RE_YA_ZAN Telegram 2303
....አየህ....የሆነ ጊዜ ላይ ደግሞ በሂደት ከልጅነት ችኩል አስተሳሰቦች መውጣት ያስፈልጋል.... ፊልም ላይ ከምናያቸው ድራማዊ ምላሾች ረገብ ማለት.... ነገሮችን በመጀመሪያ ምላሻችን ሳይሆን አዳምጦ በመረዳት፣ ከልብ ብቻ ሳይሆን ከአእምሮም ተማክሮ የመወሰን፣ ወደ ቀጣዩ የህይወት እርከን ለመሻገር የመቁረጥ አይነት.... ተረዳኸኝ?

....ደግሞ የሆነ.... ትውልዳችን ሁለት አደገኛ ማማዎች ላይ ተንጠልጥሎ የቀረ አይመስልህም?.... አንዱን ስታየው ስሜቱን ከማዳመጡ የተነሳ በሱ ብቻ የሚመራ.... ራሱን ቀድሞ እንዳደገ የቆጠረ.... እቺንም ሲያይ የሚጓጓ፣ ያለፈችዋም ሚስት የምትሆነው የሚመስለው.... ትናንት ላግባት ስላለህ ምኗን አይተህላት ብለህ ሳትጨርስ ሌላዋን የሚጎትትብህ... ምን አዘጋጅተሃል ስትለው ገና የእናቱን ቤት የሚጠራ ብዙ ፊዚክስ የሆነ ሰው አለ። ከሱ ብዙም ሳትርቅ ደግሞ ያለፈ ያገደመው በሬን ባንኳኳ ብላ የምትጠብቅ.... ገና ማማሰያዋን አጥብቃ መያዝ ሳትጀምር ቆማ ስለመቅረት የሚያሰጋት.... ብቻ ይምጣ እንጂ ምንምስ ቢሆን አይነቷ የዋህ... ዜማዋ ከተሰበርኩ ተከዳሁ የማይተርፍ.... ትቆጣት ይሆን ታዝንላት ግራ ታጋባለች። ለነዚ መስፈርት ትለው ነገር አይዋጥላቸውም.... የእድሜ ብስለት፣ ስክነት፣ ምክክር ይሉት የትዳር መሰሶዎች በራሳቸው ጊዜ እስኪገለጡላቸው መታገስ እንጂ ተመክሮ ሚመለስ ጥቂት ነው።

....በሌላው ማማ ላይ ደግሞ ሰርክ ወጣት ሆኖ የሚቀር የመሰለው አርቆ አሳቢ ያሳዝንሃል። ማለት.... የትዳርን ጠቀሜታ አትሰብከው ነገር ሊገባው ከሚገባው በላይ ገብቶታል.... ለሆነ... አሁንም እርምጃ ሊወስድለት ላልቆረጠው አንድ ቀን፣ ቀን ተሌት ይለፋል... ለሱ ትዳር የጠፈር ምርምር ነው... በሃሳቡ ምድር ላይ የማይወርድ ፍፁም ቤተሰብ ይስልና.... የምታቀርብለት የትኛዋም ሀዋ በዛ ፍሬም አልገጥም ትለዋለች። እሷም ከሱ ብዙ አትሻልም.... ፍራቻ አይሉት ጥላቻ... ብቻ የሆነ ሽሽት አለባት። ጆሮ ከሰጠሃት.... በሷ ስሌት ሁሌም ገና ልጅ ናት። ሁሉም ወንድ ደግሞ ገና ብቁ አይደለም። በዙሪያዋ ያሉትን ያለ ጡት ዝምድና ሃላል ያደረገቻቸው ይመስል... "ወንድሜ ነህ እያልኩ እንዴት እንዲ ታስበኛለህ?" ብላ ማስደንገጥ ልማዷ ነው... ከምትርቀኝ በሚል የተመኛት ሁሉ እህትነቷን ይመርጣል። ማለት... በቀረበን ሰው ለልጆቹ እናትነት/አባትነት ታምኖ መታጨት እኮ ከጨዋ ውይይት ጋር ይበልጥ ያከባብራል እንጂ አያጣላም... ተረዳኸኝ?.... ለዛ ነው ከማደግም በኋላ ገና አለማደግ አለ ያልኩህ። አንተ ከየትኛው ነህ... እሷ ከየትኛው ናት አላልኩም... እሱን ለናንተው። እኔም ከየትኛው ሆኜ መካሪ እንደሆንኩ ለኔ እንተወውና.... ብቻ... ሁለታቹም ስከኑና ወደምትግባቡበት ብስለት እደጉ። በሁሉም ላይ መሀከለኛ ከመሆን ጉዳት የለም። ጨዋ ውይይቱን ደግሞ ራህማኑ ዳግም ሲያቀማምጠን... ፊ አማኒላህ።

@Re_Ya_Zan

tgoop.com/Re_ya_zan/2303
Create:
Last Update:

BY TEAM HUDA

Share with your friend now:
tgoop.com/Re_ya_zan/2303

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

So far, more than a dozen different members have contributed to the group, posting voice notes of themselves screaming, yelling, groaning, and wailing in various pitches and rhythms. 4How to customize a Telegram channel? How to create a business channel on Telegram? (Tutorial) As the broader market downturn continues, yelling online has become the crypto trader’s latest coping mechanism after the rise of Goblintown Ethereum NFTs at the end of May and beginning of June, where holders made incoherent groaning sounds and role-played as urine-loving goblin creatures in late-night Twitter Spaces. Telegram is a leading cloud-based instant messages platform. It became popular in recent years for its privacy, speed, voice and video quality, and other unmatched features over its main competitor Whatsapp.
from us

Telegram TEAM HUDA
FROM American