል-ሂዛሚይ አን-ነወዊይ አድ-ዲሚሽቂይ ይባላል። በነገራችን ላይ #ሙህዪዲን የተባለው ስማቸው ቅፅል ነው። አሏህ በሳቸው ሠበብ ዲንን ህያው አድርጓልና ሠዎች 'ዲንን ህያው ያደረገ' ብለው ሠየሟቸው። ደግሞ #አቢ_ዘከርያ ያሏቸው ዘከርያ የሚባል ልጅ ስላላቸው ሳይሆን በዛ ግዜ ትልልቅ ዑለማዎችን ልጅ ባይኖራቸው እንኳን የአንድ ሠው አባት እንደሆኑ አድርገው ቅፅል ስም ይሰጧቸው ነበር። (እንጂማ ኢማሙ ነወዊይ መች ልጅ ወለዱ?!! እረ እንደድም ጭራሽ አላገቡም!! ) . አብዛህኛው ሠው ሚያውቃቸው ለቀብ(ቅፅል ስም) ደግሞ #ነወዊይ በሚለው ነው። ይህም በተወለዱበት መንደር ስም የተሠየመ ነው።(ልክ ለምሳሌ የሳሪስ ልጅ ከሆንክ አስ-ሳሪሲይ እንደምትባለው ማለት ነው😊)
የተወለዱት በወርሀ #ሙሀረም በ 631 ሒጅሪ አቆጣጠር ፥ ነዋ በምትባል የሻም መንደር ውስጥ ነው።(ነበር እያልኩ ማላወራው ሁሌም ህያው ስለሆኑና አሁንም ድረስ አብረውን ስላሉ ነው። አሏህስ 'ሞቱ ብለህ አታስብ' አይደል ያለው) እናም ወላጆቻቸው በእስልምና ስነ-ስርአት ኮትኩተውና አንፀው በአደብ በተዝኪያ እንዲያድጉ አረጓቸው። የአሏህንም መፅሀፍ ቁርአንን ገና በጨቅላ እድሜያቸው እንዲያነቡ አደረጓቸው።
ክፍል 2 ይቀጥላል....
https://www.tgoop.com/joinchat-YGFauLVOp5hiODI8
BY አል ቁርዐኑል ከሪም

Share with your friend now:
tgoop.com/Qureankeriim/1457