Telegram Web
ለአንተ እና ለኔ!
ღ¸.✻´✻.¸¸ღ
🎈تناجيك أجداث وهن صموت
🎈 وسكانها تحت التراب خفوت
🎈أيا جامع الدنيا لغير بلاغه
🎈لمن تجمع الدنيا وأنت تموت
ቀብሮች ያናግሩሃል ዝም ያሉ ሆነው
ነዋሪዎቿ ከአፈር ሥር ተደብቀው
አንተ የዱንያ ሰብሳቢ ወይ ላትደርሰው
ሟች ሆነክ ሳለ ለማን ሰበስብከው??
ღ¸.✻´✻.¸¸ღ
🕯ከመቃብር ላይ ፅሁፎች
📚 ኢህያእ_ዑሉሙዲንツ

https://www.tgoop.com/joinchat-YGFauLVOp5hiODI8
ዋ ነፍሴ!!!

ምነው መዳከርሽ፣ብሎም ማላዘንሽ
ጥፋትሽ በዝቶ ቀርቦዋል አጀልሽ

ዋ ጥፋትሽ! ወደ ጌታሽ አለመመለስሽ
ተስፋሽ በዝቶ በአጭሯ ሀያትሽ
ዋ ነፍሴ ተይ ንቂ ሞት ድንገት ሳይዝሽ❗️
😞

https://www.tgoop.com/joinchat-YGFauLVOp5hiODI8
🦋ታገስ

ቀጣዩ የጀላሉዲን አል ሩሚ ምክር የገባኝ አሁን ላይ ነው።
لا تتحدث في الثلاث
عن ذهابك ومذهبك وذهبك
ስለ 3 ነግራቶች ለማንም አትናገር
ስለመጓዝህ(ለመሄድ ስለማሰብህ)
ስለመዝሃብክ (አቂዳህ)
ስለ ወርቅህ(ስለ ሃብትክ)

አንተ ከረሱል የምክር መውጅ የቀዘፍከው ጀላሉዲን አል ሩሚ አሏህ ልሳንህን ይባርክ!
- - ሩቅ ሃገር ለመጓዝ ያስብክ ግዜ ቤታቸው የተቀመጡ የቤት ለማዳዎችን አታማክር - ይልሃል የፋርሱ ነጋሲ። እኚህ ሰዎች በአልጋቸው ሙቀት ተገርመዋል! የእናት እና አባቶቻቸውን ሃቅ የሚወጡት እንደ አራስ ህጻን ከእቅፋቸው ሥር ባለመውጣት ብቻ ይመስላቸዋል።
ለሰዎች ስለመጓዝህ የተናገርክ እንደሆነ ሞኝ መስለህ ትታያቸዋለህ ! ችኩል ነህ ይሉሃል እንግዳም ትሆንባቸዋለክ! ይኋሊት ካየህ ግን ከምርጦቹ ትውልዶች አንዱም ፍራሹ ላይ የተደላደለ የለም ! ከመቶ ሺ በላይ ሶሃባዎች ከመኖሪያቸው ተሰደዋል ! እናቶቻቸውን አስከፍተው ነው ወይንስ አባቶቻቸውን ተቃርነው? ሞኝ ይሁኑ ወይስ ችኩል? ወሏሁል ሙስተዐን !



• ስለ አቂዳህም ለሰዎች አትናገር።አቂዳ የልብ ሥራ ናት ምላስ ጨርሳ ልትገልጸው አትችልም።
አደራህን ሰዎችን ሰው በመሆናቸው እንጂ በአቂዳቸው እንዳትለካ።በያዝከው እስልምና እንጂ ዘመን ባመጣው የዐቂዳ ታርጋ ቅንጣት እንዳትኮራ ፡ እውነትን ሁሌም ፈልጋት ! አገኘጓት ብለህ የተቀመጥክ እንደሆነ ታላቅ ስህተት ላይ ወድቀሃል.
አስተውል እውነትን ከልቡ እየፈለጋት ሳያገኛት የሞተ ከእውነተኞች ጭፍራ ይቀሰቀሳል። እውነትን አውቆ ያልተገበራት ሰውስ? ያልከኝ እንደሆነ እውነትን በሃቂቃ ያወቃት ጀርባውን ሊሰጣት አይቻለውም ! አሏህ ከእዝነቱ ያራቀው ሰው ቢሆን እንጂ እልሃለው።


ሰሉ አለይህ💚
ከወደዱስ እንዲህ ነው

*የመዲናዋ (አንሷር) ሴት*

አነስ ቢን ማሊክ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዳወሩት የኡሁድ ጦርነት ጊዜ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተገደሉ የሚባል ወሬ መዲናን ከጫፍ እስከ ጫፍ ናጣት። በዚህን ጊዜ ነበር የነብዩን ሞት ማመን ያቃታት ሴት ወሬውን ለማረጋገጥ በወጣችበት በኡሁድ ጦርነት ላይ ልጇ፣ አባቷና ባለቤቷ መሞታቸውን የነገሯት።

እርሷን ያስጨነቃት የቤተሰቦችዋ ጉዳይ ሳይሆን የረሡል ሁኔታ ነበርና "ነብዩስ እንዴት ናቸው?" አለች። "ይኸውልሽ ነብዩ ፊት ለፊትሽ ናቸው" ብለው ሲያሳዩዋት ወደ እርሳቸው ሄደችና "እናቴም አባቴም ለርስዎ መሰዕዋት ይሁንልዎ ሁሉም ሀዘን ከርስዎ በኋላ ቀላል ነው" በማለት ተናገረች።
ይህ ተራ አባባል አይደለም፣ እንደዚህ ዓይነቱማ ውዴታ እንዲሁ የሚገኝ ይመስለናልን? መሰዕዋት የሆኑት እኮ ልጇ፣ አባቷ፣ ወንድሟና ባለቤቷ ናቸው እኮ ! ከዚህስ በላይ ምን ሊታጣ ይችላል !? እስቲ አንተንና እኔን በሷ ቦታ ላይ ሆነን እናስብ።

አወይ አንቺ የአንሷር ሴት! ምን እንበል ስላንቺስ ውዴታ !

join በሉ 👇👇

https://www.tgoop.com/joinchat-YGFauLVOp5hiODI8
♡ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ
⇨ ዱንያን ካሰረብህ
⇨ ሸዳኢድና ሙሲባን ካበዛብህ
እሱ ዘንድ ተወዳጅ ስለሆንክ ነው ...
የአንቢያኦቹንና የወሊዮቹን መንገድ
እየመራህ ነውና ሰብር አድርግ { ታገስ } ።
https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
🍃🌸🍃🌸🍃🌸🍃🌸

♡ አላህን በመታዘዝ ፍራው
በመፍራትም ታዘዘው
⇨ እጆችህን ከሙስሊሞች ደም ጠብቅ
⇨ ሆድህን ከንብረታቸው ጠብቅ
⇨ ምላስህንም ክብራቸውን ከመንካት ጠብቅ ።
#አቡበክር_ሲዲቅ
ረዲየላሁ ዐንሁ

https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
♡ ጥሩን ስራ ዝቅ ባለ ድምፅ ስራው
ነገ ከፍ ባለ ድምፅ ይናገራል ...
⇨ ያለምንም ቅድሚያ
ሰደቃን ከሰጠህ
አላህ ሳታስበው ይረዝቅሃል ።
https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
♡ ሴት ልጅን ከልብ ወለድ አለም
ወደ እውነተኛው አለም
ሊያመጣት የሚችለው ብቸኛው ነገር ...
⇨ ትዳር ነው ።
https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
♡ ከተብቃቃህ ትንሹ ብዙ ነው
⇨ ከተስገበገብክ ብዙው ትንሽ ነው
⇨ ከወደድክ ሩቁ ቅርብ ነው
⇨ ከጠላህ ቅርቡ ሩቅ ነው ።

https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
ከጀናዛ ማጠቢያው ክፍልየሚል እውነተኛ ታሪኮች ይዘን ቀርበናል ። ወላሂ የውሸት ፕሮሞ አደለም
በእርስዎ ሰበብ አንድ ሰው ቢቶብት ወይም ባለበት ጠንካራ አቋም ላይ ቢፀና ከፍተኛ አጅርን ይጎናፀፋሉ ። ለጓኞቻችሁ ሼር በማረግ ያስተላልፍ አልባት በዚህ ታሪክ ምክንያት ሊቶብቱ ይችላሉ ። ማስፈንጠሪያውን ስትነኩት የምትፈልጉትን ክፍል ያወጣላችሗል ።
ከ ክፍል 1 ብትጀምሩ ኸይር ነው ።

👇👇👇👇👇👇👇👇
አላህ አንድ ቀን ይሠጠኛል የሚል እምነት ነበረው።
አላሳፈረዉም፣
እጥፍ ድርብ አድርጎ ሠጠው።

ሁሌም በአላህ ላይ መልካም እንዳሰባችሁ ኑሩ።

https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
“አል-ሐሱዱ ላ የሱዱ” ይላል ዐረብ፤ “ምቀኛ መቼም አይነግስም” እንደማለት፡፡ ቀን አይወጣለትም፡፡ እንኳን ሊነግስ ለራሱም ተበልቶ ነው የሚያልቀው፡፡ ጀዛው ነዋ፡፡ አንተ ታድጋለህ እሱ ያልቃል፣ አንተ ትበራለህ እሱ ይከስማል፣ አንተ ትፋፋለህ እሱ ይከሳል፡፡

ለመቆጣጠር ከሚከብዱ ባህሪዎች መካከል አንዱ ቅናት/ምቀኝነት ነው፡፡ ቢሆንም ታገለው ወዳጄ፡፡ ማንኛዉም ክፉ ስሜት ሊመጣብህ ባለ ጊዜ ሁሉ ታገለው፡፡ ደጋጎች ዱንያን በትግል ነው የዘለቁት፡፡ እንደታገሉም ነው ቀብር የገቡት፡፡ ከሌላው ሰው ይልቅ በዋናነት በራሣቸው ላይ ነው ትልቁን ሥራ የሠሩት፡፡ ወደራሣቸው ሲመለከቱ፣ ራሣቸዉን ሲገመግሙ ነው ሐያታቸዉን የኖሩት፡፡

ከየት ልጀምር ካልክ ሁሌም ቢሆን ከራስህ ጀምር፡፡ ራስህን ያዝ፣ ራስህን ተቆጣጠር፣ ራስህን ጥረብ፣ ራስህን አስተካክል፡፡

ዘመኑ እንዲህ ነው፤ አንዳንዴ ጥሩ ነገር ሠርተህ ጥሩ ያልሠሩ ሰዎች ሊሳካላቸው ይችላል፡፡ ምን ታረገዋለህ ታዲያ! አሁንም ከመጣር ጋር አላህ የወደደዉን ዉደድ፡፡ ዉጤት ያለው ብቸኛ መፍትሄ ይኀው ነው፡፡

ቸሩ አላህ ለሰዎች በሠጣቸው ችሮታዎችና ፀጋዎች ፈጽሞ አትቅና፡፡ የበለጡትን እሱ ራሱ ነው ያስበለጣቸው፡፡ የቀሩትንም አላህ ነው ወደኋላ ያስቀራቸው፡፡
በቅናትና ምቀኝነት የሰዉን ሥም ማጥፋት ያንተን አያድስም፡፡ እነርሱን መጣልህ አንተን አያነሳህም፡፡ ፊትለፊቱ “ትችላለህ እኮ!” እያልከው እያደነቅከው ዘወር ሲል “ይሄ ምን ይችላል!” አትበል፡፡

ሰው እንዴት ሰዉን ለመቦጨቅ ብቻ ብሎ ስልኩን አንስቶ “ሄሎ!” ይላል!፡፡ በዚህን ጊዜ በትንሹ ሁለት ነገር ታጣለህ፡፡ አንድም ሳንቲምህን በብላሽ ትበላለህ፣ ሁለትም መልካም ሥራህን ላማኸው ሰው አሳልፈህ ትሠጣለህ፡፡

አንዳንድ ሰዎች በሆነ ሰው ከመቅናታቸዉና ከመመቅኘታቸው ብዛት “ባልጠፋ ቀን እንዴት ጀሙዓ ሌሊት ይሞታል” ብለው ሲንጨረጨሩ አጋጥሞ አያውቅ ይሆን?፡፡
ምቀኛ ሰው አይደለም የዱንያ የአኺራን ስኬት አይመኝልህም፤ መቃብር ወርደህም አይፋታህም፡፡

ወሚን ሸር ሓሲዲን ኢዛ ሐሰድ
ጁምዓ ሙባረክ!


https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
ይገርመኛል ...

ከዓመታት በፊት አምርሬ ስቃወማቸዉና ስከለከላቸው የነበሩትን ኃጢአቶች አሁን እኔው ራሴ እየሰራኋቸው ነው።

https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
በምላሱ 'እወድሃለሁ' የሚለኝንና ወዳጅ እና በቀልቡ ከልቡ የሚወደኝን ሰው የመውደድ ደረጃና ልዩነት እንዲሁ በማየት አውቃለሁ ። ፍቅር ከመናገርም በላይ ነዉና።
ለሁሉም ግን የምትወዱትን ሰው እንደምትወዱት ሳትነግሩት አትሙቱ።

https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
ከጀናዛ ማጠቢያው ክፍልየሚል እውነተኛ ታሪኮች ይዘን ቀርበናል ። ወላሂ የውሸት ፕሮሞ አደለም
በእርስዎ ሰበብ አንድ ሰው ቢቶብት ወይም ባለበት ጠንካራ አቋም ላይ ቢፀና ከፍተኛ አጅርን ይጎናፀፋሉ ። ለጓኞቻችሁ ሼር በማረግ ያስተላልፍ አልባት በዚህ ታሪክ ምክንያት ሊቶብቱ ይችላሉ ። ማስፈንጠሪያውን ስትነኩት የምትፈልጉትን ክፍል ያወጣላችሗል ።
ከ ክፍል 1 ብትጀምሩ ኸይር ነው ።

👇👇👇👇👇👇👇👇
'ዐሊ ሆይ ቀልብ ከፀዳች ታያለች።' አሉት ዐሊ ለዑመር
አዎ ፣ ቀልብ ካልተሸፈነች በስተቀር ዐይን አላት ታያለች ።
ቀልብ ተወልዉላ ስትፀዳ መልካምን ሁሉ ታያለች፣ ጥሩና መጥፎን ታውቃለች፣ ሐራምና ሐላሉን ትለያለች፣ ከኃጢአት ሥፍራ ትርቃለች።

ግና ቀልብ የምትፀዳው በምን ይመስላችኋል ?


https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.)
'ምርጡ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው።' ማለታቸው ይታወሳል።
ኢማም አል-አውዛዒ እንዳሉት 'በዚሁ ቀን ሊያደርጉ ብለው ዱዓቸዉን የሚያስቀምጡ ደጋግ የአላህ ባሮች አሉ።'

#የዐረፋ ቀን ማለት ነገ ሰኞ ነው። መፆሙ ያለፈዉንና የሚመጣን ዓመት ወንጀል ያስምራል፣ ሶደቃ፣ ዱዓ፣ ዚክርና ተክቢራና ይወደዳል።

ለኢድ ለቤተሰብ ለጓደኞቻችሁ መልእክት ማድረስ የምትፈልጉ በዚህ ቦት አድርሱን

-🌛ስማችሁንና ያላችሁበትን ሀገር መፃፍ እንዳይረሱ 👇👇👇👇
@BiluuBot

እኛ መልሰን ወደ ቻናሉ እንልካለን


https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
.
አሏሁ አክበር አሏህ አክበር
.
አሏሁ አክበር
.
ላኢላሃ ኢለሏህ
.
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
.
ወሊላሂል ሃምድ
.
አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር
.
ወልሃምዱሊላሂ ከሲራ
.
ወሱብሃነላሂ ቡክረተን ወአሲላ
.
ላኢላሃ ኢለሏህ
.
ሰደቀ ወአደህ
.
ወነሰረ አብደህ
.
ወአዘ ጁንደህ
.
ወሃዘመል አህዛበ ወህደህ
.
ላኢላሃ ኢለሏህ
.
ወላ ናእቡዱ ኢላ ኢያህ
.
ሙኽሊሲነ ለሁዲን
.
ወለው ከሪሃል ካፊሩን
.
አሏሁመ ሶሊ አላ ሰዪዲና ሙሐመድ
.
ወአላ አሊ ሰዪዲና ሙሐመድ
.
ወአላ አስሃቢ ሰዪዲና ሙሐመድ
.
ወአላ አንሷሪ ሰዪዲና ሙሐመድ
.
ወአላ አዝዋጂ ሰዪዲና ሙሐመድ
.
ወአላ ዙሪየቲ ሰዪዲና ሙሐመድ
.
ወሰለም ተስሊመን ከሲራ!
.
♡ዒድ ሙባረክ♡

ለኢድ ለቤተሰብ ለጓደኞቻችሁ መልእክት ማድረስ የምትፈልጉ በዚህ ቦት አድርሱን

-🌛ስማችሁንና ያላችሁበትን ሀገር መፃፍ እንዳይረሱ 👇👇👇👇
@BiluuBot

እኛ መልሰን ወደ ቻናሉ እንልካለን

ከዛ መለቀቁን ከታች ባለው ሊንክ እዩት ።👇👇

https://www.tgoop.com/joinchat-TRwS-BymXvW3d4cI
2025/07/13 23:26:38
Back to Top
HTML Embed Code: