tgoop.com/Qureankeriim/1462
Last Update:
💜 ነፍስህ ቁርአን መሀፈዝ
በጣም ከባድ ነው አትችልም ስትልህ
እንዲህ ብላህ ቅራላት...
(وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِنْ مُدَّكِرٍ)
" ቁርአንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው
ተገንዛቢም አለን? "
[አል ቀመር 17]
↪ ነፍስህ ባክህ ጊዜ የለህም ተወው ስትልህ
እንዲህ ብለህ ቅራላት...
( يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تُلْهِكُمْ أَمْوَالُكُمْ وَلَا أَوْلَادُكُمْ عَنْ ذِكْرِ اللَّهِ ۚ وَمَنْ يَفْعَلْ ذَٰلِكَ فَأُولَٰئِكَ هُمُ الْخَاسِرُونَ)
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁና ልጆቻችሁ
አላህን ከማስታወስ አያታሉዋችሁ ፡፡
ይህንንም የሚሠሩ ሰዎች እነዚያ
እነርሱ ከሳሪዎች ናቸው ፡፡"
[አል ሙናፊቁን 9]
↪ ነፍስህ ተኛ ብላ ስትጎተጉትህ
እንዲህ ብለህ ቅራላት...
( كَانُوا قَلِيلًا مِنَ اللَّيْلِ مَا يَهْجَعُونَ)
" ከሌሊቱ ጥቂትን ብቻ ይተኙ ነበሩ ፡፡"
[አዛሪያት 17]
๏ ትልቁ ጂሃድ ማለት
ከነፍስህ ጋር የምታደርገው ትግል ነው
ነፍስ በመጥፎ ነገር አዛዥ ናት
እንቢ ብለህ ካሸነፍካት
ትርፋማና ደስተኛ ትሆናለህ
↪ ካሸነፈችህ ደግሞ ትከስራለህ
ከእድለቢሶችም ትሆናለህ ።
አላህ ይጠብቀን
✍ https://www.tgoop.com/joinchat-TcSd56N1aJTYW5oA
BY አል ቁርዐኑል ከሪም

Share with your friend now:
tgoop.com/Qureankeriim/1462